label
class label 4
classes | headline
stringlengths 17
80
| text
stringlengths 1
16.8k
| headline_text
stringlengths 28
16.8k
| url
stringlengths 36
49
|
---|---|---|---|---|
5sports
| የስፖርት ኮከቦች እና የንግድ ምልክቶቻቸው- ከቦልት እስከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ | የአትሌቲክሱ ዓለም ኮከብ እና ፈጣኑ ሰው ዩሴን ቦልት ከውድድር በፊት እና በኋላ የሚያሳየውን ታዋቂ የሆነውን ምልክት ለንግድ ምልክትነት ለመጠቀም ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል። እሱ ብቻ ግን አይደለም የሚለይበትን ምልክት የሚያሳይ ኮከብ። የአሜሪካ የፓተንት እና የንግድ ምልክት ቢሮ እንደገለጸው ቦልት ታዋቂውን ምልክቱን በንግድ ምልክትነት ለማስመዝገብ ማመልከቻውን ነሐሴ 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ አስገብቷል። መቀመጫቸውን ዋሽንግተን ያደረጉት የንግድ ምልክት ጠበቃው ጆሽ ገርበን “አንድ እጁ ታጥፎ ወደ ጭንቅላቱ ሲጠቆም ሌላኛው እጁ በተመሳሳይ አቅጣጫ ወደ ላይ ከፍ ብሎ እንደሚዘረጋ” ያሳያል ብለዋል። ቦልት ይህን የሚያደርገው ዝነኛ የድል አድራጊነቱን የሚያሳየውን አርማ የንግድ ምልክት በማድረግ ልብሶችን እና የፋሽን ዕቃዎችን ለመሸጥ በማሰቡ ነው። ታዋቂዋ የአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሜጋን ራፒኖ ጎል ካስቆጠረች በኋላ ደስታዋን በምትገልጽበት የተለየ መንገድ ትታወቃለች። ከአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ እና የኦሎምፒክ ወርቅ አሸናፊ ለመሆን የበቃችው ሜጋን እጆቿን ዘርግታ በምታሳየው ፈገግታ ወይም እርካታ ትለያለች። እአአ በ2019 በፊፋ ኮከብ ተጫዋች ለመሆን የበቃችው ተጫዋቿ ቀላል እና በአድናቂዎች የተወደደ የደስታ አገላለጽ ነው ያላት። ሞ ፋራህ የበርካታ የኦሎምፒክ፣ የዓለም እና የአውሮፓ የረዥም ርቀት ሩጫዎች ሻምፒዮን ነው። ብዙዎችም "የእንግሊዝ የምንግዜም ታላቅ አትሌት" እያሉ ይጠሩታል። ውድድሮችን ሲያሸንፍ "ሞቦት" በማሳየት በጣም ታዋቂ ነው። የሁለቱን አጅቹን ጣቶች በማገናኘት የጭንቅላቱ አናት ላይ በማድረግ የስሙ መነሻ የሆነውን ‘M’ የእንግሊዘኛ ፊደል ይሠራል። ታዋቂው ፖርቹጋላዊ የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት መንገድ አዘጋጅቷል። ይሮጥና ይዘላል፣ አየር ላይ እያለ ይዞርና እጆቹን ወደ ጎን እየወረወረ “ሲ” እያለ ይጮሃል። “ሲ” በፖርቹጋል ቋንቋ አዎ እንደማለት ነው። ደቡብ ኮሪያዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሶን ሄንግ-ሚን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፈው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ይጫወታል። አጥቂው ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት የራሱን ልዩ ምልክት አዘጋጅቷል። አውራ እና ጠቋሚ ጣቶቹን በማገናኘት ያንን ቅጽበት ለመቅረጽ የሚረዳውን ካሜራን የሚወክል ቅርጽ ይሠራል። ስለእነዚህ ምልክተቶች ምን ያስባሉ? ቦልት ዝነኛ ምልክት ያለው ብቸኛው ሰው ባይሆንም በዓለም ዙሪያ በጣም ታዋቂው ነው ማለት ግን ይቻላል። የንግድ ምልክት ማመልከቻው ከተሳካ ደግሞ ምናልባት የበለጠ ዕውቅና ያገኛል። | የስፖርት ኮከቦች እና የንግድ ምልክቶቻቸው- ከቦልት እስከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የአትሌቲክሱ ዓለም ኮከብ እና ፈጣኑ ሰው ዩሴን ቦልት ከውድድር በፊት እና በኋላ የሚያሳየውን ታዋቂ የሆነውን ምልክት ለንግድ ምልክትነት ለመጠቀም ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል። እሱ ብቻ ግን አይደለም የሚለይበትን ምልክት የሚያሳይ ኮከብ። የአሜሪካ የፓተንት እና የንግድ ምልክት ቢሮ እንደገለጸው ቦልት ታዋቂውን ምልክቱን በንግድ ምልክትነት ለማስመዝገብ ማመልከቻውን ነሐሴ 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ አስገብቷል። መቀመጫቸውን ዋሽንግተን ያደረጉት የንግድ ምልክት ጠበቃው ጆሽ ገርበን “አንድ እጁ ታጥፎ ወደ ጭንቅላቱ ሲጠቆም ሌላኛው እጁ በተመሳሳይ አቅጣጫ ወደ ላይ ከፍ ብሎ እንደሚዘረጋ” ያሳያል ብለዋል። ቦልት ይህን የሚያደርገው ዝነኛ የድል አድራጊነቱን የሚያሳየውን አርማ የንግድ ምልክት በማድረግ ልብሶችን እና የፋሽን ዕቃዎችን ለመሸጥ በማሰቡ ነው። ታዋቂዋ የአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሜጋን ራፒኖ ጎል ካስቆጠረች በኋላ ደስታዋን በምትገልጽበት የተለየ መንገድ ትታወቃለች። ከአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ እና የኦሎምፒክ ወርቅ አሸናፊ ለመሆን የበቃችው ሜጋን እጆቿን ዘርግታ በምታሳየው ፈገግታ ወይም እርካታ ትለያለች። እአአ በ2019 በፊፋ ኮከብ ተጫዋች ለመሆን የበቃችው ተጫዋቿ ቀላል እና በአድናቂዎች የተወደደ የደስታ አገላለጽ ነው ያላት። ሞ ፋራህ የበርካታ የኦሎምፒክ፣ የዓለም እና የአውሮፓ የረዥም ርቀት ሩጫዎች ሻምፒዮን ነው። ብዙዎችም "የእንግሊዝ የምንግዜም ታላቅ አትሌት" እያሉ ይጠሩታል። ውድድሮችን ሲያሸንፍ "ሞቦት" በማሳየት በጣም ታዋቂ ነው። የሁለቱን አጅቹን ጣቶች በማገናኘት የጭንቅላቱ አናት ላይ በማድረግ የስሙ መነሻ የሆነውን ‘M’ የእንግሊዘኛ ፊደል ይሠራል። ታዋቂው ፖርቹጋላዊ የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት መንገድ አዘጋጅቷል። ይሮጥና ይዘላል፣ አየር ላይ እያለ ይዞርና እጆቹን ወደ ጎን እየወረወረ “ሲ” እያለ ይጮሃል። “ሲ” በፖርቹጋል ቋንቋ አዎ እንደማለት ነው። ደቡብ ኮሪያዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሶን ሄንግ-ሚን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፈው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ይጫወታል። አጥቂው ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት የራሱን ልዩ ምልክት አዘጋጅቷል። አውራ እና ጠቋሚ ጣቶቹን በማገናኘት ያንን ቅጽበት ለመቅረጽ የሚረዳውን ካሜራን የሚወክል ቅርጽ ይሠራል። ስለእነዚህ ምልክተቶች ምን ያስባሉ? ቦልት ዝነኛ ምልክት ያለው ብቸኛው ሰው ባይሆንም በዓለም ዙሪያ በጣም ታዋቂው ነው ማለት ግን ይቻላል። የንግድ ምልክት ማመልከቻው ከተሳካ ደግሞ ምናልባት የበለጠ ዕውቅና ያገኛል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/ceknk30j2xxo |
5sports
| እግር ኳስ፡ ዩናይትድ፣ አርሴናል፣ ቼልሲ . . . ምን አስበዋል? | የስፖርት ጋዜጦች ስለ እግር ኳስ ምን እያሉ ነው? በሚቀጥለው ጥር የሚከፈተው የዝውውር መስኮትስ ምን ያሳየን ይሆን?ዋና ዋናዎቹን በዚሀች አጭር ዘገባ እንዳስሳለን። አላንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ኧርሊንግ ብራውት አላንድ ፈላጊው በዝቷል። አሁን ደግሞ ቼልሲዎች ተጫዋቹን ለማስፈረም ዕቅድ እንዳላቸው እየተነገረ ነው። ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲዎች ተጫዋቹ የእኛ ነው እያሉ ነው። ይህን የዘገበው '90 ሚኒት' ጋዜጣ ነው። ቼልሲ አላንድንና የዌስትሃሙን ዴክሌን ራይስ ለማስፈረም ሰባት ተጫዋቾቹን ሊሸጥ እንደሚችል ስካይ ስፖርት ዘግቧል። ባርክሌይ፣ አሎንሶ፣ ሩዲገር፣ ክሪስቴንሰን፣ ጆርጊንሆ፣ ድሪንክዎተርና ሞሰስ ለገበያ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተነግሯል። በሌላ በኩል ማንቸስተር ዩናይትድም አላንድን ማስፈረም ይፈልጋል። ነገር ግን የተጫዋቹ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ከዩናትድ ጋር ያለው ግንኙነት ሰላማዊ ስላልሆነ ችግር ሊፈጥር ይችላል እየተባለ ነው ይላል ሚረር ባወጣው ዘገባ። ዩናይትድ አላንድን ማስፈረም ካልቻለ ፊቱን ወደ ኤቨርተኑን ዶሞኒክ ካልቨርት-ሌዊን ሊያዞር ይችላል። ሩዲገር፡ ቼልሲ ሊሸጣቸው ካሰባቸው ተጫዋቾች መካከል የሆነው ጀርመናዊው አንቶኒዮ ሩዲገር በፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን ይፈለጋል። ይህን ያተመው የፈረንሳዩ 'ለ ፓሪዚያ' ነው። ሊቨርፑል፡ ቀያዮቹ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም አቅደዋል። አርጀንቲናዊው የ34 ዓመት ተጫዋች እዝቄል ጋሬይም በሊቨርፑሎች እየተፈለገ ነው። ይህን ዜና ያሰማው የስፔኑ ቶዶፊቻሄስ ነው። አርሴናል፡ የመድፈኞቹ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ አጥቂ ቪኒሺዬስ ጁኒዬርን ወደ ኤሜሬትስ ለማምጣት አቅደዋል። የ22 ዓመቱ አጥቂ ወደ ኤሜሬትስ በሚቀጥለው ጥር ወር በውሰት ሊመጣ ይችላል ተብሏል። አርቴታ ከወጣቱ አጥቂ በተጨማሪ የ28 ዓመቱን ስፔናዊ አማካይ ኢስኮ፤ ይፈልገዋል። ነገር ግን ተጫዋቹ ወደ ዩቬንቱስ መሄድን ይመርጣል - 'የደይሊ ስታር' እንደዘገበው። ባርሴሎና፡ የካታሎኑ ክለብ የአርሴናሉን ተከላካይ ሹከርዳን መስጣፊን ይፈልገዋል ይላል 'ስፖክስ' ጋዜጣ። የ28 ዓመቱ ሙስጣፊ ከአርሴናል ጋር ያለው ውል እየተገባደደ ነው። ጆንስ፡ የደርቢ ካውንቲ አሠልጣኝ የሆነው ዋይኒ ሩኒ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ፊል ጆንስን ማስፈረም ይሻል። እንደ 'ሜትሮ' ዘገባ ከሆነ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ዕድል ያጣው ጆንስ በዌስትብሮምም ይፈለጋል። የአውሮፓ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ጥር ወር ይከፈታል። ማን ወደ የት ይሄዳል? ጊዜ ይፈታዋል። | እግር ኳስ፡ ዩናይትድ፣ አርሴናል፣ ቼልሲ . . . ምን አስበዋል? የስፖርት ጋዜጦች ስለ እግር ኳስ ምን እያሉ ነው? በሚቀጥለው ጥር የሚከፈተው የዝውውር መስኮትስ ምን ያሳየን ይሆን?ዋና ዋናዎቹን በዚሀች አጭር ዘገባ እንዳስሳለን። አላንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ኧርሊንግ ብራውት አላንድ ፈላጊው በዝቷል። አሁን ደግሞ ቼልሲዎች ተጫዋቹን ለማስፈረም ዕቅድ እንዳላቸው እየተነገረ ነው። ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲዎች ተጫዋቹ የእኛ ነው እያሉ ነው። ይህን የዘገበው '90 ሚኒት' ጋዜጣ ነው። ቼልሲ አላንድንና የዌስትሃሙን ዴክሌን ራይስ ለማስፈረም ሰባት ተጫዋቾቹን ሊሸጥ እንደሚችል ስካይ ስፖርት ዘግቧል። ባርክሌይ፣ አሎንሶ፣ ሩዲገር፣ ክሪስቴንሰን፣ ጆርጊንሆ፣ ድሪንክዎተርና ሞሰስ ለገበያ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተነግሯል። በሌላ በኩል ማንቸስተር ዩናይትድም አላንድን ማስፈረም ይፈልጋል። ነገር ግን የተጫዋቹ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ከዩናትድ ጋር ያለው ግንኙነት ሰላማዊ ስላልሆነ ችግር ሊፈጥር ይችላል እየተባለ ነው ይላል ሚረር ባወጣው ዘገባ። ዩናይትድ አላንድን ማስፈረም ካልቻለ ፊቱን ወደ ኤቨርተኑን ዶሞኒክ ካልቨርት-ሌዊን ሊያዞር ይችላል። ሩዲገር፡ ቼልሲ ሊሸጣቸው ካሰባቸው ተጫዋቾች መካከል የሆነው ጀርመናዊው አንቶኒዮ ሩዲገር በፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን ይፈለጋል። ይህን ያተመው የፈረንሳዩ 'ለ ፓሪዚያ' ነው። ሊቨርፑል፡ ቀያዮቹ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም አቅደዋል። አርጀንቲናዊው የ34 ዓመት ተጫዋች እዝቄል ጋሬይም በሊቨርፑሎች እየተፈለገ ነው። ይህን ዜና ያሰማው የስፔኑ ቶዶፊቻሄስ ነው። አርሴናል፡ የመድፈኞቹ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ አጥቂ ቪኒሺዬስ ጁኒዬርን ወደ ኤሜሬትስ ለማምጣት አቅደዋል። የ22 ዓመቱ አጥቂ ወደ ኤሜሬትስ በሚቀጥለው ጥር ወር በውሰት ሊመጣ ይችላል ተብሏል። አርቴታ ከወጣቱ አጥቂ በተጨማሪ የ28 ዓመቱን ስፔናዊ አማካይ ኢስኮ፤ ይፈልገዋል። ነገር ግን ተጫዋቹ ወደ ዩቬንቱስ መሄድን ይመርጣል - 'የደይሊ ስታር' እንደዘገበው። ባርሴሎና፡ የካታሎኑ ክለብ የአርሴናሉን ተከላካይ ሹከርዳን መስጣፊን ይፈልገዋል ይላል 'ስፖክስ' ጋዜጣ። የ28 ዓመቱ ሙስጣፊ ከአርሴናል ጋር ያለው ውል እየተገባደደ ነው። ጆንስ፡ የደርቢ ካውንቲ አሠልጣኝ የሆነው ዋይኒ ሩኒ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ፊል ጆንስን ማስፈረም ይሻል። እንደ 'ሜትሮ' ዘገባ ከሆነ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ዕድል ያጣው ጆንስ በዌስትብሮምም ይፈለጋል። የአውሮፓ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ጥር ወር ይከፈታል። ማን ወደ የት ይሄዳል? ጊዜ ይፈታዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55435608 |
0business
| ዓለምን ካስጨነቃት የዋጋ ንረት ተጠቃሚዎቹ እነማን ናቸው? | ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጽእኖ ሳያገግም የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት የገጠመው የዓለም ምጣኔ ሃብት ከቀውስ አዙሪት ውስጥ አልወጣም። የነዳጅ እና የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት በመላው ዓለም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ከባድ አድርጎታል። ታዲያ ዓለም በዋጋ ንረት በምትጨነቅበት በአሁኑ ወቅት በተለየ ሁኔታ ትርፍ እያጋበሱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዘርፎች አሉ። እነዚህ ከዋጋ ንረት የሚያተርፉ ድርጅቶች የትኞቹ ናቸው? | ዓለምን ካስጨነቃት የዋጋ ንረት ተጠቃሚዎቹ እነማን ናቸው? ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጽእኖ ሳያገግም የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት የገጠመው የዓለም ምጣኔ ሃብት ከቀውስ አዙሪት ውስጥ አልወጣም። የነዳጅ እና የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት በመላው ዓለም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ከባድ አድርጎታል። ታዲያ ዓለም በዋጋ ንረት በምትጨነቅበት በአሁኑ ወቅት በተለየ ሁኔታ ትርፍ እያጋበሱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዘርፎች አሉ። እነዚህ ከዋጋ ንረት የሚያተርፉ ድርጅቶች የትኞቹ ናቸው? | https://www.bbc.com/amharic/articles/crgj31l8mzzo |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በቫይረሱ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በምርጫ አሸነፉ | በኮሮናቫይረስ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በቅርቡ የተደረገውን ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ አሸንፈዋል። 64 በመቶ የመራጮችንም ድምፅ ማግኘት ችለዋል። በደቡባዊቷ ሮማኒያ በምትገኘው ግዛት ዴቬሴሉ ከንቲባ የነበሩት ኢዮን አሊማን ለሶስተኛ ጊዜም አሸንፈዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት በመዲናዋ ቡካሬስት ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ከንቲባ ስም ከተመራጮች ዝርዝር ውስጥ ነበር። የተመራጮች ዝርዝር ቀድሞ በመታተሙ ስማቸውን ማስወገድ እንዳልተቻለም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት የሞተ ሰው ከንቲባ ሆኖ እንደተመረጠም ተገልጿል። ሌላ ምርጫ እንደሚደረግም ባለስልጣናቱ ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን በርካታ የግዛቲቷ ነዋሪዎች የቀድሞ ከንቲባቸውን ቀብር በመጎብኘት ሃዘናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። በርካታ የመንደሪቷ ሰዎችም በመካነ መቃብሩ ተሰባስበው መታየታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ቪዲዮዎች አሳይተዋል። "ይህ የአንተ ድል ነው" ሲል አንድ ግለሰብ ሲናገር ተሰምቷል። "እውነተኛ ከንቲባችን ነበር" በማለት ሌላ ግለሰብ ለአካባቢው የቴሌቪዥን ጣቢያ መናገሯን ሮይተርስ ዘግቧል። "ሁሉንም የግዛቲቷን ነዋሪ በእኩል አይን ያይ የነበረ፤ ህግንም ያከብር ነበር። እንደሱ አይነት ከንቲባ መቼም አይኖረንም" ግለሰቧ ማለቷንም ሮይተርስ አስነብቧል። የቀድሞ የባህር ኃይል አባል የነበሩት ኢዮን የግራ ክንፍ የሚያዘመው የሶሺያል ዲሞክራት ፓርቲ (ፒኤስዲ) አባል ነበሩ፤ በትናንትናው ዕለትም 57 አመታቸው ይሆን ነበር። በከንቲባነታቸው በህዝባቸው በከፍተኛ ሁኔታ መወደዳቸውም በፓርቲያቸው ዘንድ ጥሩ ስም አስገኝቶላቸዋል። ፓርቲያቸው በአሁኑ በተደረገው አገራዊ ምርጫ በተለያዩ ከተሞችና የምክር ቤቶች መቀመጫቸውን ለቀኝ ክንፍ አክራሪው ዩኤስ አር ፕላስ አሊያስና የአገሪቱን የመንግሥት ስልጣን በበላይነት ለተቆጣጠረው ሴንትሪስት ሊበራል አጥተዋል። በበርካታ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የፍትህ ስርአቱ እንዲሻሻልና የሰፈነው ሙስና እንዲቆም የሚጠይቁ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎም ነው ፒኤስዲ በርካታ መቀመጫዎችን በፖርላመንት በድምፅ እንዲያጣ የተደረገው። የቀድሞ ከንቲባው ኢዮን ከሞቱ በኋላ በምርጫ ማሸነፍ በአገሪቷ የመጀመሪያው ክስተት አይደለም በጎሮጎሳውያኑ 2008 ኔኩላይ ኢቫስኩ የተባሉት ከንቲባም በጉበት በሽታ ከሞቱ በኋላ የቮይነስቲ ግዛት ከንቲባ ሆነዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ በቫይረሱ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በምርጫ አሸነፉ በኮሮናቫይረስ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በቅርቡ የተደረገውን ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ አሸንፈዋል። 64 በመቶ የመራጮችንም ድምፅ ማግኘት ችለዋል። በደቡባዊቷ ሮማኒያ በምትገኘው ግዛት ዴቬሴሉ ከንቲባ የነበሩት ኢዮን አሊማን ለሶስተኛ ጊዜም አሸንፈዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት በመዲናዋ ቡካሬስት ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ከንቲባ ስም ከተመራጮች ዝርዝር ውስጥ ነበር። የተመራጮች ዝርዝር ቀድሞ በመታተሙ ስማቸውን ማስወገድ እንዳልተቻለም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት የሞተ ሰው ከንቲባ ሆኖ እንደተመረጠም ተገልጿል። ሌላ ምርጫ እንደሚደረግም ባለስልጣናቱ ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን በርካታ የግዛቲቷ ነዋሪዎች የቀድሞ ከንቲባቸውን ቀብር በመጎብኘት ሃዘናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። በርካታ የመንደሪቷ ሰዎችም በመካነ መቃብሩ ተሰባስበው መታየታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ቪዲዮዎች አሳይተዋል። "ይህ የአንተ ድል ነው" ሲል አንድ ግለሰብ ሲናገር ተሰምቷል። "እውነተኛ ከንቲባችን ነበር" በማለት ሌላ ግለሰብ ለአካባቢው የቴሌቪዥን ጣቢያ መናገሯን ሮይተርስ ዘግቧል። "ሁሉንም የግዛቲቷን ነዋሪ በእኩል አይን ያይ የነበረ፤ ህግንም ያከብር ነበር። እንደሱ አይነት ከንቲባ መቼም አይኖረንም" ግለሰቧ ማለቷንም ሮይተርስ አስነብቧል። የቀድሞ የባህር ኃይል አባል የነበሩት ኢዮን የግራ ክንፍ የሚያዘመው የሶሺያል ዲሞክራት ፓርቲ (ፒኤስዲ) አባል ነበሩ፤ በትናንትናው ዕለትም 57 አመታቸው ይሆን ነበር። በከንቲባነታቸው በህዝባቸው በከፍተኛ ሁኔታ መወደዳቸውም በፓርቲያቸው ዘንድ ጥሩ ስም አስገኝቶላቸዋል። ፓርቲያቸው በአሁኑ በተደረገው አገራዊ ምርጫ በተለያዩ ከተሞችና የምክር ቤቶች መቀመጫቸውን ለቀኝ ክንፍ አክራሪው ዩኤስ አር ፕላስ አሊያስና የአገሪቱን የመንግሥት ስልጣን በበላይነት ለተቆጣጠረው ሴንትሪስት ሊበራል አጥተዋል። በበርካታ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የፍትህ ስርአቱ እንዲሻሻልና የሰፈነው ሙስና እንዲቆም የሚጠይቁ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎም ነው ፒኤስዲ በርካታ መቀመጫዎችን በፖርላመንት በድምፅ እንዲያጣ የተደረገው። የቀድሞ ከንቲባው ኢዮን ከሞቱ በኋላ በምርጫ ማሸነፍ በአገሪቷ የመጀመሪያው ክስተት አይደለም በጎሮጎሳውያኑ 2008 ኔኩላይ ኢቫስኩ የተባሉት ከንቲባም በጉበት በሽታ ከሞቱ በኋላ የቮይነስቲ ግዛት ከንቲባ ሆነዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54336166 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት? | የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው። በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል። ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል። የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል። በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መንገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል። እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ። ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል። ኦክስጅንና ኦዞን በሌላ መልኩ "አቶሚክ ኦክስጅንን" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል። ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው። ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ "የኦዞን" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል። አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም። 'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር ' በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው። ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል። ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ የአውሮፕላን አካሎችን ማፅዳት ቢቻልም ለማፅዳት ግን ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። ሌላኛው ደግሞ ሲ የሚባለው የአልትራቫዮሌት ጨረር ሲሆን ይህ ጨረር ሳርስ የተባለውን የኮሮናቫይረስ አይነት ማጥፋት ይችላል። ለዚያም ነው ከፍተኛ ወጪ የሌላቸው ጨረሮች የአውሮፕላን አካላትን ለማፅዳት እየተነደፉ እንዲሁም እየተመረቱ ያሉት። ይህንም ተከትሎ በገበያው ላይ የነዚህ ጨረሮች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ምርታቸው በሚቀጥሉት አራት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምርም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በርካታ አማራጮች በርካታ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ አማራጮች ከመኖራቸው አንፃር በተለያየ ሂደትም ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን የትኛው የበለጠ ተስማሚ እንደሆነም እስካሁንም አይታወቅም። የትኛው የፀረ ተህዋሲያን ስርአት የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ከተቻለ በኋላ ምን ያህል ጊዜም ይወስዳል የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነም እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም ስጋት ሆኖ ባለበት ወቅት በርካታ አየር መንገዶች በረራ መጀመራቸው ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነትና ሸክም ተጥሏባቸዋል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች፣ መንገደኞችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ አውሮፕላኖቹ በፀረ ተህዋሲያን መፀዳትም ግዴታ ነው። እነዚህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ ዘዴዎች ቫይረሱን መግታት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገድ ኃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪዎች የሚያስወጣቸውን ዋጋና እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፅዳት የሚችሉበትን ሁኔታ መገምገም ይጠበቅባቸዋል። በአንድ መልኩ የአየር ትራንስፖርቱ ወደቀደመ ሁኔታ እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ሲሆን በሌላ መልኩ በዚህ ወረርሽኝ መካከል የተጓዦች ደህንነት በተጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን መመለስና በወረርሽኙ ምክንያት ያጡትን ገቢ ለማግኘትም አጣጥመው መሄድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም አውሮፕላኖቹ የሚፀዱበትን ደረጃና ያለውን የስጋት መጠንን መቀነስና፤ የሚፀዳበትን ጊዜ አጣጥመው መሄድም ይጠበቅባቸዋል። የመንገደኞችን ጤንትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠትም አየር መንገዶቹ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑም አለም አቀፉ አቪየሽንም መመሪያ ሰጥቷል። ከአለም አቀፉ አቪየሽን ቡድንና፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተመራማሪዎች የተውጣጡ ግለሰቦችም ውጤታማ የሆኑትን የፀረ ተህዋሲያን የማፅጃ ዘዴዎችንም ለመቀየስ ከፍተኛ ምርምሮችን እያደረጉም ነው፤ የተለያዩ መመሪያዎችንም በማውጣትም ላይ ይገኛሉ። | ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት? የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው። በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል። ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል። የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል። በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መንገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል። እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ። ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል። ኦክስጅንና ኦዞን በሌላ መልኩ "አቶሚክ ኦክስጅንን" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል። ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው። ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ "የኦዞን" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል። አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም። 'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር ' በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው። ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል። ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ የአውሮፕላን አካሎችን ማፅዳት ቢቻልም ለማፅዳት ግን ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። ሌላኛው ደግሞ ሲ የሚባለው የአልትራቫዮሌት ጨረር ሲሆን ይህ ጨረር ሳርስ የተባለውን የኮሮናቫይረስ አይነት ማጥፋት ይችላል። ለዚያም ነው ከፍተኛ ወጪ የሌላቸው ጨረሮች የአውሮፕላን አካላትን ለማፅዳት እየተነደፉ እንዲሁም እየተመረቱ ያሉት። ይህንም ተከትሎ በገበያው ላይ የነዚህ ጨረሮች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ምርታቸው በሚቀጥሉት አራት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምርም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በርካታ አማራጮች በርካታ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ አማራጮች ከመኖራቸው አንፃር በተለያየ ሂደትም ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን የትኛው የበለጠ ተስማሚ እንደሆነም እስካሁንም አይታወቅም። የትኛው የፀረ ተህዋሲያን ስርአት የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ከተቻለ በኋላ ምን ያህል ጊዜም ይወስዳል የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነም እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም ስጋት ሆኖ ባለበት ወቅት በርካታ አየር መንገዶች በረራ መጀመራቸው ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነትና ሸክም ተጥሏባቸዋል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች፣ መንገደኞችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ አውሮፕላኖቹ በፀረ ተህዋሲያን መፀዳትም ግዴታ ነው። እነዚህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ ዘዴዎች ቫይረሱን መግታት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገድ ኃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪዎች የሚያስወጣቸውን ዋጋና እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፅዳት የሚችሉበትን ሁኔታ መገምገም ይጠበቅባቸዋል። በአንድ መልኩ የአየር ትራንስፖርቱ ወደቀደመ ሁኔታ እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ሲሆን በሌላ መልኩ በዚህ ወረርሽኝ መካከል የተጓዦች ደህንነት በተጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን መመለስና በወረርሽኙ ምክንያት ያጡትን ገቢ ለማግኘትም አጣጥመው መሄድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም አውሮፕላኖቹ የሚፀዱበትን ደረጃና ያለውን የስጋት መጠንን መቀነስና፤ የሚፀዳበትን ጊዜ አጣጥመው መሄድም ይጠበቅባቸዋል። የመንገደኞችን ጤንትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠትም አየር መንገዶቹ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑም አለም አቀፉ አቪየሽንም መመሪያ ሰጥቷል። ከአለም አቀፉ አቪየሽን ቡድንና፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተመራማሪዎች የተውጣጡ ግለሰቦችም ውጤታማ የሆኑትን የፀረ ተህዋሲያን የማፅጃ ዘዴዎችንም ለመቀየስ ከፍተኛ ምርምሮችን እያደረጉም ነው፤ የተለያዩ መመሪያዎችንም በማውጣትም ላይ ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/53627279 |
3politics
| ቤኒቶ ሙሶሊኒ ላይ የተኮሰችው አየርላንዳዊት | ጊዜው በፈረንጆቹ ሚያዝያ 7 1926 ነበር። ቦታው ደግሞ የጣልያኗ መዲና ሮም። የሃገሬው ሰው በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ ኃያላን መካከል አንዱ የነበረውን ግለሰብ ለማየት ተኮልኩሏል። አንዲት አየርላንዳዊት ሴት ግን በሰውዬው ወሬ ብዙም አልተማረከችም። ዓላማዋ ሌላ ነበር። ድንገት የተኩስ ድምፅ ተሰማ። ሰው ወዲያ ወዲህ ተበታተነ። ለተሰበሰበው ሰው መልዕክቱን ሲያስተላልፍ የነበረው ቤኒቶ ሙሴሊኒም ወደኋላ ተዘረጋ። ጥይቷ የፈለቀችው ከአየርላንዳዊቷ ሴት አፈሙዝ ነበር። ዒላማዋን አልሳተችም። የሙሶሊኒን አፍንጫ ቦረሸችው። ሙሶሊኒ ግን አልሞተም። የጣልያኑ መሪ ከተቃጣበት የግድያ ሙከራ መትረፍ ቻለ። አውሮፓውያን በ20ኛው ክፍለ ዘመን ፋሺስታዊነትን ለመከላከል ከፈፀሟቸው ድርጊቶች መካከል የቫዮሌት ጊብሰን ድርጊት ሁሌም ይነሳል። ሙሶሊኒን ለመግደል ጥረት ካደረጉ አራት ሰዎች መካከል የተሻለ ሙከራ ያደረገችው እሷ ናት። አየርላንዳዊቷ ሙሶሊኒን ለመግደል ሙከራ ካደረገች እነሆ መቶ ዓመት ሊደፍን ጥቂት ዓመታት ይቀሩታል። ይህን ለማሰብ ደብሊን ውስጥ መታሰቢያ እንዲቆምላት ሥራዎች ተጀምረዋል። ቫዮሌት ሙሶሊኒ ላይ ሶስት ጥይቶች ተኩሳለች። አራተኛውን ልትለቀው ስትል ግን ሽጉጧ ነከሰ። ይሄኔ የሙሶሊኒ ጠባቂዎች የከበቧት። የከተማዋ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ በቁጥጥር ሥር ባያውሏት ኖሮ የጠባቂዎቹ ጡጫ ሲሳይ ትሆን ነበር። ጣልያን ውስጥ ታሥራ ከቆች በኋላ ወደ እንግሊዝ እንድትሄድ ተደረገ። ይህ የሆነው ጣልያን ውስጥ የፍርድ ሂደቱ ቢካሄድ ውርደት ይሆናል በሚል ነው ይባላል። ቫዮሌት እንግሊዝ ውስጥ ባለው የቅዱስ አንድሩ የአእምሮ ሕሙማን መታከሚያ ማዕከል ገብታ በስተመጨረሻ በፈረንጆቹ 1956 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ከእንግሊዛዊ አየርላንዳዊ ከበርቴ ቤተሰብ የተወለደችው ቫዮሌት ክዊን ቪክቶሪያ ውስጥ ነበር የምትኖረው። አሁን የደብሊን ከተማ በስሟ መታሰቢያ እንዲቆም ረቂቅ አፅድቆ ወደ ሥራ ገብቷል። የከተማዋ አስተዳደር የሴትዬዋ ድርጊት በታሪክ መዝገብ ብዙም ባለመዘገቡ የሠራችውን 'ፀረ-ፋሺስት' ሥራ የሚዘክር መታሰቢያ ሊቆምላት ይገባል ብሏል። "የብሪታኒያ መንግሥትና ቤተሰቦቿ የሷን ድርጊት እንደ 'እብድ ሰው' ተግባር ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ሊያዩት ይገባል" ይላል ረቂቁ። በጀግንነቷ ምክንያት የተሰቃየችው ረቂቁን ለደብሊን ከተማ ምክር ቤት ያቀረቡት ገለልተኛው የከተማው ምክር ቤት አባል ማኒክስ ፍሊን "ቫዮሌት ጊብሰን በአየርላንድና እንግሊዝ መንግሥታት የተረሳች ናት" ሲሉ ይከራከራሉ። "ልክ እንደበርካታ ሴቶች እጅግ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ብትፈፅምም ተገፍታለች" ሲሉ ለቢቢሲ ሰሜን አየርላንድ ጣቢያ ይናገራሉ። "ቫዮሌት ጊብሰን የሠራችው ሥራ የሚያሳፍር ነው' 'እብድ ናት' በማለት እንድትደበቅ ተደርጋለች።" የቫዮሌት ቤተሰቦች ለመታሠቢያ ኃውልቱ ፈቀድ ሰጥተዋል። በሚቀጥሉት ሳምንታትም ረቂቁ ፀድቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል። መታሰቢያ በልጅነቷ ያደገችበት ደብሊን ውስጥ የሚገኘው የሜሪዬን አደባባይ እንዲሆንም ሐሳብ ቀርቧል። ደብዳቤ ለቸርችል የቫዮሌት ታሪክ ወደ አደባባይ ብቅ ያለው በፈረንጆቹ 2014 አርቲኢ የተሰኘው ራድዮ ጣቢያ በሠራው ዘጋቢ ቅንብር ምክንያት ነው። ዘገባው 'ሙሶሊኒ ላይ የተኮሰችው ሴት' ከተሰኘው መፅሐፍ ላይ የተወሰደ ነው። ታሪኳ ላይ እንደተመዘገበው ቫዮሌት ከቅዱስ አንድሩ ሆስፒታል እንድትለቀቅ በወቅቱ ለነበሩ ኃያላን መሪዎች ደብዳቤ ፅፋ ነበር። ከእነዚህ መካከል የአሁኗ የእንግሊዝ ንግሥት ኤሊዛቤት ይገኙበታል። ሌላኛው ደብዳቤ የተላከው በወቅቱ የእንግሊዝ መሪ ለነበሩት ዊንስተን ቸርችል ነበር። ቸርችል በደብሊን ከተማ ባደጉ ወቅት ከቫዮሌት ጋር እውቅና ሳይኖራቸው አይቀርም ይላል ታሪኳን የሚዘግበው መፅሐፍ። ለዊንስተን ቸርችል የተፃፈው ደብዳቤ አሁንም አለ። ነገር ግን በወቅቱ ደብዳቤው ለቸርችል ሊደርስ አልቻለም። የራድዮ ዘገባው አዘጋጆች ወደ ጣልያን ሄደው በሠሩት ጥናት መሠረት ሙሶሊኒ ላይ ከተሞከሩ ግድያዎች መካከል ብዙ መረጃ የተሰበሰበው በቫዮሌት ዙሪያ ነው። "ይህን ድርጊት የፈፀመው ወንድ ቢሆን ኖሮ ይሄን ሃውልት ወይም ሌላ መታሰቢያ ተሠርቶለት ነበር። እሷ ሴት ስለነበረች ታሠረች። እኛ ታሪኩን ለሕዝብ ይፋ በማድረጋችን ደስተኞች ነን" ይላሉ የዘገባው አዘጋጆች። ቤኒቶ ሙሶሊኒ ማነው? የሙሶሊኒ ብሔራዊ ፋሺስት ፓርቲ ጣልያን ውስጥ ወደ ሥልጣን የመጣው ከአንደኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ነው። 'ብላክሸርትስ' በተሰኙ ታጣቂዎች የሚደገፈው ፖርቲ ተቀናቃኞችን በኃይል ያስፈራራ ነበር። ፋሺስቱ ፓርቲ በ1920ዎቹ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ዴሞክራሲያዊ የሚባሉ ተቋማትን አፈራረሰ። ሙሶሊኒ የጣልያን አምባገነናዊ መሪ ሆነው የተሾሙት በፈረንጆቹ 1925 ነበር። ሙሶሊኒ በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የጁኔራል ፍራንቺስኮ ፍራንኮ ደጋፊ ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ደግሞ የአዶልፍ ሂትለር ቀኝ እጅ ነበር። ሙሶሊኒ የሂትለርን አንዳንድ ፖሊሲዎች ወስዶ በ1938 የጣልያኑ አይሁዳዊያን ሙሉ በሙሉ መብታቸው እንዲገፈፍ አድርጎ ነበር። በአይሁዶች ጅምላ ጭፍጨፋ [ሆሎኮስት] ወቅት ከ7 ሺህ 500 በላይ የጣልያን አይሁዶች እንደተገደሉ ይታመናል። ኢትዮጵያ በጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ የተወረረችው በሙሶሊኒ አምባገነናዊ ሥርዓት ወቅት ነበር። ሙሶሊኒ ከምዕራባዊያን ጦር ለማምለጥ ሲሞክር በጣሊያን ነፃ አውጭዎች ተይዞ የተገደለው በፈረንጆቹ 1945 ነው። | ቤኒቶ ሙሶሊኒ ላይ የተኮሰችው አየርላንዳዊት ጊዜው በፈረንጆቹ ሚያዝያ 7 1926 ነበር። ቦታው ደግሞ የጣልያኗ መዲና ሮም። የሃገሬው ሰው በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ ኃያላን መካከል አንዱ የነበረውን ግለሰብ ለማየት ተኮልኩሏል። አንዲት አየርላንዳዊት ሴት ግን በሰውዬው ወሬ ብዙም አልተማረከችም። ዓላማዋ ሌላ ነበር። ድንገት የተኩስ ድምፅ ተሰማ። ሰው ወዲያ ወዲህ ተበታተነ። ለተሰበሰበው ሰው መልዕክቱን ሲያስተላልፍ የነበረው ቤኒቶ ሙሴሊኒም ወደኋላ ተዘረጋ። ጥይቷ የፈለቀችው ከአየርላንዳዊቷ ሴት አፈሙዝ ነበር። ዒላማዋን አልሳተችም። የሙሶሊኒን አፍንጫ ቦረሸችው። ሙሶሊኒ ግን አልሞተም። የጣልያኑ መሪ ከተቃጣበት የግድያ ሙከራ መትረፍ ቻለ። አውሮፓውያን በ20ኛው ክፍለ ዘመን ፋሺስታዊነትን ለመከላከል ከፈፀሟቸው ድርጊቶች መካከል የቫዮሌት ጊብሰን ድርጊት ሁሌም ይነሳል። ሙሶሊኒን ለመግደል ጥረት ካደረጉ አራት ሰዎች መካከል የተሻለ ሙከራ ያደረገችው እሷ ናት። አየርላንዳዊቷ ሙሶሊኒን ለመግደል ሙከራ ካደረገች እነሆ መቶ ዓመት ሊደፍን ጥቂት ዓመታት ይቀሩታል። ይህን ለማሰብ ደብሊን ውስጥ መታሰቢያ እንዲቆምላት ሥራዎች ተጀምረዋል። ቫዮሌት ሙሶሊኒ ላይ ሶስት ጥይቶች ተኩሳለች። አራተኛውን ልትለቀው ስትል ግን ሽጉጧ ነከሰ። ይሄኔ የሙሶሊኒ ጠባቂዎች የከበቧት። የከተማዋ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ በቁጥጥር ሥር ባያውሏት ኖሮ የጠባቂዎቹ ጡጫ ሲሳይ ትሆን ነበር። ጣልያን ውስጥ ታሥራ ከቆች በኋላ ወደ እንግሊዝ እንድትሄድ ተደረገ። ይህ የሆነው ጣልያን ውስጥ የፍርድ ሂደቱ ቢካሄድ ውርደት ይሆናል በሚል ነው ይባላል። ቫዮሌት እንግሊዝ ውስጥ ባለው የቅዱስ አንድሩ የአእምሮ ሕሙማን መታከሚያ ማዕከል ገብታ በስተመጨረሻ በፈረንጆቹ 1956 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ከእንግሊዛዊ አየርላንዳዊ ከበርቴ ቤተሰብ የተወለደችው ቫዮሌት ክዊን ቪክቶሪያ ውስጥ ነበር የምትኖረው። አሁን የደብሊን ከተማ በስሟ መታሰቢያ እንዲቆም ረቂቅ አፅድቆ ወደ ሥራ ገብቷል። የከተማዋ አስተዳደር የሴትዬዋ ድርጊት በታሪክ መዝገብ ብዙም ባለመዘገቡ የሠራችውን 'ፀረ-ፋሺስት' ሥራ የሚዘክር መታሰቢያ ሊቆምላት ይገባል ብሏል። "የብሪታኒያ መንግሥትና ቤተሰቦቿ የሷን ድርጊት እንደ 'እብድ ሰው' ተግባር ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ሊያዩት ይገባል" ይላል ረቂቁ። በጀግንነቷ ምክንያት የተሰቃየችው ረቂቁን ለደብሊን ከተማ ምክር ቤት ያቀረቡት ገለልተኛው የከተማው ምክር ቤት አባል ማኒክስ ፍሊን "ቫዮሌት ጊብሰን በአየርላንድና እንግሊዝ መንግሥታት የተረሳች ናት" ሲሉ ይከራከራሉ። "ልክ እንደበርካታ ሴቶች እጅግ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ብትፈፅምም ተገፍታለች" ሲሉ ለቢቢሲ ሰሜን አየርላንድ ጣቢያ ይናገራሉ። "ቫዮሌት ጊብሰን የሠራችው ሥራ የሚያሳፍር ነው' 'እብድ ናት' በማለት እንድትደበቅ ተደርጋለች።" የቫዮሌት ቤተሰቦች ለመታሠቢያ ኃውልቱ ፈቀድ ሰጥተዋል። በሚቀጥሉት ሳምንታትም ረቂቁ ፀድቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል። መታሰቢያ በልጅነቷ ያደገችበት ደብሊን ውስጥ የሚገኘው የሜሪዬን አደባባይ እንዲሆንም ሐሳብ ቀርቧል። ደብዳቤ ለቸርችል የቫዮሌት ታሪክ ወደ አደባባይ ብቅ ያለው በፈረንጆቹ 2014 አርቲኢ የተሰኘው ራድዮ ጣቢያ በሠራው ዘጋቢ ቅንብር ምክንያት ነው። ዘገባው 'ሙሶሊኒ ላይ የተኮሰችው ሴት' ከተሰኘው መፅሐፍ ላይ የተወሰደ ነው። ታሪኳ ላይ እንደተመዘገበው ቫዮሌት ከቅዱስ አንድሩ ሆስፒታል እንድትለቀቅ በወቅቱ ለነበሩ ኃያላን መሪዎች ደብዳቤ ፅፋ ነበር። ከእነዚህ መካከል የአሁኗ የእንግሊዝ ንግሥት ኤሊዛቤት ይገኙበታል። ሌላኛው ደብዳቤ የተላከው በወቅቱ የእንግሊዝ መሪ ለነበሩት ዊንስተን ቸርችል ነበር። ቸርችል በደብሊን ከተማ ባደጉ ወቅት ከቫዮሌት ጋር እውቅና ሳይኖራቸው አይቀርም ይላል ታሪኳን የሚዘግበው መፅሐፍ። ለዊንስተን ቸርችል የተፃፈው ደብዳቤ አሁንም አለ። ነገር ግን በወቅቱ ደብዳቤው ለቸርችል ሊደርስ አልቻለም። የራድዮ ዘገባው አዘጋጆች ወደ ጣልያን ሄደው በሠሩት ጥናት መሠረት ሙሶሊኒ ላይ ከተሞከሩ ግድያዎች መካከል ብዙ መረጃ የተሰበሰበው በቫዮሌት ዙሪያ ነው። "ይህን ድርጊት የፈፀመው ወንድ ቢሆን ኖሮ ይሄን ሃውልት ወይም ሌላ መታሰቢያ ተሠርቶለት ነበር። እሷ ሴት ስለነበረች ታሠረች። እኛ ታሪኩን ለሕዝብ ይፋ በማድረጋችን ደስተኞች ነን" ይላሉ የዘገባው አዘጋጆች። ቤኒቶ ሙሶሊኒ ማነው? የሙሶሊኒ ብሔራዊ ፋሺስት ፓርቲ ጣልያን ውስጥ ወደ ሥልጣን የመጣው ከአንደኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ነው። 'ብላክሸርትስ' በተሰኙ ታጣቂዎች የሚደገፈው ፖርቲ ተቀናቃኞችን በኃይል ያስፈራራ ነበር። ፋሺስቱ ፓርቲ በ1920ዎቹ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ዴሞክራሲያዊ የሚባሉ ተቋማትን አፈራረሰ። ሙሶሊኒ የጣልያን አምባገነናዊ መሪ ሆነው የተሾሙት በፈረንጆቹ 1925 ነበር። ሙሶሊኒ በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የጁኔራል ፍራንቺስኮ ፍራንኮ ደጋፊ ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ደግሞ የአዶልፍ ሂትለር ቀኝ እጅ ነበር። ሙሶሊኒ የሂትለርን አንዳንድ ፖሊሲዎች ወስዶ በ1938 የጣልያኑ አይሁዳዊያን ሙሉ በሙሉ መብታቸው እንዲገፈፍ አድርጎ ነበር። በአይሁዶች ጅምላ ጭፍጨፋ [ሆሎኮስት] ወቅት ከ7 ሺህ 500 በላይ የጣልያን አይሁዶች እንደተገደሉ ይታመናል። ኢትዮጵያ በጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ የተወረረችው በሙሶሊኒ አምባገነናዊ ሥርዓት ወቅት ነበር። ሙሶሊኒ ከምዕራባዊያን ጦር ለማምለጥ ሲሞክር በጣሊያን ነፃ አውጭዎች ተይዞ የተገደለው በፈረንጆቹ 1945 ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-56145284 |
0business
| ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? | ኮሮናቫይረስ የማይነካው ነገር እንደሌለ እየታየ ነው። በየሰበብ አስባቡ እያሻቀበ የነበረውን ነዳጅ ዘይትን ሊነካው ዳርዳር እያለ ነው። በሽታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ትልልቆቹ የነዳጅ አምራች አገራት በሽታው ካስከተለው ችግር ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ምርታቸው ሊቀንስ ይችላል እየተባለ ነው። የነዳጅ ዋጋን ለመደገፍ እርምጃ እንዲወሰድ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነዳጅ አምራች አገራት ማህበር የሆነው ኦፔክ እና አጋሮቹ በዚህ ሳምንት ስብሰባ እንደሚቀመጡ እየተጠበቀ ነው። • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • አባቱ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረው አካል ጉዳተኛ ታዳጊ ሞተ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ዋጋ በዓመት ውስጥ ከታየው ከፍ ብሎ በ20 በመቶ ካሻቀበ በኋላ አሽቆልቁሎ ዝቅተኛው ዋጋው ላይ ይገኛል። ስለምን ይህ የቫይረስ ወረርሽኝ እንዲህ ያለው ከፍተኛ ተጽእኖን በዓለም አቀፉ የኃይል ገበያ ላይ ሊያስከትል ቻለ? የቻይናዊያን አዲስ ዓመት የበዓል ጊዜ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በበሽታው ምክንያት በመራዘሙና የጉዞ እገዳ በመደረጉ ፋብሪካዎች፣ ቢሮዎችና መደብሮች ዝግ ሆነው ይገኛሉ። ይህም ማለት አስከ 14 ሚሊዮን በርሜሎችን በቀን ውስጥ የምትጠቀመውና የዓለማችን ትልቋ የድፍድፍ ነዳጅ ገዢ አገር የሆነችው ቻይና ማሽኖቿን ለማንቀሳቀስ፣ ለተሽከርካሪዎችና ለኤሌክትሪክ ኃይል ወትሮ ከምትፈልገው ነዳጅ ዘይት በእጅጉ የቀነሰውን እንድትጠቀም አድርጓታል። በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጓቸውን በረራዎች በማቋረጣቸው የተነሳና በቻይና ውስጥ ባለው የጉዞ እገዳ ሳቢያ በረራዎች በመቀነሳቸው ለአውሮፕላን ነዳጅ ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ተብሎ ይታሰባል። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? • ካሜሮናዊው በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ብሉምበርግ በዚህ ሳምንት እንደዘገበው የቻይና ዕለታዊ የድፍድፍ ነዳጅ ፍጆታ በ20 በመቶ ቀንሷል። ይህም ማለት ብሪታኒያና ጣሊያን በአንድ ላይ በቀን የሚያስፈልጋቸውን ነው። በዚህም ሳቢያ በቻይና መንግሥት የሚተዳደረው የእስያ አህጉር ትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ሲኖፔክ በየቀኑ የሚያጣራውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን በ600 ሺህ በርሜሎች ቀንሷል። ይህም ከሥራው 12 በመቶው አቁሟል ማለት ሲሆን ከ10 ዓመታት በላይ ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛው ቅናሽ ነው። በነዳጅ ዘይት ላይ የታየው ከፍተኛ ቅናሽ የኃይል ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳሰበው የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። በነዳጅ ፍላጎት ላይ የተከሰተው ከፍተኛ ቅናሽ በቻይና ውስጥ የተከሰተውን የሥራ መቀዛቀዝን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው። በተጨማሪም ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ቻይናን ካጋጠማት የኢኮኖሚ ዕድገት መቀነስ ክስተት ውስጥ ዝቅተኛው ማጋጠሙ ደግሞ የነዳጅ ፍጆታዋን የበለጠ ይቀንሰዋል ተብሏል። የተባሉት በቻይና የሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑነት ዣንግ ሚንግ እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ባሉት ሦስት ወራት የአገሪቱን ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ከ5 በመቶ በታች ሊያወርደው ይችላል። • "ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል" ያደጉት አገራት እድገታቸውን ለማጠናከር ትግል በሚያደርጉበት ጊዜ ቻይና የዓለማችን ሁለተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚና ለዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት አንቀሳቃሽ ሞተር ናት። የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ክሪስታሊና ጆርጂዮቫ ባዚህ ሳምንት እንዳሉት ወረርሽኙ ቢያንስ ለአጭር ጊዜ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ያቀዛቅዘዋል፤ ነገር ግን የወደፊቱን ለመናገር አሁን ጊዜው ገና እንደሆነም አመልክተዋል። እያሽቆለቆለ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለማሳደግ ታላላቆቹ የዓለም ነዳጅ ዘይት አምራቾች ለገበያ የሚያቀርቡትን ምርት በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንደሚወያዩ እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ክስተት ለነዳጅ የለውን ፍላጎት እንዲቀንስ በማድረጉ ምክንያት የነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ማኅበር የሆነው ኦፔክ አባል የሆነችው ኢራን ሰኞ ዕለት እየወደቀ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለመደገፍ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በይፋ ጠይቃለች። የኦፔክ አባል አገራትና ሩሲያ በዚህ ሳምንት ያደርጉታል ተብሎ በሚጠበቀው ስብሰባ ላይ በቀን ለገበያ ከሚያርቡት የነዳጅ ምርት ከ500 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን በርሜል የሚደርሰውን ለመቀነስ ይወያያሉ ተብሏል። | ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? ኮሮናቫይረስ የማይነካው ነገር እንደሌለ እየታየ ነው። በየሰበብ አስባቡ እያሻቀበ የነበረውን ነዳጅ ዘይትን ሊነካው ዳርዳር እያለ ነው። በሽታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ትልልቆቹ የነዳጅ አምራች አገራት በሽታው ካስከተለው ችግር ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ምርታቸው ሊቀንስ ይችላል እየተባለ ነው። የነዳጅ ዋጋን ለመደገፍ እርምጃ እንዲወሰድ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነዳጅ አምራች አገራት ማህበር የሆነው ኦፔክ እና አጋሮቹ በዚህ ሳምንት ስብሰባ እንደሚቀመጡ እየተጠበቀ ነው። • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • አባቱ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረው አካል ጉዳተኛ ታዳጊ ሞተ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ዋጋ በዓመት ውስጥ ከታየው ከፍ ብሎ በ20 በመቶ ካሻቀበ በኋላ አሽቆልቁሎ ዝቅተኛው ዋጋው ላይ ይገኛል። ስለምን ይህ የቫይረስ ወረርሽኝ እንዲህ ያለው ከፍተኛ ተጽእኖን በዓለም አቀፉ የኃይል ገበያ ላይ ሊያስከትል ቻለ? የቻይናዊያን አዲስ ዓመት የበዓል ጊዜ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በበሽታው ምክንያት በመራዘሙና የጉዞ እገዳ በመደረጉ ፋብሪካዎች፣ ቢሮዎችና መደብሮች ዝግ ሆነው ይገኛሉ። ይህም ማለት አስከ 14 ሚሊዮን በርሜሎችን በቀን ውስጥ የምትጠቀመውና የዓለማችን ትልቋ የድፍድፍ ነዳጅ ገዢ አገር የሆነችው ቻይና ማሽኖቿን ለማንቀሳቀስ፣ ለተሽከርካሪዎችና ለኤሌክትሪክ ኃይል ወትሮ ከምትፈልገው ነዳጅ ዘይት በእጅጉ የቀነሰውን እንድትጠቀም አድርጓታል። በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጓቸውን በረራዎች በማቋረጣቸው የተነሳና በቻይና ውስጥ ባለው የጉዞ እገዳ ሳቢያ በረራዎች በመቀነሳቸው ለአውሮፕላን ነዳጅ ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ተብሎ ይታሰባል። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? • ካሜሮናዊው በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ብሉምበርግ በዚህ ሳምንት እንደዘገበው የቻይና ዕለታዊ የድፍድፍ ነዳጅ ፍጆታ በ20 በመቶ ቀንሷል። ይህም ማለት ብሪታኒያና ጣሊያን በአንድ ላይ በቀን የሚያስፈልጋቸውን ነው። በዚህም ሳቢያ በቻይና መንግሥት የሚተዳደረው የእስያ አህጉር ትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ሲኖፔክ በየቀኑ የሚያጣራውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን በ600 ሺህ በርሜሎች ቀንሷል። ይህም ከሥራው 12 በመቶው አቁሟል ማለት ሲሆን ከ10 ዓመታት በላይ ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛው ቅናሽ ነው። በነዳጅ ዘይት ላይ የታየው ከፍተኛ ቅናሽ የኃይል ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳሰበው የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። በነዳጅ ፍላጎት ላይ የተከሰተው ከፍተኛ ቅናሽ በቻይና ውስጥ የተከሰተውን የሥራ መቀዛቀዝን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው። በተጨማሪም ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ቻይናን ካጋጠማት የኢኮኖሚ ዕድገት መቀነስ ክስተት ውስጥ ዝቅተኛው ማጋጠሙ ደግሞ የነዳጅ ፍጆታዋን የበለጠ ይቀንሰዋል ተብሏል። የተባሉት በቻይና የሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑነት ዣንግ ሚንግ እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ባሉት ሦስት ወራት የአገሪቱን ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ከ5 በመቶ በታች ሊያወርደው ይችላል። • "ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል" ያደጉት አገራት እድገታቸውን ለማጠናከር ትግል በሚያደርጉበት ጊዜ ቻይና የዓለማችን ሁለተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚና ለዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት አንቀሳቃሽ ሞተር ናት። የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ክሪስታሊና ጆርጂዮቫ ባዚህ ሳምንት እንዳሉት ወረርሽኙ ቢያንስ ለአጭር ጊዜ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ያቀዛቅዘዋል፤ ነገር ግን የወደፊቱን ለመናገር አሁን ጊዜው ገና እንደሆነም አመልክተዋል። እያሽቆለቆለ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለማሳደግ ታላላቆቹ የዓለም ነዳጅ ዘይት አምራቾች ለገበያ የሚያቀርቡትን ምርት በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንደሚወያዩ እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ክስተት ለነዳጅ የለውን ፍላጎት እንዲቀንስ በማድረጉ ምክንያት የነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ማኅበር የሆነው ኦፔክ አባል የሆነችው ኢራን ሰኞ ዕለት እየወደቀ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለመደገፍ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በይፋ ጠይቃለች። የኦፔክ አባል አገራትና ሩሲያ በዚህ ሳምንት ያደርጉታል ተብሎ በሚጠበቀው ስብሰባ ላይ በቀን ለገበያ ከሚያርቡት የነዳጅ ምርት ከ500 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን በርሜል የሚደርሰውን ለመቀነስ ይወያያሉ ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-51368390 |
5sports
| በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የቤልግሬዱ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና | ሰርቢያ ቤልግሬድ ውስጥ ዛሬ ከመጋቢት 9 ተጀምሮ አስከ 11/2014 ዓ.ም በሚቆየው የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና አፍሪካዊያን አትሌቶች ሜዳሊያ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኬንያዊው አትሌት ፈርዲናንድ ኦሙርዋ ኦማንያላ ከእነዚህ መካከል አንዱ ሲሆን የዩሴይን ቦልትን የ100 ሜትር የዓለም ክብረወሰን መስበር እንደሚችል ተናግሯል። ኬንያዊው አትሌት በሰርቢያው ሻምፒዮና ውድድሩን 60 ሜትር ይጀምራል። የ26 ዓመቱ አትሌት በ9.77 በሆነ ሰከንድ የአፍሪካን የ100 ሜትር ክብረወሰን በእጁ አስገብቷል። በአጭር ርቀት መሻሻል ካሳየ የቦልትን ክብረ ወሰን (9.58 ሰከንድ) ለመስበር እንደሚረዳው ያምናል። "ምንም የማይቻል ነገር የለም ብዬ አምናለሁ። የዓለም ክብረ ወሰን የሚሳካ ነገር ነው" ሲል ኦማንያላ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግሯል። "ይህን ክብረ ወሰን መስበር የሚችል ሰው ካለ እኔ ነኝ ብዬ አምናለሁ።'' "የአፍሪካን ክብረ ወሰን ተመልከቱ። ሩጫ ስጀምር ሰዎች በቅርቡ አይሰበርም ብለው አስበው ነበር። ይህን ግን ባለፈው ዓመት አሳክቻለሁ።'' ይህም የኦማንያላ ክብረወሰን የምንጊዜም ፈታኝ ሰዓቶች ስምንተኛው አድርጎታል። ይህን ግን ያሳካው የ14 ወራት የአበረታች መድኃኒት እገዳ በ2017 ከተጣለበት በኋላ ነው። መድኃኒቱ የተገኘበት በውስጡ ስቴሮይድ አለበት ያለውን የህመም ማስታገሻ ከወሰደ በኋላ መሆኑን ጠቅሶ "በሁኔታው ተጎድቻለሁ" ብሏል። ሻምፒዮን ለመሆን ጣሊያናዊውን የ100 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮን ማርሴል ጃኮብስን እና የወቅቱን የቤት ውስጥ ሻምፒዮን አሜሪካዊውን ክርስቲያን ኮልማንን ማሸነፍ ይኖርበታል። በቤልግሬድ የሚወዳደሩ ሌሎች አፍሪካውያንስ? በ2022ቱ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከ137 አገራት የተውጣጡ 680 አትሌቶች ይሳተፋሉ። ውድድሩ ከመጋቢት 9 እስከ 11/2014 ሰርኒያ ቤልግሬድ ውስጥ ይካሄዳል። ስድስቱ ተጠባቂ አፍሪካዊያን ሰለሞን ባረጋ (ኢትዮጵያ) - የ22 ዓመቱ አትሌት የ10,000 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮን ነው። በ2018 በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር ያገኘውን የብር ሜዳሊያ ለማሻሻል ይወዳደራል። ለሜቻ ግርማ (ኢትዮጵያ) - በ3000 ሜትር መሰናክል የዓለም እና የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ነው። የ21 ዓመቱ አትሌት የ3000 ሜትር አሸናፊ ለመሆን ከሰለሞን ጋር ይፎካከራል። ሳሙኤል ተፈራ (ኢትዮጵያ) - የ1500ሜ የዓለም የቤት ውስጥ ክብረ ወሰን ባለቤት ሲሆን በ2018 በርሚንግሃም ላይ ያገኘውን የወርቅ ሜዳሊያ ለማስጠበቅ ይወዳደራል። ጉዳፍ ፀጋይ (ኢትዮጵያ) - የ5,000 ሜትር የኦሊምፒክ እና የ1500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ 24 ዓመቷ አትሌት በ1500 ሜትር ትጠበቃለች። ኢሴ ብሩሜ (ናይጄሪያ) - የኦሊምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ የ26 ዓመቷ አትሌት፣ የአፍሪካ ሻምፒዮን ናት። በሴቶች የአግድሞሽ ዝላይ ውድድር ትሳተፋለች። ሃሊማ ናካዪ (ኡጋንዳ) - የ27 ዓመቷ አትሌት በ2019 ዶሃ ላይ ባስመዘገበችው የ800 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ላይ ተጨማሪ ድል ለማስመዝገብ ትፎካከራለች። ያሲር ትሪኪ (አልጄሪያ) - ባለሦስትዮሽ ዝላይ (ትሪፕል ጃምፕ) በ16.95 ሜትር በመዝለል ከወቅቱ የዓለም ምርጥ 5ቱ ውስጥ ተካቷል። | በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የቤልግሬዱ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሰርቢያ ቤልግሬድ ውስጥ ዛሬ ከመጋቢት 9 ተጀምሮ አስከ 11/2014 ዓ.ም በሚቆየው የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና አፍሪካዊያን አትሌቶች ሜዳሊያ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኬንያዊው አትሌት ፈርዲናንድ ኦሙርዋ ኦማንያላ ከእነዚህ መካከል አንዱ ሲሆን የዩሴይን ቦልትን የ100 ሜትር የዓለም ክብረወሰን መስበር እንደሚችል ተናግሯል። ኬንያዊው አትሌት በሰርቢያው ሻምፒዮና ውድድሩን 60 ሜትር ይጀምራል። የ26 ዓመቱ አትሌት በ9.77 በሆነ ሰከንድ የአፍሪካን የ100 ሜትር ክብረወሰን በእጁ አስገብቷል። በአጭር ርቀት መሻሻል ካሳየ የቦልትን ክብረ ወሰን (9.58 ሰከንድ) ለመስበር እንደሚረዳው ያምናል። "ምንም የማይቻል ነገር የለም ብዬ አምናለሁ። የዓለም ክብረ ወሰን የሚሳካ ነገር ነው" ሲል ኦማንያላ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግሯል። "ይህን ክብረ ወሰን መስበር የሚችል ሰው ካለ እኔ ነኝ ብዬ አምናለሁ።'' "የአፍሪካን ክብረ ወሰን ተመልከቱ። ሩጫ ስጀምር ሰዎች በቅርቡ አይሰበርም ብለው አስበው ነበር። ይህን ግን ባለፈው ዓመት አሳክቻለሁ።'' ይህም የኦማንያላ ክብረወሰን የምንጊዜም ፈታኝ ሰዓቶች ስምንተኛው አድርጎታል። ይህን ግን ያሳካው የ14 ወራት የአበረታች መድኃኒት እገዳ በ2017 ከተጣለበት በኋላ ነው። መድኃኒቱ የተገኘበት በውስጡ ስቴሮይድ አለበት ያለውን የህመም ማስታገሻ ከወሰደ በኋላ መሆኑን ጠቅሶ "በሁኔታው ተጎድቻለሁ" ብሏል። ሻምፒዮን ለመሆን ጣሊያናዊውን የ100 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮን ማርሴል ጃኮብስን እና የወቅቱን የቤት ውስጥ ሻምፒዮን አሜሪካዊውን ክርስቲያን ኮልማንን ማሸነፍ ይኖርበታል። በቤልግሬድ የሚወዳደሩ ሌሎች አፍሪካውያንስ? በ2022ቱ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከ137 አገራት የተውጣጡ 680 አትሌቶች ይሳተፋሉ። ውድድሩ ከመጋቢት 9 እስከ 11/2014 ሰርኒያ ቤልግሬድ ውስጥ ይካሄዳል። ስድስቱ ተጠባቂ አፍሪካዊያን ሰለሞን ባረጋ (ኢትዮጵያ) - የ22 ዓመቱ አትሌት የ10,000 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮን ነው። በ2018 በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር ያገኘውን የብር ሜዳሊያ ለማሻሻል ይወዳደራል። ለሜቻ ግርማ (ኢትዮጵያ) - በ3000 ሜትር መሰናክል የዓለም እና የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ነው። የ21 ዓመቱ አትሌት የ3000 ሜትር አሸናፊ ለመሆን ከሰለሞን ጋር ይፎካከራል። ሳሙኤል ተፈራ (ኢትዮጵያ) - የ1500ሜ የዓለም የቤት ውስጥ ክብረ ወሰን ባለቤት ሲሆን በ2018 በርሚንግሃም ላይ ያገኘውን የወርቅ ሜዳሊያ ለማስጠበቅ ይወዳደራል። ጉዳፍ ፀጋይ (ኢትዮጵያ) - የ5,000 ሜትር የኦሊምፒክ እና የ1500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ 24 ዓመቷ አትሌት በ1500 ሜትር ትጠበቃለች። ኢሴ ብሩሜ (ናይጄሪያ) - የኦሊምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ የ26 ዓመቷ አትሌት፣ የአፍሪካ ሻምፒዮን ናት። በሴቶች የአግድሞሽ ዝላይ ውድድር ትሳተፋለች። ሃሊማ ናካዪ (ኡጋንዳ) - የ27 ዓመቷ አትሌት በ2019 ዶሃ ላይ ባስመዘገበችው የ800 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ላይ ተጨማሪ ድል ለማስመዝገብ ትፎካከራለች። ያሲር ትሪኪ (አልጄሪያ) - ባለሦስትዮሽ ዝላይ (ትሪፕል ጃምፕ) በ16.95 ሜትር በመዝለል ከወቅቱ የዓለም ምርጥ 5ቱ ውስጥ ተካቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60788088 |
3politics
| ምርጫ 2013፡ የምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይገለጻል ተባለ | ሰኞ ዕለት የተካሄደው ምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው ምርጫ ጣቢዎች ውጤቶች ከማክሰኞ ንጋት ጀምሮ ይፋ ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን፤ የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ወደ ምርጫ ክልሎች ከተላኩ በኋላ "ነገ [ረቡእ] እና ከነገ ወዲያ [ሐሙስ] የምርጫ ክልል ውጤት ይፋ ይደረጋል" ሲሉ የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል። የምርጫ ክልል ውጤቶች ደግሞ ከመላው አገሪቱ ወደ ማዕከል ገብተው አስፈላጊው ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ቦርዱ አጠቃላይ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማክሰኞ ከሰዓት በበኋላ በሰጠው መግለጫ እስከ ቀጣይ 10 ቀናት ድረስ ቢያንስ ጊዜያዊ የሆነ የአጠቃላይ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጋለሁ ብሏል። ከዚህ ባሻገር የተለያዩ ግለሰቦች የምርጫ ጣቢያ ውጤቶችን በመያዝ የመጨረሻ ውጤት በማስመሰል ይፋ ከማድረግ ተግራባቸው እንዲቆጠቡ ቦርዱ ጠይቋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በርካታ አክቲቪስቶች እና ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከአንድ ምርጫ ጣቢያ የተገኘ ውጤን መሠረት በማድረግ 'የዚህ ምርጫ ክልል አሸናፊ እከሌ ነው' እያሉ ሲውጁ ተመልክተናል ብለዋል። የምርጫ ውጤቶችን ይፋ ማድረግ የሚችለው ምርጫ ቦርድ ብቻ መሆኑን ያስታወሱት ሶሊያና፤ መሰል ተግባራት "ተቀባይነት የሌለው እና ወንጀል ጭምር ነው" ብለዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን ያክል ሰዎች ድምጽ ለመስጥት ወጡ የሚለው አሃዝ እስካሁን እንደሌለው በመጥቀስ በርካታ ቁጥር ያለው ሰው ግን ድምጽ ለመስጥ መውጣቱን መገንዘቡ ተገልጿል። "በከተማም በገጠርም በርካታ ሕዝብ ድምጽ ለመስጥት ወጥቷል። ይህም በጣም አስደሳች ነበር" ብለዋል የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ። ሰኞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄደው ምርጫ የተሰጡትን ድምጾች በመቁጠር ከማክሰኞ ጠዋት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ሲሆን በበርካታ ቦታዎች ውጤቶች ታውቀዋል። ከዚህ ባሻገር በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠሙ መስተጓጎሎች ሰኞ ዕለት ድምጽ ሳይሰጥባቸው በቀሩ አካባቢዎች ዛሬ ማክሰኞ ዕለት መራጮች ድምጽ ሰሰጡ ውለዋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ በሆቴል ክፍላቸው ውስጥ ሕይወታቸው አልፎ ስለተገኙት አሜሪካዊ ግለሰብን በተመለከተም ቦርዱ ክስተቱን ከፖሊስ መስማቱን ተናግረዋል። "ግለሰቡ በሆቴል ክፍላቸው ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱን ሰምተናል። ሆቴል ክፍላቸው ወድቀው ነው የተገኙት። እጅግ አሳዛኝ አጋጣሚ ነው" ካሉ በኋላ የግለሰቡ አሟሟት ከምርጫው ጋር የተገናኘ አለመሆኑን ተናግረዋል። ሶሊያና ግለሰቡ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢ አለመሆናቸውን ጠቅሰው በእንግድነት ከምርጫ ቦርድ ባጅ ወስደው እንደነበረ ተናግረዋል። "የመታዘብ ሥራን የሚሰሩ አልነበሩም። ለእንግዶች የሚሰጥ ባጅ ነው የወሰዱት። ከካርተር ሴንተር ለመታዘብ የመጣ የለም" ብለዋል። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታስቦ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት ተሸጋግሮ በሁለት ዙሮች ምርጫው እንዲካሄድ በተወሰነው መሰረት የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሰኞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ተካሂዷል። ሁለተኛው ዙር ምርጫ በሶማሌና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች ከሁለት ወራት በኋላ ጳጉሜ 01/2013 ዓ.ም ይካሄዳል። | ምርጫ 2013፡ የምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይገለጻል ተባለ ሰኞ ዕለት የተካሄደው ምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው ምርጫ ጣቢዎች ውጤቶች ከማክሰኞ ንጋት ጀምሮ ይፋ ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን፤ የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ወደ ምርጫ ክልሎች ከተላኩ በኋላ "ነገ [ረቡእ] እና ከነገ ወዲያ [ሐሙስ] የምርጫ ክልል ውጤት ይፋ ይደረጋል" ሲሉ የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል። የምርጫ ክልል ውጤቶች ደግሞ ከመላው አገሪቱ ወደ ማዕከል ገብተው አስፈላጊው ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ቦርዱ አጠቃላይ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማክሰኞ ከሰዓት በበኋላ በሰጠው መግለጫ እስከ ቀጣይ 10 ቀናት ድረስ ቢያንስ ጊዜያዊ የሆነ የአጠቃላይ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጋለሁ ብሏል። ከዚህ ባሻገር የተለያዩ ግለሰቦች የምርጫ ጣቢያ ውጤቶችን በመያዝ የመጨረሻ ውጤት በማስመሰል ይፋ ከማድረግ ተግራባቸው እንዲቆጠቡ ቦርዱ ጠይቋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በርካታ አክቲቪስቶች እና ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከአንድ ምርጫ ጣቢያ የተገኘ ውጤን መሠረት በማድረግ 'የዚህ ምርጫ ክልል አሸናፊ እከሌ ነው' እያሉ ሲውጁ ተመልክተናል ብለዋል። የምርጫ ውጤቶችን ይፋ ማድረግ የሚችለው ምርጫ ቦርድ ብቻ መሆኑን ያስታወሱት ሶሊያና፤ መሰል ተግባራት "ተቀባይነት የሌለው እና ወንጀል ጭምር ነው" ብለዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን ያክል ሰዎች ድምጽ ለመስጥት ወጡ የሚለው አሃዝ እስካሁን እንደሌለው በመጥቀስ በርካታ ቁጥር ያለው ሰው ግን ድምጽ ለመስጥ መውጣቱን መገንዘቡ ተገልጿል። "በከተማም በገጠርም በርካታ ሕዝብ ድምጽ ለመስጥት ወጥቷል። ይህም በጣም አስደሳች ነበር" ብለዋል የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ። ሰኞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄደው ምርጫ የተሰጡትን ድምጾች በመቁጠር ከማክሰኞ ጠዋት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ሲሆን በበርካታ ቦታዎች ውጤቶች ታውቀዋል። ከዚህ ባሻገር በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠሙ መስተጓጎሎች ሰኞ ዕለት ድምጽ ሳይሰጥባቸው በቀሩ አካባቢዎች ዛሬ ማክሰኞ ዕለት መራጮች ድምጽ ሰሰጡ ውለዋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ በሆቴል ክፍላቸው ውስጥ ሕይወታቸው አልፎ ስለተገኙት አሜሪካዊ ግለሰብን በተመለከተም ቦርዱ ክስተቱን ከፖሊስ መስማቱን ተናግረዋል። "ግለሰቡ በሆቴል ክፍላቸው ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱን ሰምተናል። ሆቴል ክፍላቸው ወድቀው ነው የተገኙት። እጅግ አሳዛኝ አጋጣሚ ነው" ካሉ በኋላ የግለሰቡ አሟሟት ከምርጫው ጋር የተገናኘ አለመሆኑን ተናግረዋል። ሶሊያና ግለሰቡ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢ አለመሆናቸውን ጠቅሰው በእንግድነት ከምርጫ ቦርድ ባጅ ወስደው እንደነበረ ተናግረዋል። "የመታዘብ ሥራን የሚሰሩ አልነበሩም። ለእንግዶች የሚሰጥ ባጅ ነው የወሰዱት። ከካርተር ሴንተር ለመታዘብ የመጣ የለም" ብለዋል። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታስቦ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት ተሸጋግሮ በሁለት ዙሮች ምርጫው እንዲካሄድ በተወሰነው መሰረት የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሰኞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ተካሂዷል። ሁለተኛው ዙር ምርጫ በሶማሌና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች ከሁለት ወራት በኋላ ጳጉሜ 01/2013 ዓ.ም ይካሄዳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57554222 |
2health
| በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው | በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚተገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው አገሮች ኔዘርላንድ እና ካናዳ ይጠቀሳሉ። ኒው ዚላንዳውያን ባለፈው ወር መሪያቸውን ሲመርጡ ስለ ፈቃድ ሞት እና ዕጸ ፋርስ ሕዝበ ውሳኔ አድርገዋል። ዕጸ ፋርስን ለመዝናኛ መጠቀም ሕጋዊ እንዲሆን ድምጽ የሰጡት 46.1% ብቻ ሲሆኑ፤ 53.1% ተቃውመዋል። የፈቃድ ሞትን ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ጁዲት ኮሊንስም ይደግፉታል። ሕዝቡም ሕጋዊ ይሁን ብሎ እንደሚመርጥ ይጠበቅ ነበር። ባለቤቱ የሞተችበት ማት ቪከርስ "ርህራሄ እና ደግነት አሸንፈዋል። በጠና የታመሙ ኒው ዚላንዳውያን ሕይወታቸውን ማሳለፍ ስለሚችሉ ደስ ብሎኛል" ሲል የተሰማውን ገልጿል። ጠበቃ የነበረችው ባለቤቱ የአንጎል እጢ ሲገኝባት በፈቃዷ ለመሞት ክስ ብትመሠረትም ሳታሸንፍ በጠና ታማ ከአምስት ዓመታት በፊት ሞታለች። "ባለቤቴ መሞት አትሻም ነበር። ማንም ሰው መሞት አይፈልግም። ነገር ግን መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው። ስቃይ እየበረታ ሲሄድ መሞት አንዱ ምርጫ መሆን አለበት" ብሏል። አንድ ሰው በፈቃዱ ለመሞት በጠና የታመመ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖር የተረጋገጠ መሆን አለበት። ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንደሄደና ውሳኔው ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ እንዳለው ማረጋገጥም ተገቢ ነው። ሂደቱ የሚመራው በዶክተር ወይም በነርስ ነው። አንድ ሰው እድሜው ስለገፋ፣ የአእምሮ ህመም ስላለበት ወይም የአካል ጉዳት ስላለበት የፍቃድ ሞት ሕግን መተግበር አይችልም። ሕጉን የሚቃወሙ ሰዎች "እንድንኖር እንጂ እንድንሞት አትርዱን" ሲሉ ምክር ቤት ሄደው ተቃውሞ አሰምተዋል። ሕጉ ለማኅበረሰቡ አስጊ እንደሆነ እና ራስን ማጥፋትን ለመግታት ከወጣ መርህ ጋር እንደሚቃረን ይናገራሉ። ሌላው መከራከሪያ ነጥብ በጠና የታመሙ ሰዎች የቤተሰብ ሸክም ላለመሆን ብለው በፈቃዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ነው። ዩትኔዝያን አጥብቆ ሲተች የነበረ ቡድን "የኒው ዚላንድ ዜጎች የተሳሳተ ሕግ እንዲጸድቅ ድምጽ በመስጠታቸው አዝነናል" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የፈቃድ ሞትን ሕጋዊ ያደረጉ አገሮች የኒው ዚላንድን ሕዝበ ውሳኔ በቅርበት ሲከታተሉ ነበር። ከነዚህ መካከል ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድስ ይጠቀሳሉ። በኔዘርላንድስ በህክምና ታግዞ ራስን ማጥፋት ይቻላል። በአሜሪካ ያሉ ብዙ ግዛቶች እና የአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ በህክምና የታገዘ ሞትን ፈቅደዋል። | በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚተገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው አገሮች ኔዘርላንድ እና ካናዳ ይጠቀሳሉ። ኒው ዚላንዳውያን ባለፈው ወር መሪያቸውን ሲመርጡ ስለ ፈቃድ ሞት እና ዕጸ ፋርስ ሕዝበ ውሳኔ አድርገዋል። ዕጸ ፋርስን ለመዝናኛ መጠቀም ሕጋዊ እንዲሆን ድምጽ የሰጡት 46.1% ብቻ ሲሆኑ፤ 53.1% ተቃውመዋል። የፈቃድ ሞትን ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ጁዲት ኮሊንስም ይደግፉታል። ሕዝቡም ሕጋዊ ይሁን ብሎ እንደሚመርጥ ይጠበቅ ነበር። ባለቤቱ የሞተችበት ማት ቪከርስ "ርህራሄ እና ደግነት አሸንፈዋል። በጠና የታመሙ ኒው ዚላንዳውያን ሕይወታቸውን ማሳለፍ ስለሚችሉ ደስ ብሎኛል" ሲል የተሰማውን ገልጿል። ጠበቃ የነበረችው ባለቤቱ የአንጎል እጢ ሲገኝባት በፈቃዷ ለመሞት ክስ ብትመሠረትም ሳታሸንፍ በጠና ታማ ከአምስት ዓመታት በፊት ሞታለች። "ባለቤቴ መሞት አትሻም ነበር። ማንም ሰው መሞት አይፈልግም። ነገር ግን መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው። ስቃይ እየበረታ ሲሄድ መሞት አንዱ ምርጫ መሆን አለበት" ብሏል። አንድ ሰው በፈቃዱ ለመሞት በጠና የታመመ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖር የተረጋገጠ መሆን አለበት። ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንደሄደና ውሳኔው ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ እንዳለው ማረጋገጥም ተገቢ ነው። ሂደቱ የሚመራው በዶክተር ወይም በነርስ ነው። አንድ ሰው እድሜው ስለገፋ፣ የአእምሮ ህመም ስላለበት ወይም የአካል ጉዳት ስላለበት የፍቃድ ሞት ሕግን መተግበር አይችልም። ሕጉን የሚቃወሙ ሰዎች "እንድንኖር እንጂ እንድንሞት አትርዱን" ሲሉ ምክር ቤት ሄደው ተቃውሞ አሰምተዋል። ሕጉ ለማኅበረሰቡ አስጊ እንደሆነ እና ራስን ማጥፋትን ለመግታት ከወጣ መርህ ጋር እንደሚቃረን ይናገራሉ። ሌላው መከራከሪያ ነጥብ በጠና የታመሙ ሰዎች የቤተሰብ ሸክም ላለመሆን ብለው በፈቃዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ነው። ዩትኔዝያን አጥብቆ ሲተች የነበረ ቡድን "የኒው ዚላንድ ዜጎች የተሳሳተ ሕግ እንዲጸድቅ ድምጽ በመስጠታቸው አዝነናል" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የፈቃድ ሞትን ሕጋዊ ያደረጉ አገሮች የኒው ዚላንድን ሕዝበ ውሳኔ በቅርበት ሲከታተሉ ነበር። ከነዚህ መካከል ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድስ ይጠቀሳሉ። በኔዘርላንድስ በህክምና ታግዞ ራስን ማጥፋት ይቻላል። በአሜሪካ ያሉ ብዙ ግዛቶች እና የአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ በህክምና የታገዘ ሞትን ፈቅደዋል። | https://www.bbc.com/amharic/54744271 |
0business
| "የቻይናና የአሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ከኮሮናቫይረስ በላይ ለዓለም ያሰጋል" | በመጪዎቹ ዓመታት በአሜሪካና በቻይና መካከል ሊከሰት የሚችለው ቀዝቃዛ ጦርነት ዓለምን ከኮሮናቫይረስ በላይ ሊያስጨንቅ እንደሚገባ ዕውቁ የምጣኔ ሀብት ሊቅ ጄፍሪ ሳክስ ተናገሩ። የኮሎምቢያው ዩኒቨርስቲ ዕውቅ ፕሮፌሰር ጄፍ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዓለም ወደ አንዳች መደነቃቀፍ እያመራች ነው፤ መሪ አልባም ሆናለች ብለዋል። እንዲሁም የዓለም ሁኔታ መልክ ባልያዘበት ሁኔታ በሁለቱ የዓለም ኃያላን መካከል ያለው ቁርሾና ቅራኔ እየባሰ ከሄደ ሁኔታዎችን ያባብሳል፤ ጦሱም ለተቀረው ዓለም ይተርፋል ብለዋል። እኚህ ፕሮፌሰር ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ አሜሪካና አመራሯ ነው ብለዋል። • አገራዊ መድረክ ማዘጋጀት እንጂ ከህወሓት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይትን አንቀበልም፡ ደብረፅዮን (ዶ/ር) • "አባላቶቻችን በአካባቢው ይህን የደንብ ልብስ መልበስ ካቆሙ ስድስት ወራት አልፈዋል" የኦሮሚያ ፖሊስ አሁን ያለው የአሜሪካ አመራር ከትብብር ይልቅ ክፍፍልን የሚያፋፍም ነው ሲሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አመራሩ አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት ከቻይና ጋር ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ዓለምን ዳግም ወደ ሰላም ለመመለስ በጣም ይቸገራል" ብለዋል ፕሮፌሰሩ። የፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ አስተያየት የመጣው ሰሞኑን ቻይናና አሜሪካ ከምጣኔ ሀብት ጦርነት ጋር ብቻም ሳይሆን ፖለቲካዊ መቆራቆዝ ውስጥ እየገቡ ስለመሆኑ ምልክቶች መታየታቸውን ተከትሎ ነው። በያዝነው ሳምንት ለምሳሌ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በቻይና ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የሚጥለው ሰነድ ላይ ይፈርማሉ ተብሏል። ማዕቀቡን የሚጥሉት በዢንጂያንግ ግዛት የቻይና ሙስሊሞችን ለርዕዮተ ዓለም ጥምቀት ማጎርያ ውስጥ መከተታቸውን ተከትሎ ነው። ያም ሆኖ የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞው የደኅንነት አማካሪ ሰሞኑን ለአንባቢዎች ያደርሱታል በተባለው አዲስ መጽሐፋቸው እንደጠቀሱት፤ ፕሬዝዳንቱ ቻይና ይህንን የሙስሊሞች ማጎርያ እንድትገነባ አበረታተው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ ከዎልስትሪት ጆርናል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቻይና ኮሮናቫይረስን ለዓለም ያቀበለችውና ብሎም ያሰራጨችው ሆን ብላ የአሜሪካንን ምጣኔ ሀብት ለማንኮታኮት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናና የአሜሪካንን የኢኮኖሚ ጦርነት ካመላከቱ ነገሮች አንዱ አሜሪካ በቻይናው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ላይ የጣለችው እቀባ ነው። አሜሪካ እንደምትለው ሁዋዌ የደንበኞችን መረጃ ለመሰለል የተቋቋመ ነው። ቻይና ይህንን ክስ ታስተባብላለች። የቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ የደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አዲስ በጻፉት መጽሐፍ እንዳጋለጡት ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ ህዋዌ ላይ እቀባ ያደረጉት በድጋሚ የመመረጥ ዕድላቸውን ለማስፋት ብቻ ነው። • ትራምፕ እንዳይታተም ባሉት መጽሐፍ ይፋ የሚደረጉ 6 ምስጢሮች • በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ድርድር፡ የግብፅ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ውሳኔ ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስም በዚህ የቦልተን ሐሳብ ይስማማሉ። ሁዋዌን ትራምፕ ያገዱት የምርም የደኅንነት ጉዳይ አሳስቧቸው ሊሆን አይችልም። "አሜሪካ በ5ጂ የሞባይል ቴክኖሎጂ ተቀድማለች። ሁዋዌ ደግሞ የዓለምን የገበያ ድርሻ ተቀራምቶታል፤ ይህ ነው አሜሪካንን የረበሻት" ይላሉ። ከቻይና ጋር ፍጥጫ ላይ ያለችው አገር አሜሪካ ብቻ አይደለችም። ቻይና ባለፈው ሳምንት ከሕንድ ጋር የድንበር ግጭት ውስጥ ገብታ 20 የሕንድ ወታደሮችን መገደላቸው አይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እናዳለ ቻይና በፓኪስታን፣ በምያንማር፣ በሲሪሊንካና በኔፓል በርካታ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እያገዘች ነው። እነዚህ አገራት ደግሞ የሕንድ ጎረቤቶች ናቸው። ሕንድ ቻይና የአካባቢው ተጽእኖ ፈጣሪ አገር የመሆኗን ጉዳይ ማስቆም ትፈልጋለች። ፕሮፌሰር ሳክስ እንደሚያምኑት ቻይና በአካባቢው አገራት ላይ የትብብር መንፈስ ካሳየች ነገሮች የተሻሉ ይሆናሉ። ቻይና እድሏ ያለው በእጇ ነው። ቻይና ተባባሪ ከሆነች፣ በዲፕሎማሲ ችግሮችን ለመፍታት ከፈለገችና የትብብር መንፈስ ካሳየች ጉልበት ያላት አገር ስለሆነች ብዙ ነገር መቀየር ትችላለች፤ የእሲያ አህጉርም የተሻለ መጻኢ እድል ይኖረዋል። | "የቻይናና የአሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ከኮሮናቫይረስ በላይ ለዓለም ያሰጋል" በመጪዎቹ ዓመታት በአሜሪካና በቻይና መካከል ሊከሰት የሚችለው ቀዝቃዛ ጦርነት ዓለምን ከኮሮናቫይረስ በላይ ሊያስጨንቅ እንደሚገባ ዕውቁ የምጣኔ ሀብት ሊቅ ጄፍሪ ሳክስ ተናገሩ። የኮሎምቢያው ዩኒቨርስቲ ዕውቅ ፕሮፌሰር ጄፍ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዓለም ወደ አንዳች መደነቃቀፍ እያመራች ነው፤ መሪ አልባም ሆናለች ብለዋል። እንዲሁም የዓለም ሁኔታ መልክ ባልያዘበት ሁኔታ በሁለቱ የዓለም ኃያላን መካከል ያለው ቁርሾና ቅራኔ እየባሰ ከሄደ ሁኔታዎችን ያባብሳል፤ ጦሱም ለተቀረው ዓለም ይተርፋል ብለዋል። እኚህ ፕሮፌሰር ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ አሜሪካና አመራሯ ነው ብለዋል። • አገራዊ መድረክ ማዘጋጀት እንጂ ከህወሓት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይትን አንቀበልም፡ ደብረፅዮን (ዶ/ር) • "አባላቶቻችን በአካባቢው ይህን የደንብ ልብስ መልበስ ካቆሙ ስድስት ወራት አልፈዋል" የኦሮሚያ ፖሊስ አሁን ያለው የአሜሪካ አመራር ከትብብር ይልቅ ክፍፍልን የሚያፋፍም ነው ሲሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አመራሩ አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት ከቻይና ጋር ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ዓለምን ዳግም ወደ ሰላም ለመመለስ በጣም ይቸገራል" ብለዋል ፕሮፌሰሩ። የፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ አስተያየት የመጣው ሰሞኑን ቻይናና አሜሪካ ከምጣኔ ሀብት ጦርነት ጋር ብቻም ሳይሆን ፖለቲካዊ መቆራቆዝ ውስጥ እየገቡ ስለመሆኑ ምልክቶች መታየታቸውን ተከትሎ ነው። በያዝነው ሳምንት ለምሳሌ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በቻይና ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የሚጥለው ሰነድ ላይ ይፈርማሉ ተብሏል። ማዕቀቡን የሚጥሉት በዢንጂያንግ ግዛት የቻይና ሙስሊሞችን ለርዕዮተ ዓለም ጥምቀት ማጎርያ ውስጥ መከተታቸውን ተከትሎ ነው። ያም ሆኖ የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞው የደኅንነት አማካሪ ሰሞኑን ለአንባቢዎች ያደርሱታል በተባለው አዲስ መጽሐፋቸው እንደጠቀሱት፤ ፕሬዝዳንቱ ቻይና ይህንን የሙስሊሞች ማጎርያ እንድትገነባ አበረታተው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ ከዎልስትሪት ጆርናል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቻይና ኮሮናቫይረስን ለዓለም ያቀበለችውና ብሎም ያሰራጨችው ሆን ብላ የአሜሪካንን ምጣኔ ሀብት ለማንኮታኮት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናና የአሜሪካንን የኢኮኖሚ ጦርነት ካመላከቱ ነገሮች አንዱ አሜሪካ በቻይናው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ላይ የጣለችው እቀባ ነው። አሜሪካ እንደምትለው ሁዋዌ የደንበኞችን መረጃ ለመሰለል የተቋቋመ ነው። ቻይና ይህንን ክስ ታስተባብላለች። የቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ የደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አዲስ በጻፉት መጽሐፍ እንዳጋለጡት ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ ህዋዌ ላይ እቀባ ያደረጉት በድጋሚ የመመረጥ ዕድላቸውን ለማስፋት ብቻ ነው። • ትራምፕ እንዳይታተም ባሉት መጽሐፍ ይፋ የሚደረጉ 6 ምስጢሮች • በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ድርድር፡ የግብፅ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ውሳኔ ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስም በዚህ የቦልተን ሐሳብ ይስማማሉ። ሁዋዌን ትራምፕ ያገዱት የምርም የደኅንነት ጉዳይ አሳስቧቸው ሊሆን አይችልም። "አሜሪካ በ5ጂ የሞባይል ቴክኖሎጂ ተቀድማለች። ሁዋዌ ደግሞ የዓለምን የገበያ ድርሻ ተቀራምቶታል፤ ይህ ነው አሜሪካንን የረበሻት" ይላሉ። ከቻይና ጋር ፍጥጫ ላይ ያለችው አገር አሜሪካ ብቻ አይደለችም። ቻይና ባለፈው ሳምንት ከሕንድ ጋር የድንበር ግጭት ውስጥ ገብታ 20 የሕንድ ወታደሮችን መገደላቸው አይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እናዳለ ቻይና በፓኪስታን፣ በምያንማር፣ በሲሪሊንካና በኔፓል በርካታ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እያገዘች ነው። እነዚህ አገራት ደግሞ የሕንድ ጎረቤቶች ናቸው። ሕንድ ቻይና የአካባቢው ተጽእኖ ፈጣሪ አገር የመሆኗን ጉዳይ ማስቆም ትፈልጋለች። ፕሮፌሰር ሳክስ እንደሚያምኑት ቻይና በአካባቢው አገራት ላይ የትብብር መንፈስ ካሳየች ነገሮች የተሻሉ ይሆናሉ። ቻይና እድሏ ያለው በእጇ ነው። ቻይና ተባባሪ ከሆነች፣ በዲፕሎማሲ ችግሮችን ለመፍታት ከፈለገችና የትብብር መንፈስ ካሳየች ጉልበት ያላት አገር ስለሆነች ብዙ ነገር መቀየር ትችላለች፤ የእሲያ አህጉርም የተሻለ መጻኢ እድል ይኖረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53135326 |
2health
| በኮሮና የተያዙ ሰዎች በድባቴ እና የመርሳት በሽታ የመጠቃት እድላቸው እንደሚጨምር ጥናት አመለከተ | ባለፈው ስድስት ወራት ውስጥ የኮሮናቫይረስ የያዛቸው ሰዎች በድባቴ፣ የመርሳት በሽታ፣ ስትሮክ እና በሳይኮሲስ ህመሞች የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን በኦክስፎርድ ተመራማሪዎች የተሰራ ጥናት አመላከተ። ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ቀድመው የነበሩባቸው የስነ ልቦና እና የነርቭ ችግሮች ያገረሽባቸዋል ወይም እንደ አዲስ ሕመሞቹ ያጠቋቸዋል ሲል ጥናቱ አመልክቷል። በቫይረሱ ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ወይም በፅኑ ህሙማን ማቆያ ከነበሩ ደግሞ የመያዝ እድላቸው የበለጠ ይሰፋል ሲል ጥናቱ አመላክቷል። እነዚህ ጫናዎችም ጭንቀትን በማስከተል ወይም ቫይረሱ አዕምሮ ላይ በሚያስከትለው ቀጥተኛ ጫና ላይ ሊመሰረት እንደሚችልም አክሏል። እንግሊዛዊያን ሳይንቲስቶቹ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎችን የኤሌክትሮኒክ መረጃ በመመልከት እና በተለይም 14 ለሚሆኑ የስነ-ልቦና እና የነርቭ ችግሮች የመጋለጥ እድሎችን መርምረዋል። ከእነዚህም መካከል የአዕምሮ ውስጥ የደም መፍሰስ፣ ስትሮክ፣ ፓርኪንሰን፣ የመርሳት በሽታ፣ ሳይኮሲስ፣ የስሜት መቃወስ እና የጭንቀት ችግሮች ይገኙበታል፡፡ በጣም መታመምን ወይም ወደ ሆስፒታል መወሰድ ከሚያስከትለው የጭንቀት ጫና የተነሳ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ለጭንቀት እና የስሜት መቃወስ መዳረግ በተደጋጋሚ የታዩባቸው ችግሮች ናቸው ሲል ገልጿል። እንደ ስትሮክ እና የመርሳት በሽታ ያሉት ደግሞ ቫይረሱ በራሱ በሚያስከትለው አካላዊ ጉዳት ላይ ተመስርተው የሚከሰቱ ወይም ሰውነታችን ለቫይረሱ በሚሰጠው ምላሽ ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ ሲልም አስረድቷል። ጥናቱ የኮሮናቫይረስ በቀጥታ ለፓርኪንሰን ወይም ለጊላይን-ባሬ ሲንድሮም የማጋለጥ እድሉን አላረጋገጠም። ምርምሩ ሁለት በጉንፋን የተያዙ ሰዎችን የያዙ ቡድኖችን በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ጋር በማነፃፀር የተሰራ ሲሆን፣ ጥናቱን ያካሄዱት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ኮሮና ከሌሎች የመተንፈሻ ህመሞች በበለጠ ከአዕምሮ ጉዳቶች ጋር እንደሚያያዝ ገልፀዋል። ቫይረሱ ወደ አዕምሮ ውስጥ እንደሚገባ እና ጉዳቶችን እንደሚያደርስ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ተገኝተዋል ሲሉ ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆኑት የኦክስፎርዱ የኑሮሎጂ ፕሮፌሰር መሱድ ሃሰን አብራርተዋል፡፡ ከቀጥተኛ ጉዳቶችም ባሻገር የደም መርጋትን በማስከተሉ እና ይህም ስትሮክን ሊያመጣ እንደሚችል አክለዋል፡፡ በአጠቃላይም ሰውነታችን ቫይረሱን ለመከላከል ሲል የሚያደርገው ግብ ግብ አእምሮን ሊጎዳ ይችላል ሲሉም ገልፀዋል፡፡ | በኮሮና የተያዙ ሰዎች በድባቴ እና የመርሳት በሽታ የመጠቃት እድላቸው እንደሚጨምር ጥናት አመለከተ ባለፈው ስድስት ወራት ውስጥ የኮሮናቫይረስ የያዛቸው ሰዎች በድባቴ፣ የመርሳት በሽታ፣ ስትሮክ እና በሳይኮሲስ ህመሞች የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን በኦክስፎርድ ተመራማሪዎች የተሰራ ጥናት አመላከተ። ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ቀድመው የነበሩባቸው የስነ ልቦና እና የነርቭ ችግሮች ያገረሽባቸዋል ወይም እንደ አዲስ ሕመሞቹ ያጠቋቸዋል ሲል ጥናቱ አመልክቷል። በቫይረሱ ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ወይም በፅኑ ህሙማን ማቆያ ከነበሩ ደግሞ የመያዝ እድላቸው የበለጠ ይሰፋል ሲል ጥናቱ አመላክቷል። እነዚህ ጫናዎችም ጭንቀትን በማስከተል ወይም ቫይረሱ አዕምሮ ላይ በሚያስከትለው ቀጥተኛ ጫና ላይ ሊመሰረት እንደሚችልም አክሏል። እንግሊዛዊያን ሳይንቲስቶቹ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎችን የኤሌክትሮኒክ መረጃ በመመልከት እና በተለይም 14 ለሚሆኑ የስነ-ልቦና እና የነርቭ ችግሮች የመጋለጥ እድሎችን መርምረዋል። ከእነዚህም መካከል የአዕምሮ ውስጥ የደም መፍሰስ፣ ስትሮክ፣ ፓርኪንሰን፣ የመርሳት በሽታ፣ ሳይኮሲስ፣ የስሜት መቃወስ እና የጭንቀት ችግሮች ይገኙበታል፡፡ በጣም መታመምን ወይም ወደ ሆስፒታል መወሰድ ከሚያስከትለው የጭንቀት ጫና የተነሳ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ለጭንቀት እና የስሜት መቃወስ መዳረግ በተደጋጋሚ የታዩባቸው ችግሮች ናቸው ሲል ገልጿል። እንደ ስትሮክ እና የመርሳት በሽታ ያሉት ደግሞ ቫይረሱ በራሱ በሚያስከትለው አካላዊ ጉዳት ላይ ተመስርተው የሚከሰቱ ወይም ሰውነታችን ለቫይረሱ በሚሰጠው ምላሽ ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ ሲልም አስረድቷል። ጥናቱ የኮሮናቫይረስ በቀጥታ ለፓርኪንሰን ወይም ለጊላይን-ባሬ ሲንድሮም የማጋለጥ እድሉን አላረጋገጠም። ምርምሩ ሁለት በጉንፋን የተያዙ ሰዎችን የያዙ ቡድኖችን በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ጋር በማነፃፀር የተሰራ ሲሆን፣ ጥናቱን ያካሄዱት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ኮሮና ከሌሎች የመተንፈሻ ህመሞች በበለጠ ከአዕምሮ ጉዳቶች ጋር እንደሚያያዝ ገልፀዋል። ቫይረሱ ወደ አዕምሮ ውስጥ እንደሚገባ እና ጉዳቶችን እንደሚያደርስ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ተገኝተዋል ሲሉ ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆኑት የኦክስፎርዱ የኑሮሎጂ ፕሮፌሰር መሱድ ሃሰን አብራርተዋል፡፡ ከቀጥተኛ ጉዳቶችም ባሻገር የደም መርጋትን በማስከተሉ እና ይህም ስትሮክን ሊያመጣ እንደሚችል አክለዋል፡፡ በአጠቃላይም ሰውነታችን ቫይረሱን ለመከላከል ሲል የሚያደርገው ግብ ግብ አእምሮን ሊጎዳ ይችላል ሲሉም ገልፀዋል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-56664358 |
5sports
| ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሁሉ ቀድመው ካሜሮን የገቡት ዋሊያዎች | በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ዓመት የዘገየው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሁንም በወረርሽኙ ስጋት ውስጥ ሆኖ በመጪው ወር ጥር 01/2014 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ መካሄድ ይጀምራል። በዚሁ ውድድር መሳተፋቸውን ያረጋገጡት ዋልያዎቹም ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት ቀድመው ካሜሩን በመድረስ ዝግጅታቸውን ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ጌታነህ ከበደን ጨምሮ 25 ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን፣ ካፍ ካስቀመጠው ገደብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሦስት ተጫዋቾች እንዲካተቱ ተደርጓ። ታኅሣሥ 14/ 2014 ይፋ ከተደረገው የብሔራዊ ቡድኑ 25 ተጫዋቾች ዝርዝር ከዚህ ቀደም በተጠባባቂነት ተይዘው የነበሩት ሱራፌል ዳኛቸው፣ ፍሬው ጌታሁን እና ይሁን እንደሻው ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቅለው ዋሊያዎቹ 28 ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ካሜሩን አቅንተዋል። የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈው ከ8 ዓመታት በፊት ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው ውድድር ላይ ነበር። ባለፈው እሁድ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ የተነሳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልዑክ በቀዳሚነት የካሜሩን ሁለተኛ ከተማ ወደሆነችው ዱዋላ ደርሶ ለአንድ ሰዓት ከቆየ በኋላ ወደ ዋና ከተማዋ ያውንዴ ደርሷል። ብሔራዊ ቡድኑ ያውንዴ አየር ማረፊያ እንደደረሰ የኮቪድ-19 ምርመራን ያደረገ ሲሆን በመቀጠል ወደ ሆቴል ዴ ዴፕዩቴ አምርቶ ማረፊያውን ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያሳያል። ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ቀላል እና ጠንከር ያሉ አራት ልምምዶችን አከናውኗል። በዋሊያዎቹ ከሁሉ ቀድመው ለምን ወደ ካሜሩን ሄዱ? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደሚሉት የመጀመሪያ እቅድ ተደርጎ የነበረው በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ አገራት መካከል በአንዱ ውስጥ ዝግጅት ለማድረግ ነበር። "ከሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ማኅበር ጋር ንግግሮች ነበሩ። እንዲያውም ሙሉ ወጪያችንን ሸፍነው እነሱ ጋር ሄደን እንድንዘጋጅ ተነጋግረን ነበር።" ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጉዞ እግዳዎችን ከጣለባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ በመሆኗ ሀሳቡ ሳይሳካ እንደቀረ ኃላፊው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ቢሆን በተፈጠረው ነገር ማዘኑን እንደገለጸና ይቅርታ እንደመጠየቀም ኃላፊው አመልክተዋል። የመጀመሪያው እቅድ አለመሳካቱን ተከትሎ ደግሞ ፌደሬሽኑ ወደ ሁለተኛ እቅዱ ፊቱን ለማዞር ተገዷል። ይህም ደግሞ ወደ ምዕራብ አፍሪካ አገራት በመሄድ ልምምድ ማካሄድ ነበር። በስተመጨረሻም ወደ አዘጋጇ አገር ካሜሩን በመሄድ ልምምድ ለማድረግ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም ብሔራዊ ቡድኑ ቀድሞ ወደ ካሜሩን ማቅናቱ የአገሪቱን የአየር ጸባይ ለመልመድ ይእንደሚረዳ የገለጹት አቶ ባሕሩ፣ የአፍሪካ ዋንጫ ዘንድሮ እንዳይካሄድ ከተለያዩ ወገኖች ግፊት ይደረግ ስለነበረ ያን በመቃወም ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንዲከናወን ኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ ለማሳየት መሆኑን ጠቅሰዋል። ፊፋንና የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበርን ጨምሮ አንዳንድ የእግር ኳስ ማኅበራት የወረርሽኙን ስርጨት ተከትሎ የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ ጊዜ መካሄድ የለበትም የሚል አስተያየት ሲሰጡ እንደነበር ዋና ፀሐፊው ተናግረዋል። "እኛ ደግሞ የፓንአፍሪካኒዝም ጀማሪዎች እንዲሁም የካፍ መስራች እንደመሆናችን ይሄ ውድድር በተያዘለት ጊዜ በካሜሩን እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ለመስጠትና ይህንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ቀድመን ወደ ካሜሩን ለማቅናት የወሰንነው።" ኦሚክሮን የተባለው አዲሱን የኮቪድ-19 ዝርያ በስፋት መሰራጨትን ተከትሎ በርካቶች ውድድሩ ላይካሄድ ይችላል በሚል ስጋታቸውን ቢገልጹም፣ የየካሜሩን መንግሥት እና የእግር ኳስ ማኅበሩ እንዲሁም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ግን ጨዋታው በወጣለት መረሃ ግብር መሠረት እንደሚከናወን አረጋግጠዋል። ነገር ግን በካሜሩን በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ላይ መታደም የሚችሉት የኮቪድ-19 ክትባትን ሙሉ ለሙሉ የወሰዱ እና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠ ደጋፊዎች ብቻ እንደሚሆኑ አዘጋጆቹ ገልጸዋል። የካሜሩን ቆይታና ዝግጅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሁን የሚገኘው የፊፋ ወኪል በሆነ ኤጀንት አማካይነት በተመቻቸ የስልጠና ካምፕ አገልግሎት መስጫ ውስጥ ነው። ይህ የስልጠና አገልግሎት መስጫ ካምፕ ሆቴል፣ መስተንግዶ፣ የስልጠና ቦታና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ያሟላ እንደሆነ አቶ ባህሩ ይገልጻሉ። "አሁን ብሔራዊ ቡድኑ ያለበት ቦታ ሁሉንም ፍላጎታቸውን የሚያሟላ ነው። አሁን ላይም ተጫዋቾቹ አስፈላጊውን ስልጠናና ዝግጅት በዚህ ማዕከል እያደረጉ ነው'' ሲሉ ዋሊያዎቹ ለውድድሩ አስፋለጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተዋል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዝግጅት ያውንዴ ከከተመ ሳምንት ሊሆነው ተቃርቧል። በቆይታውም መደበኛ ልምምድ በማድረግ ከሳምንት ለሚጀመረው ውድድር እየተዘጋጀ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከዋሊያዎቹ ቀጥሎ ካሜሩን ከደረሰው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ሐሙስ ዕለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አድርጓል። በምድብ 'መ' ከግብፅ፣ ከናይጄሪያ እና ከጊኒ ቢሳዎ ጋር ከተደለደለችው ሱዳን ጋር በተደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታው አማኑኤል ገ/ሚካኤል ሁለት፣ ሽመልስ በቀለ ደግሞ አንድ ግቦችን አስቆጥረው ዋሊያዎቹ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ ችለዋል። ዋሊያዎቹ በካሜሩን በሚኖራቸው ቆይታ አጠቃላይ ወጪያቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እንደሚሸፍን የፌደሬሽኑ ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የአፍሪካ አህጉር ትንቁ የእግር ኳስ ውድድር በሆነው ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚቀርበው ቡድን የሚያስፈልገውን ገንዘብ ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት አግኝቷል። "ለዚህ ውድድር 51 ሚሊየን ብር እንዲመድብ ጠይቀን 35 ሚሊየን ብር ጸድቆልናል። በዚህ ገንዘብ ነው ብሔራዊ ቡድኑ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው። በዚህ አጋጣሚ መንግሥት ላደረገው ነገር በሙሉ ፌዴሬሽኑ ያመስግናል'' ብለዋል አቶ ባሕሩ። ከዋሊያዎቹ ምን እንጠብቅ? የአፍሪካ እግር ኳስ ውድድር መስራች የሆነችው ኢትዮጵያ ከውድድሩ ርቃ ከመቆየቷ በተጨማሪ ከአንድ ጊዜ በላይ የጎላ ውጤትን ሳታስመዘገብ ቆይታለች። በዚህ 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳታፈው ቡድን ግን ይህንን ታሪክ የመቀየር ከፍ ያለ ፍላጎት አለው። ለዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋሊያዎቹ በምድብ ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት አስመዝግበው ከምድባቸው ማለፍን በቀዳሚነት የሚጠበቅ ውጤት እንደሆነ አቶ ባህሩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ካሜሩን፣ ከቡርኪና ፋሶ እና ኬፕ ቬርድ ጋር ተደልድሏል። በዚህ ሂደትም ዋሊያዎቹ ከምድባቸው ወደቀጣይ ዙር ማለፍን የመጀመሪያ ግብ ከመሆኑ ጎን ለጎን "በስፖርት ዲፐሎማሲው ዘርም ሌሎች ኃላፊነቶችን እንመዲወስዱም" አቶ ባሕሩ ጠቅሰው "ኢትዮጵያን ለዓለም ሕዝብ በደንብ ማስተዋወቅና ማሳየት እንፈልጋለን። በዚህ ትልቅ አጋጣሚ አንድነታችንን ለመላው ዓለም በደንብ አድርገን እናሳያለን" ብለዋል። በተጨማሪም ካሜሩን ውስጥ 20 የሚደርሱ የኢትዮጵያውያን ስብስቦች እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ባህሩ እነዚህን ኢትዮጵያውያን በማሰባብ ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም ከ500 በላይ የሚሆኑ ደጋፊዎች ከኢትዮጵያ ወደ ካሜሩን ለመጓዝ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የዋሊያዎቹ ስብስብ ግብ ጠባቂዎች፡ ተክለማርያም ሻንቆ ከሲዳማ ቡና፣ ፋሲል ገብረሚካኤል ከባሕር ዳር ከተማ፣ ጀማል ጣሰው ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ፍሬው ጌታሁን ከድሬዳዋ ከተማ ናቸው። ተከላካዮች፡ አስራት ቱንጆ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሱሌማን ሐሚድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ረመዳን የሱፍ ከወልቂጤ ከተማ፣ ደስታ ዮሐንስ ከአዳማ ከተማ፣ አስቻለው ታመነ ከፋሲል ከነማ፣ ያሬድ ባየህ ከፋሲል ከነማ፣ ምኞት ደበበ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና መናፍ አወል ከባሕር ዳር ከተማ። አማካዮች፡ አማኑኤል ዮሐንስ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጋቶች ፓኖም ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሽመልስ በቀለ ከአል ጎውና፣ መስዑድ መሐመድ ከጅማ አባጅፋር፣ ሱራፌል ዳኛቸው ከፋሲል ከነማ፣ ፍጹም ዓለሙ ከባሕር ዳር ከተማ፣ ፍሬው ሰለሞን ከሲዳማ ቡና፣ በዛብህ መላዮ ከፋሲል ከነማ እንዲሁም ይሁን እንደሻው ከፋሲል ከነማ። አጥቂዎች፡ አቡበክር ናስር ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጌታን ከበደ ከወልቂጤ ከተማ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሽመክት ጉግሳ ከፋሲል ከነማ፣ ሙጂብ ቃሲም ከጄይኒስ ስፖርቲቭ ዲ ካቢሌ፣ መስፍን ታደሰ ከሐዋሳ ከተማ እንዲሁም ዳዋ ሁጤሳ ከአዳማ ከተማ ተመርጠዋል። ዋሊያዎቹ በካሜሩን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ የደረሰችው ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ ነው። በ1962 (እአአ) የአህጉሪቱን ትልቁን ዋንጫ ያነሱት ዋሊያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ሲሳተፉ ይህኛው ለ11ኛ ጊዜ ነው። በዓለም እግር ኳስ 137ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በአሠልጣኝ ውበቱ አባተና በአምበሉ ጌታነህ ከበደ እየተመራች ወደ ያውንዴ አቅንታለች። ይህ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለአሠልጣኝ ውበቱ አባቱና ለቡድኑ አባላት ከአፍሪካ ዋንጫ መሥራቾች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ያላትን ተሰጥዖ የሚያሳዩበት መድረክ እንደሚሆን ይገመታል። ውበቱ ለዓይን ገዥ የሆነውን ኳስ እግር ላይ ሳይቆዩ እየተቀባበሉ መጫወትን የሚመርጥ አሠልጣኝ ነው። የመሃል ሜዳው ሞተር ሽመልስ በቀለና አጥቂው ጌታነህ ከበደ ከወጣቱ የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አቡበከር ናስር ጋር በመጣመር ለተቀናቃኞቻቸው አደጋ ሊሆኑ ይችላሉ። ውበቱ በሚመርጠው የ4-3-3 አሠላለፍ ማለትም 4 የኋላ ደጀን ሦስት አማካዮችና ሦስት አጥቂዎች ተመርቶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይገመታል። ብሔራዊ ቡድኗን በውበቱ አባተ እያጠናከረች ያለችው ኢትዮጵያ ወደ ዙር 16 መሻገር እንደ ትልቅ ውጤት ቢታይ የሚገርም አይሆንም። አልፎም ብሔራዊ ቡድናቸው በአፍሪካ ትልቁ ውድድር ሲሳተፍ ማየት ለጓጉ ኢትዮጵያዊያን ይህ ትልቅ ዕድል ነው። | ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሁሉ ቀድመው ካሜሮን የገቡት ዋሊያዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ዓመት የዘገየው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሁንም በወረርሽኙ ስጋት ውስጥ ሆኖ በመጪው ወር ጥር 01/2014 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ መካሄድ ይጀምራል። በዚሁ ውድድር መሳተፋቸውን ያረጋገጡት ዋልያዎቹም ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት ቀድመው ካሜሩን በመድረስ ዝግጅታቸውን ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ጌታነህ ከበደን ጨምሮ 25 ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን፣ ካፍ ካስቀመጠው ገደብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሦስት ተጫዋቾች እንዲካተቱ ተደርጓ። ታኅሣሥ 14/ 2014 ይፋ ከተደረገው የብሔራዊ ቡድኑ 25 ተጫዋቾች ዝርዝር ከዚህ ቀደም በተጠባባቂነት ተይዘው የነበሩት ሱራፌል ዳኛቸው፣ ፍሬው ጌታሁን እና ይሁን እንደሻው ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቅለው ዋሊያዎቹ 28 ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ካሜሩን አቅንተዋል። የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈው ከ8 ዓመታት በፊት ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው ውድድር ላይ ነበር። ባለፈው እሁድ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ የተነሳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልዑክ በቀዳሚነት የካሜሩን ሁለተኛ ከተማ ወደሆነችው ዱዋላ ደርሶ ለአንድ ሰዓት ከቆየ በኋላ ወደ ዋና ከተማዋ ያውንዴ ደርሷል። ብሔራዊ ቡድኑ ያውንዴ አየር ማረፊያ እንደደረሰ የኮቪድ-19 ምርመራን ያደረገ ሲሆን በመቀጠል ወደ ሆቴል ዴ ዴፕዩቴ አምርቶ ማረፊያውን ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያሳያል። ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ቀላል እና ጠንከር ያሉ አራት ልምምዶችን አከናውኗል። በዋሊያዎቹ ከሁሉ ቀድመው ለምን ወደ ካሜሩን ሄዱ? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደሚሉት የመጀመሪያ እቅድ ተደርጎ የነበረው በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ አገራት መካከል በአንዱ ውስጥ ዝግጅት ለማድረግ ነበር። "ከሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ማኅበር ጋር ንግግሮች ነበሩ። እንዲያውም ሙሉ ወጪያችንን ሸፍነው እነሱ ጋር ሄደን እንድንዘጋጅ ተነጋግረን ነበር።" ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጉዞ እግዳዎችን ከጣለባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ በመሆኗ ሀሳቡ ሳይሳካ እንደቀረ ኃላፊው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ቢሆን በተፈጠረው ነገር ማዘኑን እንደገለጸና ይቅርታ እንደመጠየቀም ኃላፊው አመልክተዋል። የመጀመሪያው እቅድ አለመሳካቱን ተከትሎ ደግሞ ፌደሬሽኑ ወደ ሁለተኛ እቅዱ ፊቱን ለማዞር ተገዷል። ይህም ደግሞ ወደ ምዕራብ አፍሪካ አገራት በመሄድ ልምምድ ማካሄድ ነበር። በስተመጨረሻም ወደ አዘጋጇ አገር ካሜሩን በመሄድ ልምምድ ለማድረግ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም ብሔራዊ ቡድኑ ቀድሞ ወደ ካሜሩን ማቅናቱ የአገሪቱን የአየር ጸባይ ለመልመድ ይእንደሚረዳ የገለጹት አቶ ባሕሩ፣ የአፍሪካ ዋንጫ ዘንድሮ እንዳይካሄድ ከተለያዩ ወገኖች ግፊት ይደረግ ስለነበረ ያን በመቃወም ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንዲከናወን ኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ ለማሳየት መሆኑን ጠቅሰዋል። ፊፋንና የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበርን ጨምሮ አንዳንድ የእግር ኳስ ማኅበራት የወረርሽኙን ስርጨት ተከትሎ የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ ጊዜ መካሄድ የለበትም የሚል አስተያየት ሲሰጡ እንደነበር ዋና ፀሐፊው ተናግረዋል። "እኛ ደግሞ የፓንአፍሪካኒዝም ጀማሪዎች እንዲሁም የካፍ መስራች እንደመሆናችን ይሄ ውድድር በተያዘለት ጊዜ በካሜሩን እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ለመስጠትና ይህንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ቀድመን ወደ ካሜሩን ለማቅናት የወሰንነው።" ኦሚክሮን የተባለው አዲሱን የኮቪድ-19 ዝርያ በስፋት መሰራጨትን ተከትሎ በርካቶች ውድድሩ ላይካሄድ ይችላል በሚል ስጋታቸውን ቢገልጹም፣ የየካሜሩን መንግሥት እና የእግር ኳስ ማኅበሩ እንዲሁም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ግን ጨዋታው በወጣለት መረሃ ግብር መሠረት እንደሚከናወን አረጋግጠዋል። ነገር ግን በካሜሩን በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ላይ መታደም የሚችሉት የኮቪድ-19 ክትባትን ሙሉ ለሙሉ የወሰዱ እና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠ ደጋፊዎች ብቻ እንደሚሆኑ አዘጋጆቹ ገልጸዋል። የካሜሩን ቆይታና ዝግጅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሁን የሚገኘው የፊፋ ወኪል በሆነ ኤጀንት አማካይነት በተመቻቸ የስልጠና ካምፕ አገልግሎት መስጫ ውስጥ ነው። ይህ የስልጠና አገልግሎት መስጫ ካምፕ ሆቴል፣ መስተንግዶ፣ የስልጠና ቦታና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ያሟላ እንደሆነ አቶ ባህሩ ይገልጻሉ። "አሁን ብሔራዊ ቡድኑ ያለበት ቦታ ሁሉንም ፍላጎታቸውን የሚያሟላ ነው። አሁን ላይም ተጫዋቾቹ አስፈላጊውን ስልጠናና ዝግጅት በዚህ ማዕከል እያደረጉ ነው'' ሲሉ ዋሊያዎቹ ለውድድሩ አስፋለጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተዋል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዝግጅት ያውንዴ ከከተመ ሳምንት ሊሆነው ተቃርቧል። በቆይታውም መደበኛ ልምምድ በማድረግ ከሳምንት ለሚጀመረው ውድድር እየተዘጋጀ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከዋሊያዎቹ ቀጥሎ ካሜሩን ከደረሰው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ሐሙስ ዕለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አድርጓል። በምድብ 'መ' ከግብፅ፣ ከናይጄሪያ እና ከጊኒ ቢሳዎ ጋር ከተደለደለችው ሱዳን ጋር በተደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታው አማኑኤል ገ/ሚካኤል ሁለት፣ ሽመልስ በቀለ ደግሞ አንድ ግቦችን አስቆጥረው ዋሊያዎቹ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ ችለዋል። ዋሊያዎቹ በካሜሩን በሚኖራቸው ቆይታ አጠቃላይ ወጪያቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እንደሚሸፍን የፌደሬሽኑ ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የአፍሪካ አህጉር ትንቁ የእግር ኳስ ውድድር በሆነው ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚቀርበው ቡድን የሚያስፈልገውን ገንዘብ ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት አግኝቷል። "ለዚህ ውድድር 51 ሚሊየን ብር እንዲመድብ ጠይቀን 35 ሚሊየን ብር ጸድቆልናል። በዚህ ገንዘብ ነው ብሔራዊ ቡድኑ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው። በዚህ አጋጣሚ መንግሥት ላደረገው ነገር በሙሉ ፌዴሬሽኑ ያመስግናል'' ብለዋል አቶ ባሕሩ። ከዋሊያዎቹ ምን እንጠብቅ? የአፍሪካ እግር ኳስ ውድድር መስራች የሆነችው ኢትዮጵያ ከውድድሩ ርቃ ከመቆየቷ በተጨማሪ ከአንድ ጊዜ በላይ የጎላ ውጤትን ሳታስመዘገብ ቆይታለች። በዚህ 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳታፈው ቡድን ግን ይህንን ታሪክ የመቀየር ከፍ ያለ ፍላጎት አለው። ለዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋሊያዎቹ በምድብ ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት አስመዝግበው ከምድባቸው ማለፍን በቀዳሚነት የሚጠበቅ ውጤት እንደሆነ አቶ ባህሩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ካሜሩን፣ ከቡርኪና ፋሶ እና ኬፕ ቬርድ ጋር ተደልድሏል። በዚህ ሂደትም ዋሊያዎቹ ከምድባቸው ወደቀጣይ ዙር ማለፍን የመጀመሪያ ግብ ከመሆኑ ጎን ለጎን "በስፖርት ዲፐሎማሲው ዘርም ሌሎች ኃላፊነቶችን እንመዲወስዱም" አቶ ባሕሩ ጠቅሰው "ኢትዮጵያን ለዓለም ሕዝብ በደንብ ማስተዋወቅና ማሳየት እንፈልጋለን። በዚህ ትልቅ አጋጣሚ አንድነታችንን ለመላው ዓለም በደንብ አድርገን እናሳያለን" ብለዋል። በተጨማሪም ካሜሩን ውስጥ 20 የሚደርሱ የኢትዮጵያውያን ስብስቦች እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ባህሩ እነዚህን ኢትዮጵያውያን በማሰባብ ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም ከ500 በላይ የሚሆኑ ደጋፊዎች ከኢትዮጵያ ወደ ካሜሩን ለመጓዝ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የዋሊያዎቹ ስብስብ ግብ ጠባቂዎች፡ ተክለማርያም ሻንቆ ከሲዳማ ቡና፣ ፋሲል ገብረሚካኤል ከባሕር ዳር ከተማ፣ ጀማል ጣሰው ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ፍሬው ጌታሁን ከድሬዳዋ ከተማ ናቸው። ተከላካዮች፡ አስራት ቱንጆ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሱሌማን ሐሚድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ረመዳን የሱፍ ከወልቂጤ ከተማ፣ ደስታ ዮሐንስ ከአዳማ ከተማ፣ አስቻለው ታመነ ከፋሲል ከነማ፣ ያሬድ ባየህ ከፋሲል ከነማ፣ ምኞት ደበበ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና መናፍ አወል ከባሕር ዳር ከተማ። አማካዮች፡ አማኑኤል ዮሐንስ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጋቶች ፓኖም ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሽመልስ በቀለ ከአል ጎውና፣ መስዑድ መሐመድ ከጅማ አባጅፋር፣ ሱራፌል ዳኛቸው ከፋሲል ከነማ፣ ፍጹም ዓለሙ ከባሕር ዳር ከተማ፣ ፍሬው ሰለሞን ከሲዳማ ቡና፣ በዛብህ መላዮ ከፋሲል ከነማ እንዲሁም ይሁን እንደሻው ከፋሲል ከነማ። አጥቂዎች፡ አቡበክር ናስር ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጌታን ከበደ ከወልቂጤ ከተማ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሽመክት ጉግሳ ከፋሲል ከነማ፣ ሙጂብ ቃሲም ከጄይኒስ ስፖርቲቭ ዲ ካቢሌ፣ መስፍን ታደሰ ከሐዋሳ ከተማ እንዲሁም ዳዋ ሁጤሳ ከአዳማ ከተማ ተመርጠዋል። ዋሊያዎቹ በካሜሩን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ የደረሰችው ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ ነው። በ1962 (እአአ) የአህጉሪቱን ትልቁን ዋንጫ ያነሱት ዋሊያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ሲሳተፉ ይህኛው ለ11ኛ ጊዜ ነው። በዓለም እግር ኳስ 137ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በአሠልጣኝ ውበቱ አባተና በአምበሉ ጌታነህ ከበደ እየተመራች ወደ ያውንዴ አቅንታለች። ይህ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለአሠልጣኝ ውበቱ አባቱና ለቡድኑ አባላት ከአፍሪካ ዋንጫ መሥራቾች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ያላትን ተሰጥዖ የሚያሳዩበት መድረክ እንደሚሆን ይገመታል። ውበቱ ለዓይን ገዥ የሆነውን ኳስ እግር ላይ ሳይቆዩ እየተቀባበሉ መጫወትን የሚመርጥ አሠልጣኝ ነው። የመሃል ሜዳው ሞተር ሽመልስ በቀለና አጥቂው ጌታነህ ከበደ ከወጣቱ የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አቡበከር ናስር ጋር በመጣመር ለተቀናቃኞቻቸው አደጋ ሊሆኑ ይችላሉ። ውበቱ በሚመርጠው የ4-3-3 አሠላለፍ ማለትም 4 የኋላ ደጀን ሦስት አማካዮችና ሦስት አጥቂዎች ተመርቶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይገመታል። ብሔራዊ ቡድኗን በውበቱ አባተ እያጠናከረች ያለችው ኢትዮጵያ ወደ ዙር 16 መሻገር እንደ ትልቅ ውጤት ቢታይ የሚገርም አይሆንም። አልፎም ብሔራዊ ቡድናቸው በአፍሪካ ትልቁ ውድድር ሲሳተፍ ማየት ለጓጉ ኢትዮጵያዊያን ይህ ትልቅ ዕድል ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-59840259 |
2health
| የተከተቡ ሰዎች ለምን በድጋሚ ኮሮናቫይረስ ይይዛቸዋል? | ኮቪድ የሰው ልጅን የሙጥኝ እንዳለ አለ። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል እና ሌሎም አገራት ውስጥ ኦሚክሮን ተመልሶ እያመሳቸው ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሆስፒታል አልጋን እየያዙ ነው። ከእነዚህ የሚበዙት የተከተቡ ናቸው። ታዲያ መከተብ ከተህዋሲው ካልተከላከለ ምንድነው ፋይዳው? እርግጥ ነው ተከተቡ በተባሉ ሰዎች የሚታይ የጎንዮሽ ጉዳት ዝቅተኛ ነው። ብዙ ሰዎች በድኅረ ክትባት ጊዜ ከትኩሳት፣ ከራስ ምታት፣ ከክንድ መለስተኛ ሕመም፣ ከድካምና ከማቅለሽለሽ የከፋ ስሜት አይሰማቸውም። በክትባቱ ታይተዋል የሚባሉት አናፊላክሲስ፣ ቶምቦሲስ፣ ሚዮካርዲቲስ (የልብ አካባቢ መለብለብ) ወዘተ እጅግ ቁጥሩ ባነሱ ተከታቢ ሰዎች ዘንድ ብቻ ነው የተስተዋሉት። አሁን ድፍን ዓለም እየጠየቀ ያለው ጥያቄ ግን አንድ ነው። መከተብ ከተህዋሲው መያዝ ካላዳነ ምንድነው ፋይዳው? የሚል። ቢቢሲ ከሕጻናት ሕክምና አዋቂና የተላላፊ በሽታዎች አጥኚ ሬናቶ ክፎሪ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርጎ ነበር። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ እነ ፋይዘር እና አስትራዜኒካ እንዲሁም ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባታቸውን ሲያበለጽጉ ግብ የነበረው ተህዋሲው ሰዎችን ለከፋ የጤና ችግር እንዳይዳርጋቸው፣ ሲከፋ ደግሞ ለሞት እንዳያበቃቸው እንጂ ተህዋሲው እንዳይዛቸው ለማድረግ አልነበረም። ሐኪሙ ይህ ግባቸው ተሳክቷል ብለው ያምናሉ። "ክትባቶቹ እጅግ ለከፋው የጤና ችግር አጋላጭ ሁኔታ በቂና አስተማማኝ ምላሽ ይሰጣሉ። ቀላልና መለስተኛ ለሆኑ የተህዋሲው ምልክቶች ደግሞ ክትባቶቹ እምብዛምም ናቸው።" እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ መጀመሪያውኑም እኮ ክትባቶቹ ሥሪታቸው ወረርሽኙን ማቆም ወይም ሰው በተህዋሲው መልሶ እንዳይያዝ ማድረግ አልነበረም ይላሉ። "ዋናው የክትባቶቹ ተልዕኮ አንድ ነው። ተህዋሲው ሰውነትን ለከፋ አደጋ ብሎም ለሞት እንዳያበቃ ጉዳቱን መቀነስ ነበር፤ ይህም ስኬታማ ነው" ይላሉ። እንደ ምሳሌ የሚያቀርቡት በተለምዶ የጉንፋን ማስታገሻ የምንለው ክትባትን ነው። ያ ክትባት ለዘመናት ሲሰጥ ነው የተኖረው። አንድም ጊዜ ግን ጉንፋኑን ለማጥፋት ተብሎ አግልግሎት ላይ አልዋለም። ሰዎች በጉንፋን የተነሳ ወደከፋ ደዌ እንዳይወደቁ ማገዝ ነው ተግባሩ። ይህ ክትባት ኢንፍሌዌንዛን ለማጥፋት አልተመረተም። ነገር ግን ልጆች፣ ነፍሰጡሮች፣ ሽማግሌዎች እና ገመምተኞች ይህ የኢንፍሌውዛ ተህዋሲዊ ችግር ውስጥ እንዳይጥላቸው ያደርጋቸዋል። የኮቪድ-19 ክትባትም ተመሳሳይ ነው። ወረርሽኝ የማቆም ተልዕኮ የለውም ይላሉ። የኮቪድ-19 ክትባቶች ምን ያህል ሞትን ታድገዋል የሚለውን ብንመለከት ይህን የሐኪሙን ሙግት የሚደግፍ ሆኖ እናገኘዋለን። የኮመንዌልዝ ፈንድ ባወጣው አንድ ሰነድ ላይ እንደተመላከተው ኮሮናቫይረስ ክትባቶች ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ብቻ አንድ ሚሊዮን ሞትን ተከላክሏል። ነገር ግን 10 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል እንዳይገቡና አልጋ እንዳይዙ የሆኑት ክትባት በመውሰዳቸው ነው። ይህ አሐዝ የአሜሪካንን ሕዝብ ብቻ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። የዓለም ጤና ድርጅትና የአውሮፓ የተላላፊ በሽታ ቁጥጥጥር ማዕከል እንደሚገምቱት ደግሞ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ፣ በ33 የአውሮፓ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ክትባቱ ከሞት ታድጓቸዋል። ይህ በሌላ አነጋገር ሲገለጽ እነዚህ ሰዎች ክትባቱን በወቅቱ ባይከተቡ ኖሮ የመሞት ዕድላቸው ሰፊ ነበር። ከእነዚህ መካከል ምናልባትም በርካታ ሰዎች ተህዋሲው መልሶ አልያዛቸውም ባይባልም፣ ለከፋ ጉዳት እንዳያደርሳቸው የሆነው ግን በመከተባቸውና በመከተባቸው ብቻ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከተቡ ሰዎች ለምን በተህዋሲው በብዛት መያዝ ጀመሩ? ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙሉ ክትባት የወሰዱ ሰዎች ሳይቀር በኦሚክሮን እየተያዙ እንደሆነ የሚስተባበል ጉዳይ አይደለም። ይህ በሦስት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። በተለይ በምዕራቡ ዓለም ገና እና አዲስ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በርካታ ሰዎች በጋራ ብዙ ተቀራርበዋል። ይህ መቀራረብ ተህዋሲው እንደልብ እንዲዛመት ሳያስችለው አልቀረም። ሁለተኛው ምክንያት ክትባቱ ለተቀረው ዓለም ከተሰራጨ ከዓመት በኋላ ተመራማሪዎች የደረሱበት አንድ ፍንትው ያለ ሐቅ ቢኖር፣ ክትባቱ አንድ ጊዜ ተወስዶ በቃ ከዚህ ወዲያ እምብዛም አያስፈልግም የሚባል እንዳልሆነ ነው። "በጊዜ ሂደት የክትባቱ የመከላከል አቅም እንደሚወርድ ደርሰንበታል። አቅሙ የመውረዱ ፍጥነት ደግሞ ከተከታቢው ዕድሜና የተፈጥሮ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው" ይላሉ ሐኪም ክፎሪ። ይህም ሐቅ ነው ሦስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻ እንዲከፈት ምክንያት የሆነው። ይህ ዘመቻ በቅድሚያ ዕድሜያቸው ለገፋ ብቻ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ሌሎች ሰዎችም ቢወስዱት ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደሌለው ተደርሶበታል። ያም ሆኖ አሁንም የተከተቡ ሰዎች በተህዋሲው እየተያዙ ነው ያሉት። በዚህ ጉዳይ ላይ ሐኪሙ የሚሉት ይህንን ነው። "ነገሩ እንደ ኢንፍሌዎንዛ ክትባት ነው። ከዚህ ሁኔታ ጋር፣ ከሐቁ ጋር ተስማምተን መኖር መቀጠል ነው የሚኖርብን። ሌላ ነገር የለም።" መልካሙ ነገር ተከትበው ሳለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመጣው ልውጥ የኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ነው። ይህም የሚያሳየው ክትባቱ ይነስም ይብዛ ሥራውን እየሠራ መሆኑን ነው። ይህን ሐቅ ለማስረዳት ኒውዮርክ ከተማን እንደ ማሳያ መውሰድ ብቻ በቂ ነው። በታኅሣሥ ወር ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች እና የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ አሻቀበ። ከእነዚህ ውስጥ እጅግ የበዙት ክትባት ያልወሰዱ ናቸው። ክትባት የወሰዱ ሰዎች ግን በተህዋሲው ቢያዙም ለሆስፒታል የሚያበቃ ችግር ላይ አልወደቁም። የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ቢሮም ቢሆን ከዚህ የተለየ ድምዳሜ ላይ አልደረሰም። የኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ባወጣው አንድ የጥናት አሐዝ አንድ ሙሉ ጠብታ የተከተበ ሰው በኦሚክሮን ቢያዝ ወደ ሆስፒታል የማይመጣበት ዕድል 81 ከመቶ በላይ ነው። ሐኪሙ የመጨረሻ መልዕክታቸው ይህ ነው። "ብከተብም ባልከተብም ያው በቫይረሱ መያዜ አይቀርምና ቢቀርብኝስ የሚሉት ሰዎች ፍጹም የተሳሳቱ ናቸው። እውነት ነው፣ የተከተበም ያልተከተበም በተህዋሲው ሊያዝ ይችላል። ነገር ግን ውጤታቸው አንድ አይደለም። የተከተቡት በቤታቸው ያልፉታል፤ ያልተከተቡት ግን ይሞታሉ።" | የተከተቡ ሰዎች ለምን በድጋሚ ኮሮናቫይረስ ይይዛቸዋል? ኮቪድ የሰው ልጅን የሙጥኝ እንዳለ አለ። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል እና ሌሎም አገራት ውስጥ ኦሚክሮን ተመልሶ እያመሳቸው ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሆስፒታል አልጋን እየያዙ ነው። ከእነዚህ የሚበዙት የተከተቡ ናቸው። ታዲያ መከተብ ከተህዋሲው ካልተከላከለ ምንድነው ፋይዳው? እርግጥ ነው ተከተቡ በተባሉ ሰዎች የሚታይ የጎንዮሽ ጉዳት ዝቅተኛ ነው። ብዙ ሰዎች በድኅረ ክትባት ጊዜ ከትኩሳት፣ ከራስ ምታት፣ ከክንድ መለስተኛ ሕመም፣ ከድካምና ከማቅለሽለሽ የከፋ ስሜት አይሰማቸውም። በክትባቱ ታይተዋል የሚባሉት አናፊላክሲስ፣ ቶምቦሲስ፣ ሚዮካርዲቲስ (የልብ አካባቢ መለብለብ) ወዘተ እጅግ ቁጥሩ ባነሱ ተከታቢ ሰዎች ዘንድ ብቻ ነው የተስተዋሉት። አሁን ድፍን ዓለም እየጠየቀ ያለው ጥያቄ ግን አንድ ነው። መከተብ ከተህዋሲው መያዝ ካላዳነ ምንድነው ፋይዳው? የሚል። ቢቢሲ ከሕጻናት ሕክምና አዋቂና የተላላፊ በሽታዎች አጥኚ ሬናቶ ክፎሪ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርጎ ነበር። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ እነ ፋይዘር እና አስትራዜኒካ እንዲሁም ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባታቸውን ሲያበለጽጉ ግብ የነበረው ተህዋሲው ሰዎችን ለከፋ የጤና ችግር እንዳይዳርጋቸው፣ ሲከፋ ደግሞ ለሞት እንዳያበቃቸው እንጂ ተህዋሲው እንዳይዛቸው ለማድረግ አልነበረም። ሐኪሙ ይህ ግባቸው ተሳክቷል ብለው ያምናሉ። "ክትባቶቹ እጅግ ለከፋው የጤና ችግር አጋላጭ ሁኔታ በቂና አስተማማኝ ምላሽ ይሰጣሉ። ቀላልና መለስተኛ ለሆኑ የተህዋሲው ምልክቶች ደግሞ ክትባቶቹ እምብዛምም ናቸው።" እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ መጀመሪያውኑም እኮ ክትባቶቹ ሥሪታቸው ወረርሽኙን ማቆም ወይም ሰው በተህዋሲው መልሶ እንዳይያዝ ማድረግ አልነበረም ይላሉ። "ዋናው የክትባቶቹ ተልዕኮ አንድ ነው። ተህዋሲው ሰውነትን ለከፋ አደጋ ብሎም ለሞት እንዳያበቃ ጉዳቱን መቀነስ ነበር፤ ይህም ስኬታማ ነው" ይላሉ። እንደ ምሳሌ የሚያቀርቡት በተለምዶ የጉንፋን ማስታገሻ የምንለው ክትባትን ነው። ያ ክትባት ለዘመናት ሲሰጥ ነው የተኖረው። አንድም ጊዜ ግን ጉንፋኑን ለማጥፋት ተብሎ አግልግሎት ላይ አልዋለም። ሰዎች በጉንፋን የተነሳ ወደከፋ ደዌ እንዳይወደቁ ማገዝ ነው ተግባሩ። ይህ ክትባት ኢንፍሌዌንዛን ለማጥፋት አልተመረተም። ነገር ግን ልጆች፣ ነፍሰጡሮች፣ ሽማግሌዎች እና ገመምተኞች ይህ የኢንፍሌውዛ ተህዋሲዊ ችግር ውስጥ እንዳይጥላቸው ያደርጋቸዋል። የኮቪድ-19 ክትባትም ተመሳሳይ ነው። ወረርሽኝ የማቆም ተልዕኮ የለውም ይላሉ። የኮቪድ-19 ክትባቶች ምን ያህል ሞትን ታድገዋል የሚለውን ብንመለከት ይህን የሐኪሙን ሙግት የሚደግፍ ሆኖ እናገኘዋለን። የኮመንዌልዝ ፈንድ ባወጣው አንድ ሰነድ ላይ እንደተመላከተው ኮሮናቫይረስ ክትባቶች ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ብቻ አንድ ሚሊዮን ሞትን ተከላክሏል። ነገር ግን 10 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል እንዳይገቡና አልጋ እንዳይዙ የሆኑት ክትባት በመውሰዳቸው ነው። ይህ አሐዝ የአሜሪካንን ሕዝብ ብቻ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። የዓለም ጤና ድርጅትና የአውሮፓ የተላላፊ በሽታ ቁጥጥጥር ማዕከል እንደሚገምቱት ደግሞ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ፣ በ33 የአውሮፓ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ክትባቱ ከሞት ታድጓቸዋል። ይህ በሌላ አነጋገር ሲገለጽ እነዚህ ሰዎች ክትባቱን በወቅቱ ባይከተቡ ኖሮ የመሞት ዕድላቸው ሰፊ ነበር። ከእነዚህ መካከል ምናልባትም በርካታ ሰዎች ተህዋሲው መልሶ አልያዛቸውም ባይባልም፣ ለከፋ ጉዳት እንዳያደርሳቸው የሆነው ግን በመከተባቸውና በመከተባቸው ብቻ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከተቡ ሰዎች ለምን በተህዋሲው በብዛት መያዝ ጀመሩ? ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙሉ ክትባት የወሰዱ ሰዎች ሳይቀር በኦሚክሮን እየተያዙ እንደሆነ የሚስተባበል ጉዳይ አይደለም። ይህ በሦስት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። በተለይ በምዕራቡ ዓለም ገና እና አዲስ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በርካታ ሰዎች በጋራ ብዙ ተቀራርበዋል። ይህ መቀራረብ ተህዋሲው እንደልብ እንዲዛመት ሳያስችለው አልቀረም። ሁለተኛው ምክንያት ክትባቱ ለተቀረው ዓለም ከተሰራጨ ከዓመት በኋላ ተመራማሪዎች የደረሱበት አንድ ፍንትው ያለ ሐቅ ቢኖር፣ ክትባቱ አንድ ጊዜ ተወስዶ በቃ ከዚህ ወዲያ እምብዛም አያስፈልግም የሚባል እንዳልሆነ ነው። "በጊዜ ሂደት የክትባቱ የመከላከል አቅም እንደሚወርድ ደርሰንበታል። አቅሙ የመውረዱ ፍጥነት ደግሞ ከተከታቢው ዕድሜና የተፈጥሮ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው" ይላሉ ሐኪም ክፎሪ። ይህም ሐቅ ነው ሦስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻ እንዲከፈት ምክንያት የሆነው። ይህ ዘመቻ በቅድሚያ ዕድሜያቸው ለገፋ ብቻ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ሌሎች ሰዎችም ቢወስዱት ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደሌለው ተደርሶበታል። ያም ሆኖ አሁንም የተከተቡ ሰዎች በተህዋሲው እየተያዙ ነው ያሉት። በዚህ ጉዳይ ላይ ሐኪሙ የሚሉት ይህንን ነው። "ነገሩ እንደ ኢንፍሌዎንዛ ክትባት ነው። ከዚህ ሁኔታ ጋር፣ ከሐቁ ጋር ተስማምተን መኖር መቀጠል ነው የሚኖርብን። ሌላ ነገር የለም።" መልካሙ ነገር ተከትበው ሳለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመጣው ልውጥ የኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ነው። ይህም የሚያሳየው ክትባቱ ይነስም ይብዛ ሥራውን እየሠራ መሆኑን ነው። ይህን ሐቅ ለማስረዳት ኒውዮርክ ከተማን እንደ ማሳያ መውሰድ ብቻ በቂ ነው። በታኅሣሥ ወር ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች እና የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ አሻቀበ። ከእነዚህ ውስጥ እጅግ የበዙት ክትባት ያልወሰዱ ናቸው። ክትባት የወሰዱ ሰዎች ግን በተህዋሲው ቢያዙም ለሆስፒታል የሚያበቃ ችግር ላይ አልወደቁም። የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ቢሮም ቢሆን ከዚህ የተለየ ድምዳሜ ላይ አልደረሰም። የኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ባወጣው አንድ የጥናት አሐዝ አንድ ሙሉ ጠብታ የተከተበ ሰው በኦሚክሮን ቢያዝ ወደ ሆስፒታል የማይመጣበት ዕድል 81 ከመቶ በላይ ነው። ሐኪሙ የመጨረሻ መልዕክታቸው ይህ ነው። "ብከተብም ባልከተብም ያው በቫይረሱ መያዜ አይቀርምና ቢቀርብኝስ የሚሉት ሰዎች ፍጹም የተሳሳቱ ናቸው። እውነት ነው፣ የተከተበም ያልተከተበም በተህዋሲው ሊያዝ ይችላል። ነገር ግን ውጤታቸው አንድ አይደለም። የተከተቡት በቤታቸው ያልፉታል፤ ያልተከተቡት ግን ይሞታሉ።" | https://www.bbc.com/amharic/news-59925005 |
3politics
| ኡጋንዳ ከሙዚቀኛው ተቃዋሚ ጋር ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠየቀች | የኡጋንዳ መንግሥት ከታዋቂው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ ቦቢ ዋይን ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠይቋል። በኡጋንዳ የኮሚዩኒኬሽን ዘርፉን በዋነኝነት የሚቆጣጠረው አካል አስራ አራት የዩቲየብ ቻናሎች እንዲዘጉ ጠይቋል። ተቆጣጣሪው አካል ደብዳቤውን የፃፈው የዩቲዩብ ባለቤት ለሆነው ጉግል ሲሆን በባለፈው ወር ከደረስው ነውጥም ጋር ግንኙነት ያላቸውና ለ50 ሰዎችም መሞት ተጠያቂ ናቸው ያላቸው እንደሆነም አስፍሯል። በአገሪቱ ውስጥ ዋነኛ ተቃዋሚ የሚባለው ሮበርት ካያጉላንይ ወይም ቦቢ ዋይን እስር ተከትሎም በመዲናዋም ካምፓላም ሆነ በዋነኞቹ ከተሞች ነውጥ ተከስቷል። ሙዚቀኛው ቦቢ ዋይን የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ጥሷል በሚልም ነው ለእስር የተዳረገው። እንዲታገዱ የተወሰኑት የዩቲዩብ ቻናሎች ከሙዚቀኛው ጋር ግንኙነት አላቸው ቢባልም የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን የህግ ጉዳዮች ኃላፊ በበኩላቸው "የአጋጣሚ ጉዳይ ነው" ማለታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ኮሚሽኑ ለጉግል በፃፈው ደብዳቤ የዩቲብ ቻናሎቹን ነውጡን ለማነሳሳት ተጠቅመውበታል፤ ከህግ ውጭ ያላቸውንም ይዘቶች አሳይተዋል በማለትም ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ ፅፏል። ኡጋንዳ በጥር ወር ምርጫዋን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ናት። አገሪቷን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የመሯት ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪንም በምርጫው ይወዳደራሉ። | ኡጋንዳ ከሙዚቀኛው ተቃዋሚ ጋር ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠየቀች የኡጋንዳ መንግሥት ከታዋቂው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ ቦቢ ዋይን ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠይቋል። በኡጋንዳ የኮሚዩኒኬሽን ዘርፉን በዋነኝነት የሚቆጣጠረው አካል አስራ አራት የዩቲየብ ቻናሎች እንዲዘጉ ጠይቋል። ተቆጣጣሪው አካል ደብዳቤውን የፃፈው የዩቲዩብ ባለቤት ለሆነው ጉግል ሲሆን በባለፈው ወር ከደረስው ነውጥም ጋር ግንኙነት ያላቸውና ለ50 ሰዎችም መሞት ተጠያቂ ናቸው ያላቸው እንደሆነም አስፍሯል። በአገሪቱ ውስጥ ዋነኛ ተቃዋሚ የሚባለው ሮበርት ካያጉላንይ ወይም ቦቢ ዋይን እስር ተከትሎም በመዲናዋም ካምፓላም ሆነ በዋነኞቹ ከተሞች ነውጥ ተከስቷል። ሙዚቀኛው ቦቢ ዋይን የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ጥሷል በሚልም ነው ለእስር የተዳረገው። እንዲታገዱ የተወሰኑት የዩቲዩብ ቻናሎች ከሙዚቀኛው ጋር ግንኙነት አላቸው ቢባልም የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን የህግ ጉዳዮች ኃላፊ በበኩላቸው "የአጋጣሚ ጉዳይ ነው" ማለታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ኮሚሽኑ ለጉግል በፃፈው ደብዳቤ የዩቲብ ቻናሎቹን ነውጡን ለማነሳሳት ተጠቅመውበታል፤ ከህግ ውጭ ያላቸውንም ይዘቶች አሳይተዋል በማለትም ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ ፅፏል። ኡጋንዳ በጥር ወር ምርጫዋን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ናት። አገሪቷን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የመሯት ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪንም በምርጫው ይወዳደራሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-55329580 |
5sports
| እግር ኳስ፡ አምስት ቁልፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ | ኢትዮጵያ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ከኒጀር ጋር ለምታደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ተጠርተው ከነበሩት ተጫዋቾች መካከል አምስት ቁልፍ ተጫዋቾች ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው ተነገረ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ለብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተው ከነበሩት 36 ተጫዋቾች መካከል ለቡድኑ ወሳኝ የሆኑት አምስት ተጫዋቾች በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አቶ ባህሩ ለውድድሩ 41 ተጫዋቾች መጠራታቸውን አስታውሰው፣ አምስቱ በተለያየ ምክንያት ቡድኑን አለመቀላቀላቸውን አመልክተዋል። ከአምስቱ መካከል ሁለቱ በአሁን ሰዓት በውጭ አገር በሙከራና በመጫወት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ሁለት ተጫዋቾች ዘግይተው ቡድኑን መቀላቀላቸውን ገልፀው፤ አንደኛው ደግሞ ከዚህ ቀደም በነበረበት ጉዳት ምክንያት ቡድኑን መቀላለቀል ያልቸለ መሆኑን ተናግረዋል። ለእግር ኳስ ቡድኑ አባላት የኮቪድ-19 ምርመራ ከመደረጉ በፊት የልብ ምርመራን ጨምሮ አጠቃላይ የጤና ምርመራ መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው፤ የኮቪድ-19 ምርመራውም ለሁሉም መሰጠቱን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ለብሔራዊ ቡድኑ ለተጠሩት ለአጠቃላዩ 36 ተጫዋቾች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎ አምስት ተጫዋቾች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል አቶ ባሕሩ። ቫይረሱ ከተገኘባቸው ተጫዋቾች ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉትን የመለየት ሥራ እየተሰራም መሆኑን ጨምረው አመልክተዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው አምስት ተጫዋቾች በአሁኑ ጊዜ በሆቴል ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ መደረጉን በመግለጽ፣ ልምምድ እየሰሩ በቶሎ እንዲያገግሙ ፌዴሬሽኑ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ መሆን አብራርተዋል። የአምስቱ ተጫዋቾች ውጤት እንደተሰማ በቡድኑ አባላት መካከል ድንጋጤ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ከኅብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት የመጡ ባለሙያዎች ሙያዊ ምክር እንደሰጧቸውም ተገልጿል። እነዚህ በኮቪድ-19 የተያዙ አምስት ተጫዋቾች ለለይቶ ማቆያነት ፈቃድ ወደ ተሰጣቸው ሆቴሎች ዛሬ፣ ሰኞ፣ እንደሚዛወሩም ኃፊው አክለው ተናግረዋል። አምስቱ ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ ቁልፍ ሚና እንደነበራቸው ያስታወሱት አቶ ባሕሩ በቡድኑ ላይ የሥነ ልቦና ጫና ቢኖረውም ቶሎ አገግመው ወደ ቡድኑ እንዲቀላቀሉ ይደረጋል ብለዋል። ተጫዋቾቹ ከ14 ቀን ለይቶ ማቆያ በኋላ ለጨዋታው ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚገመት ተናግረው፣ እነዚህን ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ የመቀላቀል ውሳኔ ግን የአሰልጣኙ መሆኑን አስረድተዋል። ቀሪ የቡድኑ አባላትን ከኮሮናቫይረስ ለመጠበቅ የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከኒጀር ጋር የሚኖራት ጨዋታ የሚካሄደው ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም መሆኑ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል። በተያያዘ ዜና ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ተቆርጠው የቆዩት ከፍተኛ ሊግ፣ አንደኛ ሊግና የሴቶች ፕሪሚየር ሊግን ኅዳር አጋማሽ ላይ ለመጀመር የእግር ስ ፌዴሬሽኑ አቅዶ ለቡድኖች ማሳወቁንና እነርሱም ዝግጅት ማድረጋቸውን አክለው ተናግረዋል። ውድድሮቹ የሚካሄዱት በዝግ ስታዲየም መሆኑን ገልፀው በሂደት አማራጮች እየታዩ ደጋፊዎች የሚገቡበት ሁኔታ ይፈቀዳል ብለው እንደሚያስቡ ለቢቢሲ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ተናግረዋል። | እግር ኳስ፡ አምስት ቁልፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ኢትዮጵያ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ከኒጀር ጋር ለምታደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ተጠርተው ከነበሩት ተጫዋቾች መካከል አምስት ቁልፍ ተጫዋቾች ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው ተነገረ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ለብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተው ከነበሩት 36 ተጫዋቾች መካከል ለቡድኑ ወሳኝ የሆኑት አምስት ተጫዋቾች በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አቶ ባህሩ ለውድድሩ 41 ተጫዋቾች መጠራታቸውን አስታውሰው፣ አምስቱ በተለያየ ምክንያት ቡድኑን አለመቀላቀላቸውን አመልክተዋል። ከአምስቱ መካከል ሁለቱ በአሁን ሰዓት በውጭ አገር በሙከራና በመጫወት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ሁለት ተጫዋቾች ዘግይተው ቡድኑን መቀላቀላቸውን ገልፀው፤ አንደኛው ደግሞ ከዚህ ቀደም በነበረበት ጉዳት ምክንያት ቡድኑን መቀላለቀል ያልቸለ መሆኑን ተናግረዋል። ለእግር ኳስ ቡድኑ አባላት የኮቪድ-19 ምርመራ ከመደረጉ በፊት የልብ ምርመራን ጨምሮ አጠቃላይ የጤና ምርመራ መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው፤ የኮቪድ-19 ምርመራውም ለሁሉም መሰጠቱን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ለብሔራዊ ቡድኑ ለተጠሩት ለአጠቃላዩ 36 ተጫዋቾች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎ አምስት ተጫዋቾች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል አቶ ባሕሩ። ቫይረሱ ከተገኘባቸው ተጫዋቾች ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉትን የመለየት ሥራ እየተሰራም መሆኑን ጨምረው አመልክተዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው አምስት ተጫዋቾች በአሁኑ ጊዜ በሆቴል ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ መደረጉን በመግለጽ፣ ልምምድ እየሰሩ በቶሎ እንዲያገግሙ ፌዴሬሽኑ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ መሆን አብራርተዋል። የአምስቱ ተጫዋቾች ውጤት እንደተሰማ በቡድኑ አባላት መካከል ድንጋጤ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ከኅብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት የመጡ ባለሙያዎች ሙያዊ ምክር እንደሰጧቸውም ተገልጿል። እነዚህ በኮቪድ-19 የተያዙ አምስት ተጫዋቾች ለለይቶ ማቆያነት ፈቃድ ወደ ተሰጣቸው ሆቴሎች ዛሬ፣ ሰኞ፣ እንደሚዛወሩም ኃፊው አክለው ተናግረዋል። አምስቱ ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ ቁልፍ ሚና እንደነበራቸው ያስታወሱት አቶ ባሕሩ በቡድኑ ላይ የሥነ ልቦና ጫና ቢኖረውም ቶሎ አገግመው ወደ ቡድኑ እንዲቀላቀሉ ይደረጋል ብለዋል። ተጫዋቾቹ ከ14 ቀን ለይቶ ማቆያ በኋላ ለጨዋታው ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚገመት ተናግረው፣ እነዚህን ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ የመቀላቀል ውሳኔ ግን የአሰልጣኙ መሆኑን አስረድተዋል። ቀሪ የቡድኑ አባላትን ከኮሮናቫይረስ ለመጠበቅ የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከኒጀር ጋር የሚኖራት ጨዋታ የሚካሄደው ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም መሆኑ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል። በተያያዘ ዜና ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ተቆርጠው የቆዩት ከፍተኛ ሊግ፣ አንደኛ ሊግና የሴቶች ፕሪሚየር ሊግን ኅዳር አጋማሽ ላይ ለመጀመር የእግር ስ ፌዴሬሽኑ አቅዶ ለቡድኖች ማሳወቁንና እነርሱም ዝግጅት ማድረጋቸውን አክለው ተናግረዋል። ውድድሮቹ የሚካሄዱት በዝግ ስታዲየም መሆኑን ገልፀው በሂደት አማራጮች እየታዩ ደጋፊዎች የሚገቡበት ሁኔታ ይፈቀዳል ብለው እንደሚያስቡ ለቢቢሲ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54417243 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስጂን እጥረት በርካቶች በሚሞቱባት ሕንድ ሆስፒታል ላይ በተነሳ እሳት 13 ህሙማን ሞቱ | ዛሬ አርብ በሕንዷ ከተማ ሙምባይ አቅራቢያ ባለ ኮቪድ-19 ህክምና ሆስፒታል ላይ በተነሳ ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። አርብ ጠዋት የተቀሰቀሰው እሳት ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆነ በኋላ በቁጥጥር ሰር የዋለ ሲሆን ከአደጋው ተረፉት ህሙማን በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተዘዋውረዋል። በርካታ ሰዎች በወረርሽኙ እየተያዙባት ባለችው ሕንድ በዛሬው ዕለት ብቻ 332,730 ሰዎች ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በዓለም በአንድ ቀን የተመዘገበው የህሙማን ቁጥር ነው ተብሏል። በበሽታው ሰበብ ህይወታቸው ሚያልፍ ሰዎች አሃዝም እጅግ ከፍተኛ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓታት 2,263 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። በሕንድ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ በዋና ከተማዋ ኒው ደልሂ ያሉ ሆስፒታሎች ከፍተኛ የኦክስጂን እጥረት አጋጥሟቸዋል። በዚህም ኦክስጂን በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ታማሚዎች ህይወት እያለፈ መሆኑን እና በሕንድ ምርጥ የተባለ የጤና መሰረተ ልማት ባያላት ኒው ደልሂ ከተማ ለጽኑ ህሙማን የሚሆኑ አልጋዎች ሞልተዋል ተብሏል። እስከ አሁን ድረስ 16 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ሕንድ አረጋግጣለች። ትናንት ሐሙስ ይፋ የተደረገው የ24 ሰዓታት የምርመራ ውጤት ብቻ ከ314 ሺህ በላይ ሰዎች በአንድ ቀን በወረርሽኙ መያዛቸውን እና ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ያሳያል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲም በቫይረሱ ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ግዛቶች መሪዎች እና ከኦክስጂን አምራቾች ጋር ዛሬ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከኒው ደልሂ ውጪ ጉጃራት፣ ኡታር ፕራዴሽ እና ሃርያና የተሰኙት ግዛቶች ተመሳሳይ የኦክስጂን እጥረት ገጥሟቸዋል። ግዛቶች የኦክስጂን መያዣ ጋኖች ወደ ሌሎች ግዛቶች እንዳይዘዋወሩ በማገድ ላይ ሲሆኑ፤ የተወሰኑ ተቋማት ምርቶቻቸውን ማከማቸት መጀመራቸውን የደልሂ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በኮቪድ-19 ተይዞ በህክምና ላይ ያለው የሕንድ ፖለቲከኛ ሳውራህ ባራድዋጅ በትዊተር ገጹ የተገጠመለት ኦክስጂን ሊያልቅ የቀረው ሦስት ሰዓታት ብቻ መሆኑን አጋርቶ ነበር። "ብዙ ሰዎች በኦክስጅን ላይ ጥገኛ ሆነው ነው ያሉት። የተገጠመላቸው ኦክስጂን ሲጠናቀቅ ህይወታቸው ያልፋል። ይህ ጊዜ በጋራ ተባብረን የምንሰራበት ነው" ሲል ተማፅኗል። በበሽታው ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በሕንድ ባህል መሰረት የሞቱ ሰዎች አስከሬንን ለማቃጠል ከፍተኛ ወረፋ መኖሩን ቤተሰቦች ገልጸዋል። አንድ ሐኪም በሆስፒታ ውስጥ ተራ የሚጠብቁ በርካታ አስከሬኖች መኖራቸውንም ገልጿል። | ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስጂን እጥረት በርካቶች በሚሞቱባት ሕንድ ሆስፒታል ላይ በተነሳ እሳት 13 ህሙማን ሞቱ ዛሬ አርብ በሕንዷ ከተማ ሙምባይ አቅራቢያ ባለ ኮቪድ-19 ህክምና ሆስፒታል ላይ በተነሳ ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። አርብ ጠዋት የተቀሰቀሰው እሳት ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆነ በኋላ በቁጥጥር ሰር የዋለ ሲሆን ከአደጋው ተረፉት ህሙማን በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተዘዋውረዋል። በርካታ ሰዎች በወረርሽኙ እየተያዙባት ባለችው ሕንድ በዛሬው ዕለት ብቻ 332,730 ሰዎች ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በዓለም በአንድ ቀን የተመዘገበው የህሙማን ቁጥር ነው ተብሏል። በበሽታው ሰበብ ህይወታቸው ሚያልፍ ሰዎች አሃዝም እጅግ ከፍተኛ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓታት 2,263 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። በሕንድ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ በዋና ከተማዋ ኒው ደልሂ ያሉ ሆስፒታሎች ከፍተኛ የኦክስጂን እጥረት አጋጥሟቸዋል። በዚህም ኦክስጂን በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ታማሚዎች ህይወት እያለፈ መሆኑን እና በሕንድ ምርጥ የተባለ የጤና መሰረተ ልማት ባያላት ኒው ደልሂ ከተማ ለጽኑ ህሙማን የሚሆኑ አልጋዎች ሞልተዋል ተብሏል። እስከ አሁን ድረስ 16 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ሕንድ አረጋግጣለች። ትናንት ሐሙስ ይፋ የተደረገው የ24 ሰዓታት የምርመራ ውጤት ብቻ ከ314 ሺህ በላይ ሰዎች በአንድ ቀን በወረርሽኙ መያዛቸውን እና ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ያሳያል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲም በቫይረሱ ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ግዛቶች መሪዎች እና ከኦክስጂን አምራቾች ጋር ዛሬ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከኒው ደልሂ ውጪ ጉጃራት፣ ኡታር ፕራዴሽ እና ሃርያና የተሰኙት ግዛቶች ተመሳሳይ የኦክስጂን እጥረት ገጥሟቸዋል። ግዛቶች የኦክስጂን መያዣ ጋኖች ወደ ሌሎች ግዛቶች እንዳይዘዋወሩ በማገድ ላይ ሲሆኑ፤ የተወሰኑ ተቋማት ምርቶቻቸውን ማከማቸት መጀመራቸውን የደልሂ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በኮቪድ-19 ተይዞ በህክምና ላይ ያለው የሕንድ ፖለቲከኛ ሳውራህ ባራድዋጅ በትዊተር ገጹ የተገጠመለት ኦክስጂን ሊያልቅ የቀረው ሦስት ሰዓታት ብቻ መሆኑን አጋርቶ ነበር። "ብዙ ሰዎች በኦክስጅን ላይ ጥገኛ ሆነው ነው ያሉት። የተገጠመላቸው ኦክስጂን ሲጠናቀቅ ህይወታቸው ያልፋል። ይህ ጊዜ በጋራ ተባብረን የምንሰራበት ነው" ሲል ተማፅኗል። በበሽታው ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በሕንድ ባህል መሰረት የሞቱ ሰዎች አስከሬንን ለማቃጠል ከፍተኛ ወረፋ መኖሩን ቤተሰቦች ገልጸዋል። አንድ ሐኪም በሆስፒታ ውስጥ ተራ የሚጠብቁ በርካታ አስከሬኖች መኖራቸውንም ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56827449 |
5sports
| የጀርመን ቡንደስሊጋ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' ያላቸውን ድጋፍ አሳዩ | የጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ያላቸውን ድጋፍ በትናንትናው ዕለት በተለያዩ ተቃውሞዎች አሳይተዋል። የብሮሲያ ዶርትሙንድና ሄርታ በርሊን ተጫዋቾች በሲግናል ኢዱና ፓርክ በመገኘት ሜዳውን በመክበብም በጉልበታቸው ተንበርክከው ነበር። የዶርትሙንድ ተጫዋቾች ከውድድሩ በፊት ሲያሟሙቁ "ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም" እንዲሁም "ተባብረን እንቁም" የሚሉ መልእክቶች በተፃፈባቸው ማሊያዎች (ካናቴራዎች) ነው። የባየር ሙኒክ ተወዳዳሪዎች "ለዘረኝነት ቀይ ካርድ" የሚል ማሊያ (ካናቴራ) ለብሰው የነበረ ሲሆን፤ በዛኑ ዕለት ባየር ሌቨርኩሰንን 4 ለ2 በሆነ ውጤት ረትተዋል። የቡንደስሊጋ ቡድኑ አመራሮችም እንዲሁም የቡድኑ አባላት በጨዋታዎች ላይ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' የሚል ፅሁፍ ያለበት እጃቸው ላይ አጥልቀው ነበር ተብሏል። የሜይንዝ ቡድን አጥቂ ካሜሮናዊው ፒየር ኩንዴ ከኤይንትራችት ፍራንክፈርት ጋር ባደረጉት ጨዋታም ላይ ጎል ካስቆጠረ በኋላ በጉልበቱ ተንበርክኳል። በግጥሚያው ቡድኑ 2 ለ0 ረትቷል። በዚህ ሳምንትም ታዋቂዎቹ የስፖርት ሰዎች ሴረና ዊልያምስ፣ ፓውል ፖግባና ሊውስ ሃሚልተን በአሜሪካ በጥቁሮች ላይ የሚፈፀመውን የፖሊስ ጭካኔ አስመልክቶ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት በሚኒያፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ ከመሬት ላይ ተጣብቆ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ለዘጠኝ ደቂቃ ተጭኖት ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በበርካታ ግዛቶች ተቃውሞች ተቀጣጥለዋል። | የጀርመን ቡንደስሊጋ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' ያላቸውን ድጋፍ አሳዩ የጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ያላቸውን ድጋፍ በትናንትናው ዕለት በተለያዩ ተቃውሞዎች አሳይተዋል። የብሮሲያ ዶርትሙንድና ሄርታ በርሊን ተጫዋቾች በሲግናል ኢዱና ፓርክ በመገኘት ሜዳውን በመክበብም በጉልበታቸው ተንበርክከው ነበር። የዶርትሙንድ ተጫዋቾች ከውድድሩ በፊት ሲያሟሙቁ "ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም" እንዲሁም "ተባብረን እንቁም" የሚሉ መልእክቶች በተፃፈባቸው ማሊያዎች (ካናቴራዎች) ነው። የባየር ሙኒክ ተወዳዳሪዎች "ለዘረኝነት ቀይ ካርድ" የሚል ማሊያ (ካናቴራ) ለብሰው የነበረ ሲሆን፤ በዛኑ ዕለት ባየር ሌቨርኩሰንን 4 ለ2 በሆነ ውጤት ረትተዋል። የቡንደስሊጋ ቡድኑ አመራሮችም እንዲሁም የቡድኑ አባላት በጨዋታዎች ላይ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' የሚል ፅሁፍ ያለበት እጃቸው ላይ አጥልቀው ነበር ተብሏል። የሜይንዝ ቡድን አጥቂ ካሜሮናዊው ፒየር ኩንዴ ከኤይንትራችት ፍራንክፈርት ጋር ባደረጉት ጨዋታም ላይ ጎል ካስቆጠረ በኋላ በጉልበቱ ተንበርክኳል። በግጥሚያው ቡድኑ 2 ለ0 ረትቷል። በዚህ ሳምንትም ታዋቂዎቹ የስፖርት ሰዎች ሴረና ዊልያምስ፣ ፓውል ፖግባና ሊውስ ሃሚልተን በአሜሪካ በጥቁሮች ላይ የሚፈፀመውን የፖሊስ ጭካኔ አስመልክቶ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት በሚኒያፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ ከመሬት ላይ ተጣብቆ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ለዘጠኝ ደቂቃ ተጭኖት ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በበርካታ ግዛቶች ተቃውሞች ተቀጣጥለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-52954511 |
2health
| የአውሮፓ ዕለታዊ የኮቪድ ሞት ካለፈው ሳምንት አንጻር 40 በመቶ ከፍ ብሏል | በአውሮፓ በየቀኑ የሚመዘገበው የሞት መጠን ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ እንደተናገሩት ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ሩሲያ በአንድ ሦስተኛ ባደገው ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። "በሆስፒታሎች ውስጥ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በጣም በታመሙ ሰዎች መሞላት ጀምረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በቀን 320 የሆነ ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ26ሺህ በላይ አድርሶታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በ 221 ሰዎች ሞት ምክንያት በጣሊያን ውስጥም እንዲሁ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። በአጠቃላይ በኦስትሪያ የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ ከ 1000 በላይ ሆኗል። ጣሊያን ውስጥም ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ 22,000 ደርሰዋል። አዲስ የተጣለውን ገደብ በመቃወም ሰኞ አመሻሽ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች በጣሊያን ተካሂደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ምን አለ? ከቢቢሲ ወርልድ ጋር ቆይታ ያደረጉት ያደረጉት ዶ/ር ሃሪስ "በመላው አውሮፓ የከፋ እና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ እያየን ነው" ብለዋል። ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሦስተኛ ሲጨምር የሚመዘገበው የሞት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ብሏል። "የሆስፒታሎችን አቅም በተሻለ መንገድ ማስተዳደር ቢቻልም በበርካታ አገራት የሚገኙ ሆስፒታሎች አልጋዎች በፍጥነት እየተያዙ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "በተወሰኑ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የተጣሉ አዳዲስ ገደቦች ውጤታማነት የሚታወቀው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው" ብለዋል። ሩሲያ ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች በሚበዙባቸው እንደ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ታክሲ እና አሳንሰር ያሉ ቦታዎች ላይ የአፍና አፍኝጫ መሸፈኛዎችን ማድረግን አስገዳጅ አድርጋለች። የፈረንሳይ መንግሥት በፓሪስ እና በሌሎች ከተሞች ውስጥ ቀድሞ የተጣሉትን እገዳዎች ማራዘምን ጨምሮ ጥብቅ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ እየተወያየ ነው። ጣሊያን ካለፈው አርብ ጀምሮ ምግብና እና መጠጥ ቤቶች፣ የስፖርት መዝወተሪያ ስፍራዎች ና ሲኒማዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መዘጋታቸውን በመቃወም በቱሪን ሰልፍ ያደረጉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል። | የአውሮፓ ዕለታዊ የኮቪድ ሞት ካለፈው ሳምንት አንጻር 40 በመቶ ከፍ ብሏል በአውሮፓ በየቀኑ የሚመዘገበው የሞት መጠን ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ እንደተናገሩት ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ሩሲያ በአንድ ሦስተኛ ባደገው ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። "በሆስፒታሎች ውስጥ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በጣም በታመሙ ሰዎች መሞላት ጀምረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በቀን 320 የሆነ ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ26ሺህ በላይ አድርሶታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በ 221 ሰዎች ሞት ምክንያት በጣሊያን ውስጥም እንዲሁ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። በአጠቃላይ በኦስትሪያ የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ ከ 1000 በላይ ሆኗል። ጣሊያን ውስጥም ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ 22,000 ደርሰዋል። አዲስ የተጣለውን ገደብ በመቃወም ሰኞ አመሻሽ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች በጣሊያን ተካሂደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ምን አለ? ከቢቢሲ ወርልድ ጋር ቆይታ ያደረጉት ያደረጉት ዶ/ር ሃሪስ "በመላው አውሮፓ የከፋ እና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ እያየን ነው" ብለዋል። ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሦስተኛ ሲጨምር የሚመዘገበው የሞት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ብሏል። "የሆስፒታሎችን አቅም በተሻለ መንገድ ማስተዳደር ቢቻልም በበርካታ አገራት የሚገኙ ሆስፒታሎች አልጋዎች በፍጥነት እየተያዙ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "በተወሰኑ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የተጣሉ አዳዲስ ገደቦች ውጤታማነት የሚታወቀው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው" ብለዋል። ሩሲያ ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች በሚበዙባቸው እንደ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ታክሲ እና አሳንሰር ያሉ ቦታዎች ላይ የአፍና አፍኝጫ መሸፈኛዎችን ማድረግን አስገዳጅ አድርጋለች። የፈረንሳይ መንግሥት በፓሪስ እና በሌሎች ከተሞች ውስጥ ቀድሞ የተጣሉትን እገዳዎች ማራዘምን ጨምሮ ጥብቅ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ እየተወያየ ነው። ጣሊያን ካለፈው አርብ ጀምሮ ምግብና እና መጠጥ ቤቶች፣ የስፖርት መዝወተሪያ ስፍራዎች ና ሲኒማዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መዘጋታቸውን በመቃወም በቱሪን ሰልፍ ያደረጉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል። | https://www.bbc.com/amharic/54708506 |
2health
| የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት ላይ የተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ውጤት አሳየ | በኦክስፎርድ የኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በቡርኪናፋሶ ሳይንቲስቶች በጋራ የተሰራ አዲስ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት በተደረገለት ሙከራ ውጤታማ መሆነ ተገለጸ። በክትባቱ ላይ በተደረጉት መጀመሪያ ሙከራዎች 77 በመቶ በሆነ ውጤት ስኬታማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለህክምና ከሚውሉ መድኃኒቶች አንጻር ውጤታማነቱ በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል። የህክምና ጉዳዮች መጽሔት በሆነው 'ላንሴት' ላይ የታተመው የጥናቱ ውጤት 450 ከቡርኪናፋሶ የተወጣጡ ህጻናት የተሳተፉበት ሲሆን ከዚህ በኋላ በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበት ሙከራ ይደረግበታል። በቀጣዩ የሙከራ ሂደትም 4,800 ህጻናት የሚሳተፉ ሲሆን እነዚህም ከቡርኪናፋሶ፣ ከማሊ እና ከኬንያ ናቸው። "ይህ ሙከራ በጣም አስደሳች የሆነ ውጤታማነት ነው ያሳየው። ክትባቱ ከዚህ በፊት ከነበሩ ህክምናዊች አንጻር የተሻለ የመከላከል ብቃት አሳይቷል። "በመቀጠል የምናካሂዳቸውን ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ሙከራዎች እየተጠባበቅን ነው። በእነዚህ ሙከራዎች በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን በስፋት ቢመረት ምን አይነት ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ይረዳናል" ብለዋል በቡርኪናፋሶ የጤና ሳይንስ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ሃሊዶ ቲንቶ። ለወባ በሽታ የሚሆን ክትባት ማግኘት በህክምና ምርምር ውስጥ እግጅ ትልቅ ዜና ነው የሚሆነው። ሙከራው በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ትልቅ ግኝት እንደሚሆን ይጠበቃል። የወባ በሽታ በዓመት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ለወባ በሽታ የሚሆን አንድ ክትባት ያለ ሲሆን ውጤታማነቱ ደግሞ 50 በመቶ ብቻ ነው። በአዲሱ ክትባት የመጀመሪያ ዙር ሙከራ ላይ 77 በመቶ ውጤታማነት የታየ ሲሆን በሌሎች አገራትም ላይ ለመሞከር ታቅዷል። በጊዜ ብዛት ደግሞ ቢያንስ በአራት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ይሞከራል። በሙከራው የሚሳተፉት 5 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ እድሜያቸው ከሦስት ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። አሁን በሙከራ ላይ የሚገኘው አዲሱ ክትባት ሙሉ ፈቃድ አላገኘም። ነገር ግን ውጤታማነቱ በሙከራዎች በተገቢ ሁኔታ የሚረጋገጥ ከሆነ የበርካቶችን ህይወት የማትረፍ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል። | የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት ላይ የተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ውጤት አሳየ በኦክስፎርድ የኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በቡርኪናፋሶ ሳይንቲስቶች በጋራ የተሰራ አዲስ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት በተደረገለት ሙከራ ውጤታማ መሆነ ተገለጸ። በክትባቱ ላይ በተደረጉት መጀመሪያ ሙከራዎች 77 በመቶ በሆነ ውጤት ስኬታማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለህክምና ከሚውሉ መድኃኒቶች አንጻር ውጤታማነቱ በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል። የህክምና ጉዳዮች መጽሔት በሆነው 'ላንሴት' ላይ የታተመው የጥናቱ ውጤት 450 ከቡርኪናፋሶ የተወጣጡ ህጻናት የተሳተፉበት ሲሆን ከዚህ በኋላ በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበት ሙከራ ይደረግበታል። በቀጣዩ የሙከራ ሂደትም 4,800 ህጻናት የሚሳተፉ ሲሆን እነዚህም ከቡርኪናፋሶ፣ ከማሊ እና ከኬንያ ናቸው። "ይህ ሙከራ በጣም አስደሳች የሆነ ውጤታማነት ነው ያሳየው። ክትባቱ ከዚህ በፊት ከነበሩ ህክምናዊች አንጻር የተሻለ የመከላከል ብቃት አሳይቷል። "በመቀጠል የምናካሂዳቸውን ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ሙከራዎች እየተጠባበቅን ነው። በእነዚህ ሙከራዎች በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን በስፋት ቢመረት ምን አይነት ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ይረዳናል" ብለዋል በቡርኪናፋሶ የጤና ሳይንስ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ሃሊዶ ቲንቶ። ለወባ በሽታ የሚሆን ክትባት ማግኘት በህክምና ምርምር ውስጥ እግጅ ትልቅ ዜና ነው የሚሆነው። ሙከራው በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ትልቅ ግኝት እንደሚሆን ይጠበቃል። የወባ በሽታ በዓመት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ለወባ በሽታ የሚሆን አንድ ክትባት ያለ ሲሆን ውጤታማነቱ ደግሞ 50 በመቶ ብቻ ነው። በአዲሱ ክትባት የመጀመሪያ ዙር ሙከራ ላይ 77 በመቶ ውጤታማነት የታየ ሲሆን በሌሎች አገራትም ላይ ለመሞከር ታቅዷል። በጊዜ ብዛት ደግሞ ቢያንስ በአራት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ይሞከራል። በሙከራው የሚሳተፉት 5 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ እድሜያቸው ከሦስት ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። አሁን በሙከራ ላይ የሚገኘው አዲሱ ክትባት ሙሉ ፈቃድ አላገኘም። ነገር ግን ውጤታማነቱ በሙከራዎች በተገቢ ሁኔታ የሚረጋገጥ ከሆነ የበርካቶችን ህይወት የማትረፍ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56827450 |
0business
| መንግሥት በኦሮሚያ ባለው ታጣቂ ቡድን ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ | የመንግሥት ኃይል በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በሰጡት መግለጫ፣ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራውንና መንግሥት 'ሸኔ' ሲል በአሸባሪነት የፈረጀውን ታጣቂ ኃይል ለማስወገድ ፀረ ሽምቅ ውጊያ ኮማንዶ በማሰማራት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ዘመቻው በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ እና በምሥራቅ ወለጋ፣ በምዕራብ እና በምሥራቅ ጉጂ፣ በሰሜን፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በቦርና ዞኖች እየተካሄደ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። እየተደረገ ባለው ዘመቻ "በሺዎች የሚቆጠሩ" የታጣቂው ቡደኑ አባላት መገደላቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ፣ የቡድኑ አመራሮች፣ ታጣቂዎች፣ የስንቅና የሥልጠና ማዕከል "ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፤ መሳሪያዎችም ተማርከዋል ብለዋል። ለገሰ ቱሉ ( ዶ/ር) ታጣቂው ኃይል በተቀናጀው ኦፕሬሽን እየደረሰበት ያለውን ጉዳት መቋቋም ባለመቻሉ እየተበተነ ነው ሲሉም በመግለጫቸው አመልክተዋል። ሆኖም ከትናንት በስቲያ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( ኦፌኮ) በሰጠው መግለጫ በኦሮሚያ ዞኖች ከዓለም ዓይን የተሰወረ ጦርነት እየተካሄደ ነው ሲል በጦርነቱ በርካታ ዜጎች በጅምላ መገደላቸውን ገልጿል። ኦፌኮ እየተፈጸሙ ነው ያላቸው "የጅምላ ግድያዎች"ም ገለልተኛ በሆነ ዓለም አቀፍ አካልም እንዲጣራ ጠይቋል። እንደ ፓርቲው መግለጫ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ንጹሃን ናቸው ያላቸው ከ297 በላይ ሰዎች በክልሉ በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል፤ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ( ኦቻ) በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር እና ግጭቶች ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው እንደወጡ አመልክቷል። ቀደም ብሎም መንግሥት በዘመቻው ድል እየቀናኝ ነው ማለቱን ተከትሎ ፣ ታጣቂ ቡድኑ በታጣቂዎቹ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና የመንግሥት እርምጃ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ለቢቢሲ ገልጾ ነበር። በክልሉ በታጣቂ ቡድኑና በመንግሥት መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሥልጣናትም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መንግሥት ታጣቂ ቡድኑ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎችም በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃትም ፈጽሟል። መንግሥት ግን እነዚህን ክሶች ያጣጣላቸው ሲሆን ዘመቻው በክልሉ እየደረሰ ያለውን ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት ለማስቀረት የተጀመረ ነው ብሏል። ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ እና ምዕራብ ሸዋ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለ ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤ ከቤት ንብረታቸውም ተፈናቅለዋል። ለገሰ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ይህንን "ዘመቻ ለማጠልሸት የሚጥሩ ኃይሎች አሉ" ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ኃይሎች መንግሥት በታጣቂ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ንጹሃን ዜጎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው በሚል የሚጮሁ ናቸው" ሲሉ ማንነታቸውን ያልገለጿቸውን አካላት ከሰዋል። ይሁን እንጂ ለተከታታይ ሳምንታት እየተካሄደ ባለው ዘመቻ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች "እፎይታ እየተሰማቸው ነው" ብለዋል። በመግለጫው የተነሱ ሌሎች ጉዳዮችስ ? ስለጎንደሩ ግጭት በጎንደር በቀብር ስፍራ በተወሰኑ ሰዎች አለመግባባት በተፈጠረ ግጭት ጉዳት ቢከሰትም ታቅዶ ነበር ያሉት 'ሴራ' መክሸፉን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል። በግጭቱ የወደሙ መስጊዶችና አብያተ ክርስቲያናትን በጋራ ለመገንባት፣ ንብረታቸው የወደመባቸውና የተዘረፈባቸውን ግለሰቦች መልሶ ለማቋቋምም እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ግጭት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ አካላትም ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ እየታየ ነው ብለዋል። ከሳምንታት በፊት በጎንደር በቀብር ሥፍራ ላይ በተከሰተ ሃይማኖታዊ መልክ ያለው ግጭት ቢያንስ የ21 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ150 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ መገለጹ ይታወሳል። ይህ ግጭት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። ሚኒስትሩ ይህንን በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ የመርማሪ ቡድን እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። 'አልሸባብ' የኮሚዩኒኬሽ አገልግሎት ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የአልሻባብ የሽብር ቡድን ከሸኔ እና ከህወሓት ጋር በመቀናጀት በመሃል አገር፣ በምሥራቅና በምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃቶችን ለመፈፀም የወጠኑትን እቅድ መንግሥት በወሰደው እርምጃ ሳይሳካ መቅረቱን ተናግረዋል። በተወሰደው እርምጃም ቀደም ብሎ በርካታ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ ባለፉት ቀናት በሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖች፣ በኦሮሚያ፣ በምዕራብ ሐረርጌ እና በአርሲ፣ በምዕራብና ምሥራቅ ባሌ በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። እስካሁንም 45 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ሚኒስትሩ ገልጸው፣ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በርካታ የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውንና በየቤተ እምነቶች የተቀበሩ መሣሪያዎችም በሕዝብ ጥቆማ እየተለቀሙ ነው ብለዋል። በዚህም 105 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 13 ብሬል፣ 25 አርፒጂ፣ 25 ሳጥን የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥይቶች፣ አራት ስናይፐር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አመልክተዋል። በአማራ ክልል ስላለው የፀጥታ ሁኔታ የአማራ ክልል እና አጎራባች ክልሎችን ለማጋጨት እና ሕገ ወጥነት ለማስፋፋት ሆነ ብለው የሚሰሩ ኃይሎች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያሉ "ኢ መደበኛ አደረጃጀቶች" ሕግ በማስከበርና ክልሉን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያስችል አሰራር ተነድፎ አሳታፊ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። ሚኒስትሩ አክለውም በክልሉ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት የሚደረግ እንቅስቃሴ ለመግታት የሚሰሩ ኃይሎች ላይም ምህረት እንደማይኖር አስጠንቅቀዋል። ሰብዓዊ እርዳታ ለትግራይ ሚኒስትሩ ከሰሜኑ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ጋር በተያያዘም ወደ ትግራይ በየብስም፣ በአየርም የሚጓጓዘው ሰብዓዊ እርዳታ እንደቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ሚኒስትሩ መግለጫ ከሆነ ባለፈው ሳምንት 165 ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀለ ገብተዋል። የእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ማቅረብ የሚችሉት እርዳታ ያህል እንዲያቀርቡ መንግሥትም የተቻለውን እያደረገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን የትግራይ ኃይሎች ለእርዳታ ማጓጓዝ ሥራው እንቅፋት ሆነዋል ብለዋል። "ህወሓት ከአፋር ክልል መውጣቱን ቢገልጽም፣ አሁንም በአፋር ክልል ከበርሃሌ፣ ከኮነባ፣ ከአብአላ እና ከመጋሌ ወረዳዎች አልወጣም። በአማራ ክልልም፣ አድርቃይ፣ ጠለምት፣ አበርገሌ እና ሌሎች አካባቢዎችን ይዞ ይገኛል" ሲሉ ከሰዋል። ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ያለገደብ ትግራይ እንዲደርስ ሙሉ በሙሉ ከአፋር ክልል መውጣቱን ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ የፀጥታ ባለሥልጣናት ኃይሎቹ አሁንም በክልሉ እንደሚገኙ ለቢቢሲ መግለጻቸው የሚታወስ ነው። መንግሥት ከህወሓት የሚቃጣን ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜና ሰዓት ሙሉ ዝግጁነትና አቅም ያለው መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ግጭት ቀስቃሽ በሆኑ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ተነሳስቶ ወደ ግጭት እንደማይገባ ግን በአጽንኦት ተናግረዋል። የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ ንረትና ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳሳቢ ሆኗል። ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫም የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከምርት አቅርቦት ጋር የሚያያዝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ስኳር፣ ዘይት፣ የህጻናት አልሚ ምግቦች እና ሌሎች ምግብ ነክ ፍጆታዎችን በፍራንኮ ቫሉታ አገር ውስጥ እንዲገቡ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። ፍራንኮ ቫሉታ ሕጋዊ ከሆነ ምንጭ የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ሲሆን የባንክ ቤት ፈቃድ ሳያስፈልገው ከውጪ አገር ዕቃ ለማስገባት የሚያስችል ፈቃድ ነው። ባለፉት ወራት በ700 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ የለማ ስንዴ ውጤት በማስገኘቱ ከ25 ሚሊየን ኩንታል በላይ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ተጨማሪ ምርት ለማግኘት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ሚኒስትሩ አክለዋል። ከዚህ ባሻገርም በግንባታው ዘርፍ ላይ እና በሲሚንቶ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታትም እየተሠራ ነው ብለዋል። | መንግሥት በኦሮሚያ ባለው ታጣቂ ቡድን ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ የመንግሥት ኃይል በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በሰጡት መግለጫ፣ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራውንና መንግሥት 'ሸኔ' ሲል በአሸባሪነት የፈረጀውን ታጣቂ ኃይል ለማስወገድ ፀረ ሽምቅ ውጊያ ኮማንዶ በማሰማራት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ዘመቻው በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ እና በምሥራቅ ወለጋ፣ በምዕራብ እና በምሥራቅ ጉጂ፣ በሰሜን፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በቦርና ዞኖች እየተካሄደ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። እየተደረገ ባለው ዘመቻ "በሺዎች የሚቆጠሩ" የታጣቂው ቡደኑ አባላት መገደላቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ፣ የቡድኑ አመራሮች፣ ታጣቂዎች፣ የስንቅና የሥልጠና ማዕከል "ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፤ መሳሪያዎችም ተማርከዋል ብለዋል። ለገሰ ቱሉ ( ዶ/ር) ታጣቂው ኃይል በተቀናጀው ኦፕሬሽን እየደረሰበት ያለውን ጉዳት መቋቋም ባለመቻሉ እየተበተነ ነው ሲሉም በመግለጫቸው አመልክተዋል። ሆኖም ከትናንት በስቲያ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( ኦፌኮ) በሰጠው መግለጫ በኦሮሚያ ዞኖች ከዓለም ዓይን የተሰወረ ጦርነት እየተካሄደ ነው ሲል በጦርነቱ በርካታ ዜጎች በጅምላ መገደላቸውን ገልጿል። ኦፌኮ እየተፈጸሙ ነው ያላቸው "የጅምላ ግድያዎች"ም ገለልተኛ በሆነ ዓለም አቀፍ አካልም እንዲጣራ ጠይቋል። እንደ ፓርቲው መግለጫ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ንጹሃን ናቸው ያላቸው ከ297 በላይ ሰዎች በክልሉ በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል፤ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ( ኦቻ) በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር እና ግጭቶች ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው እንደወጡ አመልክቷል። ቀደም ብሎም መንግሥት በዘመቻው ድል እየቀናኝ ነው ማለቱን ተከትሎ ፣ ታጣቂ ቡድኑ በታጣቂዎቹ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና የመንግሥት እርምጃ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ለቢቢሲ ገልጾ ነበር። በክልሉ በታጣቂ ቡድኑና በመንግሥት መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሥልጣናትም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መንግሥት ታጣቂ ቡድኑ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎችም በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃትም ፈጽሟል። መንግሥት ግን እነዚህን ክሶች ያጣጣላቸው ሲሆን ዘመቻው በክልሉ እየደረሰ ያለውን ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት ለማስቀረት የተጀመረ ነው ብሏል። ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ እና ምዕራብ ሸዋ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለ ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤ ከቤት ንብረታቸውም ተፈናቅለዋል። ለገሰ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ይህንን "ዘመቻ ለማጠልሸት የሚጥሩ ኃይሎች አሉ" ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ኃይሎች መንግሥት በታጣቂ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ንጹሃን ዜጎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው በሚል የሚጮሁ ናቸው" ሲሉ ማንነታቸውን ያልገለጿቸውን አካላት ከሰዋል። ይሁን እንጂ ለተከታታይ ሳምንታት እየተካሄደ ባለው ዘመቻ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች "እፎይታ እየተሰማቸው ነው" ብለዋል። በመግለጫው የተነሱ ሌሎች ጉዳዮችስ ? ስለጎንደሩ ግጭት በጎንደር በቀብር ስፍራ በተወሰኑ ሰዎች አለመግባባት በተፈጠረ ግጭት ጉዳት ቢከሰትም ታቅዶ ነበር ያሉት 'ሴራ' መክሸፉን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል። በግጭቱ የወደሙ መስጊዶችና አብያተ ክርስቲያናትን በጋራ ለመገንባት፣ ንብረታቸው የወደመባቸውና የተዘረፈባቸውን ግለሰቦች መልሶ ለማቋቋምም እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ግጭት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ አካላትም ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ እየታየ ነው ብለዋል። ከሳምንታት በፊት በጎንደር በቀብር ሥፍራ ላይ በተከሰተ ሃይማኖታዊ መልክ ያለው ግጭት ቢያንስ የ21 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ150 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ መገለጹ ይታወሳል። ይህ ግጭት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። ሚኒስትሩ ይህንን በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ የመርማሪ ቡድን እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። 'አልሸባብ' የኮሚዩኒኬሽ አገልግሎት ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የአልሻባብ የሽብር ቡድን ከሸኔ እና ከህወሓት ጋር በመቀናጀት በመሃል አገር፣ በምሥራቅና በምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃቶችን ለመፈፀም የወጠኑትን እቅድ መንግሥት በወሰደው እርምጃ ሳይሳካ መቅረቱን ተናግረዋል። በተወሰደው እርምጃም ቀደም ብሎ በርካታ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ ባለፉት ቀናት በሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖች፣ በኦሮሚያ፣ በምዕራብ ሐረርጌ እና በአርሲ፣ በምዕራብና ምሥራቅ ባሌ በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። እስካሁንም 45 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ሚኒስትሩ ገልጸው፣ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በርካታ የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውንና በየቤተ እምነቶች የተቀበሩ መሣሪያዎችም በሕዝብ ጥቆማ እየተለቀሙ ነው ብለዋል። በዚህም 105 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 13 ብሬል፣ 25 አርፒጂ፣ 25 ሳጥን የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥይቶች፣ አራት ስናይፐር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አመልክተዋል። በአማራ ክልል ስላለው የፀጥታ ሁኔታ የአማራ ክልል እና አጎራባች ክልሎችን ለማጋጨት እና ሕገ ወጥነት ለማስፋፋት ሆነ ብለው የሚሰሩ ኃይሎች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያሉ "ኢ መደበኛ አደረጃጀቶች" ሕግ በማስከበርና ክልሉን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያስችል አሰራር ተነድፎ አሳታፊ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። ሚኒስትሩ አክለውም በክልሉ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት የሚደረግ እንቅስቃሴ ለመግታት የሚሰሩ ኃይሎች ላይም ምህረት እንደማይኖር አስጠንቅቀዋል። ሰብዓዊ እርዳታ ለትግራይ ሚኒስትሩ ከሰሜኑ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ጋር በተያያዘም ወደ ትግራይ በየብስም፣ በአየርም የሚጓጓዘው ሰብዓዊ እርዳታ እንደቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ሚኒስትሩ መግለጫ ከሆነ ባለፈው ሳምንት 165 ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀለ ገብተዋል። የእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ማቅረብ የሚችሉት እርዳታ ያህል እንዲያቀርቡ መንግሥትም የተቻለውን እያደረገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን የትግራይ ኃይሎች ለእርዳታ ማጓጓዝ ሥራው እንቅፋት ሆነዋል ብለዋል። "ህወሓት ከአፋር ክልል መውጣቱን ቢገልጽም፣ አሁንም በአፋር ክልል ከበርሃሌ፣ ከኮነባ፣ ከአብአላ እና ከመጋሌ ወረዳዎች አልወጣም። በአማራ ክልልም፣ አድርቃይ፣ ጠለምት፣ አበርገሌ እና ሌሎች አካባቢዎችን ይዞ ይገኛል" ሲሉ ከሰዋል። ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ያለገደብ ትግራይ እንዲደርስ ሙሉ በሙሉ ከአፋር ክልል መውጣቱን ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ የፀጥታ ባለሥልጣናት ኃይሎቹ አሁንም በክልሉ እንደሚገኙ ለቢቢሲ መግለጻቸው የሚታወስ ነው። መንግሥት ከህወሓት የሚቃጣን ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜና ሰዓት ሙሉ ዝግጁነትና አቅም ያለው መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ግጭት ቀስቃሽ በሆኑ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ተነሳስቶ ወደ ግጭት እንደማይገባ ግን በአጽንኦት ተናግረዋል። የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ ንረትና ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳሳቢ ሆኗል። ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫም የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከምርት አቅርቦት ጋር የሚያያዝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ስኳር፣ ዘይት፣ የህጻናት አልሚ ምግቦች እና ሌሎች ምግብ ነክ ፍጆታዎችን በፍራንኮ ቫሉታ አገር ውስጥ እንዲገቡ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። ፍራንኮ ቫሉታ ሕጋዊ ከሆነ ምንጭ የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ሲሆን የባንክ ቤት ፈቃድ ሳያስፈልገው ከውጪ አገር ዕቃ ለማስገባት የሚያስችል ፈቃድ ነው። ባለፉት ወራት በ700 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ የለማ ስንዴ ውጤት በማስገኘቱ ከ25 ሚሊየን ኩንታል በላይ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ተጨማሪ ምርት ለማግኘት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ሚኒስትሩ አክለዋል። ከዚህ ባሻገርም በግንባታው ዘርፍ ላይ እና በሲሚንቶ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታትም እየተሠራ ነው ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61435712 |
0business
| ‘ፓትሪዮት’፡ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጣት ብዙ የተነገረለት አየር መቃወሚያ | ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ምዕራባዊያንን አጥብቀው ሲጠይቁ የነበረው አንድ ነገር የአየር መቃወሚያ እንዲሰጣቸው ነበር። ምክንያቱም ሩሲያ በአየር ኃይሏ ኪዬቭን ጨምሮ ዋና ዋና ከተሞችን በጨለማ እንዲዋጡ አድርጋለች። በካሚካዚ ድሮንና በተወንጫፊ ሚሳኤሎች ብዙ ጥፋት አድርሳለች። ውሃና መብራት ለሚሊዮኖች ቅንጦት ሆኖ እንዲሰማቸው ሆኗል። ዩክሬናውያን የውርጩን ዘመን ያለማሞቅያ በብርድ እየተንዘፈዘፉ እንዲኖሩ ተደርገዋል። በዩክሬን ብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ ነው የሚከፋፈለው። ከዚህም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በዩክሬን ሰማይ ላይ የሚፈነጩትን ድሮኖችና ሚሳኤሎች ጭጭ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል። አንድ ነገር መደረግ ነበረበት። ዜሌንስኪ ምዕራባዊያን ድረሱልን አሉ። ይነስም ይብዛ ደርሰውላቸዋል። ይሁንና እስከዛሬ የደረሳቸው የአየር መቃወሚያ ዘመናዊ ቢሆንም ከሩሲያ አቅም አንጻር ሲታይ የልብ አያደርስም። ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ወደ አሜሪካ ማማተር ጀመሩ። ጆ ባይደን አላሳፈሯቸውም። ባይደን ለዜሌንስኪ አንድ ያረጋገጡላቸው ነገር ቢኖር ከሰሞኑ እጅግ የላቁ ናቸው የሚባሉትን የአየር መቃወሚያዎች እንደሚልኩላቸው ነው። ፓትሪዮት ይባላል ስማቸው። ይህ እርዳታ አሜሪካ ለዩክሬን 66 ቢሊዮን ዶላር ከለገሰች በኋላ የመጣ ትልቁ ስጦታ ሆኗል። ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያዎች ውድ፣ በጣም ውጤታማ እና የልብ አድርስ ናቸው ይባላል። አንድ ፓትሪዮት ሚሳኤል ዋጋው ይጠራ ከተባለ ዋጋው 3 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል። ይህ ማለት በምሕጻረ ቃል ኤንኤኤምኤስ (NASAMS) የሚባሉትን ዘመናዊ የአየር መቃወሚያዎች በሦስት እጥፍ በዋጋ ይበልጣቸዋል። ፓትሪዮት ሚሳኤሎች የተሠሩት በኢራቅ ጦርነት ጊዜ ነበር፤ የሩሲያ ሠራሽ ሚሳኤሎችን ለመቃወም። ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ በ1980ዎቹ መጀመርያ ማለት ነው። ነገር ግን ከዚያ ወዲህ ብዙ ማሻሻያዎች ተደርገውለት አሁን ወደደረሰበት ወደ ላቀ ደረጃ ደርሷል። ብዙ ያደጉ አገሮች አየር ክልላቸውን የሚጠብቁት በዚህ የአየር መቃወሚያ ነው። በቀላሉ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ይቻላል። በአንድ ጊዜ በርካታ የአየር ጥቃቶችን መመከት ይችላል። የኤሌክትሮኒክ የግንኙነት እቀባ (ጃሚንግ) ቢሰነዘርበት ራሱ ይህን መመከት የሚያስችል መሣሪያ ተገጥሞለታል። 24 ሰዓት የራዳር ቅኝት ያደርጋል። ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያዎችን ለመጠቀም የራዳር ጣቢያ፣ የዕዝ ጣቢያና ማስወንጨፊያ ማማ ያስፈልጋሉ። ከ40-160 ኪሎ ሜትር የጠላት ዒላማን ተምዘግዝገው ማደባየት ይችላሉ። በዋናነት አገልግሎታቸው የዋርዲያ ነው። ጥበቃ የማድረግ። ከተማን፣ ወይም አንድ አካባቢን፣ ወይም አንድ ግዙፍ መሠረተ ልማትን ከየትኛውም ዓይነት የአየር ጥቃት መጠበቅ። አሜሪካዊያን ወይም የኔቶ አባል አገራት ዩክሬን ገብተው እነዚህን መሣሪያዎች መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ ዩክሬናዊያን ለዚሁ ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል ሲባል ልዩ ስልጠና መውሰድ ነበረባቸው። አሜሪካ በጀርመን ባላት የጦር ሰፈር ይህንኑ ሥልጠና ለተመረጡ ዩክሬናዊያን ሰጥታቸዋለች ተብሏል። ዛሬ ሐሙስ ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያን ለዩክሬን ማስታጠቅ “የምዕራባዊያን ጠብ አጫሪነት” መቀጠሉን ማሳያ ነው ስትል ድርጊቱን አውግዛለች። ከዛሬ ጀምሮ እነዚህ መሣሪያዎች ዋንኛ ዒላማዋ እንደሚሆኑም ዝታለች። የጦር ባለሙያዎች ይህን ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያ ለዩክሬን ከተሰጡ ስጦታዎች ትልቁ ብለው ያወድሱታል። ምክንያት ሲጠቅሱም በተለይ ኼርሶን ከተማን የዩክሬን ወታደሮች ከሩሲያ ወታደሮች ከነጠቁ በኋላ የዩክሬን ሰማይ ክፍት ሆኖ መቆየቱን ያወሳሉ። በዚህ የተነሳ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ክፉኛ ውድመት ሲደርስባቸው ቆይቷል። የዕለት ተዕለት ኑሮ በዩክሬን ፈተና የሆነውም ለዚሁ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው የሩሲያ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን ማቆም የሚችል ቴክኖሎጂ በመጥፋቱ ነበር። አሁን ፓትሪዮት እንደ ስሙ አርበኝነቱን ያሳይ ይሆናል። | ‘ፓትሪዮት’፡ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጣት ብዙ የተነገረለት አየር መቃወሚያ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ምዕራባዊያንን አጥብቀው ሲጠይቁ የነበረው አንድ ነገር የአየር መቃወሚያ እንዲሰጣቸው ነበር። ምክንያቱም ሩሲያ በአየር ኃይሏ ኪዬቭን ጨምሮ ዋና ዋና ከተሞችን በጨለማ እንዲዋጡ አድርጋለች። በካሚካዚ ድሮንና በተወንጫፊ ሚሳኤሎች ብዙ ጥፋት አድርሳለች። ውሃና መብራት ለሚሊዮኖች ቅንጦት ሆኖ እንዲሰማቸው ሆኗል። ዩክሬናውያን የውርጩን ዘመን ያለማሞቅያ በብርድ እየተንዘፈዘፉ እንዲኖሩ ተደርገዋል። በዩክሬን ብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ ነው የሚከፋፈለው። ከዚህም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በዩክሬን ሰማይ ላይ የሚፈነጩትን ድሮኖችና ሚሳኤሎች ጭጭ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል። አንድ ነገር መደረግ ነበረበት። ዜሌንስኪ ምዕራባዊያን ድረሱልን አሉ። ይነስም ይብዛ ደርሰውላቸዋል። ይሁንና እስከዛሬ የደረሳቸው የአየር መቃወሚያ ዘመናዊ ቢሆንም ከሩሲያ አቅም አንጻር ሲታይ የልብ አያደርስም። ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ወደ አሜሪካ ማማተር ጀመሩ። ጆ ባይደን አላሳፈሯቸውም። ባይደን ለዜሌንስኪ አንድ ያረጋገጡላቸው ነገር ቢኖር ከሰሞኑ እጅግ የላቁ ናቸው የሚባሉትን የአየር መቃወሚያዎች እንደሚልኩላቸው ነው። ፓትሪዮት ይባላል ስማቸው። ይህ እርዳታ አሜሪካ ለዩክሬን 66 ቢሊዮን ዶላር ከለገሰች በኋላ የመጣ ትልቁ ስጦታ ሆኗል። ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያዎች ውድ፣ በጣም ውጤታማ እና የልብ አድርስ ናቸው ይባላል። አንድ ፓትሪዮት ሚሳኤል ዋጋው ይጠራ ከተባለ ዋጋው 3 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል። ይህ ማለት በምሕጻረ ቃል ኤንኤኤምኤስ (NASAMS) የሚባሉትን ዘመናዊ የአየር መቃወሚያዎች በሦስት እጥፍ በዋጋ ይበልጣቸዋል። ፓትሪዮት ሚሳኤሎች የተሠሩት በኢራቅ ጦርነት ጊዜ ነበር፤ የሩሲያ ሠራሽ ሚሳኤሎችን ለመቃወም። ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ በ1980ዎቹ መጀመርያ ማለት ነው። ነገር ግን ከዚያ ወዲህ ብዙ ማሻሻያዎች ተደርገውለት አሁን ወደደረሰበት ወደ ላቀ ደረጃ ደርሷል። ብዙ ያደጉ አገሮች አየር ክልላቸውን የሚጠብቁት በዚህ የአየር መቃወሚያ ነው። በቀላሉ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ይቻላል። በአንድ ጊዜ በርካታ የአየር ጥቃቶችን መመከት ይችላል። የኤሌክትሮኒክ የግንኙነት እቀባ (ጃሚንግ) ቢሰነዘርበት ራሱ ይህን መመከት የሚያስችል መሣሪያ ተገጥሞለታል። 24 ሰዓት የራዳር ቅኝት ያደርጋል። ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያዎችን ለመጠቀም የራዳር ጣቢያ፣ የዕዝ ጣቢያና ማስወንጨፊያ ማማ ያስፈልጋሉ። ከ40-160 ኪሎ ሜትር የጠላት ዒላማን ተምዘግዝገው ማደባየት ይችላሉ። በዋናነት አገልግሎታቸው የዋርዲያ ነው። ጥበቃ የማድረግ። ከተማን፣ ወይም አንድ አካባቢን፣ ወይም አንድ ግዙፍ መሠረተ ልማትን ከየትኛውም ዓይነት የአየር ጥቃት መጠበቅ። አሜሪካዊያን ወይም የኔቶ አባል አገራት ዩክሬን ገብተው እነዚህን መሣሪያዎች መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ ዩክሬናዊያን ለዚሁ ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል ሲባል ልዩ ስልጠና መውሰድ ነበረባቸው። አሜሪካ በጀርመን ባላት የጦር ሰፈር ይህንኑ ሥልጠና ለተመረጡ ዩክሬናዊያን ሰጥታቸዋለች ተብሏል። ዛሬ ሐሙስ ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያን ለዩክሬን ማስታጠቅ “የምዕራባዊያን ጠብ አጫሪነት” መቀጠሉን ማሳያ ነው ስትል ድርጊቱን አውግዛለች። ከዛሬ ጀምሮ እነዚህ መሣሪያዎች ዋንኛ ዒላማዋ እንደሚሆኑም ዝታለች። የጦር ባለሙያዎች ይህን ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያ ለዩክሬን ከተሰጡ ስጦታዎች ትልቁ ብለው ያወድሱታል። ምክንያት ሲጠቅሱም በተለይ ኼርሶን ከተማን የዩክሬን ወታደሮች ከሩሲያ ወታደሮች ከነጠቁ በኋላ የዩክሬን ሰማይ ክፍት ሆኖ መቆየቱን ያወሳሉ። በዚህ የተነሳ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ክፉኛ ውድመት ሲደርስባቸው ቆይቷል። የዕለት ተዕለት ኑሮ በዩክሬን ፈተና የሆነውም ለዚሁ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው የሩሲያ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን ማቆም የሚችል ቴክኖሎጂ በመጥፋቱ ነበር። አሁን ፓትሪዮት እንደ ስሙ አርበኝነቱን ያሳይ ይሆናል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g43d1n4dko |
3politics
| ሩሲያ እና ዩክሬን: ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዴት ፈጠረች? | ሩሲያ በቅርብ አመታት በአፍሪካ ተጽዕኖዋን እያሰፋች ነው። ከዩክሬን ወረራ በኋላ አዳዲሶቹ አጋሮቿ ድጋፍ እንዲሰጧት ወይም እንደተባበሩት መንግሥታት ባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢያንስ ገለልተኛ ሆነው እንዲቆዩ ትጠብቃለች። ከሊቢያ እስከ ማሊ፣ ሱዳን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በሞዛምቢክ እና ሌሎችም ሃገራት ሩሲያ ይበልጥ እየተሳተፈች ነው። አብዛኛው ተሳትፎዋ ደግሞ በወታደራዊ ኃይል ሲሆን አማፂያንን ወይም የጂሃዲስት ታጣቂዎችን መዋጋትን ይጨምራል። ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል ባትሆንም ሩስያ በዩክሬን የወሰደችውን እርምጃ አስመልክቶ ተቃውሞዋን በግልፅ አሳይታለች። ይህን የኬንያን አቋም የሚደግፉ ሌሎች ሃገራት ግን ብዙም አልታዩም። የአፍሪካ ህብረት ግጭቱ "እጅግ እንዳሳሰበው" ቢገልጽም በሩሲያ ላይ የሰነዘረው ትችት የለም። በብሪክስ ቡድን ውስጥ የሩሲያ አጋር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ሃገሪቱ ጦሯን ከዩክሬን እንድታስወጣ ስትጠይቅ በድርድር መፍትሄ እንዳለም ጨምራ ገልጻለች። ሩሲያ የዶኔስክ እና የሉሃንስክ ክልሎችን እንደ ገለልተኛ ሃገር ዕውቅና መስጠቷን እንደሚደግፉ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን-አርቻንግ ቱዋዴራ መናገራቸው ተዘግቧል። ረቡዕ ደግሞ የሱዳኑ ምክትል መሪ መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ የልዑካን ቡድን እየመሩ ወደ ሞስኮ አቅንተዋል። ይህም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ያሳያል። በአፍሪካ ያለው አጋርነት እየተቀየረ ስለመሆኑ ከሚያሳዩት ምሳሌዎች አንዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት ከመሰንዘሯ ከአንድ ሳምንት በፊት ፈረንሳይ በማሊ ጂሃዲስቶችን በመዋጋት ላይ የነበራት ተሳትፎ ማብቃቱ ነው። የማሊው ጠቅላይ ሚኒስትር ቾጌል ማይጋ ከፍራንስ 24 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶች መፈራረሟን አረጋግጠዋል። አወዛጋቢው የሩሲያ የግል ወታደራዊ ኩባንያ ዋግነር ግሩፕ እጁ እንደሌለበትም ገልጸዋል። ይህ ለማሊ የሚደረገው የሩስያ እርዳታ ለቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ከቀረበው ድጋፍ ጋር ተደምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት ሩሲያ ይፋዊ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ በአፍሪካ ላይ ያላትን ተጽዕኖ ለማሳደግ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ያሳያል። የታደሰው የሩስያ-አፍሪካ ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቶ እአአ በ2019 በደቡባዊ ሩሲያ ሶቺ ከተማ የተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከ50 በላይ የሃገራት ልዑካን ሲሳተፉ 43ቱ ርዕሳነ ብሔሮች ናቸው። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለመሪዎቹ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የነፃነት እንቅስቃሴዎችን የመደገፍ ታሪክን ለመጠበቅ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ቃል ገብተዋል። ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ መንግሥታት ግልጽ ያልሆነ የፀጥታ ጥበቃ፣ በስልጠና፣ በስለላ፣ በመሳሪያ እንዲሁም የሩሲያ ቅጥረኞችን በአካባቢው ግጭቶች ውስጥ በማሳተፍም ትታወቃለች። ፑቲን እንዳመለከቱት ታሪካዊ ግንኙነቱ ከሩሲያ በፊት ከነበረችው የሶቪየት ህብረት (ዩኤስኤስአር) ዘመን ድረስ የሚሄድ ሲሆን በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ካሉት በርካታ የውድድር ቦታዎች መካከል አንዷ አፍሪካ ነበረች። እአአ በ 1991 የሶቭየት ህብረት ስትፈራርስ ጀምሮ እስካለፉት ጥቂት ዓመታት ድረስ ሩሲያ የሽግግር ጊዜ ውስጥ እያለፈች የነበረ ሲሆን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነትም ዋነኛ አጀንዳ አልነበረም ። በድጋሚ የልዕለ ኃያልነት ደረጃን እንደገና ማግኘት ለሩሲያ ፕሬዚዳንት የውጭ ፖሊሲ ቅድሚያ የሚሰጡት ሆነ። እአአ በ 2014 ሩሲያ የክሬሚያን ሰርጥ ወደ ግዛቷ መቀላቀሏን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦችን ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላት ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ተበላሽቷል። ከዓለም አቀፍ መገለል ስጋት ጋር በተያያዘ ሞስኮ አዳዲስ አጋሮችን መፈለግ ጀመረች። በሩሲያ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት ኢሪና አብራሞቫ "በእገዳው ምክንያት ሩሲያ ወደ ውጭ ለሚላከው ምርቷ አዲስ ገበያ መፈለግ አለባት" ብለዋል። ሩሲያ የምትፈልገው ገበያ ብቻ አይደለም። እየጨመረ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ትፈልግ ነበር እአአ በ 2014 በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የተሳተፈችው ፕሬዚደንት በሽር አል አሳድን ደግፋ ምዕራባውያን እያደረጉ ያሉትን ትርምስ ለማጉላት እና ሩሲያ እንዴት ማስተካከል እንደምትችል ለማሳየት ነው። ከሶሪያ በኋላ ደግሞ ወደ አፍሪካ አህጉር አቀናች። በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ የክብር ፕሮፌሰር ኢሪና ፊላቶቫ እንደሚሉት ሩሲያ በአፍሪካ ውስጥ የነበራት ቁልፍ ተግባር እንደሶሪያ ሁሉ የምዕራባውያንን ተጽዕኖ ማቃለል ነበር። ለምሳሌ አውሮፓውያን በሳህል ያለውን የጂሃዲስት ስጋት መቆጣጠር እንዳልቻሉ ለማሳየት ፈልጋ ነበር። ይህንንም በአፍሪካ ውስጥ ለማሳካት ሁለት ፖሊሲ ተጠቀመች። የመጀመሪያው በአንዳንድ ሃገራት ይፋዊ ወታደራዊ ስልጠናዎችን መስጠት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መደበኛ ያልሆኑ እንደ ዋግነር ግሩፕ ያሉ ድርጅቶች ደግሞ በመዋጋት ጭምር እየተሳተፉ ነው። በ2017 ከዋግነር ግሩፕ የሩስያ ቅጥረኛ ገዳይ ቡድን የታየባት የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ነበረች። በኋላም እነሱን ተከትሎ ኦፊሴላዊ የሩሲያ ወታደራዊ አማካሪዎች ቡድን ገባ። ዓላማቸው ፕሬዝደንት ቱዋዴራን በስልጣን እንዲቆዩ መርዳት ነበር። በቅጥረኞቹ የሚፈጸሙት የጭካኔ ወንጀሎች እየተለመደ መጣ። ሩሲያ ግን አንድም ዜጋዋ በጦር ወንጀሎች እና በሠላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ውስጥ እንዳልተሳተፉ በተደጋጋሚ ገልጻለች። የሩስያ ቅጥረኞች በሊቢያ፣ ሱዳን፣ ሞዛምቢክ እና ማሊ የተለያዩ በተለያዩ ደረጃዎችን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። ሌላው የአህጉሪቱ ጠቀሜታ እያደገ መሄዱን የሚያመለክተው አፍሪካ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪ ዋና ገበያ መሆኗ ነው። ወደ አፍሪካ ከሚገባው የጦር መሳሪያ ግማሽ ያህሉ ከሩሲያ መሆኑን የሀገሪቱ የመንግስት የጦር መሳሪያ ላኪ ኤጀንሲ አስታውቋል። ዋና መሣሪያ ገዢዎች አልጄሪያ እና ግብፅ ናቸው። ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ እና ካሜሩንም አዲስ ደንበኞች ሆነዋል። በዲፕሎማሲው ግንባርም ለጠበቀው ግንኙነት የቀረበ ሽልማት አለ። አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከሩብ በላይ ድምጽ ያላት ሲሆን በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ድምጽ ልትሆን ትችላለች። በሞስኮ ከፍተኛ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የታተመውና ስለ አፍሪካ እና ሩሲያ ትብብር የሚገልጸው የ 2021 ዘገባ እንደሚያመለክተው ከዚህ ቀደም የሩሲያ ድርጊትን በተመለከተ የአፍሪካ ሀገራት ገለልተኛ የመሆን አዝማሚያ አሳይተዋል። | ሩሲያ እና ዩክሬን: ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዴት ፈጠረች? ሩሲያ በቅርብ አመታት በአፍሪካ ተጽዕኖዋን እያሰፋች ነው። ከዩክሬን ወረራ በኋላ አዳዲሶቹ አጋሮቿ ድጋፍ እንዲሰጧት ወይም እንደተባበሩት መንግሥታት ባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢያንስ ገለልተኛ ሆነው እንዲቆዩ ትጠብቃለች። ከሊቢያ እስከ ማሊ፣ ሱዳን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በሞዛምቢክ እና ሌሎችም ሃገራት ሩሲያ ይበልጥ እየተሳተፈች ነው። አብዛኛው ተሳትፎዋ ደግሞ በወታደራዊ ኃይል ሲሆን አማፂያንን ወይም የጂሃዲስት ታጣቂዎችን መዋጋትን ይጨምራል። ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል ባትሆንም ሩስያ በዩክሬን የወሰደችውን እርምጃ አስመልክቶ ተቃውሞዋን በግልፅ አሳይታለች። ይህን የኬንያን አቋም የሚደግፉ ሌሎች ሃገራት ግን ብዙም አልታዩም። የአፍሪካ ህብረት ግጭቱ "እጅግ እንዳሳሰበው" ቢገልጽም በሩሲያ ላይ የሰነዘረው ትችት የለም። በብሪክስ ቡድን ውስጥ የሩሲያ አጋር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ሃገሪቱ ጦሯን ከዩክሬን እንድታስወጣ ስትጠይቅ በድርድር መፍትሄ እንዳለም ጨምራ ገልጻለች። ሩሲያ የዶኔስክ እና የሉሃንስክ ክልሎችን እንደ ገለልተኛ ሃገር ዕውቅና መስጠቷን እንደሚደግፉ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን-አርቻንግ ቱዋዴራ መናገራቸው ተዘግቧል። ረቡዕ ደግሞ የሱዳኑ ምክትል መሪ መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ የልዑካን ቡድን እየመሩ ወደ ሞስኮ አቅንተዋል። ይህም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ያሳያል። በአፍሪካ ያለው አጋርነት እየተቀየረ ስለመሆኑ ከሚያሳዩት ምሳሌዎች አንዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት ከመሰንዘሯ ከአንድ ሳምንት በፊት ፈረንሳይ በማሊ ጂሃዲስቶችን በመዋጋት ላይ የነበራት ተሳትፎ ማብቃቱ ነው። የማሊው ጠቅላይ ሚኒስትር ቾጌል ማይጋ ከፍራንስ 24 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶች መፈራረሟን አረጋግጠዋል። አወዛጋቢው የሩሲያ የግል ወታደራዊ ኩባንያ ዋግነር ግሩፕ እጁ እንደሌለበትም ገልጸዋል። ይህ ለማሊ የሚደረገው የሩስያ እርዳታ ለቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ከቀረበው ድጋፍ ጋር ተደምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት ሩሲያ ይፋዊ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ በአፍሪካ ላይ ያላትን ተጽዕኖ ለማሳደግ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ያሳያል። የታደሰው የሩስያ-አፍሪካ ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቶ እአአ በ2019 በደቡባዊ ሩሲያ ሶቺ ከተማ የተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከ50 በላይ የሃገራት ልዑካን ሲሳተፉ 43ቱ ርዕሳነ ብሔሮች ናቸው። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለመሪዎቹ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የነፃነት እንቅስቃሴዎችን የመደገፍ ታሪክን ለመጠበቅ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ቃል ገብተዋል። ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ መንግሥታት ግልጽ ያልሆነ የፀጥታ ጥበቃ፣ በስልጠና፣ በስለላ፣ በመሳሪያ እንዲሁም የሩሲያ ቅጥረኞችን በአካባቢው ግጭቶች ውስጥ በማሳተፍም ትታወቃለች። ፑቲን እንዳመለከቱት ታሪካዊ ግንኙነቱ ከሩሲያ በፊት ከነበረችው የሶቪየት ህብረት (ዩኤስኤስአር) ዘመን ድረስ የሚሄድ ሲሆን በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ካሉት በርካታ የውድድር ቦታዎች መካከል አንዷ አፍሪካ ነበረች። እአአ በ 1991 የሶቭየት ህብረት ስትፈራርስ ጀምሮ እስካለፉት ጥቂት ዓመታት ድረስ ሩሲያ የሽግግር ጊዜ ውስጥ እያለፈች የነበረ ሲሆን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነትም ዋነኛ አጀንዳ አልነበረም ። በድጋሚ የልዕለ ኃያልነት ደረጃን እንደገና ማግኘት ለሩሲያ ፕሬዚዳንት የውጭ ፖሊሲ ቅድሚያ የሚሰጡት ሆነ። እአአ በ 2014 ሩሲያ የክሬሚያን ሰርጥ ወደ ግዛቷ መቀላቀሏን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦችን ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላት ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ተበላሽቷል። ከዓለም አቀፍ መገለል ስጋት ጋር በተያያዘ ሞስኮ አዳዲስ አጋሮችን መፈለግ ጀመረች። በሩሲያ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት ኢሪና አብራሞቫ "በእገዳው ምክንያት ሩሲያ ወደ ውጭ ለሚላከው ምርቷ አዲስ ገበያ መፈለግ አለባት" ብለዋል። ሩሲያ የምትፈልገው ገበያ ብቻ አይደለም። እየጨመረ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ትፈልግ ነበር እአአ በ 2014 በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የተሳተፈችው ፕሬዚደንት በሽር አል አሳድን ደግፋ ምዕራባውያን እያደረጉ ያሉትን ትርምስ ለማጉላት እና ሩሲያ እንዴት ማስተካከል እንደምትችል ለማሳየት ነው። ከሶሪያ በኋላ ደግሞ ወደ አፍሪካ አህጉር አቀናች። በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ የክብር ፕሮፌሰር ኢሪና ፊላቶቫ እንደሚሉት ሩሲያ በአፍሪካ ውስጥ የነበራት ቁልፍ ተግባር እንደሶሪያ ሁሉ የምዕራባውያንን ተጽዕኖ ማቃለል ነበር። ለምሳሌ አውሮፓውያን በሳህል ያለውን የጂሃዲስት ስጋት መቆጣጠር እንዳልቻሉ ለማሳየት ፈልጋ ነበር። ይህንንም በአፍሪካ ውስጥ ለማሳካት ሁለት ፖሊሲ ተጠቀመች። የመጀመሪያው በአንዳንድ ሃገራት ይፋዊ ወታደራዊ ስልጠናዎችን መስጠት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መደበኛ ያልሆኑ እንደ ዋግነር ግሩፕ ያሉ ድርጅቶች ደግሞ በመዋጋት ጭምር እየተሳተፉ ነው። በ2017 ከዋግነር ግሩፕ የሩስያ ቅጥረኛ ገዳይ ቡድን የታየባት የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ነበረች። በኋላም እነሱን ተከትሎ ኦፊሴላዊ የሩሲያ ወታደራዊ አማካሪዎች ቡድን ገባ። ዓላማቸው ፕሬዝደንት ቱዋዴራን በስልጣን እንዲቆዩ መርዳት ነበር። በቅጥረኞቹ የሚፈጸሙት የጭካኔ ወንጀሎች እየተለመደ መጣ። ሩሲያ ግን አንድም ዜጋዋ በጦር ወንጀሎች እና በሠላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ውስጥ እንዳልተሳተፉ በተደጋጋሚ ገልጻለች። የሩስያ ቅጥረኞች በሊቢያ፣ ሱዳን፣ ሞዛምቢክ እና ማሊ የተለያዩ በተለያዩ ደረጃዎችን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። ሌላው የአህጉሪቱ ጠቀሜታ እያደገ መሄዱን የሚያመለክተው አፍሪካ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪ ዋና ገበያ መሆኗ ነው። ወደ አፍሪካ ከሚገባው የጦር መሳሪያ ግማሽ ያህሉ ከሩሲያ መሆኑን የሀገሪቱ የመንግስት የጦር መሳሪያ ላኪ ኤጀንሲ አስታውቋል። ዋና መሣሪያ ገዢዎች አልጄሪያ እና ግብፅ ናቸው። ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ እና ካሜሩንም አዲስ ደንበኞች ሆነዋል። በዲፕሎማሲው ግንባርም ለጠበቀው ግንኙነት የቀረበ ሽልማት አለ። አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከሩብ በላይ ድምጽ ያላት ሲሆን በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ድምጽ ልትሆን ትችላለች። በሞስኮ ከፍተኛ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የታተመውና ስለ አፍሪካ እና ሩሲያ ትብብር የሚገልጸው የ 2021 ዘገባ እንደሚያመለክተው ከዚህ ቀደም የሩሲያ ድርጊትን በተመለከተ የአፍሪካ ሀገራት ገለልተኛ የመሆን አዝማሚያ አሳይተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60543495 |
3politics
| የፑቲንን አስተዳደር ሙስና የሚታገሉት የሩስያ ሴቶች | ወንዶች ጎልተው የወጡበትን የሩስያ ፖለቲካ ለመለወጥ ሙስናን የሚቃወሙ ሴቶች ቆርጠው ተነስተዋል። እነዚህ ሴቶች የለውጥ ተምሳሌት ተብለዋል። ከተቃዋሚው አሌክሲ ናቫልኒ ጋር ይሠራሉ። ናቫልኒ የጸረ ሙስና ንቅናቄን ማዕከል ያደረገው ኤፍቢኬ ፓርቲውን ለፓርላማ ምርጫ ሲያዘጋጅ የእነዚህ ሴቶች ሚና ጉልህ ነው። የሩስያ ፓርላማ ለፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታማኝ ነው። አብላጫውን ቁጥር የያዙትም ወንዶች ናቸው። ከታህታይ ምክር ቤቱ የሴቶች ድርሻ 16% ሲሆን ከላዕላይ ምክር ቤቱ ደግሞ 17% መቀመጫ አላቸው። በናቫልኒ ፓርቲ ወንዶችም ሴቶችም ቁልፍ ሚና አላቸው። በንቅናቄው ጎልተው የወጡ ሴቶች እነማን እንደሆኑ እናስተዋውቃችሁ። ዩሊያ ናቫልኒያ እአአ በ2000 ከናቫልኒ ጋር ትዳር የመሠረተችው ዩሊያ ሕይወቷ ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት በመመላለስ የተሞላ ሆኗል። ቤቷም በተደጋጋሚ ተበርብሯል። ቱርክ የተዋወቁት ጥንዶች ሁለቱም 44ኛ ዓመታቸውን ይዘዋል። ዩሊያ ያጠናችው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲሆን፤ ባንክ ውስጥ ሠርታለች። ቤታቸው ሞስኮ ሲሆን፤ ሴት ልጃቸው ዳርያ አሜሪካ እየተማረች ነው። ዩሊያ አሁን ከመገናኛ ብዙኃንና ከመንግሥት ስለላ ሸሽታ ጀርመን ነች። በመላው ሩስያ እሷን የሚደግፉ ሴቶች ቀይ ለብሰው ፎቶ በመነሳት ኢንስታግራም ላይ ለጥፈዋል። ባለቤቷ የሁለት ዓመት ከስምንት ወር እስር ሲፈረድበት ቀይ ለብሳ ነበር ፍርድ ቤት የተገኘችው። የፋሽን ጋዜጠኛዋ ካይታ ፌዶሮቫ ይህንን በማስመልከት ቀይ ከለበሰች ወዲህ ነው ሌሎች ሴቶች ቀይ በማድረግ ድጋፋቸውን ማሳየት የጀመሩት። "አትዘኚ። የከፋ ነገር አይከሰትም" በማለት ነበር ባለቤቷ ናቫልኒ ከመታሰሩ በፊት የተሰናበታት። ወደ ፓለቲካ ተሳትፎ የገባችው ባለፈው ነሐሴ ባለቤቷ ተመርዞ ለሞት በተቃረበበት ወቅት ነበር። ባለቤቷ ከተመረዘ በኋላ ከሰርቢያ ወደ ጀርመን እንዲወሰድ የወሰነችው እሷ ነበረች። ከሰመመን ሲነቃ "ትራሴን ታስተካክልልኝ የነበረችው እሷ እንደነበረች አስታውሳለሁ። እስክትመጣ እጠብቃት ነበር" ብሏል ናቫልኒ። ባለቤቷ አገግሞ ከጀርመን ወደ ሩስያ ሲመለስ ታስሯል። እስሩን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ አንዷ ደግሞ እሷ ነበረች። የባለቤቷን ጸረ ሙስና ተቃውሞ የምትደግፈው ዩሊያ፤ ሰልፍ ከወጣች በኋላ 270 ዶላር ተቀጥታለች። ሊቦቭ ሶቦል የ33 ዓመቷ ጠበቃ በናቫልኒ ቡድን ውስጥ ከሚታወቁ አንዷ ናት። አሁን በቁም እስር ላይ ትገኛለች። እሷና ሌሎችም የናቫልኒ ደጋፊዎች ከተቃውሞ ሰልፉ በኋላ ታስረዋል። ለመታሰራቸው ምክንያት የተባለው የኮቪድ-19 መከላከያ መርህን መጣስ ነው። ናቫልኒ ሙስናን የሚያጋልጥበትን የዩቲዩብ ገጽ ፕሮዲውስ የምታደርገው ሊቦቭ ናት። ገጹ በሚሊዮኖች የሚቆጡ ተከታዮች አሉት። እአአ በ2019 ባለሥልጣኖች ከሞስኮ የምርጫ ኮሚቴ ጎትተው ሲያስወጧት የሚያሳይ ቪድዮ ካሰራጨች ወዲህ ታዋቂነቷ ጨምሯል። ከዚያ በኋላ ለአንድ ወር የረሀብ አድማ አድርጋለች። እሷና ሌሎችም የግል እጩዎች በሞስኮ ከተማ አስተዳደር ምርጫ እንዳይሳተፉ ታግደዋል። መስከረም ላይ ለሩስያ ፓርላማ ምርጫ የመወዳደር እቅድ አላት። ከ2011 ጀምሮ በናቫልኒ የጸረ ሙስና ፕሮጀክት ውስጥ ሠርታለች። 2014 ላይ ሚሮሳለቫ የተባለች ልጅ የወለደች ሲሆን፤ በሥራዋ ምክንያት በ2016 ባለቤቷ ጥቃት እንደደረሰበት ትናገራለች። በጸረ ሙስና ንቅናቄ ምክንያት እሷም ናቫልኒም በተደጋጋሚ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከከሰሷቸው መካከል ዩቭጌኒ ፕሪጎዚን የተባለው ባለሀብት ይጠቀሳል። ለክሬምሊን ቅርብ የሆነው ባለጸጋው "የፑቲን ሼፍ" በሚል ይታወቃል። አንስቲዥያ ቫስሌይቫ ዶክተር ናት። በዚህ ወር ፖሊሶች ቤቷን ሲበረብሩ ችላ ብላቸው የቤትሆቨንን ሙዚቃ ስትጫወት የሚያሳይ ቪድዮ ተለቆ ዝነኛ ሆናለች። የ36 ዓመቷ አንስቴዥያ ለናቫልኒ ቅርብ የሆነ የሀኪሞች ቡድን ትመራለች። 2017 ላይ ናቫልኒ አይኑ ላይ ጉዳት ሲደርስበት እሷ ነበረች ያከመችው። የሁለት ልጆች እናት ስትሆን፤ ናቫልኒን የሚደግፍ ሰልፍ በማካሄዷ የቁም እስር ላይ ትገኛለች። ከዚህ ቀደም ከሞስኮ ታይምስ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ የሩስያ መንግሥት ለኮሮናቫይረስ የሰጠውን ምላሽ ተችታለች። እናቷ ሀኪም እንደነበሩና የፖለቲካ ተሳትፎ ለማዳበር የተነሳሳችውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ትናገራለች። "የአገራችን ጤና ሥርዓት ውስጥ ያለውን እያዩ ፖለቲካ ውስጥ አለመሳተፍ አይቻልም" ትላለች። ኪራ ያርሚሽ ከ2014 ጀምሮ የናቫልኒ ቃል አቀባይ ስትሆን፤ በቁም እስር ላይ ትገኛለች። ወደተለያዩ አገሮች ሲጓዝ አብራው ትሄዳለች። ነሐሴ ላይ አውሮፕላን ውስጥ ሳለ ተመርዞ ራሱን ሲስትም አብረው እየተጓዙ ነበር። የሞስኮ ዓለም አቀፍ ተቋምን የተቀላቀለችው የቴሌቭዥን የተሰጥኦ ውድድር አሸንፋ ሲሆን፤ ያጠናችው ጋዜጠኝነት ነው። በጸረ ሙስና ንቅናቄ ከታሰረች በኋላ በማረሚያ ቤት ስለሚገኙ ሴቶች የሚያትት ረዥም ልቦለድ ጽፋለች። በናቫልኒ የዩቲዩብ ገጽም ብዙ መሰናዶዎች መርታለች። ኦልጋ ሚካሎቫ የናቫልኒ ጠበቃ ናት። በአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ልምድ አላት። 2017 ላይ ሩስያ ናቫልኒን እና ወንድሙን ገንዘብ አጭበርብራችኋላ ብላ ከሳ ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን ክሱን ውድቅ አድርጎ የሩስያ የፍትሕ ሚንስትር በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል። ናቫልኒ ከጀርመን ወደ ሩስያ ሲመለስ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከዚህ ክስ ጋር በተያያዘ ነው። ኢኮ ሞስኪቭ ከተባለ የራድዮ ጣቢያ ጋር ባደረገችው ቆይታ ሕገ አውጪውና ሕግ አስፈጻሚው መካከል ልዩነት የለም ስትል ተችታለች። የአውሮፓ ትልቁ የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት በሆነው ካውንስል ውስጥ ለናቫልኒ ጥብቅና የምትቆመውም ኦልጋ ናት። | የፑቲንን አስተዳደር ሙስና የሚታገሉት የሩስያ ሴቶች ወንዶች ጎልተው የወጡበትን የሩስያ ፖለቲካ ለመለወጥ ሙስናን የሚቃወሙ ሴቶች ቆርጠው ተነስተዋል። እነዚህ ሴቶች የለውጥ ተምሳሌት ተብለዋል። ከተቃዋሚው አሌክሲ ናቫልኒ ጋር ይሠራሉ። ናቫልኒ የጸረ ሙስና ንቅናቄን ማዕከል ያደረገው ኤፍቢኬ ፓርቲውን ለፓርላማ ምርጫ ሲያዘጋጅ የእነዚህ ሴቶች ሚና ጉልህ ነው። የሩስያ ፓርላማ ለፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታማኝ ነው። አብላጫውን ቁጥር የያዙትም ወንዶች ናቸው። ከታህታይ ምክር ቤቱ የሴቶች ድርሻ 16% ሲሆን ከላዕላይ ምክር ቤቱ ደግሞ 17% መቀመጫ አላቸው። በናቫልኒ ፓርቲ ወንዶችም ሴቶችም ቁልፍ ሚና አላቸው። በንቅናቄው ጎልተው የወጡ ሴቶች እነማን እንደሆኑ እናስተዋውቃችሁ። ዩሊያ ናቫልኒያ እአአ በ2000 ከናቫልኒ ጋር ትዳር የመሠረተችው ዩሊያ ሕይወቷ ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት በመመላለስ የተሞላ ሆኗል። ቤቷም በተደጋጋሚ ተበርብሯል። ቱርክ የተዋወቁት ጥንዶች ሁለቱም 44ኛ ዓመታቸውን ይዘዋል። ዩሊያ ያጠናችው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲሆን፤ ባንክ ውስጥ ሠርታለች። ቤታቸው ሞስኮ ሲሆን፤ ሴት ልጃቸው ዳርያ አሜሪካ እየተማረች ነው። ዩሊያ አሁን ከመገናኛ ብዙኃንና ከመንግሥት ስለላ ሸሽታ ጀርመን ነች። በመላው ሩስያ እሷን የሚደግፉ ሴቶች ቀይ ለብሰው ፎቶ በመነሳት ኢንስታግራም ላይ ለጥፈዋል። ባለቤቷ የሁለት ዓመት ከስምንት ወር እስር ሲፈረድበት ቀይ ለብሳ ነበር ፍርድ ቤት የተገኘችው። የፋሽን ጋዜጠኛዋ ካይታ ፌዶሮቫ ይህንን በማስመልከት ቀይ ከለበሰች ወዲህ ነው ሌሎች ሴቶች ቀይ በማድረግ ድጋፋቸውን ማሳየት የጀመሩት። "አትዘኚ። የከፋ ነገር አይከሰትም" በማለት ነበር ባለቤቷ ናቫልኒ ከመታሰሩ በፊት የተሰናበታት። ወደ ፓለቲካ ተሳትፎ የገባችው ባለፈው ነሐሴ ባለቤቷ ተመርዞ ለሞት በተቃረበበት ወቅት ነበር። ባለቤቷ ከተመረዘ በኋላ ከሰርቢያ ወደ ጀርመን እንዲወሰድ የወሰነችው እሷ ነበረች። ከሰመመን ሲነቃ "ትራሴን ታስተካክልልኝ የነበረችው እሷ እንደነበረች አስታውሳለሁ። እስክትመጣ እጠብቃት ነበር" ብሏል ናቫልኒ። ባለቤቷ አገግሞ ከጀርመን ወደ ሩስያ ሲመለስ ታስሯል። እስሩን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ አንዷ ደግሞ እሷ ነበረች። የባለቤቷን ጸረ ሙስና ተቃውሞ የምትደግፈው ዩሊያ፤ ሰልፍ ከወጣች በኋላ 270 ዶላር ተቀጥታለች። ሊቦቭ ሶቦል የ33 ዓመቷ ጠበቃ በናቫልኒ ቡድን ውስጥ ከሚታወቁ አንዷ ናት። አሁን በቁም እስር ላይ ትገኛለች። እሷና ሌሎችም የናቫልኒ ደጋፊዎች ከተቃውሞ ሰልፉ በኋላ ታስረዋል። ለመታሰራቸው ምክንያት የተባለው የኮቪድ-19 መከላከያ መርህን መጣስ ነው። ናቫልኒ ሙስናን የሚያጋልጥበትን የዩቲዩብ ገጽ ፕሮዲውስ የምታደርገው ሊቦቭ ናት። ገጹ በሚሊዮኖች የሚቆጡ ተከታዮች አሉት። እአአ በ2019 ባለሥልጣኖች ከሞስኮ የምርጫ ኮሚቴ ጎትተው ሲያስወጧት የሚያሳይ ቪድዮ ካሰራጨች ወዲህ ታዋቂነቷ ጨምሯል። ከዚያ በኋላ ለአንድ ወር የረሀብ አድማ አድርጋለች። እሷና ሌሎችም የግል እጩዎች በሞስኮ ከተማ አስተዳደር ምርጫ እንዳይሳተፉ ታግደዋል። መስከረም ላይ ለሩስያ ፓርላማ ምርጫ የመወዳደር እቅድ አላት። ከ2011 ጀምሮ በናቫልኒ የጸረ ሙስና ፕሮጀክት ውስጥ ሠርታለች። 2014 ላይ ሚሮሳለቫ የተባለች ልጅ የወለደች ሲሆን፤ በሥራዋ ምክንያት በ2016 ባለቤቷ ጥቃት እንደደረሰበት ትናገራለች። በጸረ ሙስና ንቅናቄ ምክንያት እሷም ናቫልኒም በተደጋጋሚ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከከሰሷቸው መካከል ዩቭጌኒ ፕሪጎዚን የተባለው ባለሀብት ይጠቀሳል። ለክሬምሊን ቅርብ የሆነው ባለጸጋው "የፑቲን ሼፍ" በሚል ይታወቃል። አንስቲዥያ ቫስሌይቫ ዶክተር ናት። በዚህ ወር ፖሊሶች ቤቷን ሲበረብሩ ችላ ብላቸው የቤትሆቨንን ሙዚቃ ስትጫወት የሚያሳይ ቪድዮ ተለቆ ዝነኛ ሆናለች። የ36 ዓመቷ አንስቴዥያ ለናቫልኒ ቅርብ የሆነ የሀኪሞች ቡድን ትመራለች። 2017 ላይ ናቫልኒ አይኑ ላይ ጉዳት ሲደርስበት እሷ ነበረች ያከመችው። የሁለት ልጆች እናት ስትሆን፤ ናቫልኒን የሚደግፍ ሰልፍ በማካሄዷ የቁም እስር ላይ ትገኛለች። ከዚህ ቀደም ከሞስኮ ታይምስ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ የሩስያ መንግሥት ለኮሮናቫይረስ የሰጠውን ምላሽ ተችታለች። እናቷ ሀኪም እንደነበሩና የፖለቲካ ተሳትፎ ለማዳበር የተነሳሳችውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ትናገራለች። "የአገራችን ጤና ሥርዓት ውስጥ ያለውን እያዩ ፖለቲካ ውስጥ አለመሳተፍ አይቻልም" ትላለች። ኪራ ያርሚሽ ከ2014 ጀምሮ የናቫልኒ ቃል አቀባይ ስትሆን፤ በቁም እስር ላይ ትገኛለች። ወደተለያዩ አገሮች ሲጓዝ አብራው ትሄዳለች። ነሐሴ ላይ አውሮፕላን ውስጥ ሳለ ተመርዞ ራሱን ሲስትም አብረው እየተጓዙ ነበር። የሞስኮ ዓለም አቀፍ ተቋምን የተቀላቀለችው የቴሌቭዥን የተሰጥኦ ውድድር አሸንፋ ሲሆን፤ ያጠናችው ጋዜጠኝነት ነው። በጸረ ሙስና ንቅናቄ ከታሰረች በኋላ በማረሚያ ቤት ስለሚገኙ ሴቶች የሚያትት ረዥም ልቦለድ ጽፋለች። በናቫልኒ የዩቲዩብ ገጽም ብዙ መሰናዶዎች መርታለች። ኦልጋ ሚካሎቫ የናቫልኒ ጠበቃ ናት። በአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ልምድ አላት። 2017 ላይ ሩስያ ናቫልኒን እና ወንድሙን ገንዘብ አጭበርብራችኋላ ብላ ከሳ ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን ክሱን ውድቅ አድርጎ የሩስያ የፍትሕ ሚንስትር በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል። ናቫልኒ ከጀርመን ወደ ሩስያ ሲመለስ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከዚህ ክስ ጋር በተያያዘ ነው። ኢኮ ሞስኪቭ ከተባለ የራድዮ ጣቢያ ጋር ባደረገችው ቆይታ ሕገ አውጪውና ሕግ አስፈጻሚው መካከል ልዩነት የለም ስትል ተችታለች። የአውሮፓ ትልቁ የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት በሆነው ካውንስል ውስጥ ለናቫልኒ ጥብቅና የምትቆመውም ኦልጋ ናት። | https://www.bbc.com/amharic/56066793 |
2health
| ለ15 ወራት ደሞዛቸው ያልተከፈላቸው የትግራይ የሕክምና ባለሙያዎች | የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ኃይሎች ወደ ጦርነት ከመግባታቸው በፊት ማጀታቸው የሞላ፣ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት የሚልኩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው የሚተርፉ ነበሩ። በመቀለ የሚገኙ እና ቢቢሲ ያነጋገራቸው መምህራን፣ የሕክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች የመንግሥት ተቀጣሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት የነበራቸው ሕይወት የዛሬውን አይመስልም ነበር። ዛሬ በትግራይ ያለው ጦርነት ተባብሶ፣ በክልሉ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሥራ አቁመው፣ የሰብዓዊ እርዳታ ተመናምኖ ሁሉም የሰው እጅ ጠባቂ እንደሆነ ይናገራሉ። ለሌሎች ይዘረጋ የነበረ እጅ ዛሬ ለምጽዋት ደጅ ይጠናል። ለገባ ለወጣ ይቆረስበት የነበረ መሶብ ጦሙን አድሯል። ዕድለኛ የሆነ 15 ኪሎ ግራም የእርዳታ ስንዴ ዱቄት ተቀብሎ ልጆቹን ያበላል። የተቀረው እና ምንም ማድረግ የማይችለው ደግሞ የተሻለ ቀን እንዲመጣ፣ ጦርነቱ እንዲያበቃና ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ይጸልያል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ እየተባባሰ የመጣው ከባድ ውጊያ ያለውን ሁኔታ አስከፊ ሊያደርገው እንደሚችል በመግለጽ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል። ወደ ትግራይ ክልል ጋዜጠኞች እንዲገቡ ባለመፍቀዱ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ምክንያት፣ የግጭቱ መጠን እና ያስከተለው ሰብአዊ ቀውስ ስፋት በዝርዝር ለመረዳት አስቸጋሪ አድርጎታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ሕይወት እናንተ ቤት ምን ይመስላል ሲል ጠይቋቸዋል። በአይደር ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ባለሞያ የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ ዓምደሥላሴ ለረዥም ወራት ደሞዝ እንዳልተቀበሉ እና ከብዙ ወራት በኋላ “ዕድል ቀንቶ” የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች የሚሰጡትን የእርዳታ ስንዴ መቀበላቸውን ይናገራሉ። “ሕይወት አድን ምግብ ካላገኙ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ህጻናት ጋር ሲነጻጸር ልጆቼ ዕድለኞች ናቸው” በማለት ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር የሰጣቸውን እርዳታ የሚያሳይ ምስልና ጽሑፍ በትዊተር ገጻቸው ላይም አስፍረው ነበር። “እርዳታ ሳገኝ በጣም ተደሰትኩ፤ ከዚህ የባሰ መጥፋት፣ ህመም እና ሞት ነው የሚመጣው። በርካታ መልካም ሕይወት የነበራቸው ሰዎች፣ አስተማሪዎች . . . ወደ ጎዳና ወጥተው እያየናቸው ነው። የጉልበት ሥራ የሚሰሩ፣ መንገድ ላይ ሳሙና የሚሸጡ ብዙ የመንግሥት ሠራተኞች አሉ” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በግንቦት ወር 2013 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ደሞዛቸው እንደተከፈላቸው ገልፀው፣ ነገር ግን በዚያው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የትግራይ ኃይሎች ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ የወር ደሞዛቸው አልተከፈላቸውም። ዶ/ር ፋሲካ፣ አክለውም በባሕር ማዶ ወዳጅ ዘመድ ያላቸው የእነርሱን ድጋፍ እየጠበቁ አንደሚኖሩ አስታውሰው፣ ነገር ግን ሁሉም የሚደግፈው ዘመድ አለው ማለት እንዳልሆነ ያብራራሉ። አክለውም “በሰብአዊ እርዳታ የሚመጣው ስንዴ ተቀብለው ለወፍጮ ቤት የሚሆን ገንዘብ የሚቸገሩ አሉ” ሲሉ የችግሩን ግዝፈት ለማሳየት ይጥራሉ። በአይደር ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ውስጥ የሚሰራ እና ከሰኔ 30 ጀምሮ ወርሃዊ ደሞዙን ያላገኘው ስሜን አትግለፁ ያለን ዶክተር “ባልደረቦቼ በሙሉ ችግር ውስጥ ናቸው” ይላል። ይህ ዶክተር ላለፉት ሦስት ዓመታት በሆስፒታሉ ውስጥ ያገለገለ ሲሆን፣ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነው። “ከዚህ በፊት ሕይወቴን እየመራሁ ወላጆቼን ጭምር እረዳ ነበር። አሁን ግን ለአካለ መጠን እንዳልደረሰ ልጅ ተመልሰው ወላጆቼ እየረዱኝ ነው። እነሱ ገጠር ሆነው የሚያገኟትን እህል እየተካፈልን ነው የምንኖረው።” አብዛኛዎቹ የሆስፒታሉ ሠራተኞች እንደሌላው ማኅበረሰብ እርዳታ ይጠብቃሉ የምትለው ነርስ ፍሬ በበኩሏ፣ “ከገበሬ ዘመዶቼና ወዳጆቼ የሚላክልኝን እየጠበቅኩ ቀን እገፋለሁ” ትላለች። ከጦርነቱ በፊትም ቢሆን በክልሉ ውስጥ በነበሩ ማኅበራዊ ችግሮች እና ዝቅተኛ የሥራ ዕድል ምክንያት በርካታ የቤተሰብ አባላት እርስ በእርስ በመተጋገዝ ላይ ነበር የሚኖሩት። “የቤተሰብና የዘመድ ኃላፊነት የተሸከምን ዜጎች እንደመሆናችን መጠን ያለ ክፍያ ልጆችን ማሳደግ ከባድ ነው። ምግብ ተበልቶ በሕይወት መቆየት ከባድ ሆኖ ሳለ በህክምና ሥነ-ምግባር ስለ ሌሎች ሕይወት መጨነቅ ስላለብን፣ ሥራ መቋረጥ የለበትም በሚል በባዶ ሆዱ ወደ ሥራ ቦታ መጥቶ ነው እየሰራ ያለው” ስትል ነርስ ፍሬ ትገልጻለች። የመቀለ ዩኒቨርስቲ አካል የሆነው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በትምህርት ሚኒስቴር ስር የሚተዳደር ነው። ቢቢሲምለሠራተኞቹ የደመወዝ አልተከፈለንም ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በስልክና በጽሑፍ መልዕክት ብንሞክርም ጥረታችን አልተሳካም። በትግራይ ከአንድ ዓመት በላይ የባንክ እና የትራንስፖርት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን መሠረታዊ ሸቀጦች ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች "በሕገ-ወጥ" መንገድ እንደሚገቡ የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የመሠረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ንረት እና የገንዘብ እጥረት እንዳለ፣ ካለው የነዳጅ እጥረት የተነሳም የትራንስፖርት ዋጋ በመናሩ የዕለት ኑሯቸው መክበዱን ነዋሪዎች ያስረዳሉ። “ለራስና ለልጆች መሆን አለመቻል ሕይወት ዓላማ እንዲያጣ ያደርጋል። በአሁኑ ጊዜ መኮረኒ፣ ሩዝ፣ ዘይት ውድ ናቸው” ሲሉ ሌላ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሕክምና ባለሙያ ተናግረዋል። አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች የሚኖሩት በኪራይ ቤት በመሆኑ፣ ገንዘብ አለማግኘት አከራይና ተከራይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል የሚለው ደግሞ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና የጤና ባለሙያ የሆነው ዶክተር ነው። “አብዛኛው ሠራተኛ አይደለም ለቤት ኪራይ ለታክሲም መክፈል አይችልም። እኔ የሰው ፊት ላለማየት ስል የሞቀ ቤት ባይሆንም 70 ካሬ መንደር በሚገኘው ያላለቀ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው። ኤሌክትሪክ እና ውሃ በጭራሽ አይታሰቡም፤ ከጉድጓድ የሚመጣ ውሃ ነው የምንጠጣው። ውሃ ማከሚያ መድኃኒት እንኳ አናገኝም።” የትግራይ ክልል ከአንድ ዓመት በላይ ከበባ ላይ በመቆየቱ ምክንያት የሕክምና ባለሞያዎች እና ታካሚዎች የሚያደርጉት ግራ ገብቷቸዋል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ “የሰብአዊ እርዳታ እንዲሁም የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ተከትሎ በርካታ ታካሚዎች እጃችን ላይ እየሞቱ ይገኛሉ” ይላሉ። ህጻናት በምግብ እጥረት ዋነኛ ተጠቂዎች መሆናቸውን የገለፁት የሕክምና ባለሙያዎቹ፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በትግራይ 2,500 የሚጠጉ ህጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ይህ አኃዝ ግን መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማያሳይ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ ተቋማት ጦርነቱ አስከፊ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ ማስከተሉና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሎ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች አፈናቅሏል ሲሉ ይገልጻሉ። “ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ ደሞዛችን ሳይከፈለን መስራታችን ብቻ ሳይሆን ችግሩ ታካሚዎች ላይ ጭምር ሲታይ ከባድ ያደርገዋል። ተርበን መጥተንም የተራቡ ሰዎች ማከም፣ እንዲህ አይነት ምግብ ብሉ ማለት ይከብዳል። የምንሰራበት ሆስፒታል ሳይቀር የሚዘጋበት ደረጃ ላይ ደርሷል” ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ዶክተር ተናግሯል። አክሎም “ብዙውን ጊዜ የምናሳልፈው በሥራ ላይ ነው፤ ባለን ጊዜ ደግሞ ዛሬ ወይም ነገ እርዳታ እናገኛለን ብለን ስንጠብቅ እንውላለን። ገጠር የሚኖሩ ወላጆቼ እርሻ ስላላቸው አሁን እየረዱኝ ነው” ብሏል። “በእግዚአብሔር ጸጋ ነው የምኖረው” የምትለው ነርስ ፍሬ፣ ከሰባት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ልጆች እንዳሏትና ልጆቿ የለመዱት ምግብ እንድታቀርብላቸው ሲጠይቋት እንደምትጨነቅ ትናግራለች። “ምግብ ሳይበሉ የሚያድሩበት ጊዜም ስላለ፣ ለጥያቄያቸው መልስ ማጣት የሚፈጥረው ህመም ከባድ ነው። በጭንቀት ራሴን እንዳልጎዳ እፈራለሁ።” በሰኔ ወር መጀመሪያ 2022 የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ገብረሥላሴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ትልቁ ሆስፒታል በመብራት መቆራረጥ እና በመድኃኒት እጦት ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አቁሟል ብለው ነበር። ነገር ግን በጦርነቱ ምክንያት በተፈጠሩ ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት፣ ሆስፒታሉ የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት የሚፈለገው ያህል ባይሆንም ሠራተኞች በግል ችግራቸው ምክንያት ሥራ ለማቆም አስበው አያውቁም ስትል ነርስ ፍሬ ገልጻለች። “መንግሥት ግዴታውን እንዳልተወጣ አውቃለሁ፤ ሆኖም እኔ ወደ ሥራ ገበታ ባለመምጣቴ የሚጠፋ ሕይወት አለ ብዬ ስለማስብ ነው ወደ ሥራ የምመጣው። እኛ አገልግሎት ካቆምን ነገ እዚህ አገር ማን ይኖራል? ብዙ ታማሚዎች በመድኃኒት፣ በምግብ እና በኦክሲጅን እጦት ሞተዋል። ነገር ግን ሊተርፍ የሚችለውን ሰው ማዳን በመቻሌ ውጤታማ ነኝ ብዬ አስባለሁ።” ዶ/ር ፋሲካ ዓምደሥላሴ ሕክምና ባለሙያዎቹ እየሰሩ የሚገኙበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያስረዱ “ቁርስ ሳይበሉ ወደ ሥራ ቦታ መጥተው የወደቁ ነርሶች አሉ፤ በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነን። አንድ ሰው ያመጣው ምግብም ቅመሺ ተብላ ልጆቼን ቁርስ ሳልሰጣቸው ነው የመጣሁት ብላ ያለቀሰች ነርስ አለች። በችግር ምክንያት የሚለምኑና ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ አሉ” ይላሉ። “የምንኖረው ሕይወት፣ ይሆናል ብለን አስበነው የማናውቅ ነው” የሚለው ሌላው በሆስፒታሉ ውስጥ መምህርና የጤና ባለሙያ የሆነው ዶክተር በበኩሉ፣ በትራንስፖርት እና በገንዘብ ችግር ምክንያት ቤተሰቦቹ ያሉበት ሁኔታ እንደማያውቅ ይናገራል። “ሕይወታችን በቃላት ከሚገለጸው በላይ ነው፤ ነገር ግን ሥራ አላቆምንም። ለማንኛውም እኛ የምንሄደው መድኃኒት ቢያጡም ‘አይዟችሁ’ ለማለት ከታካሚዎች መራቅ ስለሌለብን ነው። ሙያችን ገንዘብ አልተከፈለንም በሚል የሚተው አይደለም። እዚህ የታመሙትን ትተን ቤት እንድንቀመጥ ህሊናችን አይፈቅድልንም። የተራቡትን ማብላት ባልችልም የታመሙትን መድኃኒቱን ሰጥቼ በሕይወት ማኖር እችላለሁ።” የሆስፒታሉ ሠራተኞች በፌደራል መንግሥት ተቋም ተቀጥረው የሚሰሩ በመሆናቸው በጦርነቱ ምክንያት “ሆን ተብሎ” የወር ደሞዛችን ተይዟል የሚል ቅሬታ አላቸው። “ብዙ የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች ገንዘብ አምጥተው ለሠራተኞቻቸው ይከፍላሉ፤ የቀጠረን አካል ግን ዝም አለ። ባንክ ዝግ ነው፤ ከዚህ በፊት የቆጠብኩት በችግር ጊዜ እንዳልጠቀምበት ጭምር ነው የተከለከልኩት። ይግባኝ የማይባል ፍርድ” በማለት አንድ ሠራተኛ ቅሬታውን ለቢቢሲ ገልጿል። እስከ አሁን ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች አልተሳኩም። “በጣም የሚያሳስበኝ ነገር ይህ ሁኔታ መቼ እንደሚያበቃ ነው። ልጆቻችን ይዘን እንዳንወጣ የስደት መንገዱ በእግር የሚኬድ ስለሆነ በወታደሮች እንዳንገደል እንፈራለን። ሙሉ ለሙሉ ተከባችሁ በረሃብ ጥፉ የሚያስብል ሁኔታ ነው ያለው” ብሏል ዶክተሩ። | ለ15 ወራት ደሞዛቸው ያልተከፈላቸው የትግራይ የሕክምና ባለሙያዎች የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ኃይሎች ወደ ጦርነት ከመግባታቸው በፊት ማጀታቸው የሞላ፣ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት የሚልኩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው የሚተርፉ ነበሩ። በመቀለ የሚገኙ እና ቢቢሲ ያነጋገራቸው መምህራን፣ የሕክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች የመንግሥት ተቀጣሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት የነበራቸው ሕይወት የዛሬውን አይመስልም ነበር። ዛሬ በትግራይ ያለው ጦርነት ተባብሶ፣ በክልሉ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሥራ አቁመው፣ የሰብዓዊ እርዳታ ተመናምኖ ሁሉም የሰው እጅ ጠባቂ እንደሆነ ይናገራሉ። ለሌሎች ይዘረጋ የነበረ እጅ ዛሬ ለምጽዋት ደጅ ይጠናል። ለገባ ለወጣ ይቆረስበት የነበረ መሶብ ጦሙን አድሯል። ዕድለኛ የሆነ 15 ኪሎ ግራም የእርዳታ ስንዴ ዱቄት ተቀብሎ ልጆቹን ያበላል። የተቀረው እና ምንም ማድረግ የማይችለው ደግሞ የተሻለ ቀን እንዲመጣ፣ ጦርነቱ እንዲያበቃና ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ይጸልያል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ እየተባባሰ የመጣው ከባድ ውጊያ ያለውን ሁኔታ አስከፊ ሊያደርገው እንደሚችል በመግለጽ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል። ወደ ትግራይ ክልል ጋዜጠኞች እንዲገቡ ባለመፍቀዱ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ምክንያት፣ የግጭቱ መጠን እና ያስከተለው ሰብአዊ ቀውስ ስፋት በዝርዝር ለመረዳት አስቸጋሪ አድርጎታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ሕይወት እናንተ ቤት ምን ይመስላል ሲል ጠይቋቸዋል። በአይደር ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ባለሞያ የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ ዓምደሥላሴ ለረዥም ወራት ደሞዝ እንዳልተቀበሉ እና ከብዙ ወራት በኋላ “ዕድል ቀንቶ” የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች የሚሰጡትን የእርዳታ ስንዴ መቀበላቸውን ይናገራሉ። “ሕይወት አድን ምግብ ካላገኙ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ህጻናት ጋር ሲነጻጸር ልጆቼ ዕድለኞች ናቸው” በማለት ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር የሰጣቸውን እርዳታ የሚያሳይ ምስልና ጽሑፍ በትዊተር ገጻቸው ላይም አስፍረው ነበር። “እርዳታ ሳገኝ በጣም ተደሰትኩ፤ ከዚህ የባሰ መጥፋት፣ ህመም እና ሞት ነው የሚመጣው። በርካታ መልካም ሕይወት የነበራቸው ሰዎች፣ አስተማሪዎች . . . ወደ ጎዳና ወጥተው እያየናቸው ነው። የጉልበት ሥራ የሚሰሩ፣ መንገድ ላይ ሳሙና የሚሸጡ ብዙ የመንግሥት ሠራተኞች አሉ” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በግንቦት ወር 2013 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ደሞዛቸው እንደተከፈላቸው ገልፀው፣ ነገር ግን በዚያው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የትግራይ ኃይሎች ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ የወር ደሞዛቸው አልተከፈላቸውም። ዶ/ር ፋሲካ፣ አክለውም በባሕር ማዶ ወዳጅ ዘመድ ያላቸው የእነርሱን ድጋፍ እየጠበቁ አንደሚኖሩ አስታውሰው፣ ነገር ግን ሁሉም የሚደግፈው ዘመድ አለው ማለት እንዳልሆነ ያብራራሉ። አክለውም “በሰብአዊ እርዳታ የሚመጣው ስንዴ ተቀብለው ለወፍጮ ቤት የሚሆን ገንዘብ የሚቸገሩ አሉ” ሲሉ የችግሩን ግዝፈት ለማሳየት ይጥራሉ። በአይደር ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ውስጥ የሚሰራ እና ከሰኔ 30 ጀምሮ ወርሃዊ ደሞዙን ያላገኘው ስሜን አትግለፁ ያለን ዶክተር “ባልደረቦቼ በሙሉ ችግር ውስጥ ናቸው” ይላል። ይህ ዶክተር ላለፉት ሦስት ዓመታት በሆስፒታሉ ውስጥ ያገለገለ ሲሆን፣ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነው። “ከዚህ በፊት ሕይወቴን እየመራሁ ወላጆቼን ጭምር እረዳ ነበር። አሁን ግን ለአካለ መጠን እንዳልደረሰ ልጅ ተመልሰው ወላጆቼ እየረዱኝ ነው። እነሱ ገጠር ሆነው የሚያገኟትን እህል እየተካፈልን ነው የምንኖረው።” አብዛኛዎቹ የሆስፒታሉ ሠራተኞች እንደሌላው ማኅበረሰብ እርዳታ ይጠብቃሉ የምትለው ነርስ ፍሬ በበኩሏ፣ “ከገበሬ ዘመዶቼና ወዳጆቼ የሚላክልኝን እየጠበቅኩ ቀን እገፋለሁ” ትላለች። ከጦርነቱ በፊትም ቢሆን በክልሉ ውስጥ በነበሩ ማኅበራዊ ችግሮች እና ዝቅተኛ የሥራ ዕድል ምክንያት በርካታ የቤተሰብ አባላት እርስ በእርስ በመተጋገዝ ላይ ነበር የሚኖሩት። “የቤተሰብና የዘመድ ኃላፊነት የተሸከምን ዜጎች እንደመሆናችን መጠን ያለ ክፍያ ልጆችን ማሳደግ ከባድ ነው። ምግብ ተበልቶ በሕይወት መቆየት ከባድ ሆኖ ሳለ በህክምና ሥነ-ምግባር ስለ ሌሎች ሕይወት መጨነቅ ስላለብን፣ ሥራ መቋረጥ የለበትም በሚል በባዶ ሆዱ ወደ ሥራ ቦታ መጥቶ ነው እየሰራ ያለው” ስትል ነርስ ፍሬ ትገልጻለች። የመቀለ ዩኒቨርስቲ አካል የሆነው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በትምህርት ሚኒስቴር ስር የሚተዳደር ነው። ቢቢሲምለሠራተኞቹ የደመወዝ አልተከፈለንም ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በስልክና በጽሑፍ መልዕክት ብንሞክርም ጥረታችን አልተሳካም። በትግራይ ከአንድ ዓመት በላይ የባንክ እና የትራንስፖርት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን መሠረታዊ ሸቀጦች ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች "በሕገ-ወጥ" መንገድ እንደሚገቡ የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የመሠረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ንረት እና የገንዘብ እጥረት እንዳለ፣ ካለው የነዳጅ እጥረት የተነሳም የትራንስፖርት ዋጋ በመናሩ የዕለት ኑሯቸው መክበዱን ነዋሪዎች ያስረዳሉ። “ለራስና ለልጆች መሆን አለመቻል ሕይወት ዓላማ እንዲያጣ ያደርጋል። በአሁኑ ጊዜ መኮረኒ፣ ሩዝ፣ ዘይት ውድ ናቸው” ሲሉ ሌላ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሕክምና ባለሙያ ተናግረዋል። አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች የሚኖሩት በኪራይ ቤት በመሆኑ፣ ገንዘብ አለማግኘት አከራይና ተከራይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል የሚለው ደግሞ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና የጤና ባለሙያ የሆነው ዶክተር ነው። “አብዛኛው ሠራተኛ አይደለም ለቤት ኪራይ ለታክሲም መክፈል አይችልም። እኔ የሰው ፊት ላለማየት ስል የሞቀ ቤት ባይሆንም 70 ካሬ መንደር በሚገኘው ያላለቀ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው። ኤሌክትሪክ እና ውሃ በጭራሽ አይታሰቡም፤ ከጉድጓድ የሚመጣ ውሃ ነው የምንጠጣው። ውሃ ማከሚያ መድኃኒት እንኳ አናገኝም።” የትግራይ ክልል ከአንድ ዓመት በላይ ከበባ ላይ በመቆየቱ ምክንያት የሕክምና ባለሞያዎች እና ታካሚዎች የሚያደርጉት ግራ ገብቷቸዋል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ “የሰብአዊ እርዳታ እንዲሁም የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ተከትሎ በርካታ ታካሚዎች እጃችን ላይ እየሞቱ ይገኛሉ” ይላሉ። ህጻናት በምግብ እጥረት ዋነኛ ተጠቂዎች መሆናቸውን የገለፁት የሕክምና ባለሙያዎቹ፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በትግራይ 2,500 የሚጠጉ ህጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ይህ አኃዝ ግን መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማያሳይ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ ተቋማት ጦርነቱ አስከፊ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ ማስከተሉና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሎ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች አፈናቅሏል ሲሉ ይገልጻሉ። “ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ ደሞዛችን ሳይከፈለን መስራታችን ብቻ ሳይሆን ችግሩ ታካሚዎች ላይ ጭምር ሲታይ ከባድ ያደርገዋል። ተርበን መጥተንም የተራቡ ሰዎች ማከም፣ እንዲህ አይነት ምግብ ብሉ ማለት ይከብዳል። የምንሰራበት ሆስፒታል ሳይቀር የሚዘጋበት ደረጃ ላይ ደርሷል” ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ዶክተር ተናግሯል። አክሎም “ብዙውን ጊዜ የምናሳልፈው በሥራ ላይ ነው፤ ባለን ጊዜ ደግሞ ዛሬ ወይም ነገ እርዳታ እናገኛለን ብለን ስንጠብቅ እንውላለን። ገጠር የሚኖሩ ወላጆቼ እርሻ ስላላቸው አሁን እየረዱኝ ነው” ብሏል። “በእግዚአብሔር ጸጋ ነው የምኖረው” የምትለው ነርስ ፍሬ፣ ከሰባት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ልጆች እንዳሏትና ልጆቿ የለመዱት ምግብ እንድታቀርብላቸው ሲጠይቋት እንደምትጨነቅ ትናግራለች። “ምግብ ሳይበሉ የሚያድሩበት ጊዜም ስላለ፣ ለጥያቄያቸው መልስ ማጣት የሚፈጥረው ህመም ከባድ ነው። በጭንቀት ራሴን እንዳልጎዳ እፈራለሁ።” በሰኔ ወር መጀመሪያ 2022 የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ገብረሥላሴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ትልቁ ሆስፒታል በመብራት መቆራረጥ እና በመድኃኒት እጦት ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አቁሟል ብለው ነበር። ነገር ግን በጦርነቱ ምክንያት በተፈጠሩ ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት፣ ሆስፒታሉ የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት የሚፈለገው ያህል ባይሆንም ሠራተኞች በግል ችግራቸው ምክንያት ሥራ ለማቆም አስበው አያውቁም ስትል ነርስ ፍሬ ገልጻለች። “መንግሥት ግዴታውን እንዳልተወጣ አውቃለሁ፤ ሆኖም እኔ ወደ ሥራ ገበታ ባለመምጣቴ የሚጠፋ ሕይወት አለ ብዬ ስለማስብ ነው ወደ ሥራ የምመጣው። እኛ አገልግሎት ካቆምን ነገ እዚህ አገር ማን ይኖራል? ብዙ ታማሚዎች በመድኃኒት፣ በምግብ እና በኦክሲጅን እጦት ሞተዋል። ነገር ግን ሊተርፍ የሚችለውን ሰው ማዳን በመቻሌ ውጤታማ ነኝ ብዬ አስባለሁ።” ዶ/ር ፋሲካ ዓምደሥላሴ ሕክምና ባለሙያዎቹ እየሰሩ የሚገኙበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያስረዱ “ቁርስ ሳይበሉ ወደ ሥራ ቦታ መጥተው የወደቁ ነርሶች አሉ፤ በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነን። አንድ ሰው ያመጣው ምግብም ቅመሺ ተብላ ልጆቼን ቁርስ ሳልሰጣቸው ነው የመጣሁት ብላ ያለቀሰች ነርስ አለች። በችግር ምክንያት የሚለምኑና ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ አሉ” ይላሉ። “የምንኖረው ሕይወት፣ ይሆናል ብለን አስበነው የማናውቅ ነው” የሚለው ሌላው በሆስፒታሉ ውስጥ መምህርና የጤና ባለሙያ የሆነው ዶክተር በበኩሉ፣ በትራንስፖርት እና በገንዘብ ችግር ምክንያት ቤተሰቦቹ ያሉበት ሁኔታ እንደማያውቅ ይናገራል። “ሕይወታችን በቃላት ከሚገለጸው በላይ ነው፤ ነገር ግን ሥራ አላቆምንም። ለማንኛውም እኛ የምንሄደው መድኃኒት ቢያጡም ‘አይዟችሁ’ ለማለት ከታካሚዎች መራቅ ስለሌለብን ነው። ሙያችን ገንዘብ አልተከፈለንም በሚል የሚተው አይደለም። እዚህ የታመሙትን ትተን ቤት እንድንቀመጥ ህሊናችን አይፈቅድልንም። የተራቡትን ማብላት ባልችልም የታመሙትን መድኃኒቱን ሰጥቼ በሕይወት ማኖር እችላለሁ።” የሆስፒታሉ ሠራተኞች በፌደራል መንግሥት ተቋም ተቀጥረው የሚሰሩ በመሆናቸው በጦርነቱ ምክንያት “ሆን ተብሎ” የወር ደሞዛችን ተይዟል የሚል ቅሬታ አላቸው። “ብዙ የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች ገንዘብ አምጥተው ለሠራተኞቻቸው ይከፍላሉ፤ የቀጠረን አካል ግን ዝም አለ። ባንክ ዝግ ነው፤ ከዚህ በፊት የቆጠብኩት በችግር ጊዜ እንዳልጠቀምበት ጭምር ነው የተከለከልኩት። ይግባኝ የማይባል ፍርድ” በማለት አንድ ሠራተኛ ቅሬታውን ለቢቢሲ ገልጿል። እስከ አሁን ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች አልተሳኩም። “በጣም የሚያሳስበኝ ነገር ይህ ሁኔታ መቼ እንደሚያበቃ ነው። ልጆቻችን ይዘን እንዳንወጣ የስደት መንገዱ በእግር የሚኬድ ስለሆነ በወታደሮች እንዳንገደል እንፈራለን። ሙሉ ለሙሉ ተከባችሁ በረሃብ ጥፉ የሚያስብል ሁኔታ ነው ያለው” ብሏል ዶክተሩ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgegl7dd8k7o |
5sports
| እግር ኳስ ፡ የዲያጎ ማራዶና የአስከሬን ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ | ከአንድ ወር በፊት በልብ ችግር ምክንያት ያረፈው የቀድሞው የዓለም የእግር ኳስ ኮከብ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አስከሬን ላይ የተደረገው ምርምራ ይፋ ሆነ። የአርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ የአስከሬን ምርመራ እንዳረጋገጠው ህይወቱ ባለፈበት ጊዜ ምንም አይነት አልኮልም ሆነ ዕጽ መውሰዱን የሚያሳይ ምልክቶች እንዳልተገኙ ተገልጿል። በአውሮፓውያኑ 1986 ላይ በተደረገው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ ኮከብ በመሆን አገሩ አርጀንቲና በአሸናፊነት ዋንጫ እንድትነሳ ያስቻለው ማራዶና በኅዳር ወር ላይ ነበር በድንገት ህይወቱ ያለፈው። ማራዶና በሞተበት ጊዜ ለህይወቱ ማለፍ በርካታ መላምቶች ሲቀርቡ የነበረ ሲሆን፤ በአስከሬኑ ላይ በተደረገው ምርመራ ተገኘው ውጤት ግን ከብዙዎች ግምት የተለየ ሆኗል። ምርመራው እንዳመለከው የ60 ዓመቱ ማራዶና በኩላሊቱ፣ በልቡ ላይና በሳምባው ላይ ችግሮች ነበሩበት ተብሏል። በእግር ኳስ ኮከቡ አስከሬን ላይ ምርመራ እንዲደረግ የታዘዘው በተለይ ማራዶና ህይወቱ ከማለፉ በፊት በተደረገለት የህክምና ድጋፍ ዙሪያ ለሞቱ ምክንያት ሊሆን የሚችል ማንኛውም አይነት ቸልተኝነት ከነበረ ለማጣራት ነበር። የምን ጊዜም የእግር ኳስ ኮከብ ተደርጎ የሚታሰበው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኅዳር ወር መጀመሪያ ላይ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ የቀዶ ህክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን፤ በተጨማሪም ለነበረበት የአልኮል ሱስ ህክምና ለመጀመር እየተዘጋጀ ነበር። ከአገሩ አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ባሻገር ለቦካ ጁኒየርስና ለናፖሊ ክለቦች የተጫወተው ማራዶና ህይወቱ ባለፈበት ዕለት በአስከሬኑ ላይ ምርመራ በተደረገበት ጊዜ በከባድ የልብ ችግር ምክንያት መሞቱን ለመወቅ ተችሎ ነበር። ከማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ በመጨረሻው ሰዓት የህክምና ድጋፍ ያደረገለት ዶክተር ህይወቱን ለማዳን ተገቢውን ድጋፍ አላደረገም በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲወቀስ የቆየ ቢሆንም በመጨረሻ የተገኘው የአስከሬን ምርመራ ውጤት ግን ነጻ ያወጣዋል ተብሏል። ከማራዶና ሞት በኋላ የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀናት በመላዋ አርጀንቲና ታውጆ አስከሬኑ በዋና ከተማዋ ቦነስ አይስ ውስጥ በሚገኘው የፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውስጥ ተቀምጦ፤ አገሬው በከፍተኛ ቁጥር በመገኘት ሐዘኑን በመግለጽ እንደተሰናበተው ይታወሳል። ይሁን እንጂ የማራዶና አስከሬን እስካሁን እንደተቀመጠ ይገኛል ለዚህም ምክንያቱ ከተደረገው ምርመራ ባሻገር ከማራዶና ሞት በኋላ ኮከቡን የእግር ኳስ ተጫዋች አባትነት የሚጠይቅ አቤቱታ ለፍርድ ቤት በመቅረቡ ነው። ለዚህም የአርጀንቲና አንድ ፍርድ ቤት የማራዶና አስከሬን ለዘረ መል (DNA) ምርመራ ስለሚፈለግ "ባለበት ይጠበቅ" የሚል በሰጠው ውሳኔ መሰረት አስከሬኑ ለጊዜው ቦነስ አይረስ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል የአስከሬን ማቆያ ውስጥ እንዲቆይ ተወስኗል። | እግር ኳስ ፡ የዲያጎ ማራዶና የአስከሬን ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ ከአንድ ወር በፊት በልብ ችግር ምክንያት ያረፈው የቀድሞው የዓለም የእግር ኳስ ኮከብ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አስከሬን ላይ የተደረገው ምርምራ ይፋ ሆነ። የአርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ የአስከሬን ምርመራ እንዳረጋገጠው ህይወቱ ባለፈበት ጊዜ ምንም አይነት አልኮልም ሆነ ዕጽ መውሰዱን የሚያሳይ ምልክቶች እንዳልተገኙ ተገልጿል። በአውሮፓውያኑ 1986 ላይ በተደረገው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ ኮከብ በመሆን አገሩ አርጀንቲና በአሸናፊነት ዋንጫ እንድትነሳ ያስቻለው ማራዶና በኅዳር ወር ላይ ነበር በድንገት ህይወቱ ያለፈው። ማራዶና በሞተበት ጊዜ ለህይወቱ ማለፍ በርካታ መላምቶች ሲቀርቡ የነበረ ሲሆን፤ በአስከሬኑ ላይ በተደረገው ምርመራ ተገኘው ውጤት ግን ከብዙዎች ግምት የተለየ ሆኗል። ምርመራው እንዳመለከው የ60 ዓመቱ ማራዶና በኩላሊቱ፣ በልቡ ላይና በሳምባው ላይ ችግሮች ነበሩበት ተብሏል። በእግር ኳስ ኮከቡ አስከሬን ላይ ምርመራ እንዲደረግ የታዘዘው በተለይ ማራዶና ህይወቱ ከማለፉ በፊት በተደረገለት የህክምና ድጋፍ ዙሪያ ለሞቱ ምክንያት ሊሆን የሚችል ማንኛውም አይነት ቸልተኝነት ከነበረ ለማጣራት ነበር። የምን ጊዜም የእግር ኳስ ኮከብ ተደርጎ የሚታሰበው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኅዳር ወር መጀመሪያ ላይ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ የቀዶ ህክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን፤ በተጨማሪም ለነበረበት የአልኮል ሱስ ህክምና ለመጀመር እየተዘጋጀ ነበር። ከአገሩ አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ባሻገር ለቦካ ጁኒየርስና ለናፖሊ ክለቦች የተጫወተው ማራዶና ህይወቱ ባለፈበት ዕለት በአስከሬኑ ላይ ምርመራ በተደረገበት ጊዜ በከባድ የልብ ችግር ምክንያት መሞቱን ለመወቅ ተችሎ ነበር። ከማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ በመጨረሻው ሰዓት የህክምና ድጋፍ ያደረገለት ዶክተር ህይወቱን ለማዳን ተገቢውን ድጋፍ አላደረገም በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲወቀስ የቆየ ቢሆንም በመጨረሻ የተገኘው የአስከሬን ምርመራ ውጤት ግን ነጻ ያወጣዋል ተብሏል። ከማራዶና ሞት በኋላ የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀናት በመላዋ አርጀንቲና ታውጆ አስከሬኑ በዋና ከተማዋ ቦነስ አይስ ውስጥ በሚገኘው የፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውስጥ ተቀምጦ፤ አገሬው በከፍተኛ ቁጥር በመገኘት ሐዘኑን በመግለጽ እንደተሰናበተው ይታወሳል። ይሁን እንጂ የማራዶና አስከሬን እስካሁን እንደተቀመጠ ይገኛል ለዚህም ምክንያቱ ከተደረገው ምርመራ ባሻገር ከማራዶና ሞት በኋላ ኮከቡን የእግር ኳስ ተጫዋች አባትነት የሚጠይቅ አቤቱታ ለፍርድ ቤት በመቅረቡ ነው። ለዚህም የአርጀንቲና አንድ ፍርድ ቤት የማራዶና አስከሬን ለዘረ መል (DNA) ምርመራ ስለሚፈለግ "ባለበት ይጠበቅ" የሚል በሰጠው ውሳኔ መሰረት አስከሬኑ ለጊዜው ቦነስ አይረስ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል የአስከሬን ማቆያ ውስጥ እንዲቆይ ተወስኗል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55458658 |
2health
| በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል? | ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 አማካሪ ቡድን ኃላፊ ሳሊም አብዱል ካሪም እንደሚሉት፤ ሰዎች በብዛት፣ ተጨናንቀው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ቫይረሱ በፍጥነት ይሰራጫል። እውነታው ከዚህ የባለሙያዎች መላ ምት ተቃራኒ ቢሆንስ? የተጨናነቁ መንደሮች እንደተገመተው ለበሽታው መሰራጨት ምክንያት ሳይሆኑ እንዲያውም ቫይረሱ በስፋት እንዳይስፋፋ አድርገው ቢሆንስ? የአህጉሪቱ ድህነት እንደተፈራው ለወረርሽኙ ተጋላጭ ሳያደርጋት ቀርቶ ቢሆንስ? ሚሥጥሩ ምንድን ነው? ኮሮናቫይረስ መሰራጨት ሲጀምር ሁሉም ባለሙያዎች አፍሪካ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ቫይሮሎጂስት ሻቢር ማህዲ “ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምንገባ አስቤ ነበር። አበቃልን ብዬም ነበር” ይላሉ። በጣም ተስፋ ሰጪ ናቸው የተባሉ መላ ምቶች ሳይቀሩ ለህሙማን አልጋ እንደሚጠፋ፣ የጤና ሥርዓቱ እንደሚቃወስ ሲጠቁሙ ነበር። ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደም በሰባት እጥፍ ያንሳል። ደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ሌሎች አገራትም የተፈራው ያህል ቫይረሱ ጉዳት እያደረሰባቸው አይደለም። ሆስፒታሎች እንደተሰጋው አልተጨናነቁም። በተቀረው ዓለም እንደተከሰተው የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ ላይ ደርሶም አልታየም። ፕ/ር ሻቢር፤ “በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት የቫይረሱ ስርጭት ጫፍ አልታየም። ለምን እንደሆነ አልገባኝም። ግልጽ ያልሆነና ለማመን የሚያስቸግር ነው” ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በአስጊ ሁኔታ ያልተሰራጨው አብዛኛው የአህጉሪቱ ነዋሪ ወጣት ስለሆነ ነው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። የአፍሪካውያን አማካይ እድሜ ከአውሮፓውያኑ በግማሽ ያንሳል። የቶኒ ብሌር ተቋም የአፍሪካ ዳይሬክተር ቲም ብሮምፊልድ እንደሚሉት፤ አፍሪካ የወጣቶች አህጉር መሆኗ ከበሽታው ተከላክሏታል። ነገር ግን በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እድሜ ከግምት ያስገቡ የስታትስቲክስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እድሜ ከበሽታው የሚከላከል ብቸኛ ነገር አይደለም። ፕ/ር ሳሊም “ትልቁ ነጥብ እድሜ አይደለም” የሚሉትም ለዚህ ነው። በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎችም አገራት ወረርሽኙ መሰራጨት እንደጀመረ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ሚናው ቀላል አይደለም። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉም ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። በሌላ በኩል የአህጉሪቱ ከፍታ እና ሙቀት የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል የሚለው መላ ምት እንደማይሠራ ተገልጿል። በቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋት ባለመኖሩ ለወደፊት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው አሉ። “አፍሪካ ክፉውን ጊዜ አልፋለች ማለት አልችልም። አንድ ቀን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምር ይሆናል” ሲሉ ፕ/ር ሳሊም ያስረዳሉ። ሌሎቹ ኮሮናቫይረሶች በሶዌቶ የክትባት ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ። በቤተ ሙከራው ለአምስት ዓመታት የቆየ የሰው ደም ናሙና አለ። ይህም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ላይ ምርምር ሲካሄድ የተገኘ ናሙና ነው። ተመራማሪዎቹ፤ ሰዎች በሌሎች አይነት ኮሮናቫይረሶች መያዛቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እየፈለጉ ነው። ይህ ማለት ሰውነት ራሱን ከኮቪድ-19 የሚከላከልበት አቅም አዳብሯል ማለት ነው። “ከዚህ ቀደም በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ተችሎ ሊሆን ይችላል። ቫይረሱ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተስፋፋው ያህል በአፍሪካ ያልተሰራጨውም ለዚህ ይሆናል” ይላሉ ፕ/ር ሻቢር። በተጨናነቀ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ ምናልባትም በጊዜ ሂደት ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል አቅም አዳብረው ሊሆን እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ። “በከፍተኛ ሁኔታ በተጨናነቁ አካባቢዎች በሽታውን የመከላከል አቅም ሊፈጠር ይችላል። ብዙ ሰዎች ምንም የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ወይም መጠነኛ ምልክት የሚያሳዩት ለዚህ ይሆናል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። የአፍሪካ ድህነት የኮሮናቫይረስ ተጋላጭነትን ቀንሶት ሊሆን እንደሚችልም ያምናሉ። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል ባሉ ዜጎች ተጨናንቀው የሚኖሩባቸው አገሮች በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። | በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል? ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 አማካሪ ቡድን ኃላፊ ሳሊም አብዱል ካሪም እንደሚሉት፤ ሰዎች በብዛት፣ ተጨናንቀው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ቫይረሱ በፍጥነት ይሰራጫል። እውነታው ከዚህ የባለሙያዎች መላ ምት ተቃራኒ ቢሆንስ? የተጨናነቁ መንደሮች እንደተገመተው ለበሽታው መሰራጨት ምክንያት ሳይሆኑ እንዲያውም ቫይረሱ በስፋት እንዳይስፋፋ አድርገው ቢሆንስ? የአህጉሪቱ ድህነት እንደተፈራው ለወረርሽኙ ተጋላጭ ሳያደርጋት ቀርቶ ቢሆንስ? ሚሥጥሩ ምንድን ነው? ኮሮናቫይረስ መሰራጨት ሲጀምር ሁሉም ባለሙያዎች አፍሪካ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ቫይሮሎጂስት ሻቢር ማህዲ “ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምንገባ አስቤ ነበር። አበቃልን ብዬም ነበር” ይላሉ። በጣም ተስፋ ሰጪ ናቸው የተባሉ መላ ምቶች ሳይቀሩ ለህሙማን አልጋ እንደሚጠፋ፣ የጤና ሥርዓቱ እንደሚቃወስ ሲጠቁሙ ነበር። ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደም በሰባት እጥፍ ያንሳል። ደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ሌሎች አገራትም የተፈራው ያህል ቫይረሱ ጉዳት እያደረሰባቸው አይደለም። ሆስፒታሎች እንደተሰጋው አልተጨናነቁም። በተቀረው ዓለም እንደተከሰተው የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ ላይ ደርሶም አልታየም። ፕ/ር ሻቢር፤ “በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት የቫይረሱ ስርጭት ጫፍ አልታየም። ለምን እንደሆነ አልገባኝም። ግልጽ ያልሆነና ለማመን የሚያስቸግር ነው” ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በአስጊ ሁኔታ ያልተሰራጨው አብዛኛው የአህጉሪቱ ነዋሪ ወጣት ስለሆነ ነው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። የአፍሪካውያን አማካይ እድሜ ከአውሮፓውያኑ በግማሽ ያንሳል። የቶኒ ብሌር ተቋም የአፍሪካ ዳይሬክተር ቲም ብሮምፊልድ እንደሚሉት፤ አፍሪካ የወጣቶች አህጉር መሆኗ ከበሽታው ተከላክሏታል። ነገር ግን በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እድሜ ከግምት ያስገቡ የስታትስቲክስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እድሜ ከበሽታው የሚከላከል ብቸኛ ነገር አይደለም። ፕ/ር ሳሊም “ትልቁ ነጥብ እድሜ አይደለም” የሚሉትም ለዚህ ነው። በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎችም አገራት ወረርሽኙ መሰራጨት እንደጀመረ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ሚናው ቀላል አይደለም። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉም ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። በሌላ በኩል የአህጉሪቱ ከፍታ እና ሙቀት የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል የሚለው መላ ምት እንደማይሠራ ተገልጿል። በቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋት ባለመኖሩ ለወደፊት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው አሉ። “አፍሪካ ክፉውን ጊዜ አልፋለች ማለት አልችልም። አንድ ቀን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምር ይሆናል” ሲሉ ፕ/ር ሳሊም ያስረዳሉ። ሌሎቹ ኮሮናቫይረሶች በሶዌቶ የክትባት ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ። በቤተ ሙከራው ለአምስት ዓመታት የቆየ የሰው ደም ናሙና አለ። ይህም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ላይ ምርምር ሲካሄድ የተገኘ ናሙና ነው። ተመራማሪዎቹ፤ ሰዎች በሌሎች አይነት ኮሮናቫይረሶች መያዛቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እየፈለጉ ነው። ይህ ማለት ሰውነት ራሱን ከኮቪድ-19 የሚከላከልበት አቅም አዳብሯል ማለት ነው። “ከዚህ ቀደም በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ተችሎ ሊሆን ይችላል። ቫይረሱ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተስፋፋው ያህል በአፍሪካ ያልተሰራጨውም ለዚህ ይሆናል” ይላሉ ፕ/ር ሻቢር። በተጨናነቀ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ ምናልባትም በጊዜ ሂደት ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል አቅም አዳብረው ሊሆን እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ። “በከፍተኛ ሁኔታ በተጨናነቁ አካባቢዎች በሽታውን የመከላከል አቅም ሊፈጠር ይችላል። ብዙ ሰዎች ምንም የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ወይም መጠነኛ ምልክት የሚያሳዩት ለዚህ ይሆናል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። የአፍሪካ ድህነት የኮሮናቫይረስ ተጋላጭነትን ቀንሶት ሊሆን እንደሚችልም ያምናሉ። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል ባሉ ዜጎች ተጨናንቀው የሚኖሩባቸው አገሮች በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-54009884 |
0business
| 'ገበሬው አምርቶ የማይጠቀምባት ኢትዮጵያ' የኑሮ ውድነቱን እንዴት መቀነስ ትችላለች? | በምጣኔ ሃብታዊ ቋንቋ የአቅርቦት ሰንሰለት ይባላል። በእንግሊዝኛው 'ሰፕላይ ቼይን' የሚባለው ማለት ነው። የአቅርቦት ሰንሰለት ሸማቹ ወይም ተገልጋዩ የሚፈልገው ነገር ለገበያ እስኪቀርብ ድረስ ያለው ሂደት ነው። የምጣኔ ሃብት ሰዎች የአቅርቦት ሰንሰለት የአንዲት ሃገር ዕድገት ምሰሶ ወይም ከምሰሶዎች አንዱ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ይላሉ። የአቅርቦት ሰንሰለትን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት ወደ አርባምንጭ እንሂድ። አርባምንጭ የፍራፍሬ ሃገር ናት። በተለይ ደግሞ ሙዝ። አንድ ፍሬ ሙዝ አርባምንጭ ላይ ያለው ዋጋ እና አዲስ አበባ ተመሳሳይ አይደለም። እንዲሆንም ላይጠበቅ ይችላል። ለምሳሌ አንድ ፍሬ አርባምንጭ ከተማ 20 ሳንቲም ተሸጠ እንበል፤ አዲስ አበባ ሲደርስ ደግሞ 1 ብር [ምሳሌ ነው]። ሙዝ አርባምንጭ በቅሎና አድጎ አዲስ አበባ አሊያም ሌሎች ከተሞች የሚደርሰው የአቅርቦት ሰንሰለትን ተሳፍሮ ነው። አምራች አለ። ከአምራች ተቀብሎ የሚያከፋፍል አለ። ከአከፋፋይ ተቀብሎ የሚቸረችር ይኖራል። ከዚያ ገዥ። ስለ አቅርቦት ሰንሰለት ይህን ካልን ከለት'ተዕለት ኑሯችን ጋር ያለውን ቁርኝት እንይ። አንድ የኢትዮጵያ ኑሮ ሁኔታ የሚያሳስባቸው ግለሰብ፣ አማራ ክልል ውስጥ ያለች አንድ ሽንኩርት አምራች ሥፍራ ያለው የሽንኩርት ዋጋና ከተማ ሲደርስ ያለው ዋጋ እጅግ የተለያየ መሆኑ ያሳስባል ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አሥፍረው ነበር። ለመሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለትና የኑሮ ውድነት ግንኙነት አላቸው? የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተቃና ቢሆን ኖሮ ለውጥ ይመጣል? "እርግጥ ነው ግንኙነት አላቸው። ነገር ግን ሌሎች ምክንያቶች የበለጠ ተፅዕኖ አላቸው" ይላሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ። "ያለፈውን አሥር ዓመት ብናይ ኢሕአዴግ በገጠርም በከተማም መንገድ ሠርቷል። ግን ከአሥር ዓመት በፊት ያለውን ንረትና አሁን ያለውን ስታየው የዛሬው በጣም ትልቅ ነው። ስለዚህ ሌሎች ገፊ ምክንያቶች ናቸው ለዋጋ ንረቱ ምክንያት የሆኑት እንጂ ሰንሰለቱ ብቻ አይደለም።" ፕሮፌሰር አለማየሁ እነዚህ 'ገፊ' ያሏቸውን ምክንያቶች ያስረዳሉ። ባደረግኩት ጥናት እነዚህ ምክንያቶች አራት ናቸው ይለሉ። "አንደኛው ምርታማነት ነው። ምርታማነታችን በሄክታር ሲሰላ በጣም የሞተ ነው። ለምሳሌ በአማካይ የእርሻ ምርታማነቱ የሚያድገው በዓመት በ2.5 ነው። ይህ ከሕዝብ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ዝቅ ያለ ነው። በእያንዳንዱ የሰብል ዓይነት ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን በአጠቃላይ በቂ አይደለም። በጥናቴ መሠረት ቁጥር አንድ ምክንያት ይህ ነው። "ቁጥር ሁለት ያገኘሁት ምክንያት ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 12/13 ዓመታት ከተገቢው በላይ ብር ይታተም ነበር። ለምሳሌ 2000 ዓ.ም. ላይ የቁጠባ ሒሳብና የቼክ ሒሳብ ውስጥ ያለን ጨምሮ ጠቅላላ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ብር 67 ቢሊየን ነበር። አሁን 870 ቢሊየን ደርሷል። ይህ ማለት በአማካይ በ30 በመቶ ያድግ ነበር ማለት ነው ላለፉት 13 ዓመታት።" ፕሮፌሰር ዓለማየሁ የብር መጠኑ ከ4 እና 5 በመቶ መብለጥ አልነበረበትም ሲሉ ይሞግታሉ። ሶስተኛው ምክንያትም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ምሁሩ የኢትዮጵያ ብር አቅም ከዓመት ዓመት እየተዳከመ መምጣቱ ሌላኛው ሰበብ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። "በተለይ አዲሱ መንግሥት ከመጣ በኋላ የገንዘባችን አቅም እየወረደ ወይም እየረከሰ መጥቷል። የቀደመው መንግሥት ብዙ ብር ያትም ነበር። አዲሱ መንግሥት ደግሞ ብሩን እያረከሰው ነው። 80 በመቶ የሚሆኑ ከውጭ የምንገዛቸው ነገሮች የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ነዳጅ የመሳሰሉ ናቸው። ስለዚህ ብሩ በረከሰ ቁጥር እነዚህ ዕቃዎች ይወደዳሉ። በ21 ብር የምትገዛው የነበረው አሁን በ40 ብር ነው የምትገዛው ማለት ነው።" ፕሮፌሰር አለማየሁ ወደ አራተኛው ምክንያት ሲመጡ ከላይ ካነሳነው የአቅርቦት ሰንሰለት ጋር የተያያዘ ርዕስ ያነሳሉ። "አራተኛው ምክንያት የነጋዴዎች አለአላግባብ ትርፍ ማጋበስ ነው። ለምሳሌ አንድ ሽንኩርት የሚያመርት ገበሬ የሚያገኘው ገቢና አዲስ አበባ ያንን ሽንኩርት የሚሸጠው ነጋዴ የሚያገኘው ሲነፃፀር ይዘገንናል። ገበሬው ምንም አያገኝም። ባደጉ ሃገራት አንድ ነጋዴ 20 በመቶ ካተረፈ ትልቅ ነገር ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ መቶ ሁለት መቶ 'ፐርሰንት' ነው የምታተርፈው። መፍትሄውስ? ምሁሩ መፍትሄው ችግሮቹን 'መገልበጥ ነው' ይላሉ። እንዴት ማለት? በዝርዝር ያስረዳሉ። "ለምሳሌ የመጀመሪያው መፍትሄ የሚሆነው ምርታማነትን ማሳደግ ነው። ለምሳሌ ስንዴ ኢትዮጵያ ምን ያክል ታመርታለች? በቆሎስ? ደቡብ አፍሪካ በቆሎ የኛን እጥፍ ነው የምታመርተው። ስለዚህ ምርታማነት ላይ መሥራት ነው አንዱ መፍትሄ።" የምጣኔ ሃብት አስተማሪው ምርታማነት ማሳደግ ትልቅ 'ኢንቨስትመንት' ይጠይቃል ይላሉ። ነገር ግን በአጭር ጊዜ መፍትሄ ለማምጣት ሊደረግ የሚችለው በትናንሽ መስኖዎች ምርት ማምረት ነው ይላሉ። "ጠቅላላ ምርታማነት እንኳ ባይጨምር በዓመት ሁለቴ አመርትን ማለት ነው። ለምሳሌ 5 ኩንታል የምታመርት ከሆነ በዓመት፤ በመስኖ ሁለት ጊዜ አመርትክ ማለት 10 ኩንታል ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ሆኖ የሚታየኝ ይሄ ነው።" ፕሮፌሰር አለማየሁ ካለው የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር አንፃር ወጣቶች በዚህ መስክ ላይ እንዲሰማሩ ያሻል ይላሉ። እንደ ምሁሩ ከሆነ ሁለተኛው መፍትሄ ጥብቅ የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ ማውጣት ነው። ካልሆነ ደግሞ የሚወሰደውን ብድር ከላይ ለተጠቀሰው መፍትሄ ማዋል ይገባል ይላሉ። "የሚታተመው ብር ባለፉት ሶስት ዓመታት እየቀነሰ መጥቷል። ይሄ ቆንጆ እርምጃ ነው። ግን ከዚህ በተጓዳኝ የሚታተመው ብር የት ነው የሚገባው የሚለው ነው። የሚታተመው ብር ምርታማነት ላይ ቢጠፋ ችግር አልነበረውም ነበር። የመጀመሪያውን ችግር በፈታ ነበር።" የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ከጠ/ሚ ኃይለማርያም ዘመን ጀምሮ ብር 'ዲቫሉዌት' አልያም አቅሙ መውረድ የለበትም በማለት ሲሞግቱ እንደነበር ይናገራሉ። "ፈረንጆቹ የሚነግሯቸው 'ኤክስፖርት' [የወጪ ንግድ] ይጨምራል፤ 'ኢምፖርትን' [የገቢ ንግድ] ይቀንሳል እያሉ ነው። ባለፉት ሶስት ዓመታት እኛ ማየት አንደቻልነው ኤክስፖርት አልጨመረም፤ ያው ባለፉት አስር ዓመታት በነበረበት [3 ቢሊዮን ዶላር] እንዳለ ነው። ኢምፖርቱ አይቀንስም [ወደ 17 ቢሊዮን ዶላር ነው]። ብርን የማርከስ ጎንዮሽ ጉዳት ከውጭ የሚመጣ ነገር በሙሉ ድሮ በ20 ብር የነበረው አሁን ወደ 40 ከፍ ማለቱ ነው። ይህ ለዋጋ ንረቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።" ፕሮፌሰሩ ወደ አራተኛው መፍትሄ ሲመጡ የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተስተካከለ ቢሆን ኖሮ የምርት ዋጋ እጅጉን ይቀንስ ነበር ይላሉ። "ያለው አማራጭ መቆጣጠር ነው። ነገር ግን ነጋዴን ተቆጣጥረህ አትዘልቀውም። አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከ200 ሺህ በላይ ነጋዴዎች አሉ። ይሁንና ልቆጣጠር ብትል ችግር ሊፈጠር ይችላል። "ስለዚህ እኔ የሚታየኝ መፍትሄ ምንድነው፤ በግልና በመንግሥት ትብብር በየቀበሌው ገበያዎችን መመሥረት ነው። በተለይ መሠረታዊ ዕቃዎችን ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ። የአምራቾችና የሸማቾች ማሕበር የሚባሉ አሉ። ነገር ግን በሌብነትና በሙስና የተዘፈቁ ናቸው። ስለዚህ የትርፍ ህዳጉን ወስነህ 'ፕሮፌሽናል' የሆነ በግልና በመንግሥት የሚተዳደር [ፐብሊክ ኤንድ ፕራይቬት ፓርትነርሺፕ] ብትመሠርት አንድ መፍትሄ የሚሆን ይመስለኛል።" ምሁሩ እነዚህ ገበያዎች መሠረታዊ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ነው መሆን ያለባቸው ይላሉ። "ለዚህ ቆንጆ ምሳሌ 40ና 50 ዓመታት ያገለገሉ ልብ የማንላቸው ተቋማት አሉ። ኢትፍሩትና ከነማ ፋርማሲ የሚባሉ። የእነዚህን ተቋማት 'ስትራክቸር' ማጥናትና በዚያ መሠረት ማቋቋም ይቻላል።" የአቅርቦት ሰንሰለት በኢትዮጵያና በጎረቤት ሃገራት ጎረቤት ሃገር ኬንያ ሁለተኛ ሃገሬ ናት የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ የኬንያ መንግሥት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በገበሬውና በሸማቹ መካከል ያለውን የዋጋ ክፍተት በማጥበብ ትርፉን መልሶ ለገበሬ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት እየዘረጋ እንደሆነ ይናገራሉ። "ዓላማው ትርፉን ወስዶ ለገበሬው ጥቅም ማዋል ነው። ለምሳሌ የጤና ተቋማትን መገንባት፤ ትምህርት ቤት ማሠራት የመሳሰሉትን ለማቋቋም ነው የሚተልመው ይህ ሥርዓት።" ይህን እየቀረፁ ያሉት ኬንያዊ ባለሙያ ልክ እንደ ራይድ ወይም ኡበር ያለን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ እንዳሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። "ይህ 'ሲስተም' በኤሌክትሮኒክ አማካይነት ምርቶችንና ሸማቹን ማገናኘት ነው ዓላማው።" ኬንያ ከኛ የሚለያት ቁጥሩ አነስተኛ የሆነና የተደራጀ ነጋዴ መኖሩ ነው ይላሉ ምሁሩ። ስለዚህ ይህ ለቁጥጥር ይመቻል ሲሉ ልዩነቱን ያስረዳሉ። "እኛ አንድ 15-20 ዓመት አይቀረንም ብለህ ነው ኬንያ አሁን ያለችበት ለመድረስ?" የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ ኢትዮጵያ መወዳደር ያለባት ከነ ሩዋንዳና ማላዊ ጋር ነው ይላሉ። ምሁሩ ሐሳባቸውን ሲያጠቃልሉ 'ኋላ ቀር መሆናችን ገብቶን ወደ መፍትሄው በፍጥነት ማምራት አለብን' ይላሉ። | 'ገበሬው አምርቶ የማይጠቀምባት ኢትዮጵያ' የኑሮ ውድነቱን እንዴት መቀነስ ትችላለች? በምጣኔ ሃብታዊ ቋንቋ የአቅርቦት ሰንሰለት ይባላል። በእንግሊዝኛው 'ሰፕላይ ቼይን' የሚባለው ማለት ነው። የአቅርቦት ሰንሰለት ሸማቹ ወይም ተገልጋዩ የሚፈልገው ነገር ለገበያ እስኪቀርብ ድረስ ያለው ሂደት ነው። የምጣኔ ሃብት ሰዎች የአቅርቦት ሰንሰለት የአንዲት ሃገር ዕድገት ምሰሶ ወይም ከምሰሶዎች አንዱ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ይላሉ። የአቅርቦት ሰንሰለትን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት ወደ አርባምንጭ እንሂድ። አርባምንጭ የፍራፍሬ ሃገር ናት። በተለይ ደግሞ ሙዝ። አንድ ፍሬ ሙዝ አርባምንጭ ላይ ያለው ዋጋ እና አዲስ አበባ ተመሳሳይ አይደለም። እንዲሆንም ላይጠበቅ ይችላል። ለምሳሌ አንድ ፍሬ አርባምንጭ ከተማ 20 ሳንቲም ተሸጠ እንበል፤ አዲስ አበባ ሲደርስ ደግሞ 1 ብር [ምሳሌ ነው]። ሙዝ አርባምንጭ በቅሎና አድጎ አዲስ አበባ አሊያም ሌሎች ከተሞች የሚደርሰው የአቅርቦት ሰንሰለትን ተሳፍሮ ነው። አምራች አለ። ከአምራች ተቀብሎ የሚያከፋፍል አለ። ከአከፋፋይ ተቀብሎ የሚቸረችር ይኖራል። ከዚያ ገዥ። ስለ አቅርቦት ሰንሰለት ይህን ካልን ከለት'ተዕለት ኑሯችን ጋር ያለውን ቁርኝት እንይ። አንድ የኢትዮጵያ ኑሮ ሁኔታ የሚያሳስባቸው ግለሰብ፣ አማራ ክልል ውስጥ ያለች አንድ ሽንኩርት አምራች ሥፍራ ያለው የሽንኩርት ዋጋና ከተማ ሲደርስ ያለው ዋጋ እጅግ የተለያየ መሆኑ ያሳስባል ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አሥፍረው ነበር። ለመሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለትና የኑሮ ውድነት ግንኙነት አላቸው? የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተቃና ቢሆን ኖሮ ለውጥ ይመጣል? "እርግጥ ነው ግንኙነት አላቸው። ነገር ግን ሌሎች ምክንያቶች የበለጠ ተፅዕኖ አላቸው" ይላሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ። "ያለፈውን አሥር ዓመት ብናይ ኢሕአዴግ በገጠርም በከተማም መንገድ ሠርቷል። ግን ከአሥር ዓመት በፊት ያለውን ንረትና አሁን ያለውን ስታየው የዛሬው በጣም ትልቅ ነው። ስለዚህ ሌሎች ገፊ ምክንያቶች ናቸው ለዋጋ ንረቱ ምክንያት የሆኑት እንጂ ሰንሰለቱ ብቻ አይደለም።" ፕሮፌሰር አለማየሁ እነዚህ 'ገፊ' ያሏቸውን ምክንያቶች ያስረዳሉ። ባደረግኩት ጥናት እነዚህ ምክንያቶች አራት ናቸው ይለሉ። "አንደኛው ምርታማነት ነው። ምርታማነታችን በሄክታር ሲሰላ በጣም የሞተ ነው። ለምሳሌ በአማካይ የእርሻ ምርታማነቱ የሚያድገው በዓመት በ2.5 ነው። ይህ ከሕዝብ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ዝቅ ያለ ነው። በእያንዳንዱ የሰብል ዓይነት ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን በአጠቃላይ በቂ አይደለም። በጥናቴ መሠረት ቁጥር አንድ ምክንያት ይህ ነው። "ቁጥር ሁለት ያገኘሁት ምክንያት ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 12/13 ዓመታት ከተገቢው በላይ ብር ይታተም ነበር። ለምሳሌ 2000 ዓ.ም. ላይ የቁጠባ ሒሳብና የቼክ ሒሳብ ውስጥ ያለን ጨምሮ ጠቅላላ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ብር 67 ቢሊየን ነበር። አሁን 870 ቢሊየን ደርሷል። ይህ ማለት በአማካይ በ30 በመቶ ያድግ ነበር ማለት ነው ላለፉት 13 ዓመታት።" ፕሮፌሰር ዓለማየሁ የብር መጠኑ ከ4 እና 5 በመቶ መብለጥ አልነበረበትም ሲሉ ይሞግታሉ። ሶስተኛው ምክንያትም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ምሁሩ የኢትዮጵያ ብር አቅም ከዓመት ዓመት እየተዳከመ መምጣቱ ሌላኛው ሰበብ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። "በተለይ አዲሱ መንግሥት ከመጣ በኋላ የገንዘባችን አቅም እየወረደ ወይም እየረከሰ መጥቷል። የቀደመው መንግሥት ብዙ ብር ያትም ነበር። አዲሱ መንግሥት ደግሞ ብሩን እያረከሰው ነው። 80 በመቶ የሚሆኑ ከውጭ የምንገዛቸው ነገሮች የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ነዳጅ የመሳሰሉ ናቸው። ስለዚህ ብሩ በረከሰ ቁጥር እነዚህ ዕቃዎች ይወደዳሉ። በ21 ብር የምትገዛው የነበረው አሁን በ40 ብር ነው የምትገዛው ማለት ነው።" ፕሮፌሰር አለማየሁ ወደ አራተኛው ምክንያት ሲመጡ ከላይ ካነሳነው የአቅርቦት ሰንሰለት ጋር የተያያዘ ርዕስ ያነሳሉ። "አራተኛው ምክንያት የነጋዴዎች አለአላግባብ ትርፍ ማጋበስ ነው። ለምሳሌ አንድ ሽንኩርት የሚያመርት ገበሬ የሚያገኘው ገቢና አዲስ አበባ ያንን ሽንኩርት የሚሸጠው ነጋዴ የሚያገኘው ሲነፃፀር ይዘገንናል። ገበሬው ምንም አያገኝም። ባደጉ ሃገራት አንድ ነጋዴ 20 በመቶ ካተረፈ ትልቅ ነገር ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ መቶ ሁለት መቶ 'ፐርሰንት' ነው የምታተርፈው። መፍትሄውስ? ምሁሩ መፍትሄው ችግሮቹን 'መገልበጥ ነው' ይላሉ። እንዴት ማለት? በዝርዝር ያስረዳሉ። "ለምሳሌ የመጀመሪያው መፍትሄ የሚሆነው ምርታማነትን ማሳደግ ነው። ለምሳሌ ስንዴ ኢትዮጵያ ምን ያክል ታመርታለች? በቆሎስ? ደቡብ አፍሪካ በቆሎ የኛን እጥፍ ነው የምታመርተው። ስለዚህ ምርታማነት ላይ መሥራት ነው አንዱ መፍትሄ።" የምጣኔ ሃብት አስተማሪው ምርታማነት ማሳደግ ትልቅ 'ኢንቨስትመንት' ይጠይቃል ይላሉ። ነገር ግን በአጭር ጊዜ መፍትሄ ለማምጣት ሊደረግ የሚችለው በትናንሽ መስኖዎች ምርት ማምረት ነው ይላሉ። "ጠቅላላ ምርታማነት እንኳ ባይጨምር በዓመት ሁለቴ አመርትን ማለት ነው። ለምሳሌ 5 ኩንታል የምታመርት ከሆነ በዓመት፤ በመስኖ ሁለት ጊዜ አመርትክ ማለት 10 ኩንታል ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ሆኖ የሚታየኝ ይሄ ነው።" ፕሮፌሰር አለማየሁ ካለው የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር አንፃር ወጣቶች በዚህ መስክ ላይ እንዲሰማሩ ያሻል ይላሉ። እንደ ምሁሩ ከሆነ ሁለተኛው መፍትሄ ጥብቅ የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ ማውጣት ነው። ካልሆነ ደግሞ የሚወሰደውን ብድር ከላይ ለተጠቀሰው መፍትሄ ማዋል ይገባል ይላሉ። "የሚታተመው ብር ባለፉት ሶስት ዓመታት እየቀነሰ መጥቷል። ይሄ ቆንጆ እርምጃ ነው። ግን ከዚህ በተጓዳኝ የሚታተመው ብር የት ነው የሚገባው የሚለው ነው። የሚታተመው ብር ምርታማነት ላይ ቢጠፋ ችግር አልነበረውም ነበር። የመጀመሪያውን ችግር በፈታ ነበር።" የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ከጠ/ሚ ኃይለማርያም ዘመን ጀምሮ ብር 'ዲቫሉዌት' አልያም አቅሙ መውረድ የለበትም በማለት ሲሞግቱ እንደነበር ይናገራሉ። "ፈረንጆቹ የሚነግሯቸው 'ኤክስፖርት' [የወጪ ንግድ] ይጨምራል፤ 'ኢምፖርትን' [የገቢ ንግድ] ይቀንሳል እያሉ ነው። ባለፉት ሶስት ዓመታት እኛ ማየት አንደቻልነው ኤክስፖርት አልጨመረም፤ ያው ባለፉት አስር ዓመታት በነበረበት [3 ቢሊዮን ዶላር] እንዳለ ነው። ኢምፖርቱ አይቀንስም [ወደ 17 ቢሊዮን ዶላር ነው]። ብርን የማርከስ ጎንዮሽ ጉዳት ከውጭ የሚመጣ ነገር በሙሉ ድሮ በ20 ብር የነበረው አሁን ወደ 40 ከፍ ማለቱ ነው። ይህ ለዋጋ ንረቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።" ፕሮፌሰሩ ወደ አራተኛው መፍትሄ ሲመጡ የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተስተካከለ ቢሆን ኖሮ የምርት ዋጋ እጅጉን ይቀንስ ነበር ይላሉ። "ያለው አማራጭ መቆጣጠር ነው። ነገር ግን ነጋዴን ተቆጣጥረህ አትዘልቀውም። አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከ200 ሺህ በላይ ነጋዴዎች አሉ። ይሁንና ልቆጣጠር ብትል ችግር ሊፈጠር ይችላል። "ስለዚህ እኔ የሚታየኝ መፍትሄ ምንድነው፤ በግልና በመንግሥት ትብብር በየቀበሌው ገበያዎችን መመሥረት ነው። በተለይ መሠረታዊ ዕቃዎችን ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ። የአምራቾችና የሸማቾች ማሕበር የሚባሉ አሉ። ነገር ግን በሌብነትና በሙስና የተዘፈቁ ናቸው። ስለዚህ የትርፍ ህዳጉን ወስነህ 'ፕሮፌሽናል' የሆነ በግልና በመንግሥት የሚተዳደር [ፐብሊክ ኤንድ ፕራይቬት ፓርትነርሺፕ] ብትመሠርት አንድ መፍትሄ የሚሆን ይመስለኛል።" ምሁሩ እነዚህ ገበያዎች መሠረታዊ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ነው መሆን ያለባቸው ይላሉ። "ለዚህ ቆንጆ ምሳሌ 40ና 50 ዓመታት ያገለገሉ ልብ የማንላቸው ተቋማት አሉ። ኢትፍሩትና ከነማ ፋርማሲ የሚባሉ። የእነዚህን ተቋማት 'ስትራክቸር' ማጥናትና በዚያ መሠረት ማቋቋም ይቻላል።" የአቅርቦት ሰንሰለት በኢትዮጵያና በጎረቤት ሃገራት ጎረቤት ሃገር ኬንያ ሁለተኛ ሃገሬ ናት የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ የኬንያ መንግሥት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በገበሬውና በሸማቹ መካከል ያለውን የዋጋ ክፍተት በማጥበብ ትርፉን መልሶ ለገበሬ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት እየዘረጋ እንደሆነ ይናገራሉ። "ዓላማው ትርፉን ወስዶ ለገበሬው ጥቅም ማዋል ነው። ለምሳሌ የጤና ተቋማትን መገንባት፤ ትምህርት ቤት ማሠራት የመሳሰሉትን ለማቋቋም ነው የሚተልመው ይህ ሥርዓት።" ይህን እየቀረፁ ያሉት ኬንያዊ ባለሙያ ልክ እንደ ራይድ ወይም ኡበር ያለን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ እንዳሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። "ይህ 'ሲስተም' በኤሌክትሮኒክ አማካይነት ምርቶችንና ሸማቹን ማገናኘት ነው ዓላማው።" ኬንያ ከኛ የሚለያት ቁጥሩ አነስተኛ የሆነና የተደራጀ ነጋዴ መኖሩ ነው ይላሉ ምሁሩ። ስለዚህ ይህ ለቁጥጥር ይመቻል ሲሉ ልዩነቱን ያስረዳሉ። "እኛ አንድ 15-20 ዓመት አይቀረንም ብለህ ነው ኬንያ አሁን ያለችበት ለመድረስ?" የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ ኢትዮጵያ መወዳደር ያለባት ከነ ሩዋንዳና ማላዊ ጋር ነው ይላሉ። ምሁሩ ሐሳባቸውን ሲያጠቃልሉ 'ኋላ ቀር መሆናችን ገብቶን ወደ መፍትሄው በፍጥነት ማምራት አለብን' ይላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-56920410 |
3politics
| የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በኢትዮጵያ የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ ዘጋቢ የሆነውን ቶም ጋርድነር ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ። ዘጋቢው "የሙያ ስነ ምግባርና የሃገሪቱን ህግና መመሪያ መጣሱንም" በመግለፅ ባለስልጣኑ ለፈቃዱ መሰረዝ ምክንያት እንደሆነ በዛሬው ዕለት ግንቦት 5፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። ባለስልጣኑ ጥሰቶች ብሎ ያሰፈራቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አልገለጸም። ባለስልጣኑ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት ከዚህ ቀደም ከዘጋቢው ቶም ጋርድነር ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች አድርገናል ብሏል። ባለስልጣኑ ከሳምንታት በፊት ለዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጥቷል። ጋዜጠኛው በግል የማህበራዊ ሚዲያው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የህወሃት መሪ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ጋር በስልክ ተወያይተዋል የሚል መልዕክት ማስፈሩን ተከትሎ ባለስልጣኑ በሪፖርቱ ላይ በተለይም በብሔራዊ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስጠንቅቋል። ቶም ጋርድነርም ሆነ ዘ ኢኮኖሚስት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። ነገር ግን ይህ እርምጃ በባለስልጣናቱ የሚዲያ ሽፋንን ለመቆጣጠር የተደረገ ሙከራ ነው በሚል ትችት ቀርቦበታል። በባለፈው አመት ጥቅምት ወር መጨረሻ በትግራይ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ለጋዜጠኞች እና ለተቃዋሚዎች አስቸጋሪ ሁኔታን በመፍጠር ይወቀሳል። ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች፣ ጅምላ ግድያዎች፣ ደፈራዎች፣ እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ መጠነ ሰፊ ጥሰቶች ተፈፅመውባቸዋል በሚባሉ የጦርነቱ ስፍራዎች ደርሰን መዘገብ ተከልክለናል በሚልም ጋዜጠኞች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ይሰማል። የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪው ድርጅት (ሲፒጄ) የጸጥታ ኃይሎች በጦርነት ጊዜ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ለማሰር ተጠቅመዋል ሲል ከቅርብ ወራት በፊት መተቸቱ ይታወሳል። በወቅቱ በእስር ላይ የዋሉ በርካታ ጋዜጠኞች ከእስር ቢለቀቁም ከአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁለት ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው። ሲፒጄ በተጨማሪም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ሁለተኛ ናት በሚል ሪፖርት አውጥቷል። በቅርቡም ድርጅቱ በእስር ላይ ያሉት ደሱ ዱላ እና ቢቂላ አመኑ የተሰኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱና ክሳቸው እንዲቋረጥ ጠይቋል። የማኅበራዊ ሚዲያ የሆነው የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ ጋዜጠኞቹ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ቢሆንም የታሰሩት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም ደሱ እና ቢቂላ በእስር ቤት እንዳሉና ህገ መንግሥቱን በመፃረር በቀረበባቸው እስከ ሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ገልጿል። ከ12 ወራት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢን 'ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ አቅርቧል' በሚል የፕሬስ ፈቃዱን የነጠቀች ሲሆን ይህንን እርምጃም ጋዜጣው 'አምባገነናዊ አካሄድ' እና 'እጅጉን ተስፋ አስቆራጭ' ብሎታል። | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በኢትዮጵያ የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ ዘጋቢ የሆነውን ቶም ጋርድነር ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ። ዘጋቢው "የሙያ ስነ ምግባርና የሃገሪቱን ህግና መመሪያ መጣሱንም" በመግለፅ ባለስልጣኑ ለፈቃዱ መሰረዝ ምክንያት እንደሆነ በዛሬው ዕለት ግንቦት 5፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። ባለስልጣኑ ጥሰቶች ብሎ ያሰፈራቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አልገለጸም። ባለስልጣኑ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት ከዚህ ቀደም ከዘጋቢው ቶም ጋርድነር ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች አድርገናል ብሏል። ባለስልጣኑ ከሳምንታት በፊት ለዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጥቷል። ጋዜጠኛው በግል የማህበራዊ ሚዲያው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የህወሃት መሪ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ጋር በስልክ ተወያይተዋል የሚል መልዕክት ማስፈሩን ተከትሎ ባለስልጣኑ በሪፖርቱ ላይ በተለይም በብሔራዊ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስጠንቅቋል። ቶም ጋርድነርም ሆነ ዘ ኢኮኖሚስት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። ነገር ግን ይህ እርምጃ በባለስልጣናቱ የሚዲያ ሽፋንን ለመቆጣጠር የተደረገ ሙከራ ነው በሚል ትችት ቀርቦበታል። በባለፈው አመት ጥቅምት ወር መጨረሻ በትግራይ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ለጋዜጠኞች እና ለተቃዋሚዎች አስቸጋሪ ሁኔታን በመፍጠር ይወቀሳል። ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች፣ ጅምላ ግድያዎች፣ ደፈራዎች፣ እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ መጠነ ሰፊ ጥሰቶች ተፈፅመውባቸዋል በሚባሉ የጦርነቱ ስፍራዎች ደርሰን መዘገብ ተከልክለናል በሚልም ጋዜጠኞች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ይሰማል። የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪው ድርጅት (ሲፒጄ) የጸጥታ ኃይሎች በጦርነት ጊዜ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ለማሰር ተጠቅመዋል ሲል ከቅርብ ወራት በፊት መተቸቱ ይታወሳል። በወቅቱ በእስር ላይ የዋሉ በርካታ ጋዜጠኞች ከእስር ቢለቀቁም ከአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁለት ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው። ሲፒጄ በተጨማሪም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ሁለተኛ ናት በሚል ሪፖርት አውጥቷል። በቅርቡም ድርጅቱ በእስር ላይ ያሉት ደሱ ዱላ እና ቢቂላ አመኑ የተሰኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱና ክሳቸው እንዲቋረጥ ጠይቋል። የማኅበራዊ ሚዲያ የሆነው የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ ጋዜጠኞቹ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ቢሆንም የታሰሩት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም ደሱ እና ቢቂላ በእስር ቤት እንዳሉና ህገ መንግሥቱን በመፃረር በቀረበባቸው እስከ ሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ገልጿል። ከ12 ወራት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢን 'ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ አቅርቧል' በሚል የፕሬስ ፈቃዱን የነጠቀች ሲሆን ይህንን እርምጃም ጋዜጣው 'አምባገነናዊ አካሄድ' እና 'እጅጉን ተስፋ አስቆራጭ' ብሎታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61441551 |
3politics
| በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማት ባልደረቦች የነበሩትን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸውን የደኅንነት ምክር ቤት አስታወቀ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማትን “የከዱ” የተባሉ አባሎችን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገለጸ። ምክር ቤቱ ትላንት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ላይ “ከፀጥታ ተቋማት የከዱ አባላትን የመያዝ፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ሥር የማዋል” ሥራ መከናወኑ ተገልጿል። በአማራ ክልል ባለፉት ሳምንታት መንግሥት “የሕግ ማስከበር” በሚል በወሰደው እርምጃ፣ “ተበትነው የፀጥታ ስጋት ሲሆኑ የቆዩ የጦር መሣሪያዎች የመሰብሰብ፣ በሕገ ወጥ ተግባራት ተሰማርተው የነበሩ አክቲቪስቶችን ሥርዓት የማስያዝ” ሥራ መካሄዱንም የደኅንነት ምክር ቤቱ መግለጫ ይጠቁማል። እነዚህንም “ሕዝቡን ለእፎይታ ያበቁ ተግባሮች” ሲል ምክር ቤቱ ገልጿቸዋል። የፌደራል መንግሥት እና የአማራ ክልል መንግሥት በአማራ ክልል የጦር መሣሪያን በመመዝገብ የጀመሩት ዘመቻ ኋላ ላይ ከ4000 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉበት እንደሆነ ተገልጿል። መንግሥት ዘመቻውን “የሕግ ማስከበር” ቢለውም፣ ዘመቻው መንግሥትን የሚተቹ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ማኅበረሰብ አንቂዎችን እንዲሁም ፋኖ የተባለውን ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ኢላማ ያደረገ ነው ብለው የሚከራከሩም አሉ። ምክር ቤቱ የፋኖን ታጣቂዎች በስም ባይጠቅስም ከመንግሥት ፀጥታ መዋቅሮች ውጭ ያሉ የታጠቁ አደረጃጀቶች "እንደፈለጉ" ሊሆኑ እንደማይችሉ በመግለጫው አስፍሯል። “በአገር ውስጥ ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብት ለመንግሥት የተሰጠ መብት ነው። ዜጎች በሰላም ጊዜ አልሚ፣ በጦርነት ጊዜ ተፋላሚ መሆናቸውም ከጥንት የነበረ ነው። ያ ማለት አገር ስትወረር ሁሉም ለአገሩ ተፋላሚ ይሆናል። አገር ሰላም ስትሆን ደግሞ ሁሉም ወደ ሕጋዊ ማዕቀፍ ይገባል ማለት ነው” ብሏል። ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ. ም. ስለ አገር አቀፍ የፀጥታና ደኅንነት ያደረገውን ግምገማ ተከትሎ ባስቀመጠው አቅጣጫ፣ ከአማራ ክልል በተጨማሪ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝም የተወሰዱ እርምጃዎች እንዳሉ በትናንትናው መግለጫ አትቷል። በመግለጫው መሠረት በኦሮሚያ ክልል “በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አባላት ተገድለዋል”። “የሸኔን ልዩ ልዩ ቡድኖች የመደምሰስ፣ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን የማምከን፣ በጠላት እጅ የነበሩ አካባቢዎችን መልሶ የመቆጣጠር፣ መንግሥታዊ መዋቅሩን የማጥራት” እርምጃዎች እንደተወሰዱ ጠቅሶ፣ እነዚህንም “ውጤታማ” ሲል ገልጿቸዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው እና መንግሥት ‘ሸኔ’ የሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል ውጊያ ሲካሄድ መሰንበቱ አይዘነጋም። መንግሥት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ታግዞ በተካሄደው በዚህ ውጊያ ንጹሐን ዜጎች ሰለባ መሆናቸውን የኦሮሚያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ መክሰሳቸው ይታወሳል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ “የታጠቁ ሽፍቶችን ሥርዓት ማስያዝና መደምሰስ” መከናወኑን ጠቅሶ እነዚህን ሥራዎች “አበረታች” ሲል ምክር ቤቱ ገልጿቸዋል። በክልሉ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያን የመሰብሰብ እንዲሁም ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሥ ሥራ መሠራቱን አክሏል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ በክልሉ መንግሥትና በተለይም የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) መካከል ዘላቂ ሰላም ለማውረድ የሚደረጉ ጥረቶች በተደጋጋሚ መሰናክል ሲገጥማቸው ቆይቷል። ከቀናት በፊት በካማሺ ዞን በምትገኘው ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በጉሕዴን ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ 19 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። በሌላ በኩል በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “ሊደረግ ታስቦ የነበረው የአል-ሸባብ እንቅስቃሴ በፀጥታ አካላት ቅንጅት ከሽፏል” ሲል ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ገልጿል። በደቡብ እና በጋምቤላ ክልሎች “የታጠቁና የተደራጁ ሽፍቶችን መልክ የማስያዝ እንቅስቃሴ” መከናወኑን ጠቅሶ፣ በተጨማሪም የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታትና በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን የመፍታት ሥራ መሠራቱን መግለጫው አትቷል። ምክር ቤቱ “ዓለም አቀፍ የሚዲያ ትኩረትን ለመሳብ የሚፈልጉ” ያላቸው ቡድኖች በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ የቃጡትን ጥቃት የፀጥታና ደኅንነት መዋቅሩ ማክሸፉን አያይዞ ገልጿል። መንግሥት በአማራ ክልልና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሄ ነው ማለቱ ይታወሳል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገ ወጥነትና የሰላም መደፍረስን መንግሥት እንዲቆጣጠር ሕዝቡ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ነበር ያለው መግለጫው፣ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ መወሰኑን አስታውሷል። በዚህ መግለጫውም በአጠቃላይ የተጀመረው ሰላምና ጸጥታ የማስፈን እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፅንኦት ሰጥቷል። | በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማት ባልደረቦች የነበሩትን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸውን የደኅንነት ምክር ቤት አስታወቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማትን “የከዱ” የተባሉ አባሎችን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገለጸ። ምክር ቤቱ ትላንት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ላይ “ከፀጥታ ተቋማት የከዱ አባላትን የመያዝ፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ሥር የማዋል” ሥራ መከናወኑ ተገልጿል። በአማራ ክልል ባለፉት ሳምንታት መንግሥት “የሕግ ማስከበር” በሚል በወሰደው እርምጃ፣ “ተበትነው የፀጥታ ስጋት ሲሆኑ የቆዩ የጦር መሣሪያዎች የመሰብሰብ፣ በሕገ ወጥ ተግባራት ተሰማርተው የነበሩ አክቲቪስቶችን ሥርዓት የማስያዝ” ሥራ መካሄዱንም የደኅንነት ምክር ቤቱ መግለጫ ይጠቁማል። እነዚህንም “ሕዝቡን ለእፎይታ ያበቁ ተግባሮች” ሲል ምክር ቤቱ ገልጿቸዋል። የፌደራል መንግሥት እና የአማራ ክልል መንግሥት በአማራ ክልል የጦር መሣሪያን በመመዝገብ የጀመሩት ዘመቻ ኋላ ላይ ከ4000 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉበት እንደሆነ ተገልጿል። መንግሥት ዘመቻውን “የሕግ ማስከበር” ቢለውም፣ ዘመቻው መንግሥትን የሚተቹ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ማኅበረሰብ አንቂዎችን እንዲሁም ፋኖ የተባለውን ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ኢላማ ያደረገ ነው ብለው የሚከራከሩም አሉ። ምክር ቤቱ የፋኖን ታጣቂዎች በስም ባይጠቅስም ከመንግሥት ፀጥታ መዋቅሮች ውጭ ያሉ የታጠቁ አደረጃጀቶች "እንደፈለጉ" ሊሆኑ እንደማይችሉ በመግለጫው አስፍሯል። “በአገር ውስጥ ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብት ለመንግሥት የተሰጠ መብት ነው። ዜጎች በሰላም ጊዜ አልሚ፣ በጦርነት ጊዜ ተፋላሚ መሆናቸውም ከጥንት የነበረ ነው። ያ ማለት አገር ስትወረር ሁሉም ለአገሩ ተፋላሚ ይሆናል። አገር ሰላም ስትሆን ደግሞ ሁሉም ወደ ሕጋዊ ማዕቀፍ ይገባል ማለት ነው” ብሏል። ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ. ም. ስለ አገር አቀፍ የፀጥታና ደኅንነት ያደረገውን ግምገማ ተከትሎ ባስቀመጠው አቅጣጫ፣ ከአማራ ክልል በተጨማሪ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝም የተወሰዱ እርምጃዎች እንዳሉ በትናንትናው መግለጫ አትቷል። በመግለጫው መሠረት በኦሮሚያ ክልል “በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አባላት ተገድለዋል”። “የሸኔን ልዩ ልዩ ቡድኖች የመደምሰስ፣ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን የማምከን፣ በጠላት እጅ የነበሩ አካባቢዎችን መልሶ የመቆጣጠር፣ መንግሥታዊ መዋቅሩን የማጥራት” እርምጃዎች እንደተወሰዱ ጠቅሶ፣ እነዚህንም “ውጤታማ” ሲል ገልጿቸዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው እና መንግሥት ‘ሸኔ’ የሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል ውጊያ ሲካሄድ መሰንበቱ አይዘነጋም። መንግሥት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ታግዞ በተካሄደው በዚህ ውጊያ ንጹሐን ዜጎች ሰለባ መሆናቸውን የኦሮሚያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ መክሰሳቸው ይታወሳል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ “የታጠቁ ሽፍቶችን ሥርዓት ማስያዝና መደምሰስ” መከናወኑን ጠቅሶ እነዚህን ሥራዎች “አበረታች” ሲል ምክር ቤቱ ገልጿቸዋል። በክልሉ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያን የመሰብሰብ እንዲሁም ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሥ ሥራ መሠራቱን አክሏል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ በክልሉ መንግሥትና በተለይም የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) መካከል ዘላቂ ሰላም ለማውረድ የሚደረጉ ጥረቶች በተደጋጋሚ መሰናክል ሲገጥማቸው ቆይቷል። ከቀናት በፊት በካማሺ ዞን በምትገኘው ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በጉሕዴን ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ 19 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። በሌላ በኩል በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “ሊደረግ ታስቦ የነበረው የአል-ሸባብ እንቅስቃሴ በፀጥታ አካላት ቅንጅት ከሽፏል” ሲል ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ገልጿል። በደቡብ እና በጋምቤላ ክልሎች “የታጠቁና የተደራጁ ሽፍቶችን መልክ የማስያዝ እንቅስቃሴ” መከናወኑን ጠቅሶ፣ በተጨማሪም የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታትና በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን የመፍታት ሥራ መሠራቱን መግለጫው አትቷል። ምክር ቤቱ “ዓለም አቀፍ የሚዲያ ትኩረትን ለመሳብ የሚፈልጉ” ያላቸው ቡድኖች በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ የቃጡትን ጥቃት የፀጥታና ደኅንነት መዋቅሩ ማክሸፉን አያይዞ ገልጿል። መንግሥት በአማራ ክልልና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሄ ነው ማለቱ ይታወሳል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገ ወጥነትና የሰላም መደፍረስን መንግሥት እንዲቆጣጠር ሕዝቡ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ነበር ያለው መግለጫው፣ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ መወሰኑን አስታውሷል። በዚህ መግለጫውም በአጠቃላይ የተጀመረው ሰላምና ጸጥታ የማስፈን እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፅንኦት ሰጥቷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cx87elvg9j7o |
5sports
| እግር ኳስ ፡ የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ማልያ በልካቸው አለመሰፋቱ ቁጣን ቀሰቀሰ | የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቡድኑ ማልያ በሴቶች ልክ የለም መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን እያሰሙ ነው። የብሔራዊ ቡድኗ ከሜዳ ውጭ የምትጫወትበት ማልያ በአዲስ መልክ ቢሰራም ለሴቶች የሚሆን የለም ተብለዋል ደጋፊዎች። መቶ በመቶ ከፖሊስተር ጨርቅ የተሠራው አዲሱ ማልያ ባለፈው አርብ ከወንዶቹ ማልያ ጋር ነበር ለገበያ የቀረበው። ነገር ግን የሴቶች ብሔራዊ ቡድኗ በትዊትር ገጿ እንዳስታወቀችው አዲሱ ማልያ በሴቶች ልክ አልተሰራም፤ በወንዶች እንጂ በማለት ያጋጠመውን ችግር ገልጸዋል። 'ማቲልዳስ' በተሰኘ ቅፅል ስም የምትታወቀው ቡድን ይፋ እንዳደረገችው አዲሱ ማልያ እስከ 2022 [በአውሮፓውያኑ] ድረስ በሴቶች ልክ አይሠራም። የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ሰባተኛ ናት። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ናይኪ የተሰኘው የስፖርት አልባሳት አምራች ያመረቱት አዲሱ ቢጫ ማልያ ገበያ ላይ ፈላጊው በዝቷል። ነገር ግን ማልያው በሴቶች ልክ ባለመሠራቱ ሴቶቹም የሚለብሱት ለወንዶቹ የተሠራውን ነው ተብሏል። ምንም እንኳ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ማልያውን ለብሰው ፎቶ በመነሳት ማስታወቂያ ቢሰሩም ደጋፊዎች ግን ይህ አላስደሰታቸውም። ብሔራዊ ቡድኗ ችግሩ የሚቀረፈው በአውሮፓውያኑ 2022 አዲስ ማልያ ሲተዋወቅ ነው ብላለች። ደጋፊዎችን ጨምሮ የብሔራዊ ቡድኑ አባላት በሁኔታው የተሰማቸውን ቅሬታ በማኅበራዊ ድር አምባ ገፆቻቸው ላይ ገልፀዋል። አውስትራሊያ 2023 ላይ የሚካሄደውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ ታዘጋጃለች። የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አፈ ቀላጤ ስለጉዳዩ በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተጠይቀው "ተጨማሪ አስተያየት መስጠት አልችልም" ብለዋል። የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 'ማቲልዳስ' አባላት በአውሮፓውያኑ 2019 ከወንዶቹ እኩል ደመወዝ እንዲከፈላቸው መወሰኑ ይታወሳል። በስምምነቱ መሠረት ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች እኩል ደመወዝና የማስታወቂያ ገቢ ያገኛሉ። አልፎም በአውሮፕላን ሲጓዙ የሚደርግላቸው እንክብካቤና የልምምድ ሜዳ ቁሳቁስ አቅርቦት ከወንዶቹ እኩል እንዲሆን ሆኗል። ነገር ግን አሁንም ወንዶቹ በሚወዳደሩባቸው ውድድሮች ካሸነፉ እንዲሁም ዋንጫ ካገኙ ከሴቶቹ የተሻለ ገንዘብ ያገኛሉ። የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድን በዓለም 41ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። | እግር ኳስ ፡ የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ማልያ በልካቸው አለመሰፋቱ ቁጣን ቀሰቀሰ የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቡድኑ ማልያ በሴቶች ልክ የለም መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን እያሰሙ ነው። የብሔራዊ ቡድኗ ከሜዳ ውጭ የምትጫወትበት ማልያ በአዲስ መልክ ቢሰራም ለሴቶች የሚሆን የለም ተብለዋል ደጋፊዎች። መቶ በመቶ ከፖሊስተር ጨርቅ የተሠራው አዲሱ ማልያ ባለፈው አርብ ከወንዶቹ ማልያ ጋር ነበር ለገበያ የቀረበው። ነገር ግን የሴቶች ብሔራዊ ቡድኗ በትዊትር ገጿ እንዳስታወቀችው አዲሱ ማልያ በሴቶች ልክ አልተሰራም፤ በወንዶች እንጂ በማለት ያጋጠመውን ችግር ገልጸዋል። 'ማቲልዳስ' በተሰኘ ቅፅል ስም የምትታወቀው ቡድን ይፋ እንዳደረገችው አዲሱ ማልያ እስከ 2022 [በአውሮፓውያኑ] ድረስ በሴቶች ልክ አይሠራም። የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ሰባተኛ ናት። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ናይኪ የተሰኘው የስፖርት አልባሳት አምራች ያመረቱት አዲሱ ቢጫ ማልያ ገበያ ላይ ፈላጊው በዝቷል። ነገር ግን ማልያው በሴቶች ልክ ባለመሠራቱ ሴቶቹም የሚለብሱት ለወንዶቹ የተሠራውን ነው ተብሏል። ምንም እንኳ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ማልያውን ለብሰው ፎቶ በመነሳት ማስታወቂያ ቢሰሩም ደጋፊዎች ግን ይህ አላስደሰታቸውም። ብሔራዊ ቡድኗ ችግሩ የሚቀረፈው በአውሮፓውያኑ 2022 አዲስ ማልያ ሲተዋወቅ ነው ብላለች። ደጋፊዎችን ጨምሮ የብሔራዊ ቡድኑ አባላት በሁኔታው የተሰማቸውን ቅሬታ በማኅበራዊ ድር አምባ ገፆቻቸው ላይ ገልፀዋል። አውስትራሊያ 2023 ላይ የሚካሄደውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ ታዘጋጃለች። የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አፈ ቀላጤ ስለጉዳዩ በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተጠይቀው "ተጨማሪ አስተያየት መስጠት አልችልም" ብለዋል። የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 'ማቲልዳስ' አባላት በአውሮፓውያኑ 2019 ከወንዶቹ እኩል ደመወዝ እንዲከፈላቸው መወሰኑ ይታወሳል። በስምምነቱ መሠረት ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች እኩል ደመወዝና የማስታወቂያ ገቢ ያገኛሉ። አልፎም በአውሮፕላን ሲጓዙ የሚደርግላቸው እንክብካቤና የልምምድ ሜዳ ቁሳቁስ አቅርቦት ከወንዶቹ እኩል እንዲሆን ሆኗል። ነገር ግን አሁንም ወንዶቹ በሚወዳደሩባቸው ውድድሮች ካሸነፉ እንዲሁም ዋንጫ ካገኙ ከሴቶቹ የተሻለ ገንዘብ ያገኛሉ። የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድን በዓለም 41ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54216906 |
2health
| የወባ በሽታን 70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል አንድ ጥናት አመለከተ | በአንድ ጥናት መሰረት አዲስ አይነት የመከላከል መንገዶችን በመጠቀም አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት በወባ በሽታ የመያዝና የመሞት ዕድላቸውን በ70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተጠቆመ። የወባ በሽታ በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸው ወራት ከመድረሳቸው በፊት ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግና በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲጨምሩበት በማድረግ ሙከራው ከፍተኛ የሆነ ውጤት ማስገኘቱን በለንደን የሚገኙ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። የዚህ የወባ በሽታን የመከላከል ሙከራው የተደረገው ከቡርኪናፋሶ እና ከማሊ የተወጣጡ ከ17 ወራት በታች የሆኑ 6 ሺህ ህጻናት ላይ ነው ተብሏል። አፍሪካ በየዓመቱ በወባ በሽታ ምክንያት እስከ 400 ሺህ ሞቶችን የምታስመዘግብ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ እድሜያቸው ከአምስት ወራት በታች ነው። ይህ ጥናት 'በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜድሲን' የህክምና መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን በሙከራው ላይ ለህጻናቱ አሁን ላይ የሚገኙ የወባ ክትባቶችን ቀድሞ መስጠትና የወባ በሽታ በብዛት በሚከሰትባቸው ወራት ደግሞ (አብዛኛውን ጊዜ የዝናብ ወራት ናቸው) ሌሎች የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን በመስጠት ነው ከፍተኛ ውጤት የተገኘው። "እኛ እናገኘዋለን ብለን ካሰብነው ውጤት በጣም የተሻለ ነገር ነው ያገኘነው" ብለዋል የምርምር ቡድኑ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ብራያን ግሪንዉድ። "በሁለቱም አገራት ሙከራውን ከጀመርን በኋላ በወባ በሽታ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡና ህይወታቸው የሚያልፍ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል።" ባለፉት ሦስት ዓመታት በተሰራው ሙከራ የዝናብ ወራት ከመድረሳቸው በፊት ሦስት የወባ ክትባቶች ለህጻናቱ የተሰጣቸው ሲሆን የዝናብ ወቅት ሲገባ ደግሞ የተለያዩ አይነት የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲወስዱ ተደርጓል። በዚህም የወባ በሽታ ስርጭትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ታይቶበታል። የዚህ ሙከራ ውጤትም ከየትኛውም አይነት ክትባትና መድኃኒት በተሻለ መልኩ ውጤት ያስገኘ ሲሆን በአፍሪካ በወባ በሽታ የሚጠቁ ህጻናትን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ይህም ሚሊየኖችን ህይወት እንደሚታደግ ከወዲሁ ተገምቷል። በሙከራው ላይ ክትባቱን ቀደም ብለው ከወሰዱትና በዝናብ ወቅት ደግሞ ሌሎች መከላከያዎችን ከወሰዱት ህጻናት መካከል 624ቱ በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 11 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ወስደዋል። በተጨማሪም የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ቀንሶ 3 ብቻ ነበር። በዚህ ሙከራ እንዳይካተቱ ከተደረጉት ተመሳሳይ ቁጥር ካላቸው ህጻናት መካከል ደግሞ 1661 ህጻናት በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 37 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል። የሟቾች ቁጥር ደግሞ 11 ነበር። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ አዲስ ሙከራ በጣም ውጤታማ ስለመሆኑ ማሳያ ነው። ከዚህ በፊት በሚደረጉ ሙከራዎች ጉንፋንን ቀድሞ ለመከላከል መሰል ጥረቶች ቢደረጉም በወባ በሽታ ላይ ሲሞከር ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የወባ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ፔድሮ አሎንሶ ደግሞ "ይህን አዲስ አይነት የወባ በሽታ ክትባትና መከላከል ሥራ በመልካም ጎኑ ነው የምንመለከተው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ ሞትን ማስቀረት እንደሚያስችል እንገምታለን" ብለዋል። የወባ በሽታ ክትባቱ እስካሁን 740 ሺህ ለሚሆኑ ጋና፣ ኬንያ እና ማላዊ ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት የተሰራጨ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን እስኪሰጥ እየተጠበቀ ነው። በዚህ ሙከራ ላይ የትኛውም ህጻን ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላስተናገደ ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት ህጻናት ክትባቱን እና መከላከያ መድኃኒቶቹን እስከ 5 ዓመታቸው ድረስ እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን በዚያውም ሌሎች የተሻሉ አማራጮች ከመጡ አብረው እንደሚካተቱ ተገልጿል። | የወባ በሽታን 70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል አንድ ጥናት አመለከተ በአንድ ጥናት መሰረት አዲስ አይነት የመከላከል መንገዶችን በመጠቀም አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት በወባ በሽታ የመያዝና የመሞት ዕድላቸውን በ70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተጠቆመ። የወባ በሽታ በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸው ወራት ከመድረሳቸው በፊት ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግና በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲጨምሩበት በማድረግ ሙከራው ከፍተኛ የሆነ ውጤት ማስገኘቱን በለንደን የሚገኙ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። የዚህ የወባ በሽታን የመከላከል ሙከራው የተደረገው ከቡርኪናፋሶ እና ከማሊ የተወጣጡ ከ17 ወራት በታች የሆኑ 6 ሺህ ህጻናት ላይ ነው ተብሏል። አፍሪካ በየዓመቱ በወባ በሽታ ምክንያት እስከ 400 ሺህ ሞቶችን የምታስመዘግብ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ እድሜያቸው ከአምስት ወራት በታች ነው። ይህ ጥናት 'በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜድሲን' የህክምና መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን በሙከራው ላይ ለህጻናቱ አሁን ላይ የሚገኙ የወባ ክትባቶችን ቀድሞ መስጠትና የወባ በሽታ በብዛት በሚከሰትባቸው ወራት ደግሞ (አብዛኛውን ጊዜ የዝናብ ወራት ናቸው) ሌሎች የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን በመስጠት ነው ከፍተኛ ውጤት የተገኘው። "እኛ እናገኘዋለን ብለን ካሰብነው ውጤት በጣም የተሻለ ነገር ነው ያገኘነው" ብለዋል የምርምር ቡድኑ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ብራያን ግሪንዉድ። "በሁለቱም አገራት ሙከራውን ከጀመርን በኋላ በወባ በሽታ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡና ህይወታቸው የሚያልፍ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል።" ባለፉት ሦስት ዓመታት በተሰራው ሙከራ የዝናብ ወራት ከመድረሳቸው በፊት ሦስት የወባ ክትባቶች ለህጻናቱ የተሰጣቸው ሲሆን የዝናብ ወቅት ሲገባ ደግሞ የተለያዩ አይነት የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲወስዱ ተደርጓል። በዚህም የወባ በሽታ ስርጭትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ታይቶበታል። የዚህ ሙከራ ውጤትም ከየትኛውም አይነት ክትባትና መድኃኒት በተሻለ መልኩ ውጤት ያስገኘ ሲሆን በአፍሪካ በወባ በሽታ የሚጠቁ ህጻናትን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ይህም ሚሊየኖችን ህይወት እንደሚታደግ ከወዲሁ ተገምቷል። በሙከራው ላይ ክትባቱን ቀደም ብለው ከወሰዱትና በዝናብ ወቅት ደግሞ ሌሎች መከላከያዎችን ከወሰዱት ህጻናት መካከል 624ቱ በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 11 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ወስደዋል። በተጨማሪም የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ቀንሶ 3 ብቻ ነበር። በዚህ ሙከራ እንዳይካተቱ ከተደረጉት ተመሳሳይ ቁጥር ካላቸው ህጻናት መካከል ደግሞ 1661 ህጻናት በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 37 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል። የሟቾች ቁጥር ደግሞ 11 ነበር። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ አዲስ ሙከራ በጣም ውጤታማ ስለመሆኑ ማሳያ ነው። ከዚህ በፊት በሚደረጉ ሙከራዎች ጉንፋንን ቀድሞ ለመከላከል መሰል ጥረቶች ቢደረጉም በወባ በሽታ ላይ ሲሞከር ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የወባ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ፔድሮ አሎንሶ ደግሞ "ይህን አዲስ አይነት የወባ በሽታ ክትባትና መከላከል ሥራ በመልካም ጎኑ ነው የምንመለከተው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ ሞትን ማስቀረት እንደሚያስችል እንገምታለን" ብለዋል። የወባ በሽታ ክትባቱ እስካሁን 740 ሺህ ለሚሆኑ ጋና፣ ኬንያ እና ማላዊ ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት የተሰራጨ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን እስኪሰጥ እየተጠበቀ ነው። በዚህ ሙከራ ላይ የትኛውም ህጻን ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላስተናገደ ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት ህጻናት ክትባቱን እና መከላከያ መድኃኒቶቹን እስከ 5 ዓመታቸው ድረስ እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን በዚያውም ሌሎች የተሻሉ አማራጮች ከመጡ አብረው እንደሚካተቱ ተገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58345206 |
0business
| ቢሊየን ዓመት ያስቆጠረው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ | የዓለማችን ትልቁ የተቆረጠ አልማዝ ነው ተብሎ የሚታመነውና የቢሊየን ዓመት ዕድሜ ያለው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ። ዘ ኢኒግማ ተብሎ የተሰየመው የ555.55 ካራት አልማዝ ከአንድ ሙዝ ክብደት ጋር ተነጻጽሯል። በበይነ መረብ ግብይትም ከ4.4 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ከአስትሮይድ ጋር ወደ ምድር መምጣቱን ጨምሮ ስለ አልማዙ አመጣጥ ብዙ መላ ምቶች አሉ። አጫራቹ ሶዝባይ እንዳለው፤ ገዢው ክፍያውን በክሪፕቶከረንሲ ለማድረግ መርጧል። ሶዝባይ የገዢውን ማንነት ሳይገልጽ ቆይቶ፤ ከጨረታው በኋላ የክሪፕቶከረንሲ ባለሙያው ሪቻርድ ኸርት የዘ ኢኒግማ ገዢ መሆኑን በማኅበራዊ ገጹ ገልጿል። ሶዝባይ ከ180,000 በላይ ለሚሆኑት የትዊተር ተከታዮቹ፤ የአልማዙ ክፍያ እንደተጠናቀቀ እና ንብረቱን እንደተረከበ አልማዙ ሄክስ.ኮም ዳይመንድ (HEX.com Diamond) የሚል ስያሜ እንደሚሰጠው ገልጿል። ስያሜው የክሪፕቶከረንሲ ባለሙያው ሪቻርድ ከመሠረተውን ብሎክቼይን የተገኘ ነው። አልማዙ ካርቦንዶስ ነው ተብሏል። ይህም በጣም ጠንካራ ከሆኑ የተፈጥሮ አልማዞች አንዱ ነው። ካርቦናዶስ የሚባሉት የአልማዝ አይነቶች ጥቂት ሲሆኑ አልፎ አልፎ የተገኙትም በብራዚል እና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ብቻ ነው። በሜትሮዎች ውስጥ ብቻ የሚገኘው ኦስቦርኔት የተባለውን ማዕድን ስላላቸው ከጠፈር እንደመጡ ይታመናል። ሶዝባይ ዘ ኢኒግማን "በሰው ልጅ ዘንድ ከሚታወቁት ብርቅዬ፣ ከቢሊየን ዓመታት በላይ ካስቆጠሩት የጠፈር ድንቅ ስጦታዎች አንዱ ነው" ሲል ገልጾታል። የጥቁር አልማዝ ትክክለኛ አመጣጥ በምስጢር የተሞላ ነው። ጥቁር አልማዞች ከ2.6 እስከ 3.2 ቢሊየን ዓመታት መኖራቸው ይገመታል። ይህም ዳይኖሰር ከመፈጠሩ በፊት መሆኑ ነው። | ቢሊየን ዓመት ያስቆጠረው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ የዓለማችን ትልቁ የተቆረጠ አልማዝ ነው ተብሎ የሚታመነውና የቢሊየን ዓመት ዕድሜ ያለው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ። ዘ ኢኒግማ ተብሎ የተሰየመው የ555.55 ካራት አልማዝ ከአንድ ሙዝ ክብደት ጋር ተነጻጽሯል። በበይነ መረብ ግብይትም ከ4.4 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ከአስትሮይድ ጋር ወደ ምድር መምጣቱን ጨምሮ ስለ አልማዙ አመጣጥ ብዙ መላ ምቶች አሉ። አጫራቹ ሶዝባይ እንዳለው፤ ገዢው ክፍያውን በክሪፕቶከረንሲ ለማድረግ መርጧል። ሶዝባይ የገዢውን ማንነት ሳይገልጽ ቆይቶ፤ ከጨረታው በኋላ የክሪፕቶከረንሲ ባለሙያው ሪቻርድ ኸርት የዘ ኢኒግማ ገዢ መሆኑን በማኅበራዊ ገጹ ገልጿል። ሶዝባይ ከ180,000 በላይ ለሚሆኑት የትዊተር ተከታዮቹ፤ የአልማዙ ክፍያ እንደተጠናቀቀ እና ንብረቱን እንደተረከበ አልማዙ ሄክስ.ኮም ዳይመንድ (HEX.com Diamond) የሚል ስያሜ እንደሚሰጠው ገልጿል። ስያሜው የክሪፕቶከረንሲ ባለሙያው ሪቻርድ ከመሠረተውን ብሎክቼይን የተገኘ ነው። አልማዙ ካርቦንዶስ ነው ተብሏል። ይህም በጣም ጠንካራ ከሆኑ የተፈጥሮ አልማዞች አንዱ ነው። ካርቦናዶስ የሚባሉት የአልማዝ አይነቶች ጥቂት ሲሆኑ አልፎ አልፎ የተገኙትም በብራዚል እና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ብቻ ነው። በሜትሮዎች ውስጥ ብቻ የሚገኘው ኦስቦርኔት የተባለውን ማዕድን ስላላቸው ከጠፈር እንደመጡ ይታመናል። ሶዝባይ ዘ ኢኒግማን "በሰው ልጅ ዘንድ ከሚታወቁት ብርቅዬ፣ ከቢሊየን ዓመታት በላይ ካስቆጠሩት የጠፈር ድንቅ ስጦታዎች አንዱ ነው" ሲል ገልጾታል። የጥቁር አልማዝ ትክክለኛ አመጣጥ በምስጢር የተሞላ ነው። ጥቁር አልማዞች ከ2.6 እስከ 3.2 ቢሊየን ዓመታት መኖራቸው ይገመታል። ይህም ዳይኖሰር ከመፈጠሩ በፊት መሆኑ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-60329211 |
3politics
| ሩሲያ ለዩክሬን ተገንጣይ ክልሎች ዕውቅና ሰጠች | የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሲካሄድ የቆየው የሰላም ድርድር ማብቃቱን በመግለጽ በዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል ተገንጥለው ለሚገኙ አማፂ ክልሎችን ዕውቅና ሰጡ። ለራሳቸው ነጻነታቸውን ያወጁት የዶኔስክ እና የሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊኮች በሩሲያ የሚደገፉ አማፂያን ሲሆኑ እአአ ከ2014 ጀምሮ ከዩክሬይን ጦር ጋር ሲዋጉ ነበር። የሩሲያ ወታደሮች በሁለቱም ክልሎች "የሰላም ማስከበር ሚናቸውን" እንዲወጡ ታዘዋል። ሩሲያ ሆን ብላ ሉዓላዊነታችንን እየጣሰች ነው ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሰዋል። ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በቴሌቭዥን ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ሰላም እንደምትፈልግ ገልጸዋል። አክለውም "አንፈራም" ካሉ በኋላ "ለማንም አሳልፈን የምንሰጠው ነገር አይኖርም" ብለዋል። ኪዬቭ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ "ግልጽ እና ውጤታማ የድጋፍ እርምጃዎች" እንደሚያስፈልጋት ጨምረው ጠቅሰዋል። "አሁን እውነተኛ ወዳጃችን እና አጋራችን ማን እንደሆነ እና የሩስያ ፌዴሬሽንን በቃላት ብቻ ማስፈራራትን የሚቀጥል ማን እንደሆነ ማየት በጣም አስፈላጊ ነው" ብለዋል። የምዕራቡ ኃያላን አገራት ፑቲን በአማፂያኑ ቁጥጥር ሥር ላሉ አካባቢዎች ዕውቅና መስጠታቸው የሩስያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል በይፋ እንዲገቡ መንገድ ይከፍታል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲያ የሩስያ ፓስፖት በዶኔስክ እና በሉሃንስክ ለብዙ ሰዎች ተሰጥቷል። የምዕራባውያኑ ስጋትም ሩሲያ ዜጎቼን ለመጠበቅ በሚል ሽፋን ወታደሮቿን ልታንቀሳቅስ ትችላለች የሚል ነው። ከሰኞው መግለጫ በኋላ አንድ ሰዓት የሚፈጅ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ዘመናዊዋ ዩክሬን በሶቪየት ሩሲያ "የተፈጠረች" ናት ብለው "የጥንታዊት ሩሲያ መሬት" በማለትም ገልጸዋታል። እአአ በ1991 በተካሄደው የሶቭየት ኅብረት ውድቀት ወቅት ሩሲያ "ተዘርፋለች" ብለዋል። ዩክሬንን በአሻንጉሊት መንግሥት የምትመራ "የአሜሪካ ቅኝ ግዛት ናት" በማለት የጠቀሱ ሲሆን፤ አሁን ባለው አመራር ዜጎች እየተሰቃዩ ነው ሲሉም ተናግረዋል። እአአ በ2014 የተካሄደውን እና በሩሲያ የሚደገፍ የነበረውን አመራር ከሥልጣን ያወረደውን ተቃውሞ መፈንቅለ መንግሥት ሲሉ ገልጸውታል። 'ተቀባይነት የሌለው ነው' ዩናይትድ ስቴትስ የፑቲንን እርምጃ በፍጥነት አውግዛለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም መገንጠል በሚፈልጉት ክልሎች የአሜሪካውያንን አዲስ ኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና ፋይናንስን የሚከለክል ትዕዛዝ ፈርመዋል። እርምጃዎቹ "ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች" ለመጣል ዝግጁ ከሆኑት የምዕራባውያን ማዕቀቦች የተለዩ መሆናቸውን ኋይት ኃውስ አስታውቋል። የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የሩስያ ድርጊት ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር "የዩክሬንን ሉዓላዊነትን በግልፅ የጣሰ ነው" ብለዋል። "ጥሩ ያልሆነ ምልክት እና ጥቁር ምልክት" ነው ሲሉም ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትሩስ በበኩላቸው እንግሊዝ ማክሰኞ ዕለት በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንደምትጥል አስታውቀዋል። የአውሮፓ ኅብረት "ከዩክሬን ጎን በመቆም በአንድነት፣ በጥንካሬ እና በቁርጠኝነት ምላሽ ለመስጠት" ቃል ገብቷል ። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በበኩላቸው የሩስያ ወታደሮችን የሰላም ማስከበር መግለጫ ሐሳብ ውድቅ በማድረግ "ተቀባይነት የሌለው፣ ያልተመጣጠነ፣ ያልተገባ፣ ከንቱ ሐሳብ ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የቭላድሚር ፑቲን እርምጃ ከ150,000 በሚበልጡ የሩስያ ወታደሮች ድንበሯ ለተከበበው ዩክሬን የነበረውን ቀውስ የበለጠ ያጠናክረዋል። ሩሲያ ለመውረር አቅዳለች መባሉን ውድቅ ስታደርግ አሜሪካ ደግሞ ጥቃት አይቀሬ እንደሆነ ታምናለች። የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ሾልስ እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመግለጫቸው በፊት የሩስያውን መሪ አነጋግረዋል። ምዕራባውያን አገራት ከዩክሬን ጀርባ በመሆን ሩሲያ ወረራ ከፈጸመች ከባድ ማዕቀብ እንደሚጠብቃት ቃል ገብተዋል። ለአሁኑ የሩሲያ እርምጃ ምላሹ ምን እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም። ከአወዛጋቢው ውሳኔ ቀደም ብሎ ፑቲን የሩሲያን የፀጥታ ምክር ቤት ሰብስበው ክልሎቹ ራሳቸውን የቻሉ ነጻ ሪፐብሊካኖች መሆናቸውን በማረጋገጥ ጉዳይ ሲወያዩ ነበር። የፑቲን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሐሳባቸውን ለመስጠት ወደ መድረክ የተጠሩ ሲሆን ሁሉም እርምጃውን እንደሚደግፉ ተናግረዋል። በቴሌቭዥን የተሰራጨው የሰኞው ስብሰባ ግን ሙሉ በሙሉ የተሳካ አልነበረም። ከፑቲን ጋር በተደረገው ውይይት ወቅት ሁለት ባለሥልጣናት ክልሎቹን ወደ ሩሲያ "የማካተት" ዕድልን የሚጠቅሱ መስለው ነበር። በሁለቱም አጋጣሚዎች ፑቲን አርመዋቸዋል። "እየተነጋገርን ያለነው ለነፃነታቸው ዕውቅና ስለመስጠት ወይም ስላለመስጠት ነው" ሲሉ ለተደመጡት አንድ ባለሥልጣን "እኛ ስለእሱ እየተወያየን አይደለም" በማለት አንገታቸውን ነቅንቀዋል። | ሩሲያ ለዩክሬን ተገንጣይ ክልሎች ዕውቅና ሰጠች የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሲካሄድ የቆየው የሰላም ድርድር ማብቃቱን በመግለጽ በዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል ተገንጥለው ለሚገኙ አማፂ ክልሎችን ዕውቅና ሰጡ። ለራሳቸው ነጻነታቸውን ያወጁት የዶኔስክ እና የሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊኮች በሩሲያ የሚደገፉ አማፂያን ሲሆኑ እአአ ከ2014 ጀምሮ ከዩክሬይን ጦር ጋር ሲዋጉ ነበር። የሩሲያ ወታደሮች በሁለቱም ክልሎች "የሰላም ማስከበር ሚናቸውን" እንዲወጡ ታዘዋል። ሩሲያ ሆን ብላ ሉዓላዊነታችንን እየጣሰች ነው ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሰዋል። ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በቴሌቭዥን ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ሰላም እንደምትፈልግ ገልጸዋል። አክለውም "አንፈራም" ካሉ በኋላ "ለማንም አሳልፈን የምንሰጠው ነገር አይኖርም" ብለዋል። ኪዬቭ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ "ግልጽ እና ውጤታማ የድጋፍ እርምጃዎች" እንደሚያስፈልጋት ጨምረው ጠቅሰዋል። "አሁን እውነተኛ ወዳጃችን እና አጋራችን ማን እንደሆነ እና የሩስያ ፌዴሬሽንን በቃላት ብቻ ማስፈራራትን የሚቀጥል ማን እንደሆነ ማየት በጣም አስፈላጊ ነው" ብለዋል። የምዕራቡ ኃያላን አገራት ፑቲን በአማፂያኑ ቁጥጥር ሥር ላሉ አካባቢዎች ዕውቅና መስጠታቸው የሩስያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል በይፋ እንዲገቡ መንገድ ይከፍታል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲያ የሩስያ ፓስፖት በዶኔስክ እና በሉሃንስክ ለብዙ ሰዎች ተሰጥቷል። የምዕራባውያኑ ስጋትም ሩሲያ ዜጎቼን ለመጠበቅ በሚል ሽፋን ወታደሮቿን ልታንቀሳቅስ ትችላለች የሚል ነው። ከሰኞው መግለጫ በኋላ አንድ ሰዓት የሚፈጅ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ዘመናዊዋ ዩክሬን በሶቪየት ሩሲያ "የተፈጠረች" ናት ብለው "የጥንታዊት ሩሲያ መሬት" በማለትም ገልጸዋታል። እአአ በ1991 በተካሄደው የሶቭየት ኅብረት ውድቀት ወቅት ሩሲያ "ተዘርፋለች" ብለዋል። ዩክሬንን በአሻንጉሊት መንግሥት የምትመራ "የአሜሪካ ቅኝ ግዛት ናት" በማለት የጠቀሱ ሲሆን፤ አሁን ባለው አመራር ዜጎች እየተሰቃዩ ነው ሲሉም ተናግረዋል። እአአ በ2014 የተካሄደውን እና በሩሲያ የሚደገፍ የነበረውን አመራር ከሥልጣን ያወረደውን ተቃውሞ መፈንቅለ መንግሥት ሲሉ ገልጸውታል። 'ተቀባይነት የሌለው ነው' ዩናይትድ ስቴትስ የፑቲንን እርምጃ በፍጥነት አውግዛለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም መገንጠል በሚፈልጉት ክልሎች የአሜሪካውያንን አዲስ ኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና ፋይናንስን የሚከለክል ትዕዛዝ ፈርመዋል። እርምጃዎቹ "ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች" ለመጣል ዝግጁ ከሆኑት የምዕራባውያን ማዕቀቦች የተለዩ መሆናቸውን ኋይት ኃውስ አስታውቋል። የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የሩስያ ድርጊት ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር "የዩክሬንን ሉዓላዊነትን በግልፅ የጣሰ ነው" ብለዋል። "ጥሩ ያልሆነ ምልክት እና ጥቁር ምልክት" ነው ሲሉም ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትሩስ በበኩላቸው እንግሊዝ ማክሰኞ ዕለት በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንደምትጥል አስታውቀዋል። የአውሮፓ ኅብረት "ከዩክሬን ጎን በመቆም በአንድነት፣ በጥንካሬ እና በቁርጠኝነት ምላሽ ለመስጠት" ቃል ገብቷል ። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በበኩላቸው የሩስያ ወታደሮችን የሰላም ማስከበር መግለጫ ሐሳብ ውድቅ በማድረግ "ተቀባይነት የሌለው፣ ያልተመጣጠነ፣ ያልተገባ፣ ከንቱ ሐሳብ ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የቭላድሚር ፑቲን እርምጃ ከ150,000 በሚበልጡ የሩስያ ወታደሮች ድንበሯ ለተከበበው ዩክሬን የነበረውን ቀውስ የበለጠ ያጠናክረዋል። ሩሲያ ለመውረር አቅዳለች መባሉን ውድቅ ስታደርግ አሜሪካ ደግሞ ጥቃት አይቀሬ እንደሆነ ታምናለች። የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ሾልስ እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመግለጫቸው በፊት የሩስያውን መሪ አነጋግረዋል። ምዕራባውያን አገራት ከዩክሬን ጀርባ በመሆን ሩሲያ ወረራ ከፈጸመች ከባድ ማዕቀብ እንደሚጠብቃት ቃል ገብተዋል። ለአሁኑ የሩሲያ እርምጃ ምላሹ ምን እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም። ከአወዛጋቢው ውሳኔ ቀደም ብሎ ፑቲን የሩሲያን የፀጥታ ምክር ቤት ሰብስበው ክልሎቹ ራሳቸውን የቻሉ ነጻ ሪፐብሊካኖች መሆናቸውን በማረጋገጥ ጉዳይ ሲወያዩ ነበር። የፑቲን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሐሳባቸውን ለመስጠት ወደ መድረክ የተጠሩ ሲሆን ሁሉም እርምጃውን እንደሚደግፉ ተናግረዋል። በቴሌቭዥን የተሰራጨው የሰኞው ስብሰባ ግን ሙሉ በሙሉ የተሳካ አልነበረም። ከፑቲን ጋር በተደረገው ውይይት ወቅት ሁለት ባለሥልጣናት ክልሎቹን ወደ ሩሲያ "የማካተት" ዕድልን የሚጠቅሱ መስለው ነበር። በሁለቱም አጋጣሚዎች ፑቲን አርመዋቸዋል። "እየተነጋገርን ያለነው ለነፃነታቸው ዕውቅና ስለመስጠት ወይም ስላለመስጠት ነው" ሲሉ ለተደመጡት አንድ ባለሥልጣን "እኛ ስለእሱ እየተወያየን አይደለም" በማለት አንገታቸውን ነቅንቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60474353 |
0business
| የመንደር ውል ሕጋዊ ነው? በመንደር ውል ቤት ስንሻሻጥ ልብ ልንላቸው የሚገቡን ቁልፍ ነጥቦች | የአገሪቱ አዋዋይ በተለምዶ 'ውልና ማስረጃ' የምንለው መሥሪያ ቤት ነው። የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ደግሞ ሙሉ ስሙ ነው። አሁን ግን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። ነገሩ ከወቅቱ የአገሪቱ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም። ከሐምሌ ወዲህ ይኸው እስከዛሬም አገልግሎት እየሰጠ ያለው በከፊል ነው። የተንቀሳቃሽ ንብረት ሽያጭን ጨርሶውኑ እያዋዋለ አይደለም። ይህን ተከትሎ ዜጎች በስፋት በመንደር ውል ተጠምደዋል። "ላልከዳህ-ላልክድህ ቃል አለኝ" እያሉ በየመንደሩ እየተፈጣጠሙ ነው። ለመሆኑ በውልና ማስረጃ ያልተረጋገጡ የመንደር ውሎች በሕግ ፊት ተቀባይነት አላቸው? በዚህ ጉዳይ ላይ ቢቢሲ ሁለት ከፍተኛ የሕግ አማካሪና ጠበቆችን አነጋግሯል። ጠበቃ ሚካኤል ተሾመ እና ጠበቃ ታምራት ኪዳነማርያም ይባላሉ። ሕጉን እያመሳከሩ፣ በሥራ ተሞክሮ የሚገጥሟቸውን እያጣቀሱ ጉዳዩን በየፈርጁ ይተነትኑልናል። ውል የሚጸናው ምን ሲሟላ ነው? አራት ነገር ካልተሟላ ውል አይጸናም ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። 1ኛ• ፈቃድ (Consent) ነው። ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ምን ማለት ነው ይሄ፣ በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም። 2ኛ• ተዋዋዮቹ በሕግ 'ችሎታ ያላቸው' መሆን አለባቸው። 'ችሎታ' የሕግ ትርጉሙ ሁለት ነው። የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤና ነው። 3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት። ለምሳሌ ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው። ሌላስ? 4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ 2 ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት መረጋገጥ፣ ሕጉ ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች መሟላት ማለት ነው። የሆነስ ሆኖ፣ የመንደር ውል ሕጋዊ ነው? ጠበቃ ሚካኤል፣ ለዚህ ጥያቄ በአጭሩ "ሕጋዊ አይደለም" የሚል መልስ ይሰጣሉ። ጠበቃ ታምራት ደግሞ "ነውም፣ አይደለምም" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ይህን ያሉበትን ምክንያት ወደ ኋላ ላይ ያስረዱናል። አሁን ወደ ጠበቃ ሚካኤል ነጥቦች እንመለስ። ጠበቃ ሚካኤል ለዚህ ድምዳሜ ያበቃቸውን ነጥብ ሲያስረዱ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም ይላሉ። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ይላሉ። ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው? ከሚለው እንጀምር። ጠበቃ ሚካኤል 'ሰነድ ለሁለት ዓላማ ነው የሚረጋገጠው' ብለው የክርክሩን ፍሬ ነገር ያሲዙናል። አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ። ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። "የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው" ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው? በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል። በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው? በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። ሆኖም ግን የመንደር ውሎች አሁንም በብዙ ሰዎች ዘንድ ይሠራባቸዋል። ውልና ማስረጃ አገልግሎት ስላቆመ ብቻ ሳይሆን ድሮም ይሠራባቸዋል። የሚገርመው ፍርድ ቤትም በብዛት እነዚህን በመንደር ውል የተፈጣጠሙ አቤቱታዎች ይመለከታል። ለምን? የመንደር ውል ሕጋዊ ካልሆነ ለምን ፍርድ ቤት ይመለከተዋል? ለምን "ወዲያልኝ! ሲጀመር፣ ይሄ ሕጋዊ ውል አይደለም" ብሎ አሽቀንጥሮ አይጥለውም? ጠበቃ ሚካኤል "ሕግ በባህሪው አስተናጋጅ (Flexible) መሆን ስላለበት ነው" ይላሉ። ጉዳዩን ሲያብራሩም፣ የመንደር ውል ተዋዋዮች፣ 'አዎ የመንደር ውል አድርገናል' ብለው ሳይካካዱ የሚያነሱት ጉዳይ ውሉ የመንደር ውል ነውና 'ፎርምን ብቻ አላሟላም' ተብሎ ውድቅ አይደረግም የሚል መረዳት በፍርድ ቤት አካባቢ ስላለ ነው ይላሉ። ጠበቃ ታምራት በዚህ በአቶ ሚካኤል ነጥብ ይስማሙና ነገር ግን በመንደር ውል ሕጋዊነት ዙርያ ያለው ብዥታ "እኛ የሕግ ባለሞያዎችም እርግጠኛ ሆነን ምክር መስጠት እስክንቸገር የሚያደርሰን ሆኗል" ይላሉ፡፡ ነገሩን ሲያፍታቱት፣ በመርኅ ደረጃ አንድ ውል በመንደርም ይደረግ በውል አዋዋይ ፊትም ይደረግ፣ በቃልም ይደረግ ሕጋዊ መሆኑን በማስመር ይጀምራሉ። ሆኖም ሕግ የግድ በጽሑፍ መሆን አለባቸው የሚላቸው የውል ዓይነቶች አሉ። ከእነዚህ አንዱ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ነው። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት። አሁንም ጥያቄውን እንድገመው። ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው? ጠበቃ ታምራት "እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም" ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ላይ ቁርጥ፣ ጥርት ያለ መልስ እስከዛሬ ፍርድ ቤቶች አልሰጡም። የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ መስጠቱን ያወሳሉ። በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ "እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈጣጠሙ "ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል" ይላሉ ጠበቃ ታምራትና ጠበቃ ሚካኤል። ተዋዋዮች የመንደር ውልን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ? አሁን አሁን የተለመደው አሰራር ገዥና ሻጭ ውል የሚፈጽሙት በሁለት ዙር ነው። መጀመሪያ በመንደር ውል ይፈጣጠሙና ነው ወደ ሁለተኛ ውል አዋዋይ ዘንድ የሚመጡት። ብዙውን ጊዜ አንድ ቤት ስንት እንደተሸጠ በትክክል የሚታወቀውም በመንደር ውል ላይ እንጂ በትክክለኛው ውል ላይ አይደለም። ተዋዋዮች ወደ መንግሥት ተቋማት ሄደው የሚዋውሉት በ2ኛ ደረጃ ነው። ይህን ሲያደርጉም ብዙውን ጊዜ ዋጋ ቀንሰው ነው። "…ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ትክክለኛ ዋጋ ተናግረው የሚዋዋሉት። መንግሥት ቢቸግረው ተመን አውጥቶ ያስክፍላል። 6 በመቶ አሹራ ትከፍላለህ። የተዋዋልከው ከተመኑ ከፍ ካለ በተዋዋልከው ያስከፍላል። ዝቅ ካለ ደግሞ በተመኑ ያስከፍላል" ይላሉ ጠበቃ ታምራት። ጠበቃ ሚካኤል በበኩላቸው ይህ የሁለት ጊዜ ውል ብዙ ሰው ልብ ባይለውም አደጋ አለው ይላሉ። እንዴት? በሁለት ዓይነት ዋጋ መፈራረም የሚያመጣው አደጋ ስምምነት ሲፈርስ ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ውል ይፍረስልኝ ብሎ ፍርድ ቤት ሲሄድ ውል ይፈርሳል። ውል ሲፈርስ ደግሞ ወደነበረበት ነው የሚመለሰው። ሻጭ ገንዘብ ይመልሳል፣ ገዥ ንብረቱን ይመልሳል። በአሥር ሚሊዮን ብር የተሸጠ ቤት ውልና ማስረጃ ባረጋገጠው ውል፣ ፍርድ ቤት ተሂዶ ውል ቢፈርስ ተዋዋዮቹ ዋጋ ዝቅ አድርገው ስለሚዋዋሉ [ለምሳሌ 6ሚሊዮን ብር] ሻጭ ገንዘብ መልስ ይባላል። ይህን ጊዜ እንዲመልስ የሚገደደው በውልና ማስረጃ በገዛበትን ገንዘብ ነው። ይህ ማለት ገዥ 4 ሚሊዮን ብር መክሰሩም አይደል? ጠበቃ ታምራት በበኩላቸው ዜጎች የመንደር ውልን የሚመርጡት በዋናነት ቀላልና ምቹ ስለሆነ ነው ይላሉ። ሕጋዊው አሠራሩ ጥብቅ ነው፤ በርካታ ሰነዶች መሟላትን ይፈልጋል፤ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ ነው። ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያነሱት ካርታን ነው። "አይደለምና በገጠር፣ በአዲስ አበባ ስንቱ ቤት ነው የተሟላ ካርታ፣ የተሟላ ሰነድ ያለው? ስንቱ ከተማ ነው ማዘጋጃ ቤትስ ያለው?" ካርታው ስሙ ባንተ ነው ወይ? ዕዳና ዕገዳ የለበትም ወይ? ይሄ ሁሉ ነገር ከክፍለ ከተማ መጣራት አለበት። አቶ ታምራት "መጣራቱ በጎ ነው፣ ክፋት የለውም" ካሉ በኋላ፣ ነገር ግን ሰዎች በተለያየ ምክንያት የሚጠየቁትን ሁሉ ለማሟላት ይቸገራሉ ይላሉ። "አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ችግሩን እያወቁም ከነጉድለቱ ንብረቱን መግዛት ይፈልጋሉ። አትግዙ ልንላቸው ነው? ገዢ የፍርድ ቤት ዕግድ መኖሩን እያወቅኩ ልግዛ ቢልስ? ልንከለክለው ነው?" ልብ የማንላቸው የመንደር ውል አደጋዎች የመንደር ውል ሕጋዊ ነው አይደለም የሚለውን ሙግት እረፍት እንስጠውና ወደ አንድ ቁልፍ ነጥብ እንሻገር። የመንደር ውል ይዞብን የሚመጣው ፈተና ምንድነው? ሁለቱ ጠበቆች የነገሩንን በአጭር በአጭሩ እናካፍላችሁ። አንድ የቤት ገዥ በመንደር ውል ከተዋዋለ በኋላ ያን ይዞ ክፍለ ከተማ ሄዶ ስም ይዙርልኝ ቢል ተቀባይነት የለውም። አንድ ቤት ገዥ ቤቱን በመንደር ውል ገዝቶ አገር ሰላም ብሎ እየኖረ ድንገት የ3ኛ ወገን ጥያቄ ቤቱ ላይ ቢነሳ ለከፍተኛ ቀውስ ይጋለጣል። ይህም ከሻጭ ባል/ሚስት የሚመጣ፣ "ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ" የሚል ጥያቄ ሊሆን ይችላል። በመንደር ውል ያገባ/ያላገባ ሰነዶች ጋር ተያይዞም ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች አሉ። ኋላ ላይ በሚመጣ መቃቃር ፍቺ ቢኖር ገዢ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል። አንድ ቤት ገዥ አገር ሰላም ብሎ ቤት በመንደር ውል ገዝቶ እየኖረ፣ የሻጭ ባል/ሚስት ሽያጩ አይመለከተኝም ይፍረስልኝ ብትል/ቢል፣ ቤት ገዢ ከፍተኛ የፋይናንስና የሥነ ልቡና ጉዳት ይደርስበታል። የመንደር ውሉን ይዞ ፍርድ ቤት ቢሄድም አትስተናገድም ባይባልም፣ ከሻጭ ገንዘቡን መልሶ የማግኘት ዕድሉ ጠባብ ነው የሚሆነው። "እንዲህ ዓይነት በርካታ ጉዳዮች ያጋጥሙናል፣ ሽያጭ ውሉ አይመለከትኝ የሚሉ የትዳር አጋሮች ይኖራሉ። በቤተሰብ ሕጉ ከ500 ብር በላይ የሚደረግ ሽያጭ የሁለቱንም ይሁንታ ማግኘት አለበት፤ በዚህ የተነሳ የመንደር ውል ያልታሰበ ጣጣ ይዞ ይመጣል" ይላሉ አቶ ሚካኤል። ለምሳሌ መንግሥት ይህን ክልከላ ሲያነሳ ሥራ በቆመበት ወቅት በመንደር ውል የተዋዋላችሁ በሙሉ ውላችሁ ውድቅ ነው ቢል በርካታ ሰዎች ገንዘብ መልስልኝ-አልመልስም አተካራ ውስጥ ሊከታቸው ይችላል። ይህ ባይሆን እንኳ እነዚህ ሰዎች የመንደር ውላቸውን ለማጽደቅ ውልና ማስረጃ ሲሄዱ ገንዘብ በባንክ ያስተላለፋችሁበትን ሰነድ አምጡ ይባላሉ። በዚህን ጊዜ ሻጭ የተቀበለው ገንዘብ ተመናምኖበት ይሆናል። ገዥ ያን ከፍተኛ ገንዘብ በድጋሚ በባንክ ለማስተላለፍ ይቸገር ይሆናል። እጁ ላይ አይኖረውም ይሆናል። የቤት ዋጋ በየጊዜው ከመናሩ ጋር ተያይዞ ደግሞ ሻጭ በአዲሱ የዋጋ ተመን ሊማልልና ሐሳቡን ሊቀይር ይችላል። የከፈልኩን ቀብድ መልስልኝ አልመልስም ጣጣ ሊከተል ይችላል። በዚህ መካካድ መካከል የመንደር ውል ተይዞ ፍርድ ቤት ሲኬድ፣ ፍርድ ቤት ተዋዋዮቹ ውል ማድረጋቸውን እስካልተካካዱ ድረስ ያስተናግዳቸዋል። ነገር ግን ሻጭ በውሉ የሚገደደው በመንደር ውሉ የተመላከተውን የገንዘብ መጠን ብቻ ነው። በሐሰተኛ የብድር ውል የሚፈጸሙ የመንደር ውሎችም ዘርፈ ብዙ ጣጣን ያስከትላሉ። የብር የመግዛት ዋጋ መውረድና የቤት ዋጋ መጨመር ሻጭ በጊዜ ሂደት ሽያጩን ክዶ፣ ገንዘብ እንዲመልስ የሚያማልል ነው። "…ብቻ በአጠቃላይ በመንደር ውል ገዥው በራሱ ላይ የሚጋብዘው አደጋ የትየሌሌ ነው" ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። አቶ ታምራት በበኩላቸው በመንደር ውል ስንዋዋል አንዳንድ ጊዜ ይሆናሉ ብለን የማንጠብቃቸው ነገሮችም እንደሚከሰቱ መዘንጋት የለብንም ሲሉ ያስገነዝባሉ። "…ለምሳሌ በመሀል ሞት አለ። ከአገር መውጣት አለ። ውክልና ማንሳት አለ። በሰው ላይ ነገ ምን እንደሚደርስ ማን ያውቃል?" አቶ ሚካኤል በበኩላቸው፣ "በመንደር ውል የተፈጣጠመ ሻጭ ቢሞት የውርስ ጉዳይ ይከተላል፣ ጋብቻ ቢፈርስ የቤተሰብ ክርክር ውስጥ ይገባል፣ ወራሾች ቤቱ በሕገ ወጥ ውል የተፈጸመ ነው ብለው ሊያሳግዱት ይችላሉ። ጣጣው ብዙ ነው።" ጠበቃ ታምራት እንዲያውም ነገሩ ከዚህም የከፋ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ ጠቅሰዋል። "አንዳንድ መጥፎ ሰዎች ያጋጥማሉ። አንድን ቤት በመንደር ውል ለሁለት እና ለሦስት ሰው ከሸጡ በኋላ 'በሉ ሥራችሁ ያውጣችሁ' ብለው የሚሰወሩ።" ታዲያ ምን ይሻላል? ጠበቃ ሚካኤል፣ ምክራቸው አንድ ነው። "በቃ፣ የመንደር ውል ይቅርብን" የሚል። የግድ ከሆነስ? የግድ ከሆነም ውሉ መዘጋጀት ያለበት በሕግ አዋቂዎች ነው ይላሉ። ምክንያቱም አሁን ያሉ ውሎች ከጫፍ እስከ ጫፍ አንድና-ወጥ (standard) ናቸው። በጠበቃ ቢዘጋጁ ግን የሻጭና ገዢ ግዴታን በማያሻማ ሁኔታ ያስቀምጣሉ። ከዚያም ባሻገር ነገ ሊመጣ የሚችልን የሕግ ክፍተትን መድፈን ይቻላል። ጠበቃ ታምራት በበኩላቸው የውሎች ወጥ መሆን በራሱ ችግር አይደለም ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ወጥ ተደርገው የተበጁ ውሎች በየጊዜው ክፍተቶቻቸው እየተሞሉ መሄድ አለባቸው ባይ ናቸው። ዞሮ ዞሮ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የመንደር ውልን ጨርሶ ማቆም እንደማይቻል ያምናሉ። ተዋዋዮች አውቀው እስከገቡበት ድረስ አታድርጉት ሊባሉም አይችሉም። ሆኖም ውል ማዋዋል በውጭ አገር እንደሚደረገው በጠበቆች በኩል (ፕራይቬታይዝ) ቢደረግ የሚል አዲስ ሐሳብ አላቸው። ይህ ሐሳብ ራሱን ችሎ መፍታታት የሚፈልግ ስለሆነ በሌላ ጊዜ እንመለስበት ይሆናል። አሁን ጥያቄው የመንደር ውል ይቅርብን ወይስ? የሚለው ነው። አቶ ታምራት ሐሳባቸውን የሚጠቀልሉት በምሳሌ ነው። "የመንደር ውልን እንደ ሕክምና እንውሰደው። እጃችንን ሳንታጠብ ብንበላ ልንታመመም እንችላለን፤ ላንታመም እንችላለን። ታጥበን ብንበላ ግን ጥሩ ነው።" | የመንደር ውል ሕጋዊ ነው? በመንደር ውል ቤት ስንሻሻጥ ልብ ልንላቸው የሚገቡን ቁልፍ ነጥቦች የአገሪቱ አዋዋይ በተለምዶ 'ውልና ማስረጃ' የምንለው መሥሪያ ቤት ነው። የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ደግሞ ሙሉ ስሙ ነው። አሁን ግን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። ነገሩ ከወቅቱ የአገሪቱ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም። ከሐምሌ ወዲህ ይኸው እስከዛሬም አገልግሎት እየሰጠ ያለው በከፊል ነው። የተንቀሳቃሽ ንብረት ሽያጭን ጨርሶውኑ እያዋዋለ አይደለም። ይህን ተከትሎ ዜጎች በስፋት በመንደር ውል ተጠምደዋል። "ላልከዳህ-ላልክድህ ቃል አለኝ" እያሉ በየመንደሩ እየተፈጣጠሙ ነው። ለመሆኑ በውልና ማስረጃ ያልተረጋገጡ የመንደር ውሎች በሕግ ፊት ተቀባይነት አላቸው? በዚህ ጉዳይ ላይ ቢቢሲ ሁለት ከፍተኛ የሕግ አማካሪና ጠበቆችን አነጋግሯል። ጠበቃ ሚካኤል ተሾመ እና ጠበቃ ታምራት ኪዳነማርያም ይባላሉ። ሕጉን እያመሳከሩ፣ በሥራ ተሞክሮ የሚገጥሟቸውን እያጣቀሱ ጉዳዩን በየፈርጁ ይተነትኑልናል። ውል የሚጸናው ምን ሲሟላ ነው? አራት ነገር ካልተሟላ ውል አይጸናም ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። 1ኛ• ፈቃድ (Consent) ነው። ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ምን ማለት ነው ይሄ፣ በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም። 2ኛ• ተዋዋዮቹ በሕግ 'ችሎታ ያላቸው' መሆን አለባቸው። 'ችሎታ' የሕግ ትርጉሙ ሁለት ነው። የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤና ነው። 3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት። ለምሳሌ ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው። ሌላስ? 4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ 2 ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት መረጋገጥ፣ ሕጉ ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች መሟላት ማለት ነው። የሆነስ ሆኖ፣ የመንደር ውል ሕጋዊ ነው? ጠበቃ ሚካኤል፣ ለዚህ ጥያቄ በአጭሩ "ሕጋዊ አይደለም" የሚል መልስ ይሰጣሉ። ጠበቃ ታምራት ደግሞ "ነውም፣ አይደለምም" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ይህን ያሉበትን ምክንያት ወደ ኋላ ላይ ያስረዱናል። አሁን ወደ ጠበቃ ሚካኤል ነጥቦች እንመለስ። ጠበቃ ሚካኤል ለዚህ ድምዳሜ ያበቃቸውን ነጥብ ሲያስረዱ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም ይላሉ። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ይላሉ። ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው? ከሚለው እንጀምር። ጠበቃ ሚካኤል 'ሰነድ ለሁለት ዓላማ ነው የሚረጋገጠው' ብለው የክርክሩን ፍሬ ነገር ያሲዙናል። አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ። ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። "የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው" ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው? በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል። በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው? በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። ሆኖም ግን የመንደር ውሎች አሁንም በብዙ ሰዎች ዘንድ ይሠራባቸዋል። ውልና ማስረጃ አገልግሎት ስላቆመ ብቻ ሳይሆን ድሮም ይሠራባቸዋል። የሚገርመው ፍርድ ቤትም በብዛት እነዚህን በመንደር ውል የተፈጣጠሙ አቤቱታዎች ይመለከታል። ለምን? የመንደር ውል ሕጋዊ ካልሆነ ለምን ፍርድ ቤት ይመለከተዋል? ለምን "ወዲያልኝ! ሲጀመር፣ ይሄ ሕጋዊ ውል አይደለም" ብሎ አሽቀንጥሮ አይጥለውም? ጠበቃ ሚካኤል "ሕግ በባህሪው አስተናጋጅ (Flexible) መሆን ስላለበት ነው" ይላሉ። ጉዳዩን ሲያብራሩም፣ የመንደር ውል ተዋዋዮች፣ 'አዎ የመንደር ውል አድርገናል' ብለው ሳይካካዱ የሚያነሱት ጉዳይ ውሉ የመንደር ውል ነውና 'ፎርምን ብቻ አላሟላም' ተብሎ ውድቅ አይደረግም የሚል መረዳት በፍርድ ቤት አካባቢ ስላለ ነው ይላሉ። ጠበቃ ታምራት በዚህ በአቶ ሚካኤል ነጥብ ይስማሙና ነገር ግን በመንደር ውል ሕጋዊነት ዙርያ ያለው ብዥታ "እኛ የሕግ ባለሞያዎችም እርግጠኛ ሆነን ምክር መስጠት እስክንቸገር የሚያደርሰን ሆኗል" ይላሉ፡፡ ነገሩን ሲያፍታቱት፣ በመርኅ ደረጃ አንድ ውል በመንደርም ይደረግ በውል አዋዋይ ፊትም ይደረግ፣ በቃልም ይደረግ ሕጋዊ መሆኑን በማስመር ይጀምራሉ። ሆኖም ሕግ የግድ በጽሑፍ መሆን አለባቸው የሚላቸው የውል ዓይነቶች አሉ። ከእነዚህ አንዱ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ነው። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት። አሁንም ጥያቄውን እንድገመው። ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው? ጠበቃ ታምራት "እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም" ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ላይ ቁርጥ፣ ጥርት ያለ መልስ እስከዛሬ ፍርድ ቤቶች አልሰጡም። የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ መስጠቱን ያወሳሉ። በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ "እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈጣጠሙ "ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል" ይላሉ ጠበቃ ታምራትና ጠበቃ ሚካኤል። ተዋዋዮች የመንደር ውልን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ? አሁን አሁን የተለመደው አሰራር ገዥና ሻጭ ውል የሚፈጽሙት በሁለት ዙር ነው። መጀመሪያ በመንደር ውል ይፈጣጠሙና ነው ወደ ሁለተኛ ውል አዋዋይ ዘንድ የሚመጡት። ብዙውን ጊዜ አንድ ቤት ስንት እንደተሸጠ በትክክል የሚታወቀውም በመንደር ውል ላይ እንጂ በትክክለኛው ውል ላይ አይደለም። ተዋዋዮች ወደ መንግሥት ተቋማት ሄደው የሚዋውሉት በ2ኛ ደረጃ ነው። ይህን ሲያደርጉም ብዙውን ጊዜ ዋጋ ቀንሰው ነው። "…ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ትክክለኛ ዋጋ ተናግረው የሚዋዋሉት። መንግሥት ቢቸግረው ተመን አውጥቶ ያስክፍላል። 6 በመቶ አሹራ ትከፍላለህ። የተዋዋልከው ከተመኑ ከፍ ካለ በተዋዋልከው ያስከፍላል። ዝቅ ካለ ደግሞ በተመኑ ያስከፍላል" ይላሉ ጠበቃ ታምራት። ጠበቃ ሚካኤል በበኩላቸው ይህ የሁለት ጊዜ ውል ብዙ ሰው ልብ ባይለውም አደጋ አለው ይላሉ። እንዴት? በሁለት ዓይነት ዋጋ መፈራረም የሚያመጣው አደጋ ስምምነት ሲፈርስ ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ውል ይፍረስልኝ ብሎ ፍርድ ቤት ሲሄድ ውል ይፈርሳል። ውል ሲፈርስ ደግሞ ወደነበረበት ነው የሚመለሰው። ሻጭ ገንዘብ ይመልሳል፣ ገዥ ንብረቱን ይመልሳል። በአሥር ሚሊዮን ብር የተሸጠ ቤት ውልና ማስረጃ ባረጋገጠው ውል፣ ፍርድ ቤት ተሂዶ ውል ቢፈርስ ተዋዋዮቹ ዋጋ ዝቅ አድርገው ስለሚዋዋሉ [ለምሳሌ 6ሚሊዮን ብር] ሻጭ ገንዘብ መልስ ይባላል። ይህን ጊዜ እንዲመልስ የሚገደደው በውልና ማስረጃ በገዛበትን ገንዘብ ነው። ይህ ማለት ገዥ 4 ሚሊዮን ብር መክሰሩም አይደል? ጠበቃ ታምራት በበኩላቸው ዜጎች የመንደር ውልን የሚመርጡት በዋናነት ቀላልና ምቹ ስለሆነ ነው ይላሉ። ሕጋዊው አሠራሩ ጥብቅ ነው፤ በርካታ ሰነዶች መሟላትን ይፈልጋል፤ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ ነው። ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያነሱት ካርታን ነው። "አይደለምና በገጠር፣ በአዲስ አበባ ስንቱ ቤት ነው የተሟላ ካርታ፣ የተሟላ ሰነድ ያለው? ስንቱ ከተማ ነው ማዘጋጃ ቤትስ ያለው?" ካርታው ስሙ ባንተ ነው ወይ? ዕዳና ዕገዳ የለበትም ወይ? ይሄ ሁሉ ነገር ከክፍለ ከተማ መጣራት አለበት። አቶ ታምራት "መጣራቱ በጎ ነው፣ ክፋት የለውም" ካሉ በኋላ፣ ነገር ግን ሰዎች በተለያየ ምክንያት የሚጠየቁትን ሁሉ ለማሟላት ይቸገራሉ ይላሉ። "አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ችግሩን እያወቁም ከነጉድለቱ ንብረቱን መግዛት ይፈልጋሉ። አትግዙ ልንላቸው ነው? ገዢ የፍርድ ቤት ዕግድ መኖሩን እያወቅኩ ልግዛ ቢልስ? ልንከለክለው ነው?" ልብ የማንላቸው የመንደር ውል አደጋዎች የመንደር ውል ሕጋዊ ነው አይደለም የሚለውን ሙግት እረፍት እንስጠውና ወደ አንድ ቁልፍ ነጥብ እንሻገር። የመንደር ውል ይዞብን የሚመጣው ፈተና ምንድነው? ሁለቱ ጠበቆች የነገሩንን በአጭር በአጭሩ እናካፍላችሁ። አንድ የቤት ገዥ በመንደር ውል ከተዋዋለ በኋላ ያን ይዞ ክፍለ ከተማ ሄዶ ስም ይዙርልኝ ቢል ተቀባይነት የለውም። አንድ ቤት ገዥ ቤቱን በመንደር ውል ገዝቶ አገር ሰላም ብሎ እየኖረ ድንገት የ3ኛ ወገን ጥያቄ ቤቱ ላይ ቢነሳ ለከፍተኛ ቀውስ ይጋለጣል። ይህም ከሻጭ ባል/ሚስት የሚመጣ፣ "ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ" የሚል ጥያቄ ሊሆን ይችላል። በመንደር ውል ያገባ/ያላገባ ሰነዶች ጋር ተያይዞም ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች አሉ። ኋላ ላይ በሚመጣ መቃቃር ፍቺ ቢኖር ገዢ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል። አንድ ቤት ገዥ አገር ሰላም ብሎ ቤት በመንደር ውል ገዝቶ እየኖረ፣ የሻጭ ባል/ሚስት ሽያጩ አይመለከተኝም ይፍረስልኝ ብትል/ቢል፣ ቤት ገዢ ከፍተኛ የፋይናንስና የሥነ ልቡና ጉዳት ይደርስበታል። የመንደር ውሉን ይዞ ፍርድ ቤት ቢሄድም አትስተናገድም ባይባልም፣ ከሻጭ ገንዘቡን መልሶ የማግኘት ዕድሉ ጠባብ ነው የሚሆነው። "እንዲህ ዓይነት በርካታ ጉዳዮች ያጋጥሙናል፣ ሽያጭ ውሉ አይመለከትኝ የሚሉ የትዳር አጋሮች ይኖራሉ። በቤተሰብ ሕጉ ከ500 ብር በላይ የሚደረግ ሽያጭ የሁለቱንም ይሁንታ ማግኘት አለበት፤ በዚህ የተነሳ የመንደር ውል ያልታሰበ ጣጣ ይዞ ይመጣል" ይላሉ አቶ ሚካኤል። ለምሳሌ መንግሥት ይህን ክልከላ ሲያነሳ ሥራ በቆመበት ወቅት በመንደር ውል የተዋዋላችሁ በሙሉ ውላችሁ ውድቅ ነው ቢል በርካታ ሰዎች ገንዘብ መልስልኝ-አልመልስም አተካራ ውስጥ ሊከታቸው ይችላል። ይህ ባይሆን እንኳ እነዚህ ሰዎች የመንደር ውላቸውን ለማጽደቅ ውልና ማስረጃ ሲሄዱ ገንዘብ በባንክ ያስተላለፋችሁበትን ሰነድ አምጡ ይባላሉ። በዚህን ጊዜ ሻጭ የተቀበለው ገንዘብ ተመናምኖበት ይሆናል። ገዥ ያን ከፍተኛ ገንዘብ በድጋሚ በባንክ ለማስተላለፍ ይቸገር ይሆናል። እጁ ላይ አይኖረውም ይሆናል። የቤት ዋጋ በየጊዜው ከመናሩ ጋር ተያይዞ ደግሞ ሻጭ በአዲሱ የዋጋ ተመን ሊማልልና ሐሳቡን ሊቀይር ይችላል። የከፈልኩን ቀብድ መልስልኝ አልመልስም ጣጣ ሊከተል ይችላል። በዚህ መካካድ መካከል የመንደር ውል ተይዞ ፍርድ ቤት ሲኬድ፣ ፍርድ ቤት ተዋዋዮቹ ውል ማድረጋቸውን እስካልተካካዱ ድረስ ያስተናግዳቸዋል። ነገር ግን ሻጭ በውሉ የሚገደደው በመንደር ውሉ የተመላከተውን የገንዘብ መጠን ብቻ ነው። በሐሰተኛ የብድር ውል የሚፈጸሙ የመንደር ውሎችም ዘርፈ ብዙ ጣጣን ያስከትላሉ። የብር የመግዛት ዋጋ መውረድና የቤት ዋጋ መጨመር ሻጭ በጊዜ ሂደት ሽያጩን ክዶ፣ ገንዘብ እንዲመልስ የሚያማልል ነው። "…ብቻ በአጠቃላይ በመንደር ውል ገዥው በራሱ ላይ የሚጋብዘው አደጋ የትየሌሌ ነው" ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። አቶ ታምራት በበኩላቸው በመንደር ውል ስንዋዋል አንዳንድ ጊዜ ይሆናሉ ብለን የማንጠብቃቸው ነገሮችም እንደሚከሰቱ መዘንጋት የለብንም ሲሉ ያስገነዝባሉ። "…ለምሳሌ በመሀል ሞት አለ። ከአገር መውጣት አለ። ውክልና ማንሳት አለ። በሰው ላይ ነገ ምን እንደሚደርስ ማን ያውቃል?" አቶ ሚካኤል በበኩላቸው፣ "በመንደር ውል የተፈጣጠመ ሻጭ ቢሞት የውርስ ጉዳይ ይከተላል፣ ጋብቻ ቢፈርስ የቤተሰብ ክርክር ውስጥ ይገባል፣ ወራሾች ቤቱ በሕገ ወጥ ውል የተፈጸመ ነው ብለው ሊያሳግዱት ይችላሉ። ጣጣው ብዙ ነው።" ጠበቃ ታምራት እንዲያውም ነገሩ ከዚህም የከፋ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ ጠቅሰዋል። "አንዳንድ መጥፎ ሰዎች ያጋጥማሉ። አንድን ቤት በመንደር ውል ለሁለት እና ለሦስት ሰው ከሸጡ በኋላ 'በሉ ሥራችሁ ያውጣችሁ' ብለው የሚሰወሩ።" ታዲያ ምን ይሻላል? ጠበቃ ሚካኤል፣ ምክራቸው አንድ ነው። "በቃ፣ የመንደር ውል ይቅርብን" የሚል። የግድ ከሆነስ? የግድ ከሆነም ውሉ መዘጋጀት ያለበት በሕግ አዋቂዎች ነው ይላሉ። ምክንያቱም አሁን ያሉ ውሎች ከጫፍ እስከ ጫፍ አንድና-ወጥ (standard) ናቸው። በጠበቃ ቢዘጋጁ ግን የሻጭና ገዢ ግዴታን በማያሻማ ሁኔታ ያስቀምጣሉ። ከዚያም ባሻገር ነገ ሊመጣ የሚችልን የሕግ ክፍተትን መድፈን ይቻላል። ጠበቃ ታምራት በበኩላቸው የውሎች ወጥ መሆን በራሱ ችግር አይደለም ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ወጥ ተደርገው የተበጁ ውሎች በየጊዜው ክፍተቶቻቸው እየተሞሉ መሄድ አለባቸው ባይ ናቸው። ዞሮ ዞሮ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የመንደር ውልን ጨርሶ ማቆም እንደማይቻል ያምናሉ። ተዋዋዮች አውቀው እስከገቡበት ድረስ አታድርጉት ሊባሉም አይችሉም። ሆኖም ውል ማዋዋል በውጭ አገር እንደሚደረገው በጠበቆች በኩል (ፕራይቬታይዝ) ቢደረግ የሚል አዲስ ሐሳብ አላቸው። ይህ ሐሳብ ራሱን ችሎ መፍታታት የሚፈልግ ስለሆነ በሌላ ጊዜ እንመለስበት ይሆናል። አሁን ጥያቄው የመንደር ውል ይቅርብን ወይስ? የሚለው ነው። አቶ ታምራት ሐሳባቸውን የሚጠቀልሉት በምሳሌ ነው። "የመንደር ውልን እንደ ሕክምና እንውሰደው። እጃችንን ሳንታጠብ ብንበላ ልንታመመም እንችላለን፤ ላንታመም እንችላለን። ታጥበን ብንበላ ግን ጥሩ ነው።" | https://www.bbc.com/amharic/59633486 |
2health
| ስትወለድ በክብደት የዓለማችን ትንሿ ጨቅላ የነበረችው ከዓመት በኋላ ከሆስፒታል ወጣች | ስትወለድ ከአንድ ብርቱካን ያነሰ ክብደት ትመዝን የነበረችው የዓለማችን ጨቅላ ከ13 ወራት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቤቷ ገባች። እምቦቅቅላዋ በሲንጋፖር ሆስፒታል ባለፉት 13 ወራት በጽኑ ሕሙማን ክፍል ክትትል ሲደረግላት ቆይቷል። ዌክ ዩ ዥዋን ትባላለች። ስትወለድ የምትመዝነው 212 ግራም ነበር። ይህ ክብደት ማለት በአማካይ የአንድ ትንሽ ብርቱካን ክብደት ማለት ነው። ቁመቷ 24 ደግሞ ሴትቲ ሜትር ብቻ ነበር። አንድ ጤናማ ልጅ የሚወለደው በአማካይ ከ40 ሳምንታት ቆይታ በኋላ መሆኑ ይታወቃል። ይህቺ ልጅ የተወለደችው ግን ያለ ጊዜው በ25 ሳምንቷ ነበር። እስከዛሬ ስትወለድ የዓለማችን በኪሎ ትንሿ ትባል የነበረችው ልጅ አሜሪካዊት ነበረች። ይህች ልጅ ስትወለድ 245 ግራም ነበር የምትመዝነው። ይህ ክብረ ወሰን አሁን በሲንጋፖሯ ጨቅላ ተሻሽሏል። የዚህች ደቃቃ ልጅ እናት ልጇን የተገላገለቻት በቀዶ ህክምና ነበር። ለመውለድም ገና አራት ወራት ሲቀራት ነበር የተገላገለቻት። ከ13 ወራት ከፍተኛ ክትትል በኋላ አሁን የጨቅላዋ ክብደት 6.3 ኪሎ ግራም ሆኗል። የሲንጋፖር ብሔራዊ ሆስፒታል ይህቺ ልጅ በተወለደች ወቅት በሕይወት የመኖር ዕድሏ በጣም ጠባብ ነበር ይላል። በሆስፒታል ቆይታዋ በሕይወት እንድትቆይ የተለያዩ ሕክምናዎች እና የሕክምና ድጋፎች አስፈልገዋት ነበር። ዶክተሮች ጨቅላዋ እድገቷ አጥጋቢ በመሆኑ ከሆስፒታል እንድትወጣ መወሰኑን ተናግረዋል። ጨቅላዋ ዌክ ዩ ዥዋን አሁንም ቢሆን የከፋ የሳምባ ሕመም ያለባት ሲሆን ወደቤት ከተሰወደችም በኋላ ለመተንፈስ ድጋፍ ያስፍልጋታል ተብሏል። ሐኪሞች ጨቅላዋ ከሳምባ ሕመሟ እንደምታገግም ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል። የልጅቷ እናት ከዚህ ቀደም የወለዱት ልጅ ጤናማና መደበኛ ኪሎ የሚያሟላ ነበር። የዚህች ደቃቃ አራስ ልጅ የሆስፒታል ወጪ ከፍተኛ ሲሆን ገንዘቡን የሸፈኑት ግን ከሕዝብ በተሰበሰበ ዘመቻ ነው። ለዚህች በኪሎ ዝቅተኛ ለተባለችው የዓለማችን እንቦቀቅላ በአጭር ጊዜ 270ሺህ ዶላር ተሰብስቦላታል። | ስትወለድ በክብደት የዓለማችን ትንሿ ጨቅላ የነበረችው ከዓመት በኋላ ከሆስፒታል ወጣች ስትወለድ ከአንድ ብርቱካን ያነሰ ክብደት ትመዝን የነበረችው የዓለማችን ጨቅላ ከ13 ወራት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቤቷ ገባች። እምቦቅቅላዋ በሲንጋፖር ሆስፒታል ባለፉት 13 ወራት በጽኑ ሕሙማን ክፍል ክትትል ሲደረግላት ቆይቷል። ዌክ ዩ ዥዋን ትባላለች። ስትወለድ የምትመዝነው 212 ግራም ነበር። ይህ ክብደት ማለት በአማካይ የአንድ ትንሽ ብርቱካን ክብደት ማለት ነው። ቁመቷ 24 ደግሞ ሴትቲ ሜትር ብቻ ነበር። አንድ ጤናማ ልጅ የሚወለደው በአማካይ ከ40 ሳምንታት ቆይታ በኋላ መሆኑ ይታወቃል። ይህቺ ልጅ የተወለደችው ግን ያለ ጊዜው በ25 ሳምንቷ ነበር። እስከዛሬ ስትወለድ የዓለማችን በኪሎ ትንሿ ትባል የነበረችው ልጅ አሜሪካዊት ነበረች። ይህች ልጅ ስትወለድ 245 ግራም ነበር የምትመዝነው። ይህ ክብረ ወሰን አሁን በሲንጋፖሯ ጨቅላ ተሻሽሏል። የዚህች ደቃቃ ልጅ እናት ልጇን የተገላገለቻት በቀዶ ህክምና ነበር። ለመውለድም ገና አራት ወራት ሲቀራት ነበር የተገላገለቻት። ከ13 ወራት ከፍተኛ ክትትል በኋላ አሁን የጨቅላዋ ክብደት 6.3 ኪሎ ግራም ሆኗል። የሲንጋፖር ብሔራዊ ሆስፒታል ይህቺ ልጅ በተወለደች ወቅት በሕይወት የመኖር ዕድሏ በጣም ጠባብ ነበር ይላል። በሆስፒታል ቆይታዋ በሕይወት እንድትቆይ የተለያዩ ሕክምናዎች እና የሕክምና ድጋፎች አስፈልገዋት ነበር። ዶክተሮች ጨቅላዋ እድገቷ አጥጋቢ በመሆኑ ከሆስፒታል እንድትወጣ መወሰኑን ተናግረዋል። ጨቅላዋ ዌክ ዩ ዥዋን አሁንም ቢሆን የከፋ የሳምባ ሕመም ያለባት ሲሆን ወደቤት ከተሰወደችም በኋላ ለመተንፈስ ድጋፍ ያስፍልጋታል ተብሏል። ሐኪሞች ጨቅላዋ ከሳምባ ሕመሟ እንደምታገግም ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል። የልጅቷ እናት ከዚህ ቀደም የወለዱት ልጅ ጤናማና መደበኛ ኪሎ የሚያሟላ ነበር። የዚህች ደቃቃ አራስ ልጅ የሆስፒታል ወጪ ከፍተኛ ሲሆን ገንዘቡን የሸፈኑት ግን ከሕዝብ በተሰበሰበ ዘመቻ ነው። ለዚህች በኪሎ ዝቅተኛ ለተባለችው የዓለማችን እንቦቀቅላ በአጭር ጊዜ 270ሺህ ዶላር ተሰብስቦላታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58142407 |
5sports
| ኮሮናቫይረስ፡ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ ይችላሉ | የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሊጉ በቅርቡ ጀምሮ በዝግ ስታዲየም ቢጫወቱም እንኳን ለአገር ውስጥና ለዓለማቀፍ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ቢቢሲ ስፖርት ባገኘው መረጃ መሰረት ሊጉ ከነጭራሹ የሚቋረጥ ከሆነ አልያም ከሊጉ የሚወርዱ ቡድኖች የሚኖሩ ካልሆነ ክለቦቹ ከተገለጸው ገንዘብ ተጨማሪ ሊከፍሉም ይችላሉ። • የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በገለልተኛ ሜዳ ሊጠናቀቅ ይሆን? • ኮሮናቫይረስን ለማሸነፍ ከኢቦላ በሽታ ምን ልምድ መውሰድ ይቻላል? የፕሪምረየር ሊግ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ማስቀጠል በሚቻለበት ሁኔታ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ትናንት አስቀጥለዋል። የ2019/20 ወድድር ዘመን 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። እነዚህን ጨዋታዎች እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች ላለፉት ሳምንታት የቪድዮ ስብሰባ ሲያደርጉ ነበር። የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈለጋሉ ነው የሚሉት። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው ተብሏል። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው ተብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። ሁሉም የሊጉ ክለቦች የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ተስማምተዋል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ተብሏል። የገንዘብ ክፍያው የተጠየቀው የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በታሰበላቸው ጊዜ ባለመካሄዳቸው ነው። በተጨማሪም ሊጉ የሚቀጥል ቢሆን እንኳን ጨዋታዎቹ ያለ ተመልካች መካሄዳቸውና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር ስምምነት ከተደረሰበት ጊዜ ውጪ ስለሚካሄዱ ነው። • በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች • በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች የፕሪምየር ሊግ ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪቻርድ ማስተርስ በቅርቡ እንደገለጹት ደግሞ የዘንድሮው ሊግ የሚቋረት ከሆነ ክለቦች በአጠቃላይ እስከ 1 ቢሊየን ፓውንድ ኪሳራ ሊያጋጥማቸው ይችላል። ገለልተኛ ሜዳዎች ላይ ጨዋታዎቹን መቀጠል በሚለው ሀሳብ አንዳንድ ክለቦች አልተስማሙም። የሊጉ ኃላፊዎችም ቡድኖቹን ለማሳመንና በተቻለ መጠን ጨዋታዎቹን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለማስጀመር እየሞከሩ ነው። እስካሁን ዋትፎርድ፣ አስቶን ቪላ እና ብራይተን ጨዋታዎቹን በገለልተኛ ሜዳ ማካሄድ የሚለውን ሀሳብ በይፋ የተቃወሙ ሲሆን በሜዳቸው ደህንነቱ የተጨበቀ ጨዋታ ማካሄድ እንደሚችሉ መንግስትን ማሳመን ይጠበቅባቸዋል። የሊቨርፑል ከተማ ከንቲባ ደግሞ ጨዋታዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ተካሂደውም ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ደጋፊዎች በአንፊል ስታዲየም ዙሪያ ተሰባስበው ደስታቸውን ሊገልጹ እንደሚችሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ ይችላሉ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሊጉ በቅርቡ ጀምሮ በዝግ ስታዲየም ቢጫወቱም እንኳን ለአገር ውስጥና ለዓለማቀፍ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ቢቢሲ ስፖርት ባገኘው መረጃ መሰረት ሊጉ ከነጭራሹ የሚቋረጥ ከሆነ አልያም ከሊጉ የሚወርዱ ቡድኖች የሚኖሩ ካልሆነ ክለቦቹ ከተገለጸው ገንዘብ ተጨማሪ ሊከፍሉም ይችላሉ። • የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በገለልተኛ ሜዳ ሊጠናቀቅ ይሆን? • ኮሮናቫይረስን ለማሸነፍ ከኢቦላ በሽታ ምን ልምድ መውሰድ ይቻላል? የፕሪምረየር ሊግ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ማስቀጠል በሚቻለበት ሁኔታ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ትናንት አስቀጥለዋል። የ2019/20 ወድድር ዘመን 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። እነዚህን ጨዋታዎች እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች ላለፉት ሳምንታት የቪድዮ ስብሰባ ሲያደርጉ ነበር። የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈለጋሉ ነው የሚሉት። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው ተብሏል። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው ተብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። ሁሉም የሊጉ ክለቦች የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ተስማምተዋል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ተብሏል። የገንዘብ ክፍያው የተጠየቀው የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በታሰበላቸው ጊዜ ባለመካሄዳቸው ነው። በተጨማሪም ሊጉ የሚቀጥል ቢሆን እንኳን ጨዋታዎቹ ያለ ተመልካች መካሄዳቸውና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር ስምምነት ከተደረሰበት ጊዜ ውጪ ስለሚካሄዱ ነው። • በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች • በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች የፕሪምየር ሊግ ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪቻርድ ማስተርስ በቅርቡ እንደገለጹት ደግሞ የዘንድሮው ሊግ የሚቋረት ከሆነ ክለቦች በአጠቃላይ እስከ 1 ቢሊየን ፓውንድ ኪሳራ ሊያጋጥማቸው ይችላል። ገለልተኛ ሜዳዎች ላይ ጨዋታዎቹን መቀጠል በሚለው ሀሳብ አንዳንድ ክለቦች አልተስማሙም። የሊጉ ኃላፊዎችም ቡድኖቹን ለማሳመንና በተቻለ መጠን ጨዋታዎቹን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለማስጀመር እየሞከሩ ነው። እስካሁን ዋትፎርድ፣ አስቶን ቪላ እና ብራይተን ጨዋታዎቹን በገለልተኛ ሜዳ ማካሄድ የሚለውን ሀሳብ በይፋ የተቃወሙ ሲሆን በሜዳቸው ደህንነቱ የተጨበቀ ጨዋታ ማካሄድ እንደሚችሉ መንግስትን ማሳመን ይጠበቅባቸዋል። የሊቨርፑል ከተማ ከንቲባ ደግሞ ጨዋታዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ተካሂደውም ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ደጋፊዎች በአንፊል ስታዲየም ዙሪያ ተሰባስበው ደስታቸውን ሊገልጹ እንደሚችሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-52629957 |
0business
| በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ | በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የትምህርት ክፍያ ጭማሪ በሚፈፅሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በርካታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተረድቻለሁ ብሏል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና ምዝገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ባለስልጣን ባወጣዉ የማስፈጸሚያ ማኑዋል መስረት እየሰሩ አይደለም ብሏል። በአሁኑ ወቅት ያለውን ወሳኝና አስቸጋሪ ወቅት መሆኑን አስታውቆ ይህንንም በጋራ ለማለፍ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል። "አሁን ባለንበት ወቅት ተደጋግፈን የምናልፍበት እንጂ አንዱ በሌላዉ ላይ ጫና የሚፈጥርበት አይደለም" ብሏል። በዚህም መሰረት የግል ትምህርት ቤት ከደንበኞቻቸው ጋር በመነጋገር እና በመግባባት እንዲሰሩ አሳስቧል። ነገር ግን ይህንን ተላልፈው በሚሰሩና በሚቀርበው ጥቆማ መሰረት ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ቢሮ ለመውሰድም እንደሚገደድ አሳስቧል። ከዚህ ቀደም ለቢሮው እና ለወላጅ ምላሽ በመስጠታቸዉ እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰዳቸዉ በ41 ትምህርት ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረዉ እገዳ እንዲነሳላቸዉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን አስታውሷል። ቢሮው የግል ትምህርት ተቋማቱ የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ እና ለከተማው ነዋሪ የስራ እድል ከመፍጠር ረገድ ሚናቸው ላቅ ያለ ነው ብሏል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተቀመጡትን መመሪያዎች በማክበር ላከናወኑት ተግባርም እውቅና ሰጥቷል። | በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የትምህርት ክፍያ ጭማሪ በሚፈፅሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በርካታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተረድቻለሁ ብሏል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና ምዝገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ባለስልጣን ባወጣዉ የማስፈጸሚያ ማኑዋል መስረት እየሰሩ አይደለም ብሏል። በአሁኑ ወቅት ያለውን ወሳኝና አስቸጋሪ ወቅት መሆኑን አስታውቆ ይህንንም በጋራ ለማለፍ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል። "አሁን ባለንበት ወቅት ተደጋግፈን የምናልፍበት እንጂ አንዱ በሌላዉ ላይ ጫና የሚፈጥርበት አይደለም" ብሏል። በዚህም መሰረት የግል ትምህርት ቤት ከደንበኞቻቸው ጋር በመነጋገር እና በመግባባት እንዲሰሩ አሳስቧል። ነገር ግን ይህንን ተላልፈው በሚሰሩና በሚቀርበው ጥቆማ መሰረት ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ቢሮ ለመውሰድም እንደሚገደድ አሳስቧል። ከዚህ ቀደም ለቢሮው እና ለወላጅ ምላሽ በመስጠታቸዉ እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰዳቸዉ በ41 ትምህርት ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረዉ እገዳ እንዲነሳላቸዉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን አስታውሷል። ቢሮው የግል ትምህርት ተቋማቱ የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ እና ለከተማው ነዋሪ የስራ እድል ከመፍጠር ረገድ ሚናቸው ላቅ ያለ ነው ብሏል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተቀመጡትን መመሪያዎች በማክበር ላከናወኑት ተግባርም እውቅና ሰጥቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58391132 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ ስንት ተስፋ ሰጪ የኮቪድ-19 ክትባቶች ተገኝተዋል? | የተለያዩ ተቋሞች የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት መቃረባቸውን እያስታወቁ ነው። ይህም ለመላው ዓለም ተስፋ የሰጠ ዜና ሆኗል። ከሳምንት በፊት ፋይዘር እና ባዮቴክ የተባሉ ተቋሞች ውጤታማነቱ አስተማማኝ የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሞዴርና የተባለ ድርጅት ውጤታማ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። በኦክስፎርድ የሚካሄደው የክትባት ምርምር በ60ዎቹ እና 70ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከማዳበር አንጻር ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል። ሌለው በክትባት ምርምር ውጤታማ እየሆነ የሚገኘው የቤልጄሙ ጃንሰን ሲሆን፤ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ይገኛል። ክትባት ሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም እንዲያዳብር በማገዝ፤ ሕይወት ወደቀደመው ገጽታ እንዲመለስ ይረዳል። ሰዎች በወረርሽኙ እንዳይያዙም ያግዛል። ወይም ደግሞ የበሽታውን አደገኛንት ይቀንሳል። ክትባቶቹ ምን ልዩነት አላቸው? ክትባት የሚሠራው ሰውነት በሽታውን የሚከላከልበትን አቅም ለማዳበር ሲሆን፤ ሰውነት ቫይረሱ እንግዳና አደገኛ እንደሆነ ተገንዝቦ እንዲዋጋ ያግዛል። ፋይዘር እና ባዮቴክ እንዲሁም ሞዴርና ያገኙት አርኤንኤ የተባለ ክትባት ነው። ይህም የቫይረሱን የዘረ መል ቅንጣቶች ሰውነት ውስጥ በመክተት፤ ሰውነት በሽታውን ለይቶ የመከላከል አቅም እንዲያዳብር የሚደረግበት መንገድ ነው። በጃንሰን የሚሠራው ክትባት ደግሞ ዘረ መሉ የተሻሻለ የጉንፋን ቫይረስን በመጠቀም፣ ኮሮናቫይረስን እንዲመስል አድርጎ ጎጂነቱን ለመቀነስ ይሞክራል። በዚህ መንገድ ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም አዳብሮ ወረርሽኙን እንዲከላከል ይደረጋል። በኦክስፎር እና በሩስያ የሚሠሩት ክትባቶች ጉዳት አልባ ቫይረስን ዝንጀሮ ላይ ይሞክራሉ። ከዚያም ዘረ መሉን አሻሽሎ ከኮሮናቫይረስ ጋር እንዲመሳሰል በማድረግ ውጤት ለማግኘት ይሞከራል። በቻይና የተሠሩት ሁለት ክትባቶች የተጠቀሙት ራሱን ቫይረሱን ነው። ቫይረሱ ጉዳት እንዳያስከትል ካከሰሙት በኋላ ነው ምርምሩ የተሠራው። ሰዎችን ለቫይረሱ በማጋለጥ የሚሠሩ ምርምሮች የትኛው ክትባት የተሻለ ውጤታማ እንደሆነ ለመረዳት ያግዛሉ። ክትባት መቼ እናገኛለን? ፋይዘር በዚህ ዓመት መጨረሻ 50 ሚሊዮን ጠብታዎችን በመላው ዓለም እንደሚያከፋፍል ተናግሯል። በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ 1.3 ቢሊዮን ጠብታዎች ይገኛሉ። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንደም በዓመቱ መጨረሻ 10 ሚሊዮን የክትባት ጠብታ እንደምታገኝ ይጠበቃል። ተጨማሪ 30 ሚሊዮን ክትባቶች ማዘዟንም አስታውቃለች። ሌለው ጥያቄ ክትባቱን በቅድሚያ ማን ያገኛል? የሚለው ነው። ይህ የሚወሰነው ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በሚሰራጭባቸው እና የበለጠ ውጤታማ በሆነባቸው አካባቢዎች ነው። ዩናይትድ ኪንግደም በቅድሚያ ክትባቱን የምትሰጠው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑት በእድሜ የገፉ ሰዎችና እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ነው። ክትባቱ ውጤታማ መሆኑ የሚታወቀው ሁሉም የሙከራ ደረጃዎች ታልፈው ክትባቱ በሽታን እንደሚከላከል ወይም በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ ሲታወቅ ነው። ክትባቶች ፍቃድ አግኝተው፤ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ጠብታዎች መመረትም አለባቸው። ቫይረሱን ከምድር ላይ ለማስወገድ ከ60 እስከ 70 የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በሽታውን የመካከል አቅም ማዳበር አለበት። | ኮሮናቫይረስ ፡ ስንት ተስፋ ሰጪ የኮቪድ-19 ክትባቶች ተገኝተዋል? የተለያዩ ተቋሞች የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት መቃረባቸውን እያስታወቁ ነው። ይህም ለመላው ዓለም ተስፋ የሰጠ ዜና ሆኗል። ከሳምንት በፊት ፋይዘር እና ባዮቴክ የተባሉ ተቋሞች ውጤታማነቱ አስተማማኝ የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሞዴርና የተባለ ድርጅት ውጤታማ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። በኦክስፎርድ የሚካሄደው የክትባት ምርምር በ60ዎቹ እና 70ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከማዳበር አንጻር ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል። ሌለው በክትባት ምርምር ውጤታማ እየሆነ የሚገኘው የቤልጄሙ ጃንሰን ሲሆን፤ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ይገኛል። ክትባት ሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም እንዲያዳብር በማገዝ፤ ሕይወት ወደቀደመው ገጽታ እንዲመለስ ይረዳል። ሰዎች በወረርሽኙ እንዳይያዙም ያግዛል። ወይም ደግሞ የበሽታውን አደገኛንት ይቀንሳል። ክትባቶቹ ምን ልዩነት አላቸው? ክትባት የሚሠራው ሰውነት በሽታውን የሚከላከልበትን አቅም ለማዳበር ሲሆን፤ ሰውነት ቫይረሱ እንግዳና አደገኛ እንደሆነ ተገንዝቦ እንዲዋጋ ያግዛል። ፋይዘር እና ባዮቴክ እንዲሁም ሞዴርና ያገኙት አርኤንኤ የተባለ ክትባት ነው። ይህም የቫይረሱን የዘረ መል ቅንጣቶች ሰውነት ውስጥ በመክተት፤ ሰውነት በሽታውን ለይቶ የመከላከል አቅም እንዲያዳብር የሚደረግበት መንገድ ነው። በጃንሰን የሚሠራው ክትባት ደግሞ ዘረ መሉ የተሻሻለ የጉንፋን ቫይረስን በመጠቀም፣ ኮሮናቫይረስን እንዲመስል አድርጎ ጎጂነቱን ለመቀነስ ይሞክራል። በዚህ መንገድ ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም አዳብሮ ወረርሽኙን እንዲከላከል ይደረጋል። በኦክስፎር እና በሩስያ የሚሠሩት ክትባቶች ጉዳት አልባ ቫይረስን ዝንጀሮ ላይ ይሞክራሉ። ከዚያም ዘረ መሉን አሻሽሎ ከኮሮናቫይረስ ጋር እንዲመሳሰል በማድረግ ውጤት ለማግኘት ይሞከራል። በቻይና የተሠሩት ሁለት ክትባቶች የተጠቀሙት ራሱን ቫይረሱን ነው። ቫይረሱ ጉዳት እንዳያስከትል ካከሰሙት በኋላ ነው ምርምሩ የተሠራው። ሰዎችን ለቫይረሱ በማጋለጥ የሚሠሩ ምርምሮች የትኛው ክትባት የተሻለ ውጤታማ እንደሆነ ለመረዳት ያግዛሉ። ክትባት መቼ እናገኛለን? ፋይዘር በዚህ ዓመት መጨረሻ 50 ሚሊዮን ጠብታዎችን በመላው ዓለም እንደሚያከፋፍል ተናግሯል። በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ 1.3 ቢሊዮን ጠብታዎች ይገኛሉ። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንደም በዓመቱ መጨረሻ 10 ሚሊዮን የክትባት ጠብታ እንደምታገኝ ይጠበቃል። ተጨማሪ 30 ሚሊዮን ክትባቶች ማዘዟንም አስታውቃለች። ሌለው ጥያቄ ክትባቱን በቅድሚያ ማን ያገኛል? የሚለው ነው። ይህ የሚወሰነው ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በሚሰራጭባቸው እና የበለጠ ውጤታማ በሆነባቸው አካባቢዎች ነው። ዩናይትድ ኪንግደም በቅድሚያ ክትባቱን የምትሰጠው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑት በእድሜ የገፉ ሰዎችና እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ነው። ክትባቱ ውጤታማ መሆኑ የሚታወቀው ሁሉም የሙከራ ደረጃዎች ታልፈው ክትባቱ በሽታን እንደሚከላከል ወይም በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ ሲታወቅ ነው። ክትባቶች ፍቃድ አግኝተው፤ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ጠብታዎች መመረትም አለባቸው። ቫይረሱን ከምድር ላይ ለማስወገድ ከ60 እስከ 70 የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በሽታውን የመካከል አቅም ማዳበር አለበት። | https://www.bbc.com/amharic/news-55003274 |
5sports
| ሊቨርፑል ከ ማድሪድ፡ ታላቁ የአውሮፓ እግር ኳስ ፍልሚያ | ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የፈረንሳይዋ ዋና ከተማ ፓሪስ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የኃያላኑን ሪያል ማድሪድና ሊቨርፑል ፍልሚያ ታስተናግዳለች። ሁለቱ ቡድኖች ከአራት ዓመታት በፊት በዚሁ መድረክ ለፍጻሜ ተገናኝተው ማድሪዶች ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው። እግር ኳስ የሚወድ ማንኛውም ሰው ይህ ጨዋታ እንዲያመልጠው አይፈልግም። እግር ኳስ ለምኔ የሚሉት እንኳን ስለነዚህ ቡድኖች ፍልሚያ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሰምተዋል። በአውሮፓ ቻምፒየንስ ታሪክ ዋንጫውን 13 ጊዜ በማንሳት ተወዳዳሪ የሌላቸው ማድሪዶች ስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ከቻሉት ሊቨርፑሎች ጋር ነው የሚፋለሙት። የስፔን ኃያላኑ ማድሪዶች በዘንድሮው ውድድር ከምድብ ድልድል ጀምሮ አበቃላቸው እየተባለ ነው እዚህ የደረሱት። ቼልሲን፣ ፒኤስጂን እንዲሁም ለዋንጫው ለማለፍ ደግሞ ማንቸስተር ሲቲን ባለቀ ሰዓት ባስቆጠሯቸው ግቦች በመታገዝ ነው እዚህ የደረሱት። አጥቂው ካሪም ቤንዜማ ከምን ጊዜው በበለጠ በምርጥ አቋም ላይ ይገኛል። በዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ 15 ግቦችን በማስቆጠር ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ቤንዜማ፣ በስፔን ላሊጋም ቢሆን 27 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ነው የጨረሰው። ሌላኛው የቡድን አጋሩ ቪኒሺየስ ጁኒየርም ቢሆን እንደ ዘንድሮ ብዙ ግቦችን አስቆጥሮ አያውቅም። በዛሬው ምሽት ጨዋታ እነዚህ ኮከቦች የሊቨርፑልን የተከላካይ መስመር በእጅጉ እንደሚፈትኑ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የሊቨርፑሉ አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን በስታ ዴ ፍራንስ ስታዲየም “ማድሪድን ዝም እናሰኛለን” ሲል ተደምጧል። በዘንድሮው ውድድር ኤፍኤ ካፕ እና ካራባዎ ካፕ ያሸነፉት ሊቨርፑሎች በፕሪምየር ሊጉ ዋንጫውን በማንቸስተር ሲቲ ተነጥቀዋል። አራት ዋንጫ ለማሸነፍ አልመው የነበሩት አሰልጣኙ የርገን ክሎፕ አሁን ላይ የመጨረሻ ተስፋቸው ቻምፒየንስ ሊግ ሆኗል። የርገን ክሎፕ ስለቡድናቸው ስብስብ ሲናገሩ ይህ ቡድን በእውነት ልዩ ነው ብለዋል። ዋንጫውን አሸንፈው ደጋፊዎቻቸውን በደስታ ለማስፈንጠዝ መዘጋጀታቸውን አክለዋል። ስለጨዋታው ተጠይቆ የነበረው የማድሪዱ ቤንዜማ ሊቨርፑሎች ምናልባት ይህንን ዋንጫ ያሸነፉ ያህል ሊያስቡ ይችላሉ። እኛም እሱን ነው የምንፈልገው ብሏል። አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ በበኩላቸው የዓመታት ልምድ ባላቸው ሞድሪች እና ክሩዝ የሚመራው የመሀል ሜዳው ቤንዜማ እና ቪኒሺየስ ሲጨመሩበት ቡድናቸው አስፈሪ እንደሚሆን ዝተዋል። ከአራት ዓመት በፊት ሊቨርፑል በማድሪድ በፍጻሜው ሲሸነፍ ተጎድቶ የወጣው ሞሐመድ ሳላህ በዚህ ፍልሚያ ግብ ማስቆጠር እንደሚፈልግ ተናግሯል። ማድሪድ ለዋንጫው ማለፉን ሳያረጋግጥ በፊት እንኳን በፍጻሜው ማድሪድን መግጠም እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ተናግሮ ነበር። በቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ሊቨርፑል ከ ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከአራት ዓመታት በፊት እአአ 2018 ሁሉቱ ኃያል ቡድኖች ለፍጻሜ ተጋጥመው ነበር። በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ የሊቨርፑሉ ኮከብ ሞ ሳላህ የተፈጸመበትን ጉዳት ተከትሎ ከሜዳ ወጣ። ይህም ለሊቨርፑል ትልቅ ጉዳት ነበር። ከዚያም የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ሎሪስ ካሪየስ ቡድኑን ትልቅ ዋጋ ያስከፈሉ ሁለት ጥፋቶችን ሰራ። የመጨረሻም ማድሪድ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ሊቨርፑልን መርታት ቻለ። ሊቨርፑሎች ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ግን ሌላ ቀን ነው እያሉ ነው። የእንግሊዙ 'ዴይሊ ሜይል ኦንላይ' ከሊቨርፑል አምበል ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ በስፋት አስነብቧል። ጆርዳን ሄንደርሰን በስታ ዴ ፍራንስ ስታዲየም “ማድሪድን ዝም እናሰኛለን” ብሏል። የሊቨርፑሉ አሰልጠኝ የርገን ክሎፕ ደግሞ በቡድናቸው ስብስብ መተማመን እንዳላቸው ለቢቢሲ ብሬክፋት ተናግረዋል። ክሎፕ “ይህ ቡድን በእውነት ልዩ ነው” በማለት የቡድን አባሎቻቸውን አሞካሽተዋል። ማድሪድ ልዩ አቋም ላይ ይገኛል። ጎል አዳኙ ካሪም ቤንዜማ ከመቼም ጊዜ በላይ ድንቅ አቋም ላይ ነው። ማድሪድ ከእዚህ የፍጻሜ ውድድር የደረሰው በፒኤስ ጂ፣ ቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ ቀድሞ የተያዘበትን ብልጫ ቀልብሶ ነው። የስፔኑ እውቅ ጋዜጣ 'ማርካ' ቤንዜማን በፊት ገጽ አውጥቶታል። ለማድሪዱ አሰልጣኝ አንቼሎቲም ቢሆን የነገው ጨዋታ ሊቨርፑልን የሚበቀሉበት አጋጣሚን ይፈጥርላቸዋል። እአአ 2005 ላይ በቱርክ ኢስታንቡል በነበረው የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ፣ ሊቨርፑል ከኤስ ሚላን መገናኘታቸው ይታወሳል። በዚያ ጨዋታ ሊቨርፑል 3ለ0 ከመመራት ተነስቶ ኤስ ሚላንን ሲያሸንፍ አንቼሎቲ የኤስ ሚላን አሰልጣኝ ነበሩ። በነገው ጨዋታ ደግሞ ከ90ኛው ደቂቃ በኋላ ሊቨርፑል የበላይነቱን ይዞ ያጠናቅቃል የሚለው ግምት ሚዛን ደፍቷል። ሊቨርፑል 46 በመቶ የማሸነፍ ዕድል ተሰጥቶታል። ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን ሊረታ የሚችልበት አጋጣሚ ደግሞ 28 በመቶ የተገመተ ሲሆን፣ 26 በመቶ ጨዋታው ከ90ኛው ደቂቃ መጠናቀቅ በኋላ ሁለቱ ቡድኖች አቻ ይሆናሉ ተብሎ ተገምቷል። | ሊቨርፑል ከ ማድሪድ፡ ታላቁ የአውሮፓ እግር ኳስ ፍልሚያ ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የፈረንሳይዋ ዋና ከተማ ፓሪስ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የኃያላኑን ሪያል ማድሪድና ሊቨርፑል ፍልሚያ ታስተናግዳለች። ሁለቱ ቡድኖች ከአራት ዓመታት በፊት በዚሁ መድረክ ለፍጻሜ ተገናኝተው ማድሪዶች ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው። እግር ኳስ የሚወድ ማንኛውም ሰው ይህ ጨዋታ እንዲያመልጠው አይፈልግም። እግር ኳስ ለምኔ የሚሉት እንኳን ስለነዚህ ቡድኖች ፍልሚያ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሰምተዋል። በአውሮፓ ቻምፒየንስ ታሪክ ዋንጫውን 13 ጊዜ በማንሳት ተወዳዳሪ የሌላቸው ማድሪዶች ስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ከቻሉት ሊቨርፑሎች ጋር ነው የሚፋለሙት። የስፔን ኃያላኑ ማድሪዶች በዘንድሮው ውድድር ከምድብ ድልድል ጀምሮ አበቃላቸው እየተባለ ነው እዚህ የደረሱት። ቼልሲን፣ ፒኤስጂን እንዲሁም ለዋንጫው ለማለፍ ደግሞ ማንቸስተር ሲቲን ባለቀ ሰዓት ባስቆጠሯቸው ግቦች በመታገዝ ነው እዚህ የደረሱት። አጥቂው ካሪም ቤንዜማ ከምን ጊዜው በበለጠ በምርጥ አቋም ላይ ይገኛል። በዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ 15 ግቦችን በማስቆጠር ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ቤንዜማ፣ በስፔን ላሊጋም ቢሆን 27 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ነው የጨረሰው። ሌላኛው የቡድን አጋሩ ቪኒሺየስ ጁኒየርም ቢሆን እንደ ዘንድሮ ብዙ ግቦችን አስቆጥሮ አያውቅም። በዛሬው ምሽት ጨዋታ እነዚህ ኮከቦች የሊቨርፑልን የተከላካይ መስመር በእጅጉ እንደሚፈትኑ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የሊቨርፑሉ አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን በስታ ዴ ፍራንስ ስታዲየም “ማድሪድን ዝም እናሰኛለን” ሲል ተደምጧል። በዘንድሮው ውድድር ኤፍኤ ካፕ እና ካራባዎ ካፕ ያሸነፉት ሊቨርፑሎች በፕሪምየር ሊጉ ዋንጫውን በማንቸስተር ሲቲ ተነጥቀዋል። አራት ዋንጫ ለማሸነፍ አልመው የነበሩት አሰልጣኙ የርገን ክሎፕ አሁን ላይ የመጨረሻ ተስፋቸው ቻምፒየንስ ሊግ ሆኗል። የርገን ክሎፕ ስለቡድናቸው ስብስብ ሲናገሩ ይህ ቡድን በእውነት ልዩ ነው ብለዋል። ዋንጫውን አሸንፈው ደጋፊዎቻቸውን በደስታ ለማስፈንጠዝ መዘጋጀታቸውን አክለዋል። ስለጨዋታው ተጠይቆ የነበረው የማድሪዱ ቤንዜማ ሊቨርፑሎች ምናልባት ይህንን ዋንጫ ያሸነፉ ያህል ሊያስቡ ይችላሉ። እኛም እሱን ነው የምንፈልገው ብሏል። አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ በበኩላቸው የዓመታት ልምድ ባላቸው ሞድሪች እና ክሩዝ የሚመራው የመሀል ሜዳው ቤንዜማ እና ቪኒሺየስ ሲጨመሩበት ቡድናቸው አስፈሪ እንደሚሆን ዝተዋል። ከአራት ዓመት በፊት ሊቨርፑል በማድሪድ በፍጻሜው ሲሸነፍ ተጎድቶ የወጣው ሞሐመድ ሳላህ በዚህ ፍልሚያ ግብ ማስቆጠር እንደሚፈልግ ተናግሯል። ማድሪድ ለዋንጫው ማለፉን ሳያረጋግጥ በፊት እንኳን በፍጻሜው ማድሪድን መግጠም እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ተናግሮ ነበር። በቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ሊቨርፑል ከ ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከአራት ዓመታት በፊት እአአ 2018 ሁሉቱ ኃያል ቡድኖች ለፍጻሜ ተጋጥመው ነበር። በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ የሊቨርፑሉ ኮከብ ሞ ሳላህ የተፈጸመበትን ጉዳት ተከትሎ ከሜዳ ወጣ። ይህም ለሊቨርፑል ትልቅ ጉዳት ነበር። ከዚያም የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ሎሪስ ካሪየስ ቡድኑን ትልቅ ዋጋ ያስከፈሉ ሁለት ጥፋቶችን ሰራ። የመጨረሻም ማድሪድ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ሊቨርፑልን መርታት ቻለ። ሊቨርፑሎች ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ግን ሌላ ቀን ነው እያሉ ነው። የእንግሊዙ 'ዴይሊ ሜይል ኦንላይ' ከሊቨርፑል አምበል ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ በስፋት አስነብቧል። ጆርዳን ሄንደርሰን በስታ ዴ ፍራንስ ስታዲየም “ማድሪድን ዝም እናሰኛለን” ብሏል። የሊቨርፑሉ አሰልጠኝ የርገን ክሎፕ ደግሞ በቡድናቸው ስብስብ መተማመን እንዳላቸው ለቢቢሲ ብሬክፋት ተናግረዋል። ክሎፕ “ይህ ቡድን በእውነት ልዩ ነው” በማለት የቡድን አባሎቻቸውን አሞካሽተዋል። ማድሪድ ልዩ አቋም ላይ ይገኛል። ጎል አዳኙ ካሪም ቤንዜማ ከመቼም ጊዜ በላይ ድንቅ አቋም ላይ ነው። ማድሪድ ከእዚህ የፍጻሜ ውድድር የደረሰው በፒኤስ ጂ፣ ቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ ቀድሞ የተያዘበትን ብልጫ ቀልብሶ ነው። የስፔኑ እውቅ ጋዜጣ 'ማርካ' ቤንዜማን በፊት ገጽ አውጥቶታል። ለማድሪዱ አሰልጣኝ አንቼሎቲም ቢሆን የነገው ጨዋታ ሊቨርፑልን የሚበቀሉበት አጋጣሚን ይፈጥርላቸዋል። እአአ 2005 ላይ በቱርክ ኢስታንቡል በነበረው የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ፣ ሊቨርፑል ከኤስ ሚላን መገናኘታቸው ይታወሳል። በዚያ ጨዋታ ሊቨርፑል 3ለ0 ከመመራት ተነስቶ ኤስ ሚላንን ሲያሸንፍ አንቼሎቲ የኤስ ሚላን አሰልጣኝ ነበሩ። በነገው ጨዋታ ደግሞ ከ90ኛው ደቂቃ በኋላ ሊቨርፑል የበላይነቱን ይዞ ያጠናቅቃል የሚለው ግምት ሚዛን ደፍቷል። ሊቨርፑል 46 በመቶ የማሸነፍ ዕድል ተሰጥቶታል። ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን ሊረታ የሚችልበት አጋጣሚ ደግሞ 28 በመቶ የተገመተ ሲሆን፣ 26 በመቶ ጨዋታው ከ90ኛው ደቂቃ መጠናቀቅ በኋላ ሁለቱ ቡድኖች አቻ ይሆናሉ ተብሎ ተገምቷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c10g9zzgd11o |
3politics
| ዶናልድ ትራምፕ በአምሳያቸው የተሠሩ የኤንኤፍቲ ስብስቦችን ለገበያ አቀረቡ | የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእሳቸው ፊት አምሳያ የተሰሩ የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎችን ይፋ በማድረግ ለገበያ አቀረቡ። ትራምፕ እነዚህ ውስን የሆኑት ዲጂታል ካርዶች የሥራ እና የጥበብ ሕይወቴን የሚያንጸባርቁ ናቸው ብለዋል። ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ይፋ የማደርገው ጉዳይ አለ ማለታቸውን ተከትሎ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳግም ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ምክትላው አድርገው የሚያቀርቡትን ዕጩ ይፋ ሊያደርጉ ነው ተብሎ በስፋት ተጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አዲስ ይፋ ያደረጉትን የኤንኤፍቲ ስብስብ በቪዲዮ መልክ አስተዋውቀዋል። እያንዳንዳቸው በ99 ዶላር ለገበያ ከቀረቡት የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች መካከል አንዱ ልዕል ኃያል ሆነው የሚያሳየው ይገኝበታል። NFT የሚለው Non-fungible token የሚለው ምሕጻረ ቃል የሚወክል ነው። የnon-fungible (ነን-ፈንጀብል) ምጣኔ ሃብታዊ ትርጉም ደግሞ መተኪያ የሌለው፤ በሌላ የማይቀየር ነገር ማለት ነው። ሰዎች የዶናልድ ትራምፕን ኤንኤፍቲ በ99 ዶላር ሲገዙ የገዙት ዲጂታል ካርድ ብቸኛው ባለቤት ይሆናሉ። ከክሪፕቶከረንሲ ተቀባይነት መጨመር ጋር ተያይዞ የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች በኤንኤፍቲ በስፋት መሸጥ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የዲጂታል ጥበብ ብቸኛ ባለቤት የመሆን ፍላጎት እንዲሁም ኤንኤፍቲ የኢንቨስትመንት አማራጭ ነው የሚሉ ምክንያቶች የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች በኤንኤፍቲ አማካይነት ግብይታቸው እንዲጨምር አድርገዋል። ዶናልድ ትራምፕ እነዚህን ዲጂታል ካርዶች ሲያስተዋውቁ ጥሩ የገና ስጦታ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል። ያልተጠበቀው የትራምፕ አካሄድ ከትችት አላመጠም። ተጽዕኖ ፈጣሪ ሪፐብሊካኖችን ጨምሮ በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የትራምፕን ውሳኔ አብጠልጥለዋል። የትራምፕ የቀድሞ ስትራቴጂስት ስቲቭ ባነን፤ “ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም” ካሉ በኋላ በትራምፕ ዲጂታል ካርዶች ላይ ተሳትፎ ያደረጉ “ዛሬውኑ ከሥራቸው መባረር አለባቸው” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደግሞ ለዶናልድ ትራምፕ ምላሽ በሚመስል መልኩ በቅርብ ቀናት ያከናወኗቸውን ሥራዎች ዘርዝረዋል። ፕሬዝዳንቱ የዋጋ ንረትን ማረጋጋታቸውን፣ አዳዲስ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የከናወኗቸውን በትዊተር ገጻቸው ዝርዝረዋል። | ዶናልድ ትራምፕ በአምሳያቸው የተሠሩ የኤንኤፍቲ ስብስቦችን ለገበያ አቀረቡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእሳቸው ፊት አምሳያ የተሰሩ የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎችን ይፋ በማድረግ ለገበያ አቀረቡ። ትራምፕ እነዚህ ውስን የሆኑት ዲጂታል ካርዶች የሥራ እና የጥበብ ሕይወቴን የሚያንጸባርቁ ናቸው ብለዋል። ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ይፋ የማደርገው ጉዳይ አለ ማለታቸውን ተከትሎ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳግም ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ምክትላው አድርገው የሚያቀርቡትን ዕጩ ይፋ ሊያደርጉ ነው ተብሎ በስፋት ተጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አዲስ ይፋ ያደረጉትን የኤንኤፍቲ ስብስብ በቪዲዮ መልክ አስተዋውቀዋል። እያንዳንዳቸው በ99 ዶላር ለገበያ ከቀረቡት የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች መካከል አንዱ ልዕል ኃያል ሆነው የሚያሳየው ይገኝበታል። NFT የሚለው Non-fungible token የሚለው ምሕጻረ ቃል የሚወክል ነው። የnon-fungible (ነን-ፈንጀብል) ምጣኔ ሃብታዊ ትርጉም ደግሞ መተኪያ የሌለው፤ በሌላ የማይቀየር ነገር ማለት ነው። ሰዎች የዶናልድ ትራምፕን ኤንኤፍቲ በ99 ዶላር ሲገዙ የገዙት ዲጂታል ካርድ ብቸኛው ባለቤት ይሆናሉ። ከክሪፕቶከረንሲ ተቀባይነት መጨመር ጋር ተያይዞ የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች በኤንኤፍቲ በስፋት መሸጥ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የዲጂታል ጥበብ ብቸኛ ባለቤት የመሆን ፍላጎት እንዲሁም ኤንኤፍቲ የኢንቨስትመንት አማራጭ ነው የሚሉ ምክንያቶች የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች በኤንኤፍቲ አማካይነት ግብይታቸው እንዲጨምር አድርገዋል። ዶናልድ ትራምፕ እነዚህን ዲጂታል ካርዶች ሲያስተዋውቁ ጥሩ የገና ስጦታ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል። ያልተጠበቀው የትራምፕ አካሄድ ከትችት አላመጠም። ተጽዕኖ ፈጣሪ ሪፐብሊካኖችን ጨምሮ በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የትራምፕን ውሳኔ አብጠልጥለዋል። የትራምፕ የቀድሞ ስትራቴጂስት ስቲቭ ባነን፤ “ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም” ካሉ በኋላ በትራምፕ ዲጂታል ካርዶች ላይ ተሳትፎ ያደረጉ “ዛሬውኑ ከሥራቸው መባረር አለባቸው” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደግሞ ለዶናልድ ትራምፕ ምላሽ በሚመስል መልኩ በቅርብ ቀናት ያከናወኗቸውን ሥራዎች ዘርዝረዋል። ፕሬዝዳንቱ የዋጋ ንረትን ማረጋጋታቸውን፣ አዳዲስ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የከናወኗቸውን በትዊተር ገጻቸው ዝርዝረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cpeq0e92qveo |
2health
| ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው- የዓለም ጤና ድርጅት | አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ይህ ልውጥ ዝርያ በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። ነገር ግን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ እንዳሉት ምናልባት እስካሁን ያልታወቁ በሌሎች አገራት ውስጥ ሊኖር ይችላል ብለዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ ልውጡን ዝርያ ለመጋፈጥ በቂ ስራ አለመሰራቱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። "በእርግጥ እስካሁን ድረስ ይህ ቫይረስ የጋረጠውን አደጋ አቅልለን እንደምንመለከተው ተረድተናል ። ምንም እንኳን ኦሚክሮን ብዙም የከፋ በሽታ ባያመጣም፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት እንደገና ያልተዘጋጁ የጤና ስርዓቶችን ሊያሽመደምድ ይችላል" ብለዋል። ኦሚክሮን የተሰኘው ልውጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በደቡብ አፍሪካ በህዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሃገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር አሳይቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ባደረጉት ምርመራ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከሚታይባቸው ቀለል ካሉ ምልክቶች ለማገገም ራሳቸውን ለይተው ይገኛሉ። ኦሚክሮን መከሰቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካን እና ጎረቤቶቿን የሚጎዳ የጉዞ እቀባ በርካታ ሃገራት ቢጥሉም ይህ ግን በመላው አለም እንዳይስፋፋ ማድረግ አልቻለም። በትናንትናው ዕለት፣ ማክሰኞ ዶክተር ቴድሮስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አንዳንድ ሃገራት ለኦሚክሮን ምላሽ ለመስጠት የክትባት መርሃ ግብራቸውን ያጠናከሩ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ ስለ ክትባት ኢ-ፍትሃዊነት ያላቸውን ስጋት በድጋሜ አንፀባርቀዋል። የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የፋይዘር ክትባት በኦሚክሮን ላይ ከዋናው ዝርያ ሲነፃፀር ውጤታማነቱ በጣም ያነሰ ቢሆንም ይህ ጉድለት በሶስተኛና በማበረታቻ ክትባት ሊቀለበስ እንደሚችል አሳይቷል። | ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው- የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ይህ ልውጥ ዝርያ በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። ነገር ግን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ እንዳሉት ምናልባት እስካሁን ያልታወቁ በሌሎች አገራት ውስጥ ሊኖር ይችላል ብለዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ ልውጡን ዝርያ ለመጋፈጥ በቂ ስራ አለመሰራቱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። "በእርግጥ እስካሁን ድረስ ይህ ቫይረስ የጋረጠውን አደጋ አቅልለን እንደምንመለከተው ተረድተናል ። ምንም እንኳን ኦሚክሮን ብዙም የከፋ በሽታ ባያመጣም፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት እንደገና ያልተዘጋጁ የጤና ስርዓቶችን ሊያሽመደምድ ይችላል" ብለዋል። ኦሚክሮን የተሰኘው ልውጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በደቡብ አፍሪካ በህዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሃገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር አሳይቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ባደረጉት ምርመራ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከሚታይባቸው ቀለል ካሉ ምልክቶች ለማገገም ራሳቸውን ለይተው ይገኛሉ። ኦሚክሮን መከሰቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካን እና ጎረቤቶቿን የሚጎዳ የጉዞ እቀባ በርካታ ሃገራት ቢጥሉም ይህ ግን በመላው አለም እንዳይስፋፋ ማድረግ አልቻለም። በትናንትናው ዕለት፣ ማክሰኞ ዶክተር ቴድሮስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አንዳንድ ሃገራት ለኦሚክሮን ምላሽ ለመስጠት የክትባት መርሃ ግብራቸውን ያጠናከሩ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ ስለ ክትባት ኢ-ፍትሃዊነት ያላቸውን ስጋት በድጋሜ አንፀባርቀዋል። የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የፋይዘር ክትባት በኦሚክሮን ላይ ከዋናው ዝርያ ሲነፃፀር ውጤታማነቱ በጣም ያነሰ ቢሆንም ይህ ጉድለት በሶስተኛና በማበረታቻ ክትባት ሊቀለበስ እንደሚችል አሳይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59662932 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የስፔን ቀብር አስፈጻሚዎች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ | በስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች በኮሮረናቫይረስ የሚሞሩ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የሰራተኛ ቁጥር ይጨመርልን በማለት የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰምቷል። የሰራተኞች ማህበራት እንደገለጹት ወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ሲከሰት ቀብር አስፈጻሚዎቹ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የአንዳንድ ሰዎችን ቀብር ሳይፈልጉ እንዲያራዝሙ ተገድደዋል። በአሁኑ ሰአት ደግሞ አውሮፓ በሁለተኛ ዙር የቫይረሱ ስርጭት እየተፈተነች ትገኛለች። በርካታ አገራት ቫይረሱ እንደ አዲስ መሰራጨት መጀመሩን ተከትሎ የሰአት እላፊዎችና የእንቅስቃሴ ገደቦችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ሲሆን የሟቾችም ቁጥር ቢሆን እያንሰራራ መጥቷል። ቅዳሜ ዕለት ኦስትሪያ እና ፖርቹጋል አዳዲስ መመሪያዎችን ማስተዋወቃቸው ይታወሳል። በመላው ስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች ዕሁድ ዕለት አድማውን መትተዋል። አድማው የተካሄደው ደግሞ ፈረንሳያውያን የሞቱባቸውን ሰዎች መቃብር ስፍራ በሚጎበኙበት ቀን ነው። አንድ በዋና ከተማዋ ማድሪድ የሚገኝ የቀብር አስፈጻሚ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ሲናገር በአሁኑ ሰአት እየጨመረ የመጣውን የሟቾች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት ከ15 እስከ 20 ሰራተኞች እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አርብ ዕለት ብቻ በስፔን 239 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ የበርካታ ሰዎች አስክሬን ሳይቀበር ለተጨማሪ አንድ ሳምንት እንዲቆዩ የተገደዱ ሲሆን የቀብር ስነስርአቱም ቢሆን ከከተማዎች አካባቢ ራቅ ባሉ ቦታዎች ነበር የሚካሄደው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ስፔን እስካሁን ከ1.1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 35 ሺ 800 ደግሞ የሟቾች ቁጥር ነው። በሌሎች የአውሮፓ አገራትም ቢሆን የሁለተኛ ዙር ስርጭቱን ተከትሎ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰአታት ብቻ 46 ሺ 290 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የገለጸች ሲሆን ትናንት ከትናንት በስቲያ ደግሞ 35 ሺ 641 ሰዎች መያዛቸውን አስታውቃ ነበር። በአጠቃላይ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 37 ሺ 19 ደርሷል። ጣልያን ደግሞ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አዳዲስና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምሪያለው ብላለች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትሩ ሮቤርቶ ስፔራንዛ በጣልያን ያለውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴን መገደብ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ የስፔን ቀብር አስፈጻሚዎች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ በስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች በኮሮረናቫይረስ የሚሞሩ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የሰራተኛ ቁጥር ይጨመርልን በማለት የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰምቷል። የሰራተኞች ማህበራት እንደገለጹት ወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ሲከሰት ቀብር አስፈጻሚዎቹ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የአንዳንድ ሰዎችን ቀብር ሳይፈልጉ እንዲያራዝሙ ተገድደዋል። በአሁኑ ሰአት ደግሞ አውሮፓ በሁለተኛ ዙር የቫይረሱ ስርጭት እየተፈተነች ትገኛለች። በርካታ አገራት ቫይረሱ እንደ አዲስ መሰራጨት መጀመሩን ተከትሎ የሰአት እላፊዎችና የእንቅስቃሴ ገደቦችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ሲሆን የሟቾችም ቁጥር ቢሆን እያንሰራራ መጥቷል። ቅዳሜ ዕለት ኦስትሪያ እና ፖርቹጋል አዳዲስ መመሪያዎችን ማስተዋወቃቸው ይታወሳል። በመላው ስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች ዕሁድ ዕለት አድማውን መትተዋል። አድማው የተካሄደው ደግሞ ፈረንሳያውያን የሞቱባቸውን ሰዎች መቃብር ስፍራ በሚጎበኙበት ቀን ነው። አንድ በዋና ከተማዋ ማድሪድ የሚገኝ የቀብር አስፈጻሚ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ሲናገር በአሁኑ ሰአት እየጨመረ የመጣውን የሟቾች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት ከ15 እስከ 20 ሰራተኞች እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አርብ ዕለት ብቻ በስፔን 239 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ የበርካታ ሰዎች አስክሬን ሳይቀበር ለተጨማሪ አንድ ሳምንት እንዲቆዩ የተገደዱ ሲሆን የቀብር ስነስርአቱም ቢሆን ከከተማዎች አካባቢ ራቅ ባሉ ቦታዎች ነበር የሚካሄደው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ስፔን እስካሁን ከ1.1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 35 ሺ 800 ደግሞ የሟቾች ቁጥር ነው። በሌሎች የአውሮፓ አገራትም ቢሆን የሁለተኛ ዙር ስርጭቱን ተከትሎ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰአታት ብቻ 46 ሺ 290 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የገለጸች ሲሆን ትናንት ከትናንት በስቲያ ደግሞ 35 ሺ 641 ሰዎች መያዛቸውን አስታውቃ ነበር። በአጠቃላይ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 37 ሺ 19 ደርሷል። ጣልያን ደግሞ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አዳዲስና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምሪያለው ብላለች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትሩ ሮቤርቶ ስፔራንዛ በጣልያን ያለውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴን መገደብ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54776071 |
3politics
| የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የኡጋንዳው የትራንስፖርት ሚንስትር ቆሰሉ | የኡጋንዳ የትራንስፖርት ሚንስትር በታጣቂዎች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የቆሰሉ ሲሆን የሚንስትሩ ልጅና ሹፌር ግን በጥቃቱ መገደላቸው ተገለጸ። የቀድሞው የመከላከያ ኃላፊና የአሁኑ የትራንስፖርት ሚንስትር ጄነራል ካቱምባ ዋማላ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ካምፓላ የሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። በሞተርሳይክል ይጓዙ የነበሩ ታጣቂዎች የሚንስትሩ መኪና ላይ ደጋግመው መተኮሳቸው ነው የተነገረው። ከግድያ ሙከራው ጋር የተያያዙ ናቸው የተባሉ የስልክ ጥሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄ እንደሆነ መከላከያ ኃይሉ አስታውቋል። ጄነራል ካቱምባ የደረሰባቸው ጉዳት ለሕይወታቸው አስጊ እንዳልሆነና ሕክምና እያገኙበት ያለው ሆስፒታል በወታደሮች እየተጠበቀ እንደሆነ ተገልጿል። ኡጋንዳ ውስጥ እጅግ ከሚከበሩ ፖለቲከኞችና ወታደራዊ ግለሰቦች አንዱ ናቸው። የአገሪቱ መከላከያ ኮማንደር እንዲሁም የፖሊስ ኃላፊም ሆነው አገልግለዋል። የቢቢሲዋ የኡጋንዳ ዘጋቢ ፔሸንስ አቲሬ እንደምትለው፤ መሰል ጥቃቶች የተለመዱ ቢሆኑም የግድያ ሙከራው አስደንጋጭ ነው። ዛሬ ጥቃት ሲፈጸምባቸው በወታደር መኪና ውስጥ ነበሩ። መኪናው ላይ ከጎን እና ከፊት ተተኩሶበታል። ልጃቸው ብሬንዳ ዋማላ እና ሹፌራቸው ሀሩና ካዮንዶ ሕይወታቸው አልፏል። ጄነራሉ ደም በደም ሆነው፣ በፍርሀት ሲንቀጠቀጡና ከዚያም በሞተርሳይክል ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሞተርሳይክል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተኩስ እየከፈቱ አገሪቱን እየናጧት እንደሆነ የቢቢሲ ዘጋቢ ትናገራለች። እአአ ሰኔ 2018 ላይ ኢብራሒም አቢርጋ የተባለ ፖለቲከኛና የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ቀንደኛ ደጋፊ ቤቱ አቅራቢያ ተተኩሶበት ተገድሏል። የቀድሞው የፖሊስ ቃል አቀባይ አንድሪው ፌሊክስ ካውሲም በሚያዝያ 2017 ተገድሏል። የእስልምና መምህራንም በተመሳሳይ ሁኔታ ተገድለዋል። እስካሁን ድረስ ግድያዎቹ ተመርምረው ውጤት ሲገኝ ወይም ተጠያቂዎች ለፍርድ ሲቀርቡ አልታየም። | የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የኡጋንዳው የትራንስፖርት ሚንስትር ቆሰሉ የኡጋንዳ የትራንስፖርት ሚንስትር በታጣቂዎች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የቆሰሉ ሲሆን የሚንስትሩ ልጅና ሹፌር ግን በጥቃቱ መገደላቸው ተገለጸ። የቀድሞው የመከላከያ ኃላፊና የአሁኑ የትራንስፖርት ሚንስትር ጄነራል ካቱምባ ዋማላ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ካምፓላ የሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። በሞተርሳይክል ይጓዙ የነበሩ ታጣቂዎች የሚንስትሩ መኪና ላይ ደጋግመው መተኮሳቸው ነው የተነገረው። ከግድያ ሙከራው ጋር የተያያዙ ናቸው የተባሉ የስልክ ጥሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄ እንደሆነ መከላከያ ኃይሉ አስታውቋል። ጄነራል ካቱምባ የደረሰባቸው ጉዳት ለሕይወታቸው አስጊ እንዳልሆነና ሕክምና እያገኙበት ያለው ሆስፒታል በወታደሮች እየተጠበቀ እንደሆነ ተገልጿል። ኡጋንዳ ውስጥ እጅግ ከሚከበሩ ፖለቲከኞችና ወታደራዊ ግለሰቦች አንዱ ናቸው። የአገሪቱ መከላከያ ኮማንደር እንዲሁም የፖሊስ ኃላፊም ሆነው አገልግለዋል። የቢቢሲዋ የኡጋንዳ ዘጋቢ ፔሸንስ አቲሬ እንደምትለው፤ መሰል ጥቃቶች የተለመዱ ቢሆኑም የግድያ ሙከራው አስደንጋጭ ነው። ዛሬ ጥቃት ሲፈጸምባቸው በወታደር መኪና ውስጥ ነበሩ። መኪናው ላይ ከጎን እና ከፊት ተተኩሶበታል። ልጃቸው ብሬንዳ ዋማላ እና ሹፌራቸው ሀሩና ካዮንዶ ሕይወታቸው አልፏል። ጄነራሉ ደም በደም ሆነው፣ በፍርሀት ሲንቀጠቀጡና ከዚያም በሞተርሳይክል ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሞተርሳይክል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተኩስ እየከፈቱ አገሪቱን እየናጧት እንደሆነ የቢቢሲ ዘጋቢ ትናገራለች። እአአ ሰኔ 2018 ላይ ኢብራሒም አቢርጋ የተባለ ፖለቲከኛና የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ቀንደኛ ደጋፊ ቤቱ አቅራቢያ ተተኩሶበት ተገድሏል። የቀድሞው የፖሊስ ቃል አቀባይ አንድሪው ፌሊክስ ካውሲም በሚያዝያ 2017 ተገድሏል። የእስልምና መምህራንም በተመሳሳይ ሁኔታ ተገድለዋል። እስካሁን ድረስ ግድያዎቹ ተመርምረው ውጤት ሲገኝ ወይም ተጠያቂዎች ለፍርድ ሲቀርቡ አልታየም። | https://www.bbc.com/amharic/57318950 |
3politics
| በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ የጂቡቲ ወታደሮችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ | በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስድስት የጂቡቲ ወታደሮችን አስለቅቆ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወታደሮቹ ፍሩድ (ዘ ፍሮንት ፎር ዘ ሪስቶሬሽን ኦፍ ዩኒቲ ኤንድ ዲሞክራሲ) በተሰኙ የጂቡቲ ታጣቂዎች ታግተው እንደነበርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮቹን ከታጣቂዎቹ እገታ ማስለቀቅ የቻለው በተቀናጀ ስለላ እና የፖሊስ ዘመቻ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሐ ሻወል መናገራቸው ሰፍሯል። ወታደሮቹን በማስለቀቅ ሂደት የማኅበረሰቡ አመራሮች እና የአፋር ክልል አስተዳደር ከፍተኛ ሚና መጫወቱ ቢገለጽም ወታደሮቹ በየትኛው ስፍራ ታግተው እንደነበር አልተገለጸም። ከእገታ የተለቁትን ወታደሮች ለጂቡቲ መንግሥት ማስረከባቸውን እና በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብርን አጽንኦት መሰጠቱንም አምባሳደሩን ዋቢ አድርጎ መግለጫው አመላክቷል። የታጣቂ ቡድኑ ፍሩድ መስከረም 26/2015 ዓ.ም. ጂቡቲ ታድጁራ ክልል ውስጥ በሚገኘው ጋራብቲሳን የጦር ሰፈር ጥቃት ካደረሱ በኋላ ወታደሮቹ መታገታቸው ተገልጿል። በጋራብቲሳን ጦር ሰፈር በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ ሰባት ወታደሮች ሕይወታቸውን እንዳጡና ተጠያቂውም “የአሸባሪ ቡድን” የተባለው ፍሩድ ነው ሲል የጂቡቲ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። በዚሁም መግለጫ ላይ ከሞቱት በተጨማሪ አራት ወታደሮች መቁሰላቸው እና ስድስቱ መጥፋታቸው ተገልጿል። ፍሩድ በበኩሉ ከጦር ሰፈሩ አስራ አምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ የጂቡቲ ጦር ላደረሰበት ጥቃት ምላሽ እንደሆነም መግለጹ ተዘግቧል። ፍሩድ ታጣቂዎቹ የጦር ሰፈሩን ተቆጣጥረው መቆየታቸውን እና መሳሪያ እና ጥይቶችም መውሰዳቸውን ቢገልጹም የጂቡቲ ባለሥልጣናት ግን ውድቅ የቡድኑን የጦር መሳሪያ ምርኮ ጉዳይ ውድቅ አድርጎታል። ይህንንም ጥቃት ተከትሎ የጂቡቲ ፓርላማ ቡድኑን በአሸባሪነት ፈርጆታል። ቡድኑ በጂቡቲ ጦር ሰፈር ላይ የፈጸመውንም ጥቃት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ተቋም (ኢጋድ) እና የጅቡቲ ዋና የንግድ አጋር የሆነችውን ኢትዮጵያን ጨምሮ ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አውግዘውታል። በአውሮፓውያኑ 1991 የተቋቋመው ፍሩድ በጂቡቲ መንግሥታዊ ሥርዓት መገለል ደርሰቦቸዋል የሚለውን የአፋር ሕዝብ ጥያቄን ይዞ የተነሳ እንደሆነ ይነገራል። ከበርካታ ውጣ ውረዶች በኋላ በአውሮፓውያኑ 2001 ፍሩድ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርሞ ነበር። ነገር ግን የታጣቂው ክንፍ ስምምነቱን ውድቅ በማድረግ በትጥቅ ትግሉ እቀጥላለሁ ያለ ሲሆን፣ ለረጅም ጊዜም ይህ ነው የማይባል ጉልህ ወታደራዊ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቷል። | በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ የጂቡቲ ወታደሮችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስድስት የጂቡቲ ወታደሮችን አስለቅቆ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወታደሮቹ ፍሩድ (ዘ ፍሮንት ፎር ዘ ሪስቶሬሽን ኦፍ ዩኒቲ ኤንድ ዲሞክራሲ) በተሰኙ የጂቡቲ ታጣቂዎች ታግተው እንደነበርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮቹን ከታጣቂዎቹ እገታ ማስለቀቅ የቻለው በተቀናጀ ስለላ እና የፖሊስ ዘመቻ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሐ ሻወል መናገራቸው ሰፍሯል። ወታደሮቹን በማስለቀቅ ሂደት የማኅበረሰቡ አመራሮች እና የአፋር ክልል አስተዳደር ከፍተኛ ሚና መጫወቱ ቢገለጽም ወታደሮቹ በየትኛው ስፍራ ታግተው እንደነበር አልተገለጸም። ከእገታ የተለቁትን ወታደሮች ለጂቡቲ መንግሥት ማስረከባቸውን እና በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብርን አጽንኦት መሰጠቱንም አምባሳደሩን ዋቢ አድርጎ መግለጫው አመላክቷል። የታጣቂ ቡድኑ ፍሩድ መስከረም 26/2015 ዓ.ም. ጂቡቲ ታድጁራ ክልል ውስጥ በሚገኘው ጋራብቲሳን የጦር ሰፈር ጥቃት ካደረሱ በኋላ ወታደሮቹ መታገታቸው ተገልጿል። በጋራብቲሳን ጦር ሰፈር በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ ሰባት ወታደሮች ሕይወታቸውን እንዳጡና ተጠያቂውም “የአሸባሪ ቡድን” የተባለው ፍሩድ ነው ሲል የጂቡቲ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። በዚሁም መግለጫ ላይ ከሞቱት በተጨማሪ አራት ወታደሮች መቁሰላቸው እና ስድስቱ መጥፋታቸው ተገልጿል። ፍሩድ በበኩሉ ከጦር ሰፈሩ አስራ አምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ የጂቡቲ ጦር ላደረሰበት ጥቃት ምላሽ እንደሆነም መግለጹ ተዘግቧል። ፍሩድ ታጣቂዎቹ የጦር ሰፈሩን ተቆጣጥረው መቆየታቸውን እና መሳሪያ እና ጥይቶችም መውሰዳቸውን ቢገልጹም የጂቡቲ ባለሥልጣናት ግን ውድቅ የቡድኑን የጦር መሳሪያ ምርኮ ጉዳይ ውድቅ አድርጎታል። ይህንንም ጥቃት ተከትሎ የጂቡቲ ፓርላማ ቡድኑን በአሸባሪነት ፈርጆታል። ቡድኑ በጂቡቲ ጦር ሰፈር ላይ የፈጸመውንም ጥቃት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ተቋም (ኢጋድ) እና የጅቡቲ ዋና የንግድ አጋር የሆነችውን ኢትዮጵያን ጨምሮ ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አውግዘውታል። በአውሮፓውያኑ 1991 የተቋቋመው ፍሩድ በጂቡቲ መንግሥታዊ ሥርዓት መገለል ደርሰቦቸዋል የሚለውን የአፋር ሕዝብ ጥያቄን ይዞ የተነሳ እንደሆነ ይነገራል። ከበርካታ ውጣ ውረዶች በኋላ በአውሮፓውያኑ 2001 ፍሩድ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርሞ ነበር። ነገር ግን የታጣቂው ክንፍ ስምምነቱን ውድቅ በማድረግ በትጥቅ ትግሉ እቀጥላለሁ ያለ ሲሆን፣ ለረጅም ጊዜም ይህ ነው የማይባል ጉልህ ወታደራዊ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cyek0y9zw80o |
5sports
| እስራኤል ፡ አረቡ ባለሃብት በእስራኤሉ ዘረኛ ክለብ ላይ ገንዘባቸውን ለማፍሰስ ለምን መረጡ? | ከቀናት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፅንፈኛ የሚባለው የእስራኤሉ ቤይታር ጄሩሳሌም እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች የቡድኑን ልምምድ በማቋረጥ ሜዳውን ወረሩት። ደጋፊዎቹ በቁጣና በንዴት ሜዳውን የወረሩት ክለቡ ከሚወዳደርበት የእስራኤል ሊግ ወደታች ለመውረድ እየተንገታገተ በመሆኑ አይደለም። ነገሩ ወዲህ ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆኑት ቱጃር በክለቡ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው ቁጣቸውን የገለፁት። ክለቡም ከሁለት ቀናት በፊት ከሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አል ናይን ጋር የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር። የቤይታር ደጋፊዎች በፀረ-አረብ፣ ፀረ-ሙስሊም፣ እብሪተኛና ፀበኛ ባህርያቸው የታወቁና ስምም አትርፈዋል። ከሰሞኑም ሜዳውን ብቻ መውረር ሳይሆን በቤይታር ስታዲየምም ላይ አፀያፊ የሚባሉ የግራፊቲ ምስሎችን በግድግዳዎች ላይ ስለዋል። ምንም እንኳን የቤይታር ደጋፊዎች ምላሽ የከፋ ቢሆን በአንዳንድ አረብ አስተያየት ሰጭዎች ዘንድ ስምምነቱ ተቀባይነት አላገኘም። በሬድዮ የስፖርት ፕሮግራም አቅራቢው ሳይድ ሃስን ለኒውዮርክ ታይምስ እንደተናገረው ስምምነቱ "አሳፋሪ" ነው በማለት ነበር። በተለይም የክለቡ ደጋፊዎች ፀረ-አረብ አቋም እንዳላቸው እየታወቀ ክለቡ ላይ ኢንቨስት መደረጉን ተችቷል። በስምምነቱም መሰረት አል ናህያን በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 92 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ሲሆን 50 በመቶም የክለቡ የባለቤትነት ድርሻ ይኖራቸዋል። ክለቡ በአሁኑ ወቅት በሊጉ ባለው ደረጃ ከአስራ አራት ቡድኖች መካከል አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የእስራኤል መንግሥትና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ በመስከረም ላይ ፊርማ ማኖራቸውን ተከትሎ እንዲህ አይነት የንግድ ስምምነቶች በሁለቱ አገራት መካከል እየጎረፉ ነው ተብሏል። ባለ መጥፎ ስሙ ክለብ የአሁኑ በሁለቱ አገራት መካከል የተከናወነ ቁልፍ ስምምነት ባያደርገውም የቤይታር ስምምነት በከፍተኛ ሁኔታ አወዛጋቢ ነው። በእስራኤል ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች የይሁዲና አረብ ተጫዋቾች በአንድ ላይ ቢኖሩም ቤይታር አንድም አረብ ተጫዋች በታሪኩ አስፈርሞ አያውቅም። ሆኖም በክለቡ ታዳጊ ቡድን ውስጥ አረቦች አሉ። በጎሮጎሳውያኑ 2013 ክለቡ ሁለት ሙስሊም ተጫዋቾችን ከቺቺንያ ማስፈረሙን ተከትሎ የቤይታር ቢሮ በደጋፊዎቹ ተቃጥሏል። ክለቡ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎችም ላይ "ሞት ለአረቦች" የሚሉ መፈክሮችና ዝማሬዎች እንዲሁም አፀያፊ የሚባሉ ፅሁፎችን ከደጋፊዎቹ በኩል መሰስማትና ማየት የተለመደ ነው። የክለቡ ባለቤት ይህንን ባህርይ ለመቀየር ቢሞክሩም ብዙ ፍሬ አላፈራም ተብሏል። አዲስ ባለቤት፣ ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉ ሚሊዮነር የሆኑት ሞሼ ሆጌግ የተባሉት ግለሰብ ከሁለት ዓመት በፊት ክለቡን ገዙት። ሞሼ የተወለዱት እስራኤል ቢሆንም አባታቸው ቱኒዝያዊ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ የሞሮኮም ዝርያ አላቸው ተብሏል። ከዓመት በፊት የክለቡ ባለቤት ሞሼ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዘረኛ የሆኑ ጉዳዮችን እንደማይታገሱና ዘረኛ በሆኑ ደጋፊዎችም ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል። "የማንንም ህይወት ማበላሸት እየሞከርኩ አይደለም። የአባታቸውና እናታቸውንም ሚና እየወሰድኩ አይደለም። ለማስተማርም እየሞከርኩ አይደለም ያ የኔ ሥራ አይደለም" ብለዋል ሞሼ። አክለውም "ነገር ግን ያን ባህርይ ወደ ስታዲየም ሲያመጡት በተሰበሰበውም ሕዝብ ላይ ሆነ በአገራችን ላይ መጥፎ ነፀብራቅ ነው። ያንን ደግሞ አልቀበለውም" ብለዋል። ሞሼም ቢሆኑ "ነጥብ ለማስቆጠር" በሚል አረብ ተጫዋች እንደማያስፈርሙ ቢናገሩም፤ ለስፖርታዊ ምክንያቶች ሲሉ ግን ለማስፈረም ወደኋላ እንደማይሉና ፍራቻም እንደሌላቸው አሳውቀዋል። "የተጫዋች እምነቱ፣ ቀለሙ ምንም ይሁን ግድ አይሰጠኝም። ቡድኑን መርዳት ይችላል ወይ? ጥሩ ተጫዋች ነው የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ" ብለዋል። "የአረቦቹ ተጫዋቾች ይፈርሙም አይፈርሙም እስራኤላዊ የሆጉ ጎበዝ አረብ ተጫዋቾች አሉ። አንደኛውን ልናስፈርም እንችላለን" ብለዋል ሞሼ። በተለይም ከአረቡ ቱጃር አልናህያን ጋር የተረደገውን ስምምነት ሞሼ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለውታል። "በአንድ ላይ ሆነን ክለቡን በአዲስ መልክ በመተባበር፣ ስኬትና ወንድማማችነት በተሞላበት መልኩ እናድሰዋለን" በማለትም ተናግረዋል። ንግድና ጓደኝነት አልናህያን በቤይታር ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዋነኛ ምክንያታቸውም ከሞሼ ጋር ያላቸው የዓመታት የንግድ ሽርክናውና ወዳጅነት እንደሆነ ተናግረዋል። ስምምነቱ መፈረሙንም ተከትሎ አል ናህያ የክለቡ አጋር በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል። "ክለቡ እያከናወነው ስላለው ለውጥ ሰምቻለሁ። በዚህም ተሳታፊ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ" ብለዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁን ግለ ህይወት የፃፈው ጋዜጠኛው አንሸል ፊፈር በበኩሉ የቤይታር ደጋፊዎች ከእስራኤል ገዢ ፓርቲ ሊኩዊድ ጋር ፅኑ ቁርኝት እንዳላቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁም በጨዋታዎች ወቅት ከፅንፈኞቹ ደጋፊዎች ጋር አንድ ላይ ፎቶም ተነስተዋል። "አል ናህያ በቤይታር ጄሩሳሌም ኢንቨስት ለማድረግ መወሰናወች ምንም ተቃርኖ የለውም። ቤተሰባቸው በአጠቃላይ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ቁልፍ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል" በማለትም ጋዜጠኛው ይናገራል። ይሄ ብቻ አይደለም አል ናህያ ከሁለት ቀናት በፊት በተድበሰበሰ መልኩ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና እንደሆነች የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል። ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጥኤም ግጭትና የእየሩሳሌም ሁኔታ ዋነኛና አወዛጋቢ ጉዳያቸውም ነው። እስራኤል መላው ኢየሩሳሌም ግዛቴና መዲናዬ ናት የምትል ሲሆን ይህ በአሜሪካ ቢደገፍም በርካታ አገራት ይቃወሙታል። ፍልስጥኤማውያን በበኩላቸው እስራኤል በጎሮጎሳውያኑ 1967 በተካሄደው ጦርነት በወረራ የያዘችውን ምሥራቅ እየሩሳሌም መጪዋ መዲናችን ናት ይላሉ። እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግንኙነታቸውን ለማደስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ፍልስጥኤም መዲናዋን ምሥራቅ እየሩሳሌም ባደረገ መልኩ ግዛቷን የምትመሰርትበትን ሁኔታም እንደምታግዝ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አስታውቃለች። | እስራኤል ፡ አረቡ ባለሃብት በእስራኤሉ ዘረኛ ክለብ ላይ ገንዘባቸውን ለማፍሰስ ለምን መረጡ? ከቀናት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፅንፈኛ የሚባለው የእስራኤሉ ቤይታር ጄሩሳሌም እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች የቡድኑን ልምምድ በማቋረጥ ሜዳውን ወረሩት። ደጋፊዎቹ በቁጣና በንዴት ሜዳውን የወረሩት ክለቡ ከሚወዳደርበት የእስራኤል ሊግ ወደታች ለመውረድ እየተንገታገተ በመሆኑ አይደለም። ነገሩ ወዲህ ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆኑት ቱጃር በክለቡ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው ቁጣቸውን የገለፁት። ክለቡም ከሁለት ቀናት በፊት ከሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አል ናይን ጋር የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር። የቤይታር ደጋፊዎች በፀረ-አረብ፣ ፀረ-ሙስሊም፣ እብሪተኛና ፀበኛ ባህርያቸው የታወቁና ስምም አትርፈዋል። ከሰሞኑም ሜዳውን ብቻ መውረር ሳይሆን በቤይታር ስታዲየምም ላይ አፀያፊ የሚባሉ የግራፊቲ ምስሎችን በግድግዳዎች ላይ ስለዋል። ምንም እንኳን የቤይታር ደጋፊዎች ምላሽ የከፋ ቢሆን በአንዳንድ አረብ አስተያየት ሰጭዎች ዘንድ ስምምነቱ ተቀባይነት አላገኘም። በሬድዮ የስፖርት ፕሮግራም አቅራቢው ሳይድ ሃስን ለኒውዮርክ ታይምስ እንደተናገረው ስምምነቱ "አሳፋሪ" ነው በማለት ነበር። በተለይም የክለቡ ደጋፊዎች ፀረ-አረብ አቋም እንዳላቸው እየታወቀ ክለቡ ላይ ኢንቨስት መደረጉን ተችቷል። በስምምነቱም መሰረት አል ናህያን በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 92 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ሲሆን 50 በመቶም የክለቡ የባለቤትነት ድርሻ ይኖራቸዋል። ክለቡ በአሁኑ ወቅት በሊጉ ባለው ደረጃ ከአስራ አራት ቡድኖች መካከል አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የእስራኤል መንግሥትና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ በመስከረም ላይ ፊርማ ማኖራቸውን ተከትሎ እንዲህ አይነት የንግድ ስምምነቶች በሁለቱ አገራት መካከል እየጎረፉ ነው ተብሏል። ባለ መጥፎ ስሙ ክለብ የአሁኑ በሁለቱ አገራት መካከል የተከናወነ ቁልፍ ስምምነት ባያደርገውም የቤይታር ስምምነት በከፍተኛ ሁኔታ አወዛጋቢ ነው። በእስራኤል ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች የይሁዲና አረብ ተጫዋቾች በአንድ ላይ ቢኖሩም ቤይታር አንድም አረብ ተጫዋች በታሪኩ አስፈርሞ አያውቅም። ሆኖም በክለቡ ታዳጊ ቡድን ውስጥ አረቦች አሉ። በጎሮጎሳውያኑ 2013 ክለቡ ሁለት ሙስሊም ተጫዋቾችን ከቺቺንያ ማስፈረሙን ተከትሎ የቤይታር ቢሮ በደጋፊዎቹ ተቃጥሏል። ክለቡ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎችም ላይ "ሞት ለአረቦች" የሚሉ መፈክሮችና ዝማሬዎች እንዲሁም አፀያፊ የሚባሉ ፅሁፎችን ከደጋፊዎቹ በኩል መሰስማትና ማየት የተለመደ ነው። የክለቡ ባለቤት ይህንን ባህርይ ለመቀየር ቢሞክሩም ብዙ ፍሬ አላፈራም ተብሏል። አዲስ ባለቤት፣ ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉ ሚሊዮነር የሆኑት ሞሼ ሆጌግ የተባሉት ግለሰብ ከሁለት ዓመት በፊት ክለቡን ገዙት። ሞሼ የተወለዱት እስራኤል ቢሆንም አባታቸው ቱኒዝያዊ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ የሞሮኮም ዝርያ አላቸው ተብሏል። ከዓመት በፊት የክለቡ ባለቤት ሞሼ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዘረኛ የሆኑ ጉዳዮችን እንደማይታገሱና ዘረኛ በሆኑ ደጋፊዎችም ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል። "የማንንም ህይወት ማበላሸት እየሞከርኩ አይደለም። የአባታቸውና እናታቸውንም ሚና እየወሰድኩ አይደለም። ለማስተማርም እየሞከርኩ አይደለም ያ የኔ ሥራ አይደለም" ብለዋል ሞሼ። አክለውም "ነገር ግን ያን ባህርይ ወደ ስታዲየም ሲያመጡት በተሰበሰበውም ሕዝብ ላይ ሆነ በአገራችን ላይ መጥፎ ነፀብራቅ ነው። ያንን ደግሞ አልቀበለውም" ብለዋል። ሞሼም ቢሆኑ "ነጥብ ለማስቆጠር" በሚል አረብ ተጫዋች እንደማያስፈርሙ ቢናገሩም፤ ለስፖርታዊ ምክንያቶች ሲሉ ግን ለማስፈረም ወደኋላ እንደማይሉና ፍራቻም እንደሌላቸው አሳውቀዋል። "የተጫዋች እምነቱ፣ ቀለሙ ምንም ይሁን ግድ አይሰጠኝም። ቡድኑን መርዳት ይችላል ወይ? ጥሩ ተጫዋች ነው የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ" ብለዋል። "የአረቦቹ ተጫዋቾች ይፈርሙም አይፈርሙም እስራኤላዊ የሆጉ ጎበዝ አረብ ተጫዋቾች አሉ። አንደኛውን ልናስፈርም እንችላለን" ብለዋል ሞሼ። በተለይም ከአረቡ ቱጃር አልናህያን ጋር የተረደገውን ስምምነት ሞሼ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለውታል። "በአንድ ላይ ሆነን ክለቡን በአዲስ መልክ በመተባበር፣ ስኬትና ወንድማማችነት በተሞላበት መልኩ እናድሰዋለን" በማለትም ተናግረዋል። ንግድና ጓደኝነት አልናህያን በቤይታር ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዋነኛ ምክንያታቸውም ከሞሼ ጋር ያላቸው የዓመታት የንግድ ሽርክናውና ወዳጅነት እንደሆነ ተናግረዋል። ስምምነቱ መፈረሙንም ተከትሎ አል ናህያ የክለቡ አጋር በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል። "ክለቡ እያከናወነው ስላለው ለውጥ ሰምቻለሁ። በዚህም ተሳታፊ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ" ብለዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁን ግለ ህይወት የፃፈው ጋዜጠኛው አንሸል ፊፈር በበኩሉ የቤይታር ደጋፊዎች ከእስራኤል ገዢ ፓርቲ ሊኩዊድ ጋር ፅኑ ቁርኝት እንዳላቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁም በጨዋታዎች ወቅት ከፅንፈኞቹ ደጋፊዎች ጋር አንድ ላይ ፎቶም ተነስተዋል። "አል ናህያ በቤይታር ጄሩሳሌም ኢንቨስት ለማድረግ መወሰናወች ምንም ተቃርኖ የለውም። ቤተሰባቸው በአጠቃላይ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ቁልፍ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል" በማለትም ጋዜጠኛው ይናገራል። ይሄ ብቻ አይደለም አል ናህያ ከሁለት ቀናት በፊት በተድበሰበሰ መልኩ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና እንደሆነች የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል። ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጥኤም ግጭትና የእየሩሳሌም ሁኔታ ዋነኛና አወዛጋቢ ጉዳያቸውም ነው። እስራኤል መላው ኢየሩሳሌም ግዛቴና መዲናዬ ናት የምትል ሲሆን ይህ በአሜሪካ ቢደገፍም በርካታ አገራት ይቃወሙታል። ፍልስጥኤማውያን በበኩላቸው እስራኤል በጎሮጎሳውያኑ 1967 በተካሄደው ጦርነት በወረራ የያዘችውን ምሥራቅ እየሩሳሌም መጪዋ መዲናችን ናት ይላሉ። እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግንኙነታቸውን ለማደስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ፍልስጥኤም መዲናዋን ምሥራቅ እየሩሳሌም ባደረገ መልኩ ግዛቷን የምትመሰርትበትን ሁኔታም እንደምታግዝ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አስታውቃለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-55241937 |
0business
| ሕንድ ውስጥ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያውጣ ኮኬይን ተያዘ | የሕንድ ባለሥልጣናት ጉጃራት በምትባለው ግዛት ወደ 3ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለውን አደንዛዥ ዕጽ መያዛቸውን አስታወቁ። ይህ በጉጃራት በሚገኝ ወደብ ላይ የተያዘው ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ ኮኬይን ለገበያ ቢቀርብ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያወጣል ተብሏል። ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና በርካታ ሰዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል። የኮኬይኑ መነሻ አፍጋኒስታን መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በይፋዊ ሰነዶች ላይ እቃው 'ታልክ' የተሰኘ የማዕድን ድንጋይ መሆኑ ነበር የተመለከተው። ዕጹ በቅድሚያ ከአፍጋኒስታን ወደ ኢራን ከተጓጓዘ በኋላ ነበር በሕንድ ጉጃራት ሙንደራ ወደብ የተያዘው። የሕንድ የገቢዎች ደኅንነት ዳይሬክቶሬት እንዳለው ከሆነ፤ ኢራን ከሚገኘው ባዳር አባስ ወደብ አደንዛዥ ዕጹ ወደ ሕንድ መላኩን የሚጠቁም መረጃ ደርሶን ነበር ብሏል። ዳይሬክቶሬቱ እቃውን ወደ ሕንድ ያስገባው ተቋምም በሕንድ የሚገኝ ኩባንያ ስለመሆኑ የቀደመ መረጃ እንዳለ አመልክቷል። "ባለሙያዎቻችን እቃውን በቁጥጥር ሥር አውለው ምርመራ ሲያደርጉ፤ በኮንቴነሮቹ ውስጥ ዕጽ ተገኝቷል። ኮኬይን መሆኑም ተረጋግጧል" ብሏል ዳይሬክቶሬቱ በመግለጫው። ባለሥልጣናት እንዳሚሉት ከሆነ ከአደንዛዥ ዕጹ ዝውውር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በመዲናዋ ዴልሂ ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ዘመቻ መካሄዱን አስታውቀዋል። "እስካሁን የተካሄዱ ምርመራዎች በቁጥጥር ስር ላይ ያሉት የአፍጋኒስታን ዜጎች በዕጹ ዝውውር ውስጥ መሳተፋቸውን አሳይቷል" ብሏል ኤጀንሲው። ኮኬይንን ጨምሮ በርካታ አደንዛዥ ዕጾችን ለማምረት የሚውለው ኦፒየም ፖፒይ የተባለውን ተክል በማምረት አፍጋኒስታን ቁጥር አንድ አገር ነች። እንደ ተባበሩት መንግሥታት የዕጽ እና ወንጀል ቢሮ መረጃ ከሆነ ለዓለም ገበያ ከሚቀርበው የኦፒየም ምርት 80 በመቶው የሚመረተው በአፍጋኒስታን ነው። | ሕንድ ውስጥ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያውጣ ኮኬይን ተያዘ የሕንድ ባለሥልጣናት ጉጃራት በምትባለው ግዛት ወደ 3ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለውን አደንዛዥ ዕጽ መያዛቸውን አስታወቁ። ይህ በጉጃራት በሚገኝ ወደብ ላይ የተያዘው ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ ኮኬይን ለገበያ ቢቀርብ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያወጣል ተብሏል። ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና በርካታ ሰዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል። የኮኬይኑ መነሻ አፍጋኒስታን መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በይፋዊ ሰነዶች ላይ እቃው 'ታልክ' የተሰኘ የማዕድን ድንጋይ መሆኑ ነበር የተመለከተው። ዕጹ በቅድሚያ ከአፍጋኒስታን ወደ ኢራን ከተጓጓዘ በኋላ ነበር በሕንድ ጉጃራት ሙንደራ ወደብ የተያዘው። የሕንድ የገቢዎች ደኅንነት ዳይሬክቶሬት እንዳለው ከሆነ፤ ኢራን ከሚገኘው ባዳር አባስ ወደብ አደንዛዥ ዕጹ ወደ ሕንድ መላኩን የሚጠቁም መረጃ ደርሶን ነበር ብሏል። ዳይሬክቶሬቱ እቃውን ወደ ሕንድ ያስገባው ተቋምም በሕንድ የሚገኝ ኩባንያ ስለመሆኑ የቀደመ መረጃ እንዳለ አመልክቷል። "ባለሙያዎቻችን እቃውን በቁጥጥር ሥር አውለው ምርመራ ሲያደርጉ፤ በኮንቴነሮቹ ውስጥ ዕጽ ተገኝቷል። ኮኬይን መሆኑም ተረጋግጧል" ብሏል ዳይሬክቶሬቱ በመግለጫው። ባለሥልጣናት እንዳሚሉት ከሆነ ከአደንዛዥ ዕጹ ዝውውር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በመዲናዋ ዴልሂ ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ዘመቻ መካሄዱን አስታውቀዋል። "እስካሁን የተካሄዱ ምርመራዎች በቁጥጥር ስር ላይ ያሉት የአፍጋኒስታን ዜጎች በዕጹ ዝውውር ውስጥ መሳተፋቸውን አሳይቷል" ብሏል ኤጀንሲው። ኮኬይንን ጨምሮ በርካታ አደንዛዥ ዕጾችን ለማምረት የሚውለው ኦፒየም ፖፒይ የተባለውን ተክል በማምረት አፍጋኒስታን ቁጥር አንድ አገር ነች። እንደ ተባበሩት መንግሥታት የዕጽ እና ወንጀል ቢሮ መረጃ ከሆነ ለዓለም ገበያ ከሚቀርበው የኦፒየም ምርት 80 በመቶው የሚመረተው በአፍጋኒስታን ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-58640077 |
5sports
| በአከራካሪው የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች | ኳታር ዶሃ ላይ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ በወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸነፈ። ይህ በሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር በለሜቻ ግርማ የተገኘው የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በዘርፉ የመጀመሪያ ሲሆን የተመዘገበው ሰዓትም ለአገሪቱ ክብረ ወሰን ነው ተብሏል። ኬንያዊው አትሌት የወርቅ ሜዳሊያውን በወሰደበት በዚህ የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ለሜቻ የተቀደመው ከአንድ ሰከንድ በታች በሆነ ጠባብ ልዩነት ነው። ለሜቻ አንደኛ ሆኖ የወርቅ ሜዳሊያን ካገኘው ኬንያዊው ሯጭ ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ጋር እኩል የመጨረሻውን መስመር በማለፋቸው አሸናፊው ማን እንደሆነ በውድድሩ ማብቂያ ላይ ወዲያውኑ አልታወቀም ነበር። • "ቤተ መንግሥቱን ለማስዋብ ለሙያችን የሚከፈለን ገንዘብ የለም" መስከረም አሰግድ • ተማሪዎች መገረፍ አለባቸው የሚሉት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት • 10 ሚሊዮን ሕዝብ ይታደምበታል የተባለው ኢሬቻ በአዲስ አበባ የውድድሩ ዳኞች በቪዲዮ (ፎቶ ፊኒሽ) ታግዘው ከአንድ ሰከንድ ባነሰ የሰከንዶች ቅንጣት የመጨረሻውን መስመር ኬንያዊው ለሜቻን ቀድሞ እንዳለፈ ከለዩ በኋላ ነው አሸናፊው ሊታወቅ የቻለው። በስፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለስልጣናት ለሜቻ አንደኛ ወጥቷል ብለው አምነው ሰለነበር ይፋ የተደረገውን ውጤት በመቃወም ቅሬታ ለማቅረብ አስበው የነበረ ቢሆንም፤ የመጨረሻውን ሰከንድ የውድድሩን ቪዲዮና ምስሎችን ተመልክተው ካጣሩ በኋላ ቅሬታቸውን ማንሳታቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። 19 ዓመት ሊሆነው ሁለት ወራት የቀሩት ወጣቱ ለሜቻ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍ የጀመረው በቅርቡ ሲሆን በኬንያዊያን የበላይነት ስር በነበረው የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር ላይ የብር ሜዳሊያ ያስገኘበት የዶሃው ውድድር ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው። በውድድሩ አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው ኬንያዊው ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ በዚህ በፈረንጆች ዓመት በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል አራት ጊዜ ተሳትፎ የነበረ ቢሆንም በአራቱም ለማሸነፍ ሳይችል ቀርቶ በዓለም ሻምፒዮና ላይ እንደተሳካለት ተነግሯል። በዚህ ውድድር ላይ በማሸነፍ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ይገባል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው ጌትነት ዋሌ አራተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። ለሜቻ ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ሰዓት እስካሁን በተካሄዱት የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ ከተመዘገቡት ለአንደኛው ከቀረቡት ውጤቶች ሁሉ የበለጠ እንደሆነም ተነግሯል። እስካሁን በተካሄዱ ዓለም አቀፍ የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ ሜዳሊያ አግኝታ የማታውቅ ሲሆን ይህ በዶሃ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በለሜቻ ግርማ የተገኘው ሜዳሊያ የመጀመሪያ ነው። የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ለሜቻ ከውድድሩ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገረው በውጤቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል። አንደኛ በመሆን ያሸነፈው ኬንያዊው አትሌት ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ውድድሩ ላይ ከኢትዮጵያዊያኑ በኩል ከባድ ፈተና እንደገጠመው ተናግሯል። • "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ "ኢትዮጵያዊያኑ በደንብ ተዘጋጅተው ነበር የገቡት። ውድድሩን ለመቆጣጠርና ከፊት ከፊት ሆኜ ለመምራት እቅዱ ነበረኝ ነገር ግን ሊሆን አልቻለም። ለሜቻና ጌትነት ግን እቅዴን እንዳላሳካ አድርገውታል" ሲል ገጥሞት የነበረውን ፈተና ለጋዜጠኞች ተናገሯል። ኢትዮጵያዊያን ከኬንያዊያን በተሻለ ተዘጋጅተው መግባታቸውን የሚናገረው ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ለማሸነፍ የነበረው ጽኑ ፍላጎት በውድድሩ የወርቅ ሜዳሊያውን እንዲወስድ እንደረዳው ገልጿል። በዚህ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ እስከ ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያ አንድ ወርቅና ሦስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኬንያ በሦስት ወርቅና በሁለት የነሃስ ሜዳሊያ ሦስተኛ ስትሆን አሜሪካና ቻይና አንደኛና ሁለተኛ ሆነው የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመሩ ነው። | በአከራካሪው የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች ኳታር ዶሃ ላይ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ በወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸነፈ። ይህ በሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር በለሜቻ ግርማ የተገኘው የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በዘርፉ የመጀመሪያ ሲሆን የተመዘገበው ሰዓትም ለአገሪቱ ክብረ ወሰን ነው ተብሏል። ኬንያዊው አትሌት የወርቅ ሜዳሊያውን በወሰደበት በዚህ የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ለሜቻ የተቀደመው ከአንድ ሰከንድ በታች በሆነ ጠባብ ልዩነት ነው። ለሜቻ አንደኛ ሆኖ የወርቅ ሜዳሊያን ካገኘው ኬንያዊው ሯጭ ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ጋር እኩል የመጨረሻውን መስመር በማለፋቸው አሸናፊው ማን እንደሆነ በውድድሩ ማብቂያ ላይ ወዲያውኑ አልታወቀም ነበር። • "ቤተ መንግሥቱን ለማስዋብ ለሙያችን የሚከፈለን ገንዘብ የለም" መስከረም አሰግድ • ተማሪዎች መገረፍ አለባቸው የሚሉት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት • 10 ሚሊዮን ሕዝብ ይታደምበታል የተባለው ኢሬቻ በአዲስ አበባ የውድድሩ ዳኞች በቪዲዮ (ፎቶ ፊኒሽ) ታግዘው ከአንድ ሰከንድ ባነሰ የሰከንዶች ቅንጣት የመጨረሻውን መስመር ኬንያዊው ለሜቻን ቀድሞ እንዳለፈ ከለዩ በኋላ ነው አሸናፊው ሊታወቅ የቻለው። በስፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለስልጣናት ለሜቻ አንደኛ ወጥቷል ብለው አምነው ሰለነበር ይፋ የተደረገውን ውጤት በመቃወም ቅሬታ ለማቅረብ አስበው የነበረ ቢሆንም፤ የመጨረሻውን ሰከንድ የውድድሩን ቪዲዮና ምስሎችን ተመልክተው ካጣሩ በኋላ ቅሬታቸውን ማንሳታቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። 19 ዓመት ሊሆነው ሁለት ወራት የቀሩት ወጣቱ ለሜቻ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍ የጀመረው በቅርቡ ሲሆን በኬንያዊያን የበላይነት ስር በነበረው የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር ላይ የብር ሜዳሊያ ያስገኘበት የዶሃው ውድድር ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው። በውድድሩ አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው ኬንያዊው ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ በዚህ በፈረንጆች ዓመት በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል አራት ጊዜ ተሳትፎ የነበረ ቢሆንም በአራቱም ለማሸነፍ ሳይችል ቀርቶ በዓለም ሻምፒዮና ላይ እንደተሳካለት ተነግሯል። በዚህ ውድድር ላይ በማሸነፍ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ይገባል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው ጌትነት ዋሌ አራተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። ለሜቻ ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ሰዓት እስካሁን በተካሄዱት የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ ከተመዘገቡት ለአንደኛው ከቀረቡት ውጤቶች ሁሉ የበለጠ እንደሆነም ተነግሯል። እስካሁን በተካሄዱ ዓለም አቀፍ የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ ሜዳሊያ አግኝታ የማታውቅ ሲሆን ይህ በዶሃ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በለሜቻ ግርማ የተገኘው ሜዳሊያ የመጀመሪያ ነው። የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ለሜቻ ከውድድሩ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገረው በውጤቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል። አንደኛ በመሆን ያሸነፈው ኬንያዊው አትሌት ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ውድድሩ ላይ ከኢትዮጵያዊያኑ በኩል ከባድ ፈተና እንደገጠመው ተናግሯል። • "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ "ኢትዮጵያዊያኑ በደንብ ተዘጋጅተው ነበር የገቡት። ውድድሩን ለመቆጣጠርና ከፊት ከፊት ሆኜ ለመምራት እቅዱ ነበረኝ ነገር ግን ሊሆን አልቻለም። ለሜቻና ጌትነት ግን እቅዴን እንዳላሳካ አድርገውታል" ሲል ገጥሞት የነበረውን ፈተና ለጋዜጠኞች ተናገሯል። ኢትዮጵያዊያን ከኬንያዊያን በተሻለ ተዘጋጅተው መግባታቸውን የሚናገረው ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ለማሸነፍ የነበረው ጽኑ ፍላጎት በውድድሩ የወርቅ ሜዳሊያውን እንዲወስድ እንደረዳው ገልጿል። በዚህ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ እስከ ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያ አንድ ወርቅና ሦስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኬንያ በሦስት ወርቅና በሁለት የነሃስ ሜዳሊያ ሦስተኛ ስትሆን አሜሪካና ቻይና አንደኛና ሁለተኛ ሆነው የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመሩ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/49944141 |
5sports
| የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር ምርጫ ያስከተለው ውዝግብ | ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ጋር በተያያዘ ውዝግብ መከሰቱ ሲነገር ቆይቶ ሰኞ ዕለት በኮሚቴው ጽህፈት ቤት ውስጥ ተካሄደ የተባለን ስብሰባ ተከትሎ በአካባቢው ተቃውሞ እንደነበር ተሰምቷል። ይህ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ደጃፍ የተደረገው የተቃውሞ ሠልፍ የተጠራው የኮሚቴው አባል በሆነው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደነበረ የፌዴሬሽኑ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተቃውሞ ሠልፉን ያደረጉበትን ምክንያት ሲያስረዱም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እያደረገ ይገኛል ያሉትን ሕገ ወጥና አግባብ ያልሆነ አሰራርን በመቃወም ነው ብለዋል። በዚህ ተቃውሞ ላይ በቶኪዮ 2020 ኢትዮጵያን በአትሌቲክ የሚወክሉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የቀድሞ አትሌቶች፣ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የሌሎች አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽን አመራሮች መገኘታቸውን አቶ ስለሺ ጨምረው አስረድተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴም መጋቢት 20/2013 ዓ.ም የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለማድረግ ከሚገኝበት አቢጃ ኮትዲቯር ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ፤ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውክልና ሳይሰጣቸው በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ተገኝተዋል ያላቸው ግለሰቦች ላይ እገዳ መጣሉን አሳውቋል። በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮችን ምላሽ ለማካተት ቢቢሲ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ለአሁን አልተሳካለትም። ነገር ግን ትናንት ማምሻውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ኮሚቴውን ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በፕሬዝደንትነት፣ አትሌት ብርሃኔ አደሬ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት፣ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸውን አስፍረዋል። ቢቢሲ ይህንን መረጃ ከኮሚቴውም ሆነ መመረጣቸው ከተነገረው ሰዎች ለማረጋገጥ አልቻለም። የሁለቱ አትሌቶች በምርጫው ውስጥ መካተትን በተመለከተ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ ሂደቱ ሕጋዊ መስመርንና አሰራርን ያልተከተለ ነው በማለት ተቃውሞታል። ፌዴሬሽኑ በመግለጫው ላይ የኃይሌ ገብረሥላሴና የብርሃኔ አደሬ በኦሎምፒክ ኮሚቴው ከፍተኛ አመራርነት ውስጥ መግባታቸው ለአገር ካበረከቱት አስተዋጽኦ አንፃር ተገቢ መሆኑን ጠቅሶ፤ ነገር ግን "በማኅበር ወይም በፌዴሬሽን የተወከሉ ባለመሆናቸው ህጋዊ መስመሩን ያልተከተለ ነው" ብሏል። የአሁኑ ውዝግብ መነሻ የሆነው ከዚህ ቀደም አዲስ አመራሮችን መሰየምን በተመለከተ በኮሚቴው የተሰጠው ውሳኔ ባላከበረ ሁኔታ ምርጫ እንዲካሄድ መደረጉ እንደሆነ ይነገራል። የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ እንደሰፈረውና አቶ ስለሺ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በታኅሣሥ ወር ሐዋሳ ላይ በተደረገ ጉባኤ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ከቶኪዮ ኦሎምፒክ ማግስት በመስከረም 2014 ዓ.ም ላይ እንዲደረግ መወሰኑን በማስታወስ፣ ይህንን የጣሰ ተግባር በኮሚቴው መፈፀሙን ይናገራሉ። እንደ አቶ ስለሺ ከሆነ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ይህንን ስምምነት መጣሱ ብቻ ሳይሆን የዓለም ዓቀፉን ኦሎምፒክ ቻርተር እየተገበረ አይደለም ሲሉም ይከሳሉ። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለአባልነት የትምህርት ዝግጅት እንደመስፈርት ማስቀመጡን በተጨማሪም የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር በተለይም ፕሬዝዳንቱ የስልጣን ዘመናቸው ስምንት ዓመት እንዲሆን መደረጉንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቻርተሩ አንድ ግለሰብ ለመመረጥ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖረው ማድረጉ ለአባልነት እና ለሥራ አስፈፋሚነት አስፈላጊ አይደለም በማለት ይከራከራሉ። በዚህም የተነሳ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ አባላት ይህ አሰራር መስተካከል አለበት የሚል አቋም እንዳላቸውና ይሀንንም አቋም ሌሎቹ ፌዴሬሽኖች እንደሚጋሩት ይገልጻሉ። የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሰሞኑን በባሕር ዳር ከተማ ተሰብስቦ ምርጫ ለማከናወን ቢሞከርም ፈቃድ ባለማግኘቱ ወደ ሐዋሳ መሻገሩን እዚያም ፈቃድ ባለማግኘታቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ሰኞ መጋቢት 20/2013 ዓ.ም ኦሎምፒክ ኮሚቴ ቅጥር ግቢ ውስጥ ምርጫ አደርገው መጠናቀቁ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም 13 የስፖርት አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ተቃውሟቸውን ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በጽሁፍ ማሳወቃቸው በማስታወስ ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል። በአገር አቀፍ ደረጃም የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም ባህልና ቱሪዝም ሁለቱ አካላት በጉዳዩ ላይ በጋራ ውይይት ይኖራቸዋል በማለት ሁለቱን አካላት አቀራርቦ በማወያየት ውሳኔያቸውን እንደሚጠበቅ ይናገራሉ። ይህንን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫን በመቃወምም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማኅበር መግለጫ ሰጥተዋል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጃፓን ቶኪዮ ውስጥ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የ2020 የኦሊምፒክ ውድድር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት በዚህ ዓመት ማብቂያ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያም በሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ በሚካሄደው የዓለማችን ትልቁ የስፖርት ውድድር ላይ የምትሳታፍ ሲሆን፤ ነገር ግን ይህ በኦሊምፒክ ኮሚቴውና በፌዴሬሽኖች እንዲሁም በማኅበራት መካከል ተከሰተው ውዝግብ በቶሎ መፍትሔ ካላገኘ በአገሪቱ ተሳትፎ ላይ ምን ውጤት እንደሚኖረው ወደፊት የሚታይ ይሆናል። | የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር ምርጫ ያስከተለው ውዝግብ ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ጋር በተያያዘ ውዝግብ መከሰቱ ሲነገር ቆይቶ ሰኞ ዕለት በኮሚቴው ጽህፈት ቤት ውስጥ ተካሄደ የተባለን ስብሰባ ተከትሎ በአካባቢው ተቃውሞ እንደነበር ተሰምቷል። ይህ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ደጃፍ የተደረገው የተቃውሞ ሠልፍ የተጠራው የኮሚቴው አባል በሆነው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደነበረ የፌዴሬሽኑ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተቃውሞ ሠልፉን ያደረጉበትን ምክንያት ሲያስረዱም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እያደረገ ይገኛል ያሉትን ሕገ ወጥና አግባብ ያልሆነ አሰራርን በመቃወም ነው ብለዋል። በዚህ ተቃውሞ ላይ በቶኪዮ 2020 ኢትዮጵያን በአትሌቲክ የሚወክሉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የቀድሞ አትሌቶች፣ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የሌሎች አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽን አመራሮች መገኘታቸውን አቶ ስለሺ ጨምረው አስረድተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴም መጋቢት 20/2013 ዓ.ም የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለማድረግ ከሚገኝበት አቢጃ ኮትዲቯር ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ፤ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውክልና ሳይሰጣቸው በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ተገኝተዋል ያላቸው ግለሰቦች ላይ እገዳ መጣሉን አሳውቋል። በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮችን ምላሽ ለማካተት ቢቢሲ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ለአሁን አልተሳካለትም። ነገር ግን ትናንት ማምሻውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ኮሚቴውን ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በፕሬዝደንትነት፣ አትሌት ብርሃኔ አደሬ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት፣ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸውን አስፍረዋል። ቢቢሲ ይህንን መረጃ ከኮሚቴውም ሆነ መመረጣቸው ከተነገረው ሰዎች ለማረጋገጥ አልቻለም። የሁለቱ አትሌቶች በምርጫው ውስጥ መካተትን በተመለከተ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ ሂደቱ ሕጋዊ መስመርንና አሰራርን ያልተከተለ ነው በማለት ተቃውሞታል። ፌዴሬሽኑ በመግለጫው ላይ የኃይሌ ገብረሥላሴና የብርሃኔ አደሬ በኦሎምፒክ ኮሚቴው ከፍተኛ አመራርነት ውስጥ መግባታቸው ለአገር ካበረከቱት አስተዋጽኦ አንፃር ተገቢ መሆኑን ጠቅሶ፤ ነገር ግን "በማኅበር ወይም በፌዴሬሽን የተወከሉ ባለመሆናቸው ህጋዊ መስመሩን ያልተከተለ ነው" ብሏል። የአሁኑ ውዝግብ መነሻ የሆነው ከዚህ ቀደም አዲስ አመራሮችን መሰየምን በተመለከተ በኮሚቴው የተሰጠው ውሳኔ ባላከበረ ሁኔታ ምርጫ እንዲካሄድ መደረጉ እንደሆነ ይነገራል። የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ እንደሰፈረውና አቶ ስለሺ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በታኅሣሥ ወር ሐዋሳ ላይ በተደረገ ጉባኤ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ከቶኪዮ ኦሎምፒክ ማግስት በመስከረም 2014 ዓ.ም ላይ እንዲደረግ መወሰኑን በማስታወስ፣ ይህንን የጣሰ ተግባር በኮሚቴው መፈፀሙን ይናገራሉ። እንደ አቶ ስለሺ ከሆነ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ይህንን ስምምነት መጣሱ ብቻ ሳይሆን የዓለም ዓቀፉን ኦሎምፒክ ቻርተር እየተገበረ አይደለም ሲሉም ይከሳሉ። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለአባልነት የትምህርት ዝግጅት እንደመስፈርት ማስቀመጡን በተጨማሪም የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር በተለይም ፕሬዝዳንቱ የስልጣን ዘመናቸው ስምንት ዓመት እንዲሆን መደረጉንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቻርተሩ አንድ ግለሰብ ለመመረጥ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖረው ማድረጉ ለአባልነት እና ለሥራ አስፈፋሚነት አስፈላጊ አይደለም በማለት ይከራከራሉ። በዚህም የተነሳ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ አባላት ይህ አሰራር መስተካከል አለበት የሚል አቋም እንዳላቸውና ይሀንንም አቋም ሌሎቹ ፌዴሬሽኖች እንደሚጋሩት ይገልጻሉ። የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሰሞኑን በባሕር ዳር ከተማ ተሰብስቦ ምርጫ ለማከናወን ቢሞከርም ፈቃድ ባለማግኘቱ ወደ ሐዋሳ መሻገሩን እዚያም ፈቃድ ባለማግኘታቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ሰኞ መጋቢት 20/2013 ዓ.ም ኦሎምፒክ ኮሚቴ ቅጥር ግቢ ውስጥ ምርጫ አደርገው መጠናቀቁ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም 13 የስፖርት አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ተቃውሟቸውን ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በጽሁፍ ማሳወቃቸው በማስታወስ ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል። በአገር አቀፍ ደረጃም የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም ባህልና ቱሪዝም ሁለቱ አካላት በጉዳዩ ላይ በጋራ ውይይት ይኖራቸዋል በማለት ሁለቱን አካላት አቀራርቦ በማወያየት ውሳኔያቸውን እንደሚጠበቅ ይናገራሉ። ይህንን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫን በመቃወምም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማኅበር መግለጫ ሰጥተዋል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጃፓን ቶኪዮ ውስጥ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የ2020 የኦሊምፒክ ውድድር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት በዚህ ዓመት ማብቂያ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያም በሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ በሚካሄደው የዓለማችን ትልቁ የስፖርት ውድድር ላይ የምትሳታፍ ሲሆን፤ ነገር ግን ይህ በኦሊምፒክ ኮሚቴውና በፌዴሬሽኖች እንዲሁም በማኅበራት መካከል ተከሰተው ውዝግብ በቶሎ መፍትሔ ካላገኘ በአገሪቱ ተሳትፎ ላይ ምን ውጤት እንደሚኖረው ወደፊት የሚታይ ይሆናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56554166 |
3politics
| መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ተገለጸ | የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም ለማውረድ ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ። ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ. ም. ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንቷ መንግሥት በዚህ ዓመት ትኩረት የሚያደርግባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ነው ይህንን ያሉት። “የአገሪቱን ጥቅም ባስከበረ” እንዲሁም “ዘለቄታን ባማከለ” መልኩ ከህወሓት ጋር የሚደረገውን ድርድር የፌደራል መንግሥቱ እንደሚቀጥልበት ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቷ እንዳሉት መንግሥት የድርድር ሂደቱን ቢገፋበትም “የሰላም አማራጭ ተትቶ ትንኮሳ ከተደረገ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል” ሲሉ ተናግረዋል። ጨምረውም መንግሥት “ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር” ያለውን ፍላጎት በንግግራቸው ጠቅሰው “የሰላም በር አይዘጋም” ሲሉ አስምረውበታል። አያይዘውም ማንኛውንም ልዩነት ለመፍታት “ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት አሁንም ጥሪ ያቀርባል” ሲሉ ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል። የባለፈው ሳምንት የአፍሪካ ኅብረትን የድርድር ጥሪ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ንግግር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ ግብዣውን መቀበሉ ይታወሳል። በተመሳሳይም ህወሓት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት ይደረጋል በተባለው ንግግር ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን በአህጉራዊው ድርጅት አማካይነት ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ይደረጋል ተብሎ የነበረው ንግግር የሎጂስቲክስ በተባለ ችግር ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መዘዋወሩ ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ በዚህ ዓመት መንግሥት አገሪቱ ከጦርነት የምትወጣበት እንዲሆን ያለውን ፍላጎት ጠቁመው፣ የአፍሪካ ኅብረትም ለሰላም የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል ተስፋ እንዳለ ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቷ በዓመቱ የምክር ቤቶቹ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከህወሓት ጋር ከሚደረገው ድርድር ባሻገር አገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽኑ የሐሳብ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት መንግሥት እንደሚደግፍ ገልጸዋል። “ደም አፋሳሽ ጦርነት ከሚፈጥረው ቂምና ቁርሾ እንዲሁም ከግጭት አዙሪት ለመውጣት” ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጎን መቆም እንደሚያሻ ተናግረዋል። ከሰዓት በኋላ በተደረገው ስብሰባ የ2014 ዓ. ም. ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና የምጣኔ ሀብት ዳሰሳ አቅርበው፣ ለ2015 ዓ. ም. የተያዙ ዕቅዶችን ርዕሰ ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው ዳሰዋል። በጦርነቱ ሳቢያ የወደሙ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን መልሶ ለማቋቋም በ2014 ዓ. ም. ሥራዎች እንደተጀመሩና በያዝነው ዓመትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ጦርነት፣ የኮሮናቫይረስ፣ ጎርፍ እና ድርቅ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ጫና ቢያሳድርም፣ ውጤቶች እንደተመዘገቡም ርዕሰ ብሔሯ ሳይጠቅሱ አላለፉም። ያለፈው ዓመት ከውጭ ንግድ ከፍተኛ የሚባለው ገቢ የተመዘገበበት እንደሆነ ጠቅሰው፣ የታክስ ገቢ 93.5% እንዳደገ እንዲሁም ለ2.38 ሚሊዮን ሕዝብ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረ ተናግረዋል። ግብርናው 43% ድርሻውን እንደያዘና የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 32% ድረሻ እንደያዘ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። መንግሥት በተያዘው በጀት ዓመት ትኩረት ከሚሰጣቸው ምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያዎች መካከል የታክስ ገቢ ማሻሻል፣ የሀብት ብክነት መቀነስ እንዲሁም የመንግሥትን በጀት ድህነትን የሚቀንስ ዘርፍ ላይ እንደሚያተኩር ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ጠቅሰዋል። አያይዘውም በግጭት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ እንዲሁም ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫዎችን መልሶ ለማቋቋም ፋይናንስ በማሰባሰቡ መንግሥት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን በመሥራ እና አሮጌ ትምህርት ቤቶች በማደስ እንዲሁም ደግሞ ለአቅመ ደካሞች ቤት በመሥራት ማኅበራዊ በጎ አገልግሎቶች 1 ሚሊዮን ዜጋ እንደተሳተፈ ገልጸዋል። በምጣኔ ሀብት ረገድ ማኅበረሰቡን እየፈተነ ያለውን የዋጋ ንረት ለማርገብ የምግብ ምርትን በማሳደግ፣ የንግድ ሰንሰለትን አዘምኖ ምርትን ወደ ገበያ በማምጣት እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ድጎማ በማድረግ እንደሚሠራ አክለዋል። በ2014 ዓ. ም. ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን እንደ ስኬት የጠቀሱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ ግድቡን በተያዘለት ጊዜ አጠናቆ የሚመነጨውን ኃይል ከኢትዮጵያ ባሻገር ለጎረቤት አገራትም የመሸጥ ዕቅድን በንግግራቸው አንስተዋል። መንግሥት በተያዘው የበጀት ዓመት አገሪቱን አማራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በማድረግ እንዲሁም የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት እንደሚሠራ ጠቁመዋል። በሕዝቡ ዘንድ በፍትሕ እጦት እና መዘግየት የተፈጠረውን ቅሬታ ለመቅረፍ እንደሚሠራ እንዲሁም የአገር አቀፍ ተቋማትን አሠራር ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚሠራም ጠቅሰዋል። | መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ተገለጸ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም ለማውረድ ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ። ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ. ም. ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንቷ መንግሥት በዚህ ዓመት ትኩረት የሚያደርግባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ነው ይህንን ያሉት። “የአገሪቱን ጥቅም ባስከበረ” እንዲሁም “ዘለቄታን ባማከለ” መልኩ ከህወሓት ጋር የሚደረገውን ድርድር የፌደራል መንግሥቱ እንደሚቀጥልበት ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቷ እንዳሉት መንግሥት የድርድር ሂደቱን ቢገፋበትም “የሰላም አማራጭ ተትቶ ትንኮሳ ከተደረገ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል” ሲሉ ተናግረዋል። ጨምረውም መንግሥት “ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር” ያለውን ፍላጎት በንግግራቸው ጠቅሰው “የሰላም በር አይዘጋም” ሲሉ አስምረውበታል። አያይዘውም ማንኛውንም ልዩነት ለመፍታት “ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት አሁንም ጥሪ ያቀርባል” ሲሉ ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል። የባለፈው ሳምንት የአፍሪካ ኅብረትን የድርድር ጥሪ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ንግግር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ ግብዣውን መቀበሉ ይታወሳል። በተመሳሳይም ህወሓት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት ይደረጋል በተባለው ንግግር ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን በአህጉራዊው ድርጅት አማካይነት ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ይደረጋል ተብሎ የነበረው ንግግር የሎጂስቲክስ በተባለ ችግር ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መዘዋወሩ ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ በዚህ ዓመት መንግሥት አገሪቱ ከጦርነት የምትወጣበት እንዲሆን ያለውን ፍላጎት ጠቁመው፣ የአፍሪካ ኅብረትም ለሰላም የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል ተስፋ እንዳለ ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቷ በዓመቱ የምክር ቤቶቹ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከህወሓት ጋር ከሚደረገው ድርድር ባሻገር አገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽኑ የሐሳብ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት መንግሥት እንደሚደግፍ ገልጸዋል። “ደም አፋሳሽ ጦርነት ከሚፈጥረው ቂምና ቁርሾ እንዲሁም ከግጭት አዙሪት ለመውጣት” ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጎን መቆም እንደሚያሻ ተናግረዋል። ከሰዓት በኋላ በተደረገው ስብሰባ የ2014 ዓ. ም. ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና የምጣኔ ሀብት ዳሰሳ አቅርበው፣ ለ2015 ዓ. ም. የተያዙ ዕቅዶችን ርዕሰ ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው ዳሰዋል። በጦርነቱ ሳቢያ የወደሙ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን መልሶ ለማቋቋም በ2014 ዓ. ም. ሥራዎች እንደተጀመሩና በያዝነው ዓመትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ጦርነት፣ የኮሮናቫይረስ፣ ጎርፍ እና ድርቅ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ጫና ቢያሳድርም፣ ውጤቶች እንደተመዘገቡም ርዕሰ ብሔሯ ሳይጠቅሱ አላለፉም። ያለፈው ዓመት ከውጭ ንግድ ከፍተኛ የሚባለው ገቢ የተመዘገበበት እንደሆነ ጠቅሰው፣ የታክስ ገቢ 93.5% እንዳደገ እንዲሁም ለ2.38 ሚሊዮን ሕዝብ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረ ተናግረዋል። ግብርናው 43% ድርሻውን እንደያዘና የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 32% ድረሻ እንደያዘ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። መንግሥት በተያዘው በጀት ዓመት ትኩረት ከሚሰጣቸው ምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያዎች መካከል የታክስ ገቢ ማሻሻል፣ የሀብት ብክነት መቀነስ እንዲሁም የመንግሥትን በጀት ድህነትን የሚቀንስ ዘርፍ ላይ እንደሚያተኩር ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ጠቅሰዋል። አያይዘውም በግጭት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ እንዲሁም ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫዎችን መልሶ ለማቋቋም ፋይናንስ በማሰባሰቡ መንግሥት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን በመሥራ እና አሮጌ ትምህርት ቤቶች በማደስ እንዲሁም ደግሞ ለአቅመ ደካሞች ቤት በመሥራት ማኅበራዊ በጎ አገልግሎቶች 1 ሚሊዮን ዜጋ እንደተሳተፈ ገልጸዋል። በምጣኔ ሀብት ረገድ ማኅበረሰቡን እየፈተነ ያለውን የዋጋ ንረት ለማርገብ የምግብ ምርትን በማሳደግ፣ የንግድ ሰንሰለትን አዘምኖ ምርትን ወደ ገበያ በማምጣት እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ድጎማ በማድረግ እንደሚሠራ አክለዋል። በ2014 ዓ. ም. ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን እንደ ስኬት የጠቀሱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ ግድቡን በተያዘለት ጊዜ አጠናቆ የሚመነጨውን ኃይል ከኢትዮጵያ ባሻገር ለጎረቤት አገራትም የመሸጥ ዕቅድን በንግግራቸው አንስተዋል። መንግሥት በተያዘው የበጀት ዓመት አገሪቱን አማራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በማድረግ እንዲሁም የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት እንደሚሠራ ጠቁመዋል። በሕዝቡ ዘንድ በፍትሕ እጦት እና መዘግየት የተፈጠረውን ቅሬታ ለመቅረፍ እንደሚሠራ እንዲሁም የአገር አቀፍ ተቋማትን አሠራር ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚሠራም ጠቅሰዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn453yyr27eo |
2health
| ካናዳ ፋይዘር የተሰኘው ክትባት ለሕፃናት እንዲሰጥ ፈቀደች | ካናዳ ፋይዘር የተሰኘውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ከ12 እስከ 15 ዓመት ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጠች። ይህ ውሳኔ የኮሮናቫይረስ ክትባት በዚህ ዕድሜ ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል። የሶስተኛ ምዕራፍ ‘የክሊኒካል’ ሙከራ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ፋይዘር የተሰኘው ክትባትከ 12 እስከ 15 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ያሉ ህጻናት እንዲከተቡ ይሁንታውን የሰጠው። “በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ላይ የተሞከረው ክትባቱ አስተማማኝና ውጤታማ ነው” ሲሉ የሚኒስቴሩ አማካሪ ገልጸዋል። ፋይዘር ቀደም ብሎ በሀገሪቱ ከ16 ዓመት በላይ ያሉ ሰዎች እንዲወስዱት ካናዳ ፈቅዳ ነበር። በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባት የአልቤርታ ግዛት ከ9 ቀናት በኃላ ከ12 እስከ 15 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ታዳጊዎች ክትባቱን መውሰድ ይጀምራሉ። በካናዳ እስካሁን 1.2 ሚሊዮን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የያዛቸው ሲሆን 20 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ19 ዓመት በታች ነው። የክትባት አሰጣጡ በአንጻራዊነት የዘገየ እንደሆነ በሚነገርባት ካናድ 34 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ወስዷል። | ካናዳ ፋይዘር የተሰኘው ክትባት ለሕፃናት እንዲሰጥ ፈቀደች ካናዳ ፋይዘር የተሰኘውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ከ12 እስከ 15 ዓመት ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጠች። ይህ ውሳኔ የኮሮናቫይረስ ክትባት በዚህ ዕድሜ ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል። የሶስተኛ ምዕራፍ ‘የክሊኒካል’ ሙከራ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ፋይዘር የተሰኘው ክትባትከ 12 እስከ 15 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ያሉ ህጻናት እንዲከተቡ ይሁንታውን የሰጠው። “በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ላይ የተሞከረው ክትባቱ አስተማማኝና ውጤታማ ነው” ሲሉ የሚኒስቴሩ አማካሪ ገልጸዋል። ፋይዘር ቀደም ብሎ በሀገሪቱ ከ16 ዓመት በላይ ያሉ ሰዎች እንዲወስዱት ካናዳ ፈቅዳ ነበር። በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባት የአልቤርታ ግዛት ከ9 ቀናት በኃላ ከ12 እስከ 15 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ታዳጊዎች ክትባቱን መውሰድ ይጀምራሉ። በካናዳ እስካሁን 1.2 ሚሊዮን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የያዛቸው ሲሆን 20 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ19 ዓመት በታች ነው። የክትባት አሰጣጡ በአንጻራዊነት የዘገየ እንደሆነ በሚነገርባት ካናድ 34 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ወስዷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57029733 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኮቪድ ክትባት መስጠት ትጀምራለች ተባለ | የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም የአፍሪካ አገራት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ "ከፍተኛ ቅድሚያ" ለሚሰጣቸው ሰዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት መከተብ አለባቸው አለ። ኮቫክስ 90 ሚሊዮን ክትባቶችን ወደ አፍሪካ በቅርቡ ማሰራጨት ይጀምራል ያለው የዓለም ጤና ድርጅት፣ የስርጭት መጠኑም የሚወሰነው አገራት ባላቸው የሕዝብ ብዛት መጠን መሆኑ ተመልክቷል። ለእያንዳንዱ አገር የሚከፋፈለው ክትባት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከፊት ተሰልፈው እየሰሩ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ብቻ የሚያገኙት ሳይሆን፣ ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አካላትንም ለመከተብ ያስችላል ብሏል። ሁሉም የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባት እንዲያገኙ የሚሰራው ኮቫክስ የተሰኘው ጥምረት ክትባቱን መቼ እነደሚያጓጉዝ እና የትኛው አገር ምን ያህል እና መቼ ያገኛል የሚለውን ዝርዝር አውጥቶ መጨረሱ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባትን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ መስጠት መጀመር አለባቸው ብሏል። በዓለም ጤና ድርጅት ከክትባት ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ዶ/ር ሪቻርድ ሚሂንጎ ክትባቱ በሚቀጥሉት አንድና ሁለት ሳምንታት መሰጠት እንዲጀምር "አገራት የመጀመሪያውን ደረጃ ዝግጁነት ያሟላሉ ብለን ተስፋ አእናደርጋለን" ካሉ በኋላ በየካቲት ወር መጨረሻ ክትባቱ መሰጠት እነደሚጀምር ገልፀዋል። ይህ ኮቫክስ ለአፍሪካ አገራት የሚሰጠው 90 ሚሊዮን ክትባት የመጀመሪያው ዙር ሲሆን እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ድረስ 600 ሚሊዮን ያህል ክትባቶች ለአፍሪካ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠብቅ ተገልጿል። ይህ ክትባት አገራት ካላቸው የሕዝብ ብዛት ውስጥ እስከ 20 በመቶ ድረስ መከተብ ያስችላቸዋል ተብሏል። በፈረንጆች 2022 እያንዳንዱ አፍሪካዊ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ያገኛል ተብሎ እቅድ መቀመጡንም ጤና ድርጅቱ አስታውቋል። ከኮቫክስ በአቻነት የአፍሪካ ሕብረት የጀመረው ጥረት መኖሩን የተናገረው የዓለም ጤና ድርጅት በእነዚህ ሁለት መንገዶች በሚገኝ ክትባት በ2021 መጨረሻ እስከ 40 በመቶ የሚደርሱ አፍሪካውያን ክትባቱን ያገኛሉ ተብሎ ታቅዷል። ይህም በ2022፣ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ አፍሪካውያን ክትባቱን ማግኘት ያስችላቸዋል ማለት ነው። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ (ጅማሮ) ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ጅማሪ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ጅማሮ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል። ይህ አገራቱ የኮቪድ-19 ክትባትን ስርጭት እንዴት ለማካሄድ በሚወስኑት ውሳኔ ላይ ይመሰረታል። የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና መካለከል ላይ ከፊት ያሉ በመሆኑ ክትባቱን ቅድሚያ ማግኘት እንዳለባቸው ያስቀምጣል። በመቀጠል ደግሞ ወደ አገራት መግቢያና መውጫ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች፣ በእድሜ የገፉ ሰዎችና የተለያዩ ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ክትባቱን ከሌሎች ዜጎች ቀድመው ያገኛሉ ሲል አስቀምጧል። ቀሪው ሕዝብ እነዚህ ዜጎች ከተከተቡ በኋላ ይሰጠዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት በመመሪያ ላይ አመልክቷል። | ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኮቪድ ክትባት መስጠት ትጀምራለች ተባለ የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም የአፍሪካ አገራት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ "ከፍተኛ ቅድሚያ" ለሚሰጣቸው ሰዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት መከተብ አለባቸው አለ። ኮቫክስ 90 ሚሊዮን ክትባቶችን ወደ አፍሪካ በቅርቡ ማሰራጨት ይጀምራል ያለው የዓለም ጤና ድርጅት፣ የስርጭት መጠኑም የሚወሰነው አገራት ባላቸው የሕዝብ ብዛት መጠን መሆኑ ተመልክቷል። ለእያንዳንዱ አገር የሚከፋፈለው ክትባት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከፊት ተሰልፈው እየሰሩ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ብቻ የሚያገኙት ሳይሆን፣ ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አካላትንም ለመከተብ ያስችላል ብሏል። ሁሉም የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባት እንዲያገኙ የሚሰራው ኮቫክስ የተሰኘው ጥምረት ክትባቱን መቼ እነደሚያጓጉዝ እና የትኛው አገር ምን ያህል እና መቼ ያገኛል የሚለውን ዝርዝር አውጥቶ መጨረሱ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባትን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ መስጠት መጀመር አለባቸው ብሏል። በዓለም ጤና ድርጅት ከክትባት ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ዶ/ር ሪቻርድ ሚሂንጎ ክትባቱ በሚቀጥሉት አንድና ሁለት ሳምንታት መሰጠት እንዲጀምር "አገራት የመጀመሪያውን ደረጃ ዝግጁነት ያሟላሉ ብለን ተስፋ አእናደርጋለን" ካሉ በኋላ በየካቲት ወር መጨረሻ ክትባቱ መሰጠት እነደሚጀምር ገልፀዋል። ይህ ኮቫክስ ለአፍሪካ አገራት የሚሰጠው 90 ሚሊዮን ክትባት የመጀመሪያው ዙር ሲሆን እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ድረስ 600 ሚሊዮን ያህል ክትባቶች ለአፍሪካ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠብቅ ተገልጿል። ይህ ክትባት አገራት ካላቸው የሕዝብ ብዛት ውስጥ እስከ 20 በመቶ ድረስ መከተብ ያስችላቸዋል ተብሏል። በፈረንጆች 2022 እያንዳንዱ አፍሪካዊ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ያገኛል ተብሎ እቅድ መቀመጡንም ጤና ድርጅቱ አስታውቋል። ከኮቫክስ በአቻነት የአፍሪካ ሕብረት የጀመረው ጥረት መኖሩን የተናገረው የዓለም ጤና ድርጅት በእነዚህ ሁለት መንገዶች በሚገኝ ክትባት በ2021 መጨረሻ እስከ 40 በመቶ የሚደርሱ አፍሪካውያን ክትባቱን ያገኛሉ ተብሎ ታቅዷል። ይህም በ2022፣ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ አፍሪካውያን ክትባቱን ማግኘት ያስችላቸዋል ማለት ነው። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ (ጅማሮ) ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ጅማሪ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ጅማሮ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል። ይህ አገራቱ የኮቪድ-19 ክትባትን ስርጭት እንዴት ለማካሄድ በሚወስኑት ውሳኔ ላይ ይመሰረታል። የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና መካለከል ላይ ከፊት ያሉ በመሆኑ ክትባቱን ቅድሚያ ማግኘት እንዳለባቸው ያስቀምጣል። በመቀጠል ደግሞ ወደ አገራት መግቢያና መውጫ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች፣ በእድሜ የገፉ ሰዎችና የተለያዩ ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ክትባቱን ከሌሎች ዜጎች ቀድመው ያገኛሉ ሲል አስቀምጧል። ቀሪው ሕዝብ እነዚህ ዜጎች ከተከተቡ በኋላ ይሰጠዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት በመመሪያ ላይ አመልክቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55950980 |
0business
| የአሜሪካ ሴኔት ቦይንግ አብራሪዎችን በተሳሳተ መልኩ አሰልጥኖ ነበር አለ | የአሜሪካ ሴኔት መርማሪዎች የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላኖችን የሚፈትሹ አብራሪዎችን 'ተገቢ ባልሆነ መልኩ' ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል ሲሉ ከሰሱ። በወራት ልዩነት ሁለት አደጋዎች ማጋጠማቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ መጋቢት 2019 ላይ እንዳያበሩ ታግደው ነበር። መርማሪዎቹ እንደሚሉት ቦይንግ እና የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) በመመሳጠር ስለአውሮፕላኖቹ ወሳኝ መረጃዎችን ሆን ብለው ለመደበቅ ሞክረዋል። ቦይንግ በበኩሉ በምርመራው የተገኙትን መረጃዎች በሙሉ እየተመለከታቸው እንደሆነና ጉዳዩን በጥብቅ የሚያው እንደሆነ የገለጸ ሲሆን የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር በበኩሉ ምንም ስህተት አልሰራሁም ብሎ ነበር። ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር በነበረው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕን የደረሰው አደጋ ከመከሰቱ በፊት የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ቡድን በዚህ መሰል አውሮፕላኖች የደህንነት ስጋት እንዳለ ለኩባንያው አሳውቀው እንደነበር መገለጹ ይታወሳል። ግንቦት 2019 ላይ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በኢንዶኔዥያ ከደረሰው አደጋ በኋላ ኤምካስ (MCAS) ተብሎ በሚጠራው መቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ ችግር እንደነበረበትና በአፋጣኝ እንዲፈታ አሳስበው እንደነበርም ተገልጾ ነበር። በወቅቱ ቦይንግ ግን አብራሪዎች ያነሱትን ጥያቄ ወደጎን በመተው ወደ ፊት የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሩን ለማስተካከል ቃል መግባቱ ተገልጿል። የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር የአሜሪካ ሴኔት በመረጃ የልተደገፈ ውንጀላ እያደረገ እንደሆነ በመግለጽ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ያደረገው ምርመራ በጥልቀት የተካሄደ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የአንዶኔዥያው ላየን ኤይር ንብረት የሆነው 737 ማክስ 8 ተከስክሶ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው ነበሩት 189 ሰዎች ማለቃቸው ይታወሳል። አደጋው በተከሰተበት ወቅት የኢንዶኔዥያ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋው አውሮፕላኑ ላይ በነበረ እክል ምክንያት ነው የተከሰተው ቢሉም ድርጅቱ እጄ የለበትም ማለቱ ይታወሳል። ከአምስት ወራት በኋላ ደግሞ መጋቢት 1 ቀን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር የነበረው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ለ157 ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። ትናንት አርብ ዕለት የሴኔት መርማሪ ኮሚቴው ባወጣው ሪፖርት ላይ ከድርጅቱ በሚስጥራዊ መንገድ አገኘሁት ባለው መረጃ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር እና ቦይንግ ከምርመራው ቀደም ብለው የምርመራው ውጤት እነሱ በሚፈልጉት መንገድ እንዲሆን አድርገዋል ብሏል። ይህ ሪፖርት የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ባሳለፍነው ወር ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በድጋሚ መብረር እንዲጀምሩ ከፈቀደ በኋላ መሆኑ ቦይንግን ያስደሰተው አይመስልም። በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ የብራዚሉ ጎል አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ እንደሚመልስ ማስታወቁ የሚታወስ ነው። የብራዚል ግዙፉ አየር መንገድ ጎል እንዳለው፤ 140 የሚሆኑ አውሮፕላን አብራሪዎቹ በአውሮፕላኑ አሜሪካ ውስጥ ሥልጠና ወስደዋል። ሰባት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹን ለ27 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች ማዘጋጀቱን አየር መንገዱ ገልጿል። እስካሁን 737 ማክስ ወደ በረራ እንዲመለስ የፈቀዱት አሜሪካ እና ብራዚል ናቸው። | የአሜሪካ ሴኔት ቦይንግ አብራሪዎችን በተሳሳተ መልኩ አሰልጥኖ ነበር አለ የአሜሪካ ሴኔት መርማሪዎች የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላኖችን የሚፈትሹ አብራሪዎችን 'ተገቢ ባልሆነ መልኩ' ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል ሲሉ ከሰሱ። በወራት ልዩነት ሁለት አደጋዎች ማጋጠማቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ መጋቢት 2019 ላይ እንዳያበሩ ታግደው ነበር። መርማሪዎቹ እንደሚሉት ቦይንግ እና የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) በመመሳጠር ስለአውሮፕላኖቹ ወሳኝ መረጃዎችን ሆን ብለው ለመደበቅ ሞክረዋል። ቦይንግ በበኩሉ በምርመራው የተገኙትን መረጃዎች በሙሉ እየተመለከታቸው እንደሆነና ጉዳዩን በጥብቅ የሚያው እንደሆነ የገለጸ ሲሆን የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር በበኩሉ ምንም ስህተት አልሰራሁም ብሎ ነበር። ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር በነበረው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕን የደረሰው አደጋ ከመከሰቱ በፊት የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ቡድን በዚህ መሰል አውሮፕላኖች የደህንነት ስጋት እንዳለ ለኩባንያው አሳውቀው እንደነበር መገለጹ ይታወሳል። ግንቦት 2019 ላይ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በኢንዶኔዥያ ከደረሰው አደጋ በኋላ ኤምካስ (MCAS) ተብሎ በሚጠራው መቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ ችግር እንደነበረበትና በአፋጣኝ እንዲፈታ አሳስበው እንደነበርም ተገልጾ ነበር። በወቅቱ ቦይንግ ግን አብራሪዎች ያነሱትን ጥያቄ ወደጎን በመተው ወደ ፊት የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሩን ለማስተካከል ቃል መግባቱ ተገልጿል። የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር የአሜሪካ ሴኔት በመረጃ የልተደገፈ ውንጀላ እያደረገ እንደሆነ በመግለጽ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ያደረገው ምርመራ በጥልቀት የተካሄደ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የአንዶኔዥያው ላየን ኤይር ንብረት የሆነው 737 ማክስ 8 ተከስክሶ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው ነበሩት 189 ሰዎች ማለቃቸው ይታወሳል። አደጋው በተከሰተበት ወቅት የኢንዶኔዥያ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋው አውሮፕላኑ ላይ በነበረ እክል ምክንያት ነው የተከሰተው ቢሉም ድርጅቱ እጄ የለበትም ማለቱ ይታወሳል። ከአምስት ወራት በኋላ ደግሞ መጋቢት 1 ቀን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር የነበረው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ለ157 ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። ትናንት አርብ ዕለት የሴኔት መርማሪ ኮሚቴው ባወጣው ሪፖርት ላይ ከድርጅቱ በሚስጥራዊ መንገድ አገኘሁት ባለው መረጃ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር እና ቦይንግ ከምርመራው ቀደም ብለው የምርመራው ውጤት እነሱ በሚፈልጉት መንገድ እንዲሆን አድርገዋል ብሏል። ይህ ሪፖርት የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ባሳለፍነው ወር ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በድጋሚ መብረር እንዲጀምሩ ከፈቀደ በኋላ መሆኑ ቦይንግን ያስደሰተው አይመስልም። በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ የብራዚሉ ጎል አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ እንደሚመልስ ማስታወቁ የሚታወስ ነው። የብራዚል ግዙፉ አየር መንገድ ጎል እንዳለው፤ 140 የሚሆኑ አውሮፕላን አብራሪዎቹ በአውሮፕላኑ አሜሪካ ውስጥ ሥልጠና ወስደዋል። ሰባት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹን ለ27 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች ማዘጋጀቱን አየር መንገዱ ገልጿል። እስካሁን 737 ማክስ ወደ በረራ እንዲመለስ የፈቀዱት አሜሪካ እና ብራዚል ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-55375186 |
0business
| መርዛማ ሊድን አጋልጣ 423 ሚሊዮን ብር ያገኘችው ፊሊስ ኦሚዶ | ፊሊስ ኦሚዶ ኬንያዊት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2009 ላይ ለምትሠራበት ድርጅት ስጋቷን ስትገልጽ፤ ይህን ጉዳይ ዳግመኛ እንዳታነሺ ተብላ ነበር። ፊሊስ ትሠራበት የነበረው ድርጅት የሚያካሂደው የባትሪ መልሶ ጥቅም ላይ (ሪሳይክሊንግ) ሂደት የሰዎችን ሕይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል ነበር ለአሠሪዎቿ የተናገረችው። ነገር ግን ሰሚ ጆሮ አላገኘችም። በአሠሪዎቿ “ዝም በይ” ብትባልም ፊሊስ አልሰማቻቸውም። ያኔ 31 ዓመቷ ነበር። ገና ከዩኒቨርስቲ እንደተመረቀች ሞምባሳ የሚገኝ ‘ኬንያ ሜታል ሪፈረንስስ’ የሚባል ድርጅት ውስጥ ተቀጠረች። ድርጅቱ የመኪና ባትሪን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ሊድ የተሰኘውን ንጥረ ነገር ያመርታል። መርዛማ ጭስ ፊሊስ የድርጅቱ ክንውኖች አካባቢ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ተጽዕኖ እንድታጠና ተጠይቃ ነበር። ሆኖም ግን ግኝቷን ለድርጅቱ ስታሳውቅ እርምጃ ከመውሰድ ይቆጠባሉ። ባትሪ የማቅለጥ ሂደቱ አየር ከመበከሉም በላይ ተረፈ ምርቱ የሚጣለው በድርጅቱ አቅራቢያ የሚገኘው የኦዊኖ ማኅበረሰብ መኖሪያ አካባቢ ነው። ድርጅቱ የአካባቢውን አየርም ውሀም እየበከለ ነበር። ሠራተኞቹ ላይም ጉዳት ደርሷል። • ዶናልድ ትራምፕ 'ቲክቶክ' አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ ሊያግዱ ነው ከልጅነቷ ጀምሮ ተፈጥሮን የምትወደው ፊሊስ፤ 2009 ላይ ችግሩ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ አልተረዳችም ነበር። ፊሊስ የ15 ዓመት ወጣት ሳለች እናቷ ከሞቱ በኋላ ወደ ሞምበሳ አቀናች። ዩኒቨርስቲ ስትገባ መማር የምትፈልገው የአካባቢ ጥናት ነበር። ሆኖም የቢሮ ሠራተኛ የሚያደርጋት ዘርፍን ማጥናት ግድ ሆነባት። ምንነቱ ያልታወቀው ህመም በቢሮ ሠራተኛነት የተቀጠረችበት ድርጅት እሷ ለምትወደው ነገር ደንታ አልነበረውም። ፊሊስም ቅሬታዋን ይዛ በድርጅቱ መሥራት ቀጠለች። 2010 ላይ የሁለት ኣመት ልጇ ታመመ። የተለያዩ ሕክምናዎች ቢሰጡትም፤ ህመሙ ሊታወቅለች፣ ሊያገግምም አልቻለም። የልጇ ህመም ተባብሶ ሆስፒታል አልጋ ያዘ። ያኔ አንድ ጓደኛዋ ልጇ በሊድ ተመርዞ ከሆነ እንድታስመረምረው መከረቻት። • ፌስቡክ እና ጉግል ለሚያወጡት ዜና እንዲከፍሉ ሊገደዱ ነው ምርመራ ሲደረግለት ደሙ ውስጥ ከፍተኛ የሊድ መጠን ተገኘ። ልጇ ጡት ሲጠባ ለንጥረ ነገሩ ተጋልጦ እንደሆነ ስትረዳ እጅግ ተደናገጠች። ተበሳጭታ ሥራዋን ለቀቀች። ከዛም ድርጅቱ የልጇን የሕክምና ወጪ እንዲሸፍን መጎትጎት ጀመረች። ማኅበረሰቡ ውስጥ ከሚኖሩ ልጆች ሦስቱ ምርመራ እንዲደረግላቸው ገፋፍታ ያገኘችው ውጤት ፍርሀቷን እውን ያደረገ ነበር። “ውሸትሽን ነው” ፊሊስ የምርመራ ውጤቶቹን ይዛ የመንግሥት ተቋሞች ጣልቃ እንዲገቡ ደብዳቤ መጻፍ ጀመረች። ቢሆንም ምላሽ እንዳልሰጧት ትናገራለች። “ብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የማወራው ነገር ውሸት እንደሆነና ፍርድ ቤት ብሄድም ራሳቸውን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ጻፉልኝ” ስትል ትገልጻለች። ለድርጅቱ ፍቃድ እንዲሰጥ ያደረገው ይህ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ነው። • ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች ፊሊስ ያላት እውነተኛ መረጃ እንደሆነ ለማሳየት ከአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ድርጅት ጋር በመጣመር ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሄዱ አደረገች። ማስረጃ ቢኖራትም የመንግሥት ባለሥልጣኖች ጫና ሊያሳድሩባት ሞክረዋል። “ቀስ በቀስ ነበር የምንቀሳቀሰው። ሥራችን በበጎ ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ነበር። በኢ-ፍትሐዊ መንገድ ስታሰር ለዋስ የምከፍለው ገንዘብ እንኳን አልነበረኝም። 17 ሰዎች በዋስ እንድወጣ አደረጉ።” 2012 ላይ ሞምባሳ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ካስተባበች በኋላ፤ ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረሻል ተብላ ለአንድ ምሽት ታስራ ነበር። ‘ፍሮንት ላይን ዲፌንደርስ’ እና ‘ኢስት አፍሪካን ሎው ሶሳይቲ’ የተባሉ የሕግ ጉዳዮች የተራድኦ ድርጅቶች ፊሊስ ክሱን እንድትከላከል የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተዋል። ኋላ ላይ የሰልፉ አስተባባሪዎች ላይ ማስረጃ ባለመገኘቱ ክሱ ተቋረጠ። ድብደባ ፊሊስ ከ204 በፊት የነበረውን ጊዜ “በጣም ከባድ” ስትል ትገልጸዋለች። ትግሏን ለማቀረጥ የተቃበረችበት ወቅት እንደነበረም ታስታውሳለች። ከመንግሥት ባለሥለጣኖች የሚደርሳት ማስፈራሪያ ያስጨንቃት ነበር። ቤቷ በር ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ወንዶች ድብደባ ደርሶባት ለአንድ ወር ተደብቃም ነበር። “ሲደበድቡኝ ጎረቤቴ ስለደረሰ ነው የተረፍኩት። ተደብድቤ የተጣልኩበት ቦታ የመኪናው መብራት ሲበራ ልጄ እየጮኸ ነበር።” • ኮሮናቫይረስ ለምን ጥቁሮች ላይ እንደሚበረታ ሊጠና ነው የፊሊስ ቤተሰቦች ልጇ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነገር ውስጥ እንደገባች በማሰብ፤ በተፈጠረው ነገር ደስተኛ አልነበሩም። እሷ ግን የሚተማመኑባትን የማኅበረሰቡ አባላት ችላ ማለት አልፈለገችም። በተለይ 2011 ላይ ማኅበረሰቡ ውይይት አድርጎ ሲጨርስ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ የተኮሱባቸውን ጊዜ አትዘነጋም። “አደገኛ እፅ እየፈለግን ነው በሚል ሰበብ የሰዎች ቤት ላይ ጉዳት አደረሱ። ትንሽ ገቢ ያላቸው ድሆች አሉ። የነሱን ቤት ከሚጎዱ እኔን ቢያስሩኝ ይሻለኝ ነበር።” ካሳ ፊሊስን መሰናክሎቹ አላስቋሟትም። ማኅበረሰቡን ለመታደግ ለዓሥር ዓመታት ያለመታከት ፍድድ ቤት ቆማ ታግላለች። በስተመጨረሻም ድል ቀንቶት፤ ፍርድ ቤቱ 12 ሚሊዮን ዶላር (423 ሚሊዮን ዶላር ገደማ) ካሳ አግኝታለች። ካሳውን የሚከፍሉት አካባቢ ያለ እየደረሰ የነበረውን ጉዳት ችላ ያሉ የመንግሥት ተቋሞች እና የመኪና ባትሪ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውለው ድርጅት ነው። ፍርድ ቤቱ አካባቢው በአራት ወር ውስጥ እንዲጸዳም ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔው ካልተተገበተ ሌላ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። “ገንዘቡ 3000 የሚሆኑት የማኅበረሰቡ አባለት ያዩትን ስቃይ አይተካም። ሆኖም ግን ገንዘቡ ለሕምናና መድኃኒት መግዣ ይውላል” ብላለች። ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት የተበየኑ የካሳ ክፍያዎች በአፋጣኝ ተጎጂዎች እጅ እንዳልገቡ ስለምታውቅ፤ ፊልሰን ትግሉ እንዳልተቋጨ ትናገራለች። እስከ መስከረም አጋማሽ የካሳ ገንዘቡ እጃቸው ካልገባ ዝም እንደማትልም ታስረግጣለች። | መርዛማ ሊድን አጋልጣ 423 ሚሊዮን ብር ያገኘችው ፊሊስ ኦሚዶ ፊሊስ ኦሚዶ ኬንያዊት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2009 ላይ ለምትሠራበት ድርጅት ስጋቷን ስትገልጽ፤ ይህን ጉዳይ ዳግመኛ እንዳታነሺ ተብላ ነበር። ፊሊስ ትሠራበት የነበረው ድርጅት የሚያካሂደው የባትሪ መልሶ ጥቅም ላይ (ሪሳይክሊንግ) ሂደት የሰዎችን ሕይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል ነበር ለአሠሪዎቿ የተናገረችው። ነገር ግን ሰሚ ጆሮ አላገኘችም። በአሠሪዎቿ “ዝም በይ” ብትባልም ፊሊስ አልሰማቻቸውም። ያኔ 31 ዓመቷ ነበር። ገና ከዩኒቨርስቲ እንደተመረቀች ሞምባሳ የሚገኝ ‘ኬንያ ሜታል ሪፈረንስስ’ የሚባል ድርጅት ውስጥ ተቀጠረች። ድርጅቱ የመኪና ባትሪን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ሊድ የተሰኘውን ንጥረ ነገር ያመርታል። መርዛማ ጭስ ፊሊስ የድርጅቱ ክንውኖች አካባቢ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ተጽዕኖ እንድታጠና ተጠይቃ ነበር። ሆኖም ግን ግኝቷን ለድርጅቱ ስታሳውቅ እርምጃ ከመውሰድ ይቆጠባሉ። ባትሪ የማቅለጥ ሂደቱ አየር ከመበከሉም በላይ ተረፈ ምርቱ የሚጣለው በድርጅቱ አቅራቢያ የሚገኘው የኦዊኖ ማኅበረሰብ መኖሪያ አካባቢ ነው። ድርጅቱ የአካባቢውን አየርም ውሀም እየበከለ ነበር። ሠራተኞቹ ላይም ጉዳት ደርሷል። • ዶናልድ ትራምፕ 'ቲክቶክ' አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ ሊያግዱ ነው ከልጅነቷ ጀምሮ ተፈጥሮን የምትወደው ፊሊስ፤ 2009 ላይ ችግሩ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ አልተረዳችም ነበር። ፊሊስ የ15 ዓመት ወጣት ሳለች እናቷ ከሞቱ በኋላ ወደ ሞምበሳ አቀናች። ዩኒቨርስቲ ስትገባ መማር የምትፈልገው የአካባቢ ጥናት ነበር። ሆኖም የቢሮ ሠራተኛ የሚያደርጋት ዘርፍን ማጥናት ግድ ሆነባት። ምንነቱ ያልታወቀው ህመም በቢሮ ሠራተኛነት የተቀጠረችበት ድርጅት እሷ ለምትወደው ነገር ደንታ አልነበረውም። ፊሊስም ቅሬታዋን ይዛ በድርጅቱ መሥራት ቀጠለች። 2010 ላይ የሁለት ኣመት ልጇ ታመመ። የተለያዩ ሕክምናዎች ቢሰጡትም፤ ህመሙ ሊታወቅለች፣ ሊያገግምም አልቻለም። የልጇ ህመም ተባብሶ ሆስፒታል አልጋ ያዘ። ያኔ አንድ ጓደኛዋ ልጇ በሊድ ተመርዞ ከሆነ እንድታስመረምረው መከረቻት። • ፌስቡክ እና ጉግል ለሚያወጡት ዜና እንዲከፍሉ ሊገደዱ ነው ምርመራ ሲደረግለት ደሙ ውስጥ ከፍተኛ የሊድ መጠን ተገኘ። ልጇ ጡት ሲጠባ ለንጥረ ነገሩ ተጋልጦ እንደሆነ ስትረዳ እጅግ ተደናገጠች። ተበሳጭታ ሥራዋን ለቀቀች። ከዛም ድርጅቱ የልጇን የሕክምና ወጪ እንዲሸፍን መጎትጎት ጀመረች። ማኅበረሰቡ ውስጥ ከሚኖሩ ልጆች ሦስቱ ምርመራ እንዲደረግላቸው ገፋፍታ ያገኘችው ውጤት ፍርሀቷን እውን ያደረገ ነበር። “ውሸትሽን ነው” ፊሊስ የምርመራ ውጤቶቹን ይዛ የመንግሥት ተቋሞች ጣልቃ እንዲገቡ ደብዳቤ መጻፍ ጀመረች። ቢሆንም ምላሽ እንዳልሰጧት ትናገራለች። “ብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የማወራው ነገር ውሸት እንደሆነና ፍርድ ቤት ብሄድም ራሳቸውን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ጻፉልኝ” ስትል ትገልጻለች። ለድርጅቱ ፍቃድ እንዲሰጥ ያደረገው ይህ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ነው። • ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች ፊሊስ ያላት እውነተኛ መረጃ እንደሆነ ለማሳየት ከአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ድርጅት ጋር በመጣመር ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሄዱ አደረገች። ማስረጃ ቢኖራትም የመንግሥት ባለሥልጣኖች ጫና ሊያሳድሩባት ሞክረዋል። “ቀስ በቀስ ነበር የምንቀሳቀሰው። ሥራችን በበጎ ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ነበር። በኢ-ፍትሐዊ መንገድ ስታሰር ለዋስ የምከፍለው ገንዘብ እንኳን አልነበረኝም። 17 ሰዎች በዋስ እንድወጣ አደረጉ።” 2012 ላይ ሞምባሳ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ካስተባበች በኋላ፤ ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረሻል ተብላ ለአንድ ምሽት ታስራ ነበር። ‘ፍሮንት ላይን ዲፌንደርስ’ እና ‘ኢስት አፍሪካን ሎው ሶሳይቲ’ የተባሉ የሕግ ጉዳዮች የተራድኦ ድርጅቶች ፊሊስ ክሱን እንድትከላከል የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተዋል። ኋላ ላይ የሰልፉ አስተባባሪዎች ላይ ማስረጃ ባለመገኘቱ ክሱ ተቋረጠ። ድብደባ ፊሊስ ከ204 በፊት የነበረውን ጊዜ “በጣም ከባድ” ስትል ትገልጸዋለች። ትግሏን ለማቀረጥ የተቃበረችበት ወቅት እንደነበረም ታስታውሳለች። ከመንግሥት ባለሥለጣኖች የሚደርሳት ማስፈራሪያ ያስጨንቃት ነበር። ቤቷ በር ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ወንዶች ድብደባ ደርሶባት ለአንድ ወር ተደብቃም ነበር። “ሲደበድቡኝ ጎረቤቴ ስለደረሰ ነው የተረፍኩት። ተደብድቤ የተጣልኩበት ቦታ የመኪናው መብራት ሲበራ ልጄ እየጮኸ ነበር።” • ኮሮናቫይረስ ለምን ጥቁሮች ላይ እንደሚበረታ ሊጠና ነው የፊሊስ ቤተሰቦች ልጇ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነገር ውስጥ እንደገባች በማሰብ፤ በተፈጠረው ነገር ደስተኛ አልነበሩም። እሷ ግን የሚተማመኑባትን የማኅበረሰቡ አባላት ችላ ማለት አልፈለገችም። በተለይ 2011 ላይ ማኅበረሰቡ ውይይት አድርጎ ሲጨርስ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ የተኮሱባቸውን ጊዜ አትዘነጋም። “አደገኛ እፅ እየፈለግን ነው በሚል ሰበብ የሰዎች ቤት ላይ ጉዳት አደረሱ። ትንሽ ገቢ ያላቸው ድሆች አሉ። የነሱን ቤት ከሚጎዱ እኔን ቢያስሩኝ ይሻለኝ ነበር።” ካሳ ፊሊስን መሰናክሎቹ አላስቋሟትም። ማኅበረሰቡን ለመታደግ ለዓሥር ዓመታት ያለመታከት ፍድድ ቤት ቆማ ታግላለች። በስተመጨረሻም ድል ቀንቶት፤ ፍርድ ቤቱ 12 ሚሊዮን ዶላር (423 ሚሊዮን ዶላር ገደማ) ካሳ አግኝታለች። ካሳውን የሚከፍሉት አካባቢ ያለ እየደረሰ የነበረውን ጉዳት ችላ ያሉ የመንግሥት ተቋሞች እና የመኪና ባትሪ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውለው ድርጅት ነው። ፍርድ ቤቱ አካባቢው በአራት ወር ውስጥ እንዲጸዳም ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔው ካልተተገበተ ሌላ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። “ገንዘቡ 3000 የሚሆኑት የማኅበረሰቡ አባለት ያዩትን ስቃይ አይተካም። ሆኖም ግን ገንዘቡ ለሕምናና መድኃኒት መግዣ ይውላል” ብላለች። ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት የተበየኑ የካሳ ክፍያዎች በአፋጣኝ ተጎጂዎች እጅ እንዳልገቡ ስለምታውቅ፤ ፊልሰን ትግሉ እንዳልተቋጨ ትናገራለች። እስከ መስከረም አጋማሽ የካሳ ገንዘቡ እጃቸው ካልገባ ዝም እንደማትልም ታስረግጣለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-53620643 |
3politics
| የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ድምፅ መስጠት ተጀመረ | የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ዛሬ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል፡፡ ከአረብ ሊግ የተወከሉ የምርጫው ታዛቢ ሁሉም ነገር በሰላም እየተካሄደ ነው ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ከ 200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ጉሌህ ለ 22 አመታት አገሪቷን አስተዳድረዋል፡፡ የበቢሲው ዘጋቢ መሃመድ አብዲራሂም እንዳለው ዋና ዋና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫው የማስመሰል ምርጫ ነው በሚል ጥለው ወጥተዋል፡፡ ብቸኛ ተፎካካሪያቸው ዘካሪያ ኢስማኤል እምብዛም የማይታወቁ ነጋዴ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሰራወት ውስጥ አባልም ነበሩ፡ ተፎካካሪያቸው የፅዳት እቃዎችን ከውጪ አገራት የሚያስገቡ ሲሆን ባለፈው ጥር ለምርጫ እንደሚወዳደሩ ይፋ እስከሚያደርጉ ድረስ በሕዝቡ ዘንድ የሚያውቃቸው አልነበረም፡፡ የ 57 አመት ጎልማሳው ለጉሌህ ስጋት እንደማይሀኑ እና ፕሬዘዳንት ጉሌህ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡ በስትራቴጂያዊ አቀማመጧ ለቀጠናው ቁልፍ ከሚባሉ አገራት መካከል የሆነችው ትንሿ አገር ጂቡቲ ከአንድ ሚሊዮን የሚያንስ ህዝብ ያላት ሲሆን አሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ የሃያላን አገራት የወታደራዊ መቀመጫ መሆኗ ይታወቃል፡፡ | የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ድምፅ መስጠት ተጀመረ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ዛሬ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል፡፡ ከአረብ ሊግ የተወከሉ የምርጫው ታዛቢ ሁሉም ነገር በሰላም እየተካሄደ ነው ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ከ 200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ጉሌህ ለ 22 አመታት አገሪቷን አስተዳድረዋል፡፡ የበቢሲው ዘጋቢ መሃመድ አብዲራሂም እንዳለው ዋና ዋና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫው የማስመሰል ምርጫ ነው በሚል ጥለው ወጥተዋል፡፡ ብቸኛ ተፎካካሪያቸው ዘካሪያ ኢስማኤል እምብዛም የማይታወቁ ነጋዴ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሰራወት ውስጥ አባልም ነበሩ፡ ተፎካካሪያቸው የፅዳት እቃዎችን ከውጪ አገራት የሚያስገቡ ሲሆን ባለፈው ጥር ለምርጫ እንደሚወዳደሩ ይፋ እስከሚያደርጉ ድረስ በሕዝቡ ዘንድ የሚያውቃቸው አልነበረም፡፡ የ 57 አመት ጎልማሳው ለጉሌህ ስጋት እንደማይሀኑ እና ፕሬዘዳንት ጉሌህ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡ በስትራቴጂያዊ አቀማመጧ ለቀጠናው ቁልፍ ከሚባሉ አገራት መካከል የሆነችው ትንሿ አገር ጂቡቲ ከአንድ ሚሊዮን የሚያንስ ህዝብ ያላት ሲሆን አሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ የሃያላን አገራት የወታደራዊ መቀመጫ መሆኗ ይታወቃል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-56686721 |
2health
| የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ | በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ "ማዕከል" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። "ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመላው አህጉሪቱ ክትባቱን የመስጠት ምጣኔው ቀንሷል። በስፔን ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሁለቱን ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ቁጥር በፈረንሳይ እና በጀርመን ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ፣ 68 በመቶ እና 66 በመቶ ላይ ይገኛል። የአንዳንድ የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች አሃዝ ደግሞ ከዚህም ዝቅተኛ ነው። እአአ ጥቅምት 2021 ሙሉ ለሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሩሲያውያን 32 በመቶ ብቻ ናቸው። ክሉጅ የማዕከላዊ እስያ ክፍልን ጨምሮ 53 ሃገሮችን በሚሸፍነው የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ዞን የህዝብ ጤና እርምጃዎችን መላላትን ለበሽታው መባባስ እንደተጨማሪ ምክንያት አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በአካባቢው እስካሁን 1.4 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን መዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካል ኃላፊ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ምንም እንኳን "በቂ የክትባት እና የመሳሪያ አቅርቦት" ቢኖርም ወረርሽኙ ባለፉት አራት ሳምንታት በመላው አውሮፓ ከ 55 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል ብለዋል። ባልደረባቸው ዶክተር ማይክ ሪያን የአውሮፓ ተሞክሮ "ለዓለም የማስጠንቀቂያ ደወል ነው" ሲሉ ገልጸውታል። በጀርመን ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወደ 34000 የሚጠጉ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በጀርመን ያለው የኮቪድ ስርጭት በዕለት ከ 37000 የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ ከሚያዙባት የዩኬ የቅርብ ጊዜ ቁጥሮች በታች ነው። የህብረተሰብ ጤና ባለሥልጣናት ግን አራተኛው ማዕበል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ሊያስከትል እና በጤና ስርዓቱ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 165 ሰዎች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከአንድ ሳምንት በፊት ከነበረው 126 ሞት ጨማሪ አሳይቷል። የጀርመን አርኬአይ ኢንስቲትዩቱ ሎተር ዊለር ስለ አስፈሪ ቁጥሮች ተናግረዋል። "አሁን የመከላከያ እርምጃዎችን ካልወሰድን አራተኛው ማዕበል የበለጠ አደጋ ያመጣል" ብለዋል። ክትባቱን ካልወሰዱት ጀርመናውያን መካከል ከ60 በላይ ዕድሜ ያላቸው ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሲሆን እነዚሀም ለበለጠ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። ሃንስ ክሉጅ እንደሚሉት የቫይረሱ መጨመር በጀርመን ብቻ የተገደበ አይደለም። ባለፈው ሳምንት የሟቾች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በሩሲያ ሲሆን ከ 8,100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በዩክሬን ደግሞ 3800 ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱም ሀገራት በጣም ዝቅተኛ ክትባት የሰጡ ሲሆን ዩክሬን ባለፉት 24 ሰዓታት 27377 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ሮማኒያ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የ591 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች። በሃንጋሪ በየዕለቱ በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ከእጥፍ በላይ አድጎ ባለፈው ሳምንት 6268 ደርሷል። ጭንብል መልበስ አስገዳጅ የሆነው በሕዝብ ማመላለሻዎች እና በሆስፒታሎች ብቻ ነው። ዶክተር ሪያን "በአሁን ተጨማሪ ጥቂት ሰዎችን ከከተብን ወረርሽኙ አብቅቷል የሚል ሃሳብ ላይ ነን። ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም" ብለው ሃገራት ቀዳዳቸውን እንዲደፍኑ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። የደች መንግሥት ጭንብል መልበስ እና አካላዊ መራራቅን ህዝብ በሚሰባሰብበት ቦታዎች ላይ እንደሚጀምር በዚህ ሳምንት ተናግሯል። ምክንያቱ ያለው ደግሞ በሳምንት ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች የመያዝ ምጣኔ በ 31 በመቶ ከፍ በማለቱ ነው ። የኮቪድ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ላትቪያ ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥታለች። ክሮሺያ ሐሙስ ዕለት 6310 አዳዲስ በቫእረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ይህ ቁጥር እስካሁን ድረስ ከታየው ከፍተኛው ቁጥር ነው። ስሎቫኪያ ሁለተኛውን ከፍተኛ ቁጥር መዝግባለች። የቼክ ስርጭት በፀደይ ወቅት ወደ ነበረበት ደረጃ ተመልሷል። የእንግሊዝ ምክትል ዋና የህክምና መኮንን ፕሮፌሰር ጆናታን ቫን ታም በበኩላቸው በጣም ብዙ ሰዎች ወረርሽኙ እንዳበቃ ያምናሉ ብለዋል። ከፍተኛ የክትባት መጠን በደረሰባቸው ሃገሮች የስርጭት መጠኑ አሁንም በአንጻራዊነት ሁኔታ ዝቅተኛ ነው። ጣሊያን ከ12 አመት በላይ ለሆኑት ዜጎቿ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ክትባት ብትሰጥም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በ16.6 በመቶ ጨምሯል። ከመስከረም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖርቹጋል የስርጭት መጠን ከ 1000 በላይ ሆኗል። ረቡዕ 2287 ሰዎች በቫይረሱ የታዩዛበት ስፔን የስርጭት መጨመር ካላዩት ጥቂት ሃገሮች አንዷ ሆናለች። | የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ "ማዕከል" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። "ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመላው አህጉሪቱ ክትባቱን የመስጠት ምጣኔው ቀንሷል። በስፔን ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሁለቱን ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ቁጥር በፈረንሳይ እና በጀርመን ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ፣ 68 በመቶ እና 66 በመቶ ላይ ይገኛል። የአንዳንድ የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች አሃዝ ደግሞ ከዚህም ዝቅተኛ ነው። እአአ ጥቅምት 2021 ሙሉ ለሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሩሲያውያን 32 በመቶ ብቻ ናቸው። ክሉጅ የማዕከላዊ እስያ ክፍልን ጨምሮ 53 ሃገሮችን በሚሸፍነው የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ዞን የህዝብ ጤና እርምጃዎችን መላላትን ለበሽታው መባባስ እንደተጨማሪ ምክንያት አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በአካባቢው እስካሁን 1.4 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን መዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካል ኃላፊ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ምንም እንኳን "በቂ የክትባት እና የመሳሪያ አቅርቦት" ቢኖርም ወረርሽኙ ባለፉት አራት ሳምንታት በመላው አውሮፓ ከ 55 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል ብለዋል። ባልደረባቸው ዶክተር ማይክ ሪያን የአውሮፓ ተሞክሮ "ለዓለም የማስጠንቀቂያ ደወል ነው" ሲሉ ገልጸውታል። በጀርመን ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወደ 34000 የሚጠጉ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በጀርመን ያለው የኮቪድ ስርጭት በዕለት ከ 37000 የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ ከሚያዙባት የዩኬ የቅርብ ጊዜ ቁጥሮች በታች ነው። የህብረተሰብ ጤና ባለሥልጣናት ግን አራተኛው ማዕበል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ሊያስከትል እና በጤና ስርዓቱ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 165 ሰዎች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከአንድ ሳምንት በፊት ከነበረው 126 ሞት ጨማሪ አሳይቷል። የጀርመን አርኬአይ ኢንስቲትዩቱ ሎተር ዊለር ስለ አስፈሪ ቁጥሮች ተናግረዋል። "አሁን የመከላከያ እርምጃዎችን ካልወሰድን አራተኛው ማዕበል የበለጠ አደጋ ያመጣል" ብለዋል። ክትባቱን ካልወሰዱት ጀርመናውያን መካከል ከ60 በላይ ዕድሜ ያላቸው ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሲሆን እነዚሀም ለበለጠ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። ሃንስ ክሉጅ እንደሚሉት የቫይረሱ መጨመር በጀርመን ብቻ የተገደበ አይደለም። ባለፈው ሳምንት የሟቾች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በሩሲያ ሲሆን ከ 8,100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በዩክሬን ደግሞ 3800 ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱም ሀገራት በጣም ዝቅተኛ ክትባት የሰጡ ሲሆን ዩክሬን ባለፉት 24 ሰዓታት 27377 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ሮማኒያ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የ591 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች። በሃንጋሪ በየዕለቱ በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ከእጥፍ በላይ አድጎ ባለፈው ሳምንት 6268 ደርሷል። ጭንብል መልበስ አስገዳጅ የሆነው በሕዝብ ማመላለሻዎች እና በሆስፒታሎች ብቻ ነው። ዶክተር ሪያን "በአሁን ተጨማሪ ጥቂት ሰዎችን ከከተብን ወረርሽኙ አብቅቷል የሚል ሃሳብ ላይ ነን። ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም" ብለው ሃገራት ቀዳዳቸውን እንዲደፍኑ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። የደች መንግሥት ጭንብል መልበስ እና አካላዊ መራራቅን ህዝብ በሚሰባሰብበት ቦታዎች ላይ እንደሚጀምር በዚህ ሳምንት ተናግሯል። ምክንያቱ ያለው ደግሞ በሳምንት ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች የመያዝ ምጣኔ በ 31 በመቶ ከፍ በማለቱ ነው ። የኮቪድ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ላትቪያ ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥታለች። ክሮሺያ ሐሙስ ዕለት 6310 አዳዲስ በቫእረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ይህ ቁጥር እስካሁን ድረስ ከታየው ከፍተኛው ቁጥር ነው። ስሎቫኪያ ሁለተኛውን ከፍተኛ ቁጥር መዝግባለች። የቼክ ስርጭት በፀደይ ወቅት ወደ ነበረበት ደረጃ ተመልሷል። የእንግሊዝ ምክትል ዋና የህክምና መኮንን ፕሮፌሰር ጆናታን ቫን ታም በበኩላቸው በጣም ብዙ ሰዎች ወረርሽኙ እንዳበቃ ያምናሉ ብለዋል። ከፍተኛ የክትባት መጠን በደረሰባቸው ሃገሮች የስርጭት መጠኑ አሁንም በአንጻራዊነት ሁኔታ ዝቅተኛ ነው። ጣሊያን ከ12 አመት በላይ ለሆኑት ዜጎቿ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ክትባት ብትሰጥም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በ16.6 በመቶ ጨምሯል። ከመስከረም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖርቹጋል የስርጭት መጠን ከ 1000 በላይ ሆኗል። ረቡዕ 2287 ሰዎች በቫይረሱ የታዩዛበት ስፔን የስርጭት መጨመር ካላዩት ጥቂት ሃገሮች አንዷ ሆናለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-59165910 |
3politics
| በሶማሌ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አባላት መካከል የተከሰተው ምንድን ነው? | የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የቀድሞ አባላት ነን ያሉ አካላት የክልሉን ብልጽግና ፓርቲ 'ለማረም እና ለማስተካከል' በሚል እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ጅግጅጋ ላይ የተሰባሰቡ የፓርቲው የቀድሞ አመራሮች በቁጥር ከ10 በላይ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም ሌሎች የፓርቲው የቀድሞ አባላትና አመራሮች አብረዋቸው መኖራቸውን ገልፀዋል። ቡድኑ እንቅስቃሴውን 'የክልሉን ሕዝብ ለማዳን' በሚል መጀመሩን ጨምረው ተናግርዋል። የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ኃላፊ የነበሩት እና አሁን የተቃዋሚው ቡድኑ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙት አቶ ሐቢብ ሐጂ መሐሙድ ለቢቢሲ ሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት፣ 'የብልጽግና ፓርቲ መስመሩን ስቷል' ሲሉ ተናግረዋል። እንደ አቶ ሐቢብ ገለጻ አሁን ያለውን የብልጽግና አመራር በመቃወም የተሰባሰቡት አካላት ከዚህ ቀደም የቢሮ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላት የነበሩ እና ክልሉን ከ15 እስከ 20 ዓመት በተለያዩ የፖለቲካ ዘርፎች ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው። የክልሉ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ በበኩላቸው እነዚህ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ያሉ አካላት "ከድርጅቱ አባልነት የተባረሩና ከኃላፊነታቸው የተነሱ ግለሰቦች ናቸው" ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። "ከኃላፊነታቸው የተባረሩ እና ያኮረፉ ግለሰቦች ስብሰብ ነው" ሲሉ የተናገሩት የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ በፓርቲው ውስጥ ያለውን ስህተት ለማስተካከል እንደ ድርጅት ዝግጅት ላይ ነን ሲሉ አክለዋል። ኢንጂነር መሐመድ አክለውም በማኅበራዊ ሚዲያዎች የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ተከፋፍሏል በሚል የሚናፈሰው መረጃ "ስህተት እና ተቀባይነት የሌለው" መሆኑን ጨምረው ያስረዳሉ። አቶ ሐቢብ በበኩላቸው ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት የተባረሩ የብልጽግና የቀድሞ አባላት ናቸው የሚለው የጽህፈት ቤት ኃላፊውን ምላሽ "ሐሰት" ሲሉ አጣጥለውታል። አቶ ሐቢብ አክለውም በፓርቲው ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲሁም በሁሉም ደረጃ ሙስና መኖሩንም ይናገራሉ። አክለውም የክልሉ መንግሥት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን አስሯል በሚል ተጨማሪ ክስ ያቀርባሉ። አቶ መሐመድ በበኩላቸው ፓርቲው በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሄድ እና አስፈላጊውን ማስተካከያ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። አቶ መሐመድ ሻሌ የተቃዋሚ አባላት ታስረዋል የሚለውን ክስ ውድቅ አድርገዋል። በገዢው ፓርቲ ውስጥ አሉ ያሏቸውን ችግሮች አንስተው ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት ግለሰቦች በፓርቲው ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን ከማንሳታቸው ባሻገር ሌሎችም ነገሮችን ጠቅሰዋል። በዚህም በድርቅ የተጎዳው የክልሉ ሕዝብ በቂ ድጋፍ እየተደረገለት አይደለም የሚሉት አቶ ሐቢብ፣ የኑሮ ውድነት በሕዝብ ላይ እያስከተለ ስላለው ጫና፣ በክልሉ ስላለው የወጣቶች ሥራ አጥነት ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል እንደሚገኙበት ይናገራሉ። በአጠቃላይ ሕዝቡ 'የወደፊት ራዕዩ' የጨለመ አካሄድ በክልሉ ሰፍኗል ሲሉ የሚናገሩት አቶ ሐቢብ፣ በስልጣን ላይ ያሉት የፓርቲው አባላት በቂ ልምድ እና እውቀት የላቸውም ሲሉ ይተቻሉ። የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ ግን ከፓርቲው እራሳቸውን የነጠሉት ግለሰቦች ያቀረቧቸው ክሶች ተቀባይነት የሌላቸውና ክልሉ ለተጠቀሱትን ችግሮች መፍትሔ ለማበጀት ፓርቲውና የክልሉ መስተዳደር የሚጠበቅባቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። | በሶማሌ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አባላት መካከል የተከሰተው ምንድን ነው? የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የቀድሞ አባላት ነን ያሉ አካላት የክልሉን ብልጽግና ፓርቲ 'ለማረም እና ለማስተካከል' በሚል እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ጅግጅጋ ላይ የተሰባሰቡ የፓርቲው የቀድሞ አመራሮች በቁጥር ከ10 በላይ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም ሌሎች የፓርቲው የቀድሞ አባላትና አመራሮች አብረዋቸው መኖራቸውን ገልፀዋል። ቡድኑ እንቅስቃሴውን 'የክልሉን ሕዝብ ለማዳን' በሚል መጀመሩን ጨምረው ተናግርዋል። የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ኃላፊ የነበሩት እና አሁን የተቃዋሚው ቡድኑ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙት አቶ ሐቢብ ሐጂ መሐሙድ ለቢቢሲ ሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት፣ 'የብልጽግና ፓርቲ መስመሩን ስቷል' ሲሉ ተናግረዋል። እንደ አቶ ሐቢብ ገለጻ አሁን ያለውን የብልጽግና አመራር በመቃወም የተሰባሰቡት አካላት ከዚህ ቀደም የቢሮ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላት የነበሩ እና ክልሉን ከ15 እስከ 20 ዓመት በተለያዩ የፖለቲካ ዘርፎች ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው። የክልሉ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ በበኩላቸው እነዚህ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ያሉ አካላት "ከድርጅቱ አባልነት የተባረሩና ከኃላፊነታቸው የተነሱ ግለሰቦች ናቸው" ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። "ከኃላፊነታቸው የተባረሩ እና ያኮረፉ ግለሰቦች ስብሰብ ነው" ሲሉ የተናገሩት የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ በፓርቲው ውስጥ ያለውን ስህተት ለማስተካከል እንደ ድርጅት ዝግጅት ላይ ነን ሲሉ አክለዋል። ኢንጂነር መሐመድ አክለውም በማኅበራዊ ሚዲያዎች የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ተከፋፍሏል በሚል የሚናፈሰው መረጃ "ስህተት እና ተቀባይነት የሌለው" መሆኑን ጨምረው ያስረዳሉ። አቶ ሐቢብ በበኩላቸው ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት የተባረሩ የብልጽግና የቀድሞ አባላት ናቸው የሚለው የጽህፈት ቤት ኃላፊውን ምላሽ "ሐሰት" ሲሉ አጣጥለውታል። አቶ ሐቢብ አክለውም በፓርቲው ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲሁም በሁሉም ደረጃ ሙስና መኖሩንም ይናገራሉ። አክለውም የክልሉ መንግሥት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን አስሯል በሚል ተጨማሪ ክስ ያቀርባሉ። አቶ መሐመድ በበኩላቸው ፓርቲው በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሄድ እና አስፈላጊውን ማስተካከያ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። አቶ መሐመድ ሻሌ የተቃዋሚ አባላት ታስረዋል የሚለውን ክስ ውድቅ አድርገዋል። በገዢው ፓርቲ ውስጥ አሉ ያሏቸውን ችግሮች አንስተው ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት ግለሰቦች በፓርቲው ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን ከማንሳታቸው ባሻገር ሌሎችም ነገሮችን ጠቅሰዋል። በዚህም በድርቅ የተጎዳው የክልሉ ሕዝብ በቂ ድጋፍ እየተደረገለት አይደለም የሚሉት አቶ ሐቢብ፣ የኑሮ ውድነት በሕዝብ ላይ እያስከተለ ስላለው ጫና፣ በክልሉ ስላለው የወጣቶች ሥራ አጥነት ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል እንደሚገኙበት ይናገራሉ። በአጠቃላይ ሕዝቡ 'የወደፊት ራዕዩ' የጨለመ አካሄድ በክልሉ ሰፍኗል ሲሉ የሚናገሩት አቶ ሐቢብ፣ በስልጣን ላይ ያሉት የፓርቲው አባላት በቂ ልምድ እና እውቀት የላቸውም ሲሉ ይተቻሉ። የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ ግን ከፓርቲው እራሳቸውን የነጠሉት ግለሰቦች ያቀረቧቸው ክሶች ተቀባይነት የሌላቸውና ክልሉ ለተጠቀሱትን ችግሮች መፍትሔ ለማበጀት ፓርቲውና የክልሉ መስተዳደር የሚጠበቅባቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60333655 |
3politics
| የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡ ኡጋንዳ በምርጫው ዋዜማ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ አደረገች | በዛሬው ዕለት ምርጫ በምታካሂደው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ከዋዜማው ጀምሮ እንዲቋረጥ መደረጉ ተገልጿል። የኢንተርኔትን ሁኔታ በበላይነት የሚቆጣጠር ኔት ብሎክስ የተሰኘው ቡድን በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ከትናንትና ምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ በመላው አገሪቱ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ነው። ይህ የባለስልጣናቱ ኢንተርኔት የማቋረጥ ውሳኔም በቅርቡ የትኛውም የትኛውም አይነት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ የተላለፈውንም ይከተላል። ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኑ እንዳሉት ፌስቡክ የፓርቲያቸውን ደጋፊዎች አካውንት እንዲታገድ በማድረጉ ይህ ውሳኔ እንደተላለፈ አስታውቀዋል። በአፍሪካ ውስጥ ለረዥም ዘመናት ስልጣን ከተቆጣጠሩት አንዱ በሆኑት ዩዌሪ ሙሴቪኒና በታዋቂው ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚጠበቅም እየተነገረ ነው። ሙዚቀኛውና ለእጬ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው ቦቢ ዋይን በበኩሉ የኢንተርኔት መቋረጥ ምርጫውን የማጭበርበር አካልም እንደሆነ በትዊተር ገፁ አስፍሯል። "የኡጋንዳ ህዝብ በከፍተኛ ፅናትና ውሳኔ ላይ ነው። ይህንን ጨቋኝ መንግሥትም ከስልጣን ለማውረድ የሚያግደው ኃይል አይኖርም" በማለትም አስፍሯል። የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር መሰረት ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ የሚከፈቱ ሲሆን ውጤቱም እስከ ቅዳሜ ድረስ ይፋ እንደማይሆንም ተገልጿል። አገሪቱ ዘንድሮ ልታካሂደው ያሰበችው ምርጫ ከፍተኛ ሁከቶችን አስተናግዷል። በተለይም በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት በተነሱ አመፆችና ሁከቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል። ለ35 አመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ለስድስተኛ ጊዜም አገሪቷን ለማስተዳደር ይወዳደራሉ። | የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡ ኡጋንዳ በምርጫው ዋዜማ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ አደረገች በዛሬው ዕለት ምርጫ በምታካሂደው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ከዋዜማው ጀምሮ እንዲቋረጥ መደረጉ ተገልጿል። የኢንተርኔትን ሁኔታ በበላይነት የሚቆጣጠር ኔት ብሎክስ የተሰኘው ቡድን በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ከትናንትና ምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ በመላው አገሪቱ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ነው። ይህ የባለስልጣናቱ ኢንተርኔት የማቋረጥ ውሳኔም በቅርቡ የትኛውም የትኛውም አይነት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ የተላለፈውንም ይከተላል። ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኑ እንዳሉት ፌስቡክ የፓርቲያቸውን ደጋፊዎች አካውንት እንዲታገድ በማድረጉ ይህ ውሳኔ እንደተላለፈ አስታውቀዋል። በአፍሪካ ውስጥ ለረዥም ዘመናት ስልጣን ከተቆጣጠሩት አንዱ በሆኑት ዩዌሪ ሙሴቪኒና በታዋቂው ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚጠበቅም እየተነገረ ነው። ሙዚቀኛውና ለእጬ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው ቦቢ ዋይን በበኩሉ የኢንተርኔት መቋረጥ ምርጫውን የማጭበርበር አካልም እንደሆነ በትዊተር ገፁ አስፍሯል። "የኡጋንዳ ህዝብ በከፍተኛ ፅናትና ውሳኔ ላይ ነው። ይህንን ጨቋኝ መንግሥትም ከስልጣን ለማውረድ የሚያግደው ኃይል አይኖርም" በማለትም አስፍሯል። የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር መሰረት ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ የሚከፈቱ ሲሆን ውጤቱም እስከ ቅዳሜ ድረስ ይፋ እንደማይሆንም ተገልጿል። አገሪቱ ዘንድሮ ልታካሂደው ያሰበችው ምርጫ ከፍተኛ ሁከቶችን አስተናግዷል። በተለይም በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት በተነሱ አመፆችና ሁከቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል። ለ35 አመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ለስድስተኛ ጊዜም አገሪቷን ለማስተዳደር ይወዳደራሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-55657685 |
2health
| በአሜሪካ የኮቪድ ክትባት ያልተከተበው ግለሰብ የልብ ንቅለ ተከላ ተሰረዘ | በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ታካሚው የኮቪድ-19 ክትባት ባለመውሰዱ የልብ ንቅለ ተከላውን ሰረዘ። ዲጄ ፈርጉሰን የተሰኘው የ31 ዓመት ታካሚ አንገብጋቢ የሆነ የልብ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ቢሆንም በቦስተን የሚገኘው ሆስፒታል ግን ግለሰቡን ከታካሚዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል። የብሪንግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል የልብ ንቅለ ተከላውን የሰረዘው ታካሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ባለመውሰዱ ነው። የታካሚው ወላጅ አባት ዴቪክ፤ የኮቪድ ክትባት ከልጃቸው መሠረታዊ መርሆች ጋር የሚቃረን መሆኑን በመግለጽ ልጃቸው በክትባት እንደማያምን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በበኩሉ ንቅለ ተከላውን የሰረዝኩት መመሪያ በመከተል ነው ብሏል። "በውስጥ አካላት ጉዳት ምክንያት በንቅለ ተከላ አዲስ የውስጥ አካል የተቀበለ ታካሚ በሕይወት የመትረፍ እድሉ ከፍተኛ እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲል የብሪግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል ለቢቢሲ ገልጿል። የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ሆስፒታላቸው የታካሚዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ከግምት በማስገባት ንቅለ ተከላው የመሳካት እድሉን እና ታካሚዎች ከቀዶ ጥገናው በኋላ የመትረፍ እድላቸው ከፍ ለማድረግ ከንቅለ ተከላ በፊት የኮቪድ-19 ክትባት እና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደሚመለከቱ ገልጸዋል። በሆስፒታሉ የአካል ክፍሎችን ለመተካት በተጠባባቂ መዝገብ ውስጥ ከሚገኙት 100,000 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአምስት ዓአመት ጊዜ ውስጥ የውስጥ አካል እንደማያገኙ እና የአካል ክፍሎች እጥረት ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፈርጉሰን ባጋጠመው የልብ ሕመም ምክንያት ላለፉት አራት ወራት ሆስፒታል ተኝቶ በመታከም ላይ ይገኛል። ለግለሰቡ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ላይ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ፈርጉሰን ክትባቱን ከወሰደ በልቡ ላይ ተጨማሪ ሕመሞች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ሰግተዋል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ኤጄንሲ ሲዲሲ በበኩሉ የንቅለ ተከላ ተቀባዮች እና በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ እንዲሁም ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ያበረታታል። ዶ/ር አርተር ካፕላን በኒዩ ግሮስማን የሕክምና ትምህርት ቤት የሕክምና ሥነ ምግባር ኃላፊ ናቸው። ለሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም የሰውነት አካል ከተቀየረ በኋላ የታካሚው በሽታ የመከላከል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። በተጨማሪም በተራ ጉንፋን እንኳን ለሞት ሊዳርግ ይችላል። "የውስጥ አካል ክፍሎቹ በጣም አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው አናሳ የመዳን እድል ላለው ሰው ላለመስጠት እንሞክራለን። ሌሎች ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ከንቅለ ተከላው በኋላ የመዳን እድላቸው ከፍተኛ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ወላጅ አባቱም ልጃቸው በራሱ ሰውነት ላይ የመወሰን መብት እንዳለው እና ሕመሙንም በጀግንነት እየታገለ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ አስቸጋሪ ግዜ ውስጥ ባሳየው ቁርጠኝነትም ለልጃቸው ያላቸው ክብር መጨመሩን ተናግረዋል። | በአሜሪካ የኮቪድ ክትባት ያልተከተበው ግለሰብ የልብ ንቅለ ተከላ ተሰረዘ በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ታካሚው የኮቪድ-19 ክትባት ባለመውሰዱ የልብ ንቅለ ተከላውን ሰረዘ። ዲጄ ፈርጉሰን የተሰኘው የ31 ዓመት ታካሚ አንገብጋቢ የሆነ የልብ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ቢሆንም በቦስተን የሚገኘው ሆስፒታል ግን ግለሰቡን ከታካሚዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል። የብሪንግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል የልብ ንቅለ ተከላውን የሰረዘው ታካሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ባለመውሰዱ ነው። የታካሚው ወላጅ አባት ዴቪክ፤ የኮቪድ ክትባት ከልጃቸው መሠረታዊ መርሆች ጋር የሚቃረን መሆኑን በመግለጽ ልጃቸው በክትባት እንደማያምን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በበኩሉ ንቅለ ተከላውን የሰረዝኩት መመሪያ በመከተል ነው ብሏል። "በውስጥ አካላት ጉዳት ምክንያት በንቅለ ተከላ አዲስ የውስጥ አካል የተቀበለ ታካሚ በሕይወት የመትረፍ እድሉ ከፍተኛ እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲል የብሪግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል ለቢቢሲ ገልጿል። የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ሆስፒታላቸው የታካሚዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ከግምት በማስገባት ንቅለ ተከላው የመሳካት እድሉን እና ታካሚዎች ከቀዶ ጥገናው በኋላ የመትረፍ እድላቸው ከፍ ለማድረግ ከንቅለ ተከላ በፊት የኮቪድ-19 ክትባት እና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደሚመለከቱ ገልጸዋል። በሆስፒታሉ የአካል ክፍሎችን ለመተካት በተጠባባቂ መዝገብ ውስጥ ከሚገኙት 100,000 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአምስት ዓአመት ጊዜ ውስጥ የውስጥ አካል እንደማያገኙ እና የአካል ክፍሎች እጥረት ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፈርጉሰን ባጋጠመው የልብ ሕመም ምክንያት ላለፉት አራት ወራት ሆስፒታል ተኝቶ በመታከም ላይ ይገኛል። ለግለሰቡ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ላይ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ፈርጉሰን ክትባቱን ከወሰደ በልቡ ላይ ተጨማሪ ሕመሞች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ሰግተዋል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ኤጄንሲ ሲዲሲ በበኩሉ የንቅለ ተከላ ተቀባዮች እና በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ እንዲሁም ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ያበረታታል። ዶ/ር አርተር ካፕላን በኒዩ ግሮስማን የሕክምና ትምህርት ቤት የሕክምና ሥነ ምግባር ኃላፊ ናቸው። ለሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም የሰውነት አካል ከተቀየረ በኋላ የታካሚው በሽታ የመከላከል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። በተጨማሪም በተራ ጉንፋን እንኳን ለሞት ሊዳርግ ይችላል። "የውስጥ አካል ክፍሎቹ በጣም አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው አናሳ የመዳን እድል ላለው ሰው ላለመስጠት እንሞክራለን። ሌሎች ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ከንቅለ ተከላው በኋላ የመዳን እድላቸው ከፍተኛ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ወላጅ አባቱም ልጃቸው በራሱ ሰውነት ላይ የመወሰን መብት እንዳለው እና ሕመሙንም በጀግንነት እየታገለ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ አስቸጋሪ ግዜ ውስጥ ባሳየው ቁርጠኝነትም ለልጃቸው ያላቸው ክብር መጨመሩን ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60136750 |
0business
| ኮሮናቫይረስ ፡ አርጀንቲና በኮቪድ-19 ሰበብ ባለሀብቶች ላይ አዲስ ግብር ጣለች | አርጀንቲና ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ሕክምና የሚያስፈልጉ የሕክምና አቅርቦቶችን ለማሟላትና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላትን ወጪ ለመሸፈን ሀብታም ዜጓቿ ላይ አዲስ ግብር ጣለች። ይህ አንድ ጊዜ የሚከፈለውና "የሚሊየነሮች ግብር" የተባለውን ታክስ ለመጣል የወጣው ረቂቅ ለአርጀንቲና ምክር ቤት አባላት ቀርቦ 26 እንደራሴዎች ቢቃወሙትም የ42ቱን ድጋፍ በማግኘቱ ጸድቋል። ይህ ግብር ይመለከታቸዋል የተባሉት የአርጀንቲና ባለጸጋዎች ሀብታቸው ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን ብዛታቸውም 12 ሺህ እንደሚሆኑ ታውቋል። አርጀንቲና እስካሁን 1.5 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያረጋገጠች ሲሆን 40 ሺህ የሚደርሱት ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ለሞት ተዳርገውባታል። አርጀንቲና በወረርሽኙ ክፉኛ ከተመቱ የዓለም አገራት መካከል አንዷ ስትሆን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህሙማን በማስመዝገብ አምስተኛዋ አገር ሆናለች። አገሪቱ ያላት አጠቃላይ ሕዝብ 45 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን ከቁጥር አንጻር በበሽታው የተያዙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከተገኙባቸው አገራት መካከል ትንሽ የሕዝብ ቁጥር ያላት አገር ሆናለች። ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ የምትገኘው አርጀንቲና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በሚል የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ በሥራ አጥነት፣ በድህነትና በመንግሥት ዕዳ ላይ ተጨማሪ ጫናን ፈጥሯል።. በአገሪቱ ባለሀብቶች ላይ የተጣለው አዲሱ ግብር ከአጠቃላዩ ግብር ከፋይ 0.8 በመቶውን ብቻ የሚመለከት መሆኑን የግብሩን ደንብ ካረቀቁት ሰዎች መካከል አንዱ ተናግረዋል። ግብሩን ይከፍላሉ ተብለው የሚጠበቁት ሚሊየነሮች በአገር ውስጥ ካላቸው ሀብት እየጨመረ በሚሄድ ሁኔታ አስከ 3.5 በመቶ እንዲሁም በውጪ አገር ካላቸው ሀብት ደግሞ 5.25 በመቶ እንደሚሆን ተገልጿል። የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደዘገበው፤ በአዲሱ ግብር አማካይነት ከሚሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 20 በመቶው ለሕክምና አቅርቦቶች፣ 20 በመቶው ለአነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት ድጋፍ፣ 20 በመቶው ለተማሪዎች የነጻ ትምርት ዕድል ድጋፍ፣ 15 በመቶው ለማኅበራዊ ልማትና ቀሪው 25 በመቶው ደግሞ ለተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ሥራ ይውላል። በአዲሱ ታክስ አማካይነት በፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ የሚመራው የአርጀንቲና መንግሥት 300 የአርጀንቲና ፔሶ ወይም ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ተቃዋሚዎች አዲሱ ግብር እንደተባለው የአንድ ጊዜ ብቻ ላይሆን እንደሚችልና የውጭ መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾችን ሊያሸሽ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አንደኛው ተቃዋሚ ፓርቲ አዲሱን ሕግ ሀብት "የመውረስ" ድርጊት ሲል ተቃውሞታል። | ኮሮናቫይረስ ፡ አርጀንቲና በኮቪድ-19 ሰበብ ባለሀብቶች ላይ አዲስ ግብር ጣለች አርጀንቲና ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ሕክምና የሚያስፈልጉ የሕክምና አቅርቦቶችን ለማሟላትና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላትን ወጪ ለመሸፈን ሀብታም ዜጓቿ ላይ አዲስ ግብር ጣለች። ይህ አንድ ጊዜ የሚከፈለውና "የሚሊየነሮች ግብር" የተባለውን ታክስ ለመጣል የወጣው ረቂቅ ለአርጀንቲና ምክር ቤት አባላት ቀርቦ 26 እንደራሴዎች ቢቃወሙትም የ42ቱን ድጋፍ በማግኘቱ ጸድቋል። ይህ ግብር ይመለከታቸዋል የተባሉት የአርጀንቲና ባለጸጋዎች ሀብታቸው ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን ብዛታቸውም 12 ሺህ እንደሚሆኑ ታውቋል። አርጀንቲና እስካሁን 1.5 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያረጋገጠች ሲሆን 40 ሺህ የሚደርሱት ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ለሞት ተዳርገውባታል። አርጀንቲና በወረርሽኙ ክፉኛ ከተመቱ የዓለም አገራት መካከል አንዷ ስትሆን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህሙማን በማስመዝገብ አምስተኛዋ አገር ሆናለች። አገሪቱ ያላት አጠቃላይ ሕዝብ 45 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን ከቁጥር አንጻር በበሽታው የተያዙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከተገኙባቸው አገራት መካከል ትንሽ የሕዝብ ቁጥር ያላት አገር ሆናለች። ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ የምትገኘው አርጀንቲና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በሚል የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ በሥራ አጥነት፣ በድህነትና በመንግሥት ዕዳ ላይ ተጨማሪ ጫናን ፈጥሯል።. በአገሪቱ ባለሀብቶች ላይ የተጣለው አዲሱ ግብር ከአጠቃላዩ ግብር ከፋይ 0.8 በመቶውን ብቻ የሚመለከት መሆኑን የግብሩን ደንብ ካረቀቁት ሰዎች መካከል አንዱ ተናግረዋል። ግብሩን ይከፍላሉ ተብለው የሚጠበቁት ሚሊየነሮች በአገር ውስጥ ካላቸው ሀብት እየጨመረ በሚሄድ ሁኔታ አስከ 3.5 በመቶ እንዲሁም በውጪ አገር ካላቸው ሀብት ደግሞ 5.25 በመቶ እንደሚሆን ተገልጿል። የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደዘገበው፤ በአዲሱ ግብር አማካይነት ከሚሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 20 በመቶው ለሕክምና አቅርቦቶች፣ 20 በመቶው ለአነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት ድጋፍ፣ 20 በመቶው ለተማሪዎች የነጻ ትምርት ዕድል ድጋፍ፣ 15 በመቶው ለማኅበራዊ ልማትና ቀሪው 25 በመቶው ደግሞ ለተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ሥራ ይውላል። በአዲሱ ታክስ አማካይነት በፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ የሚመራው የአርጀንቲና መንግሥት 300 የአርጀንቲና ፔሶ ወይም ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ተቃዋሚዎች አዲሱ ግብር እንደተባለው የአንድ ጊዜ ብቻ ላይሆን እንደሚችልና የውጭ መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾችን ሊያሸሽ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አንደኛው ተቃዋሚ ፓርቲ አዲሱን ሕግ ሀብት "የመውረስ" ድርጊት ሲል ተቃውሞታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55200359 |
3politics
| ተጨማሪ ሁለት ፓርቲዎች በሶማሌ ክልል ከሚደረገው ምርጫ እራሳቸውን አገለሉ | በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሶማሌ ክልል ተሳታፊ የነበሩ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አስታወቁ። በሶማሌ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት እጩዎችን አቅርበው የነበሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የነፃነትና የእኩልነት ፓርቲ (ነዕፓ) ከመጪው ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል። ከሁለቱ ፓርቲዎች በተጨማሪ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) መስከረም 20 ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ እንደማይሳተፍ ማስታወቁ ይታወሳል። ኦብነግ በምርጫው አልሳተፍም ያለው፤ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ መፍትሄ ባለማግኘቱ እንደሆነ፣ የኦብነግ የአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብዱላሂ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ኢዜማ እና ነዕፓ በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ ሂደት እንዲሁም ከአጠቃላይ የምርጫ ሕግ እና ሥርዓት ጋር በተያያዘ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረብናቸው ቅሬታዎች ሊፈቱ ባለመቻላቸው እራሳችንን ከምርጫው አግልለናል ብለዋል። ሁለቱ ፓርቲዎች፤ ከዚህ በፊት ተሰርቆ የነበረው የምርጫ ቁሳቁስ በአዲስ እንዲተካ የጠየቅን ቢሆንም አሁን ግን ቀድሞ ተዘርፎ በነበረው ካርድ ወደ ምርጫ በመገባቱ ምርጫው ተዓማኒነት አይኖረውም" ብለዋል በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ። ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲዎቹ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መዋቅር ከመንግሥት መዋቅር ጋር የተዋሀደ በመሆኑ የምርጫውን ፍትሀዊነት እና ተዓማኒነት ያሳጣል የሚሉ እና ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር ከምርጫው እራሳቸውን ማግለላቸውን ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ መስከረም 20 የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ ትናንት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ምርጫ ባልተደረገበት የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ በነበረበት ወቅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቱታ ቀርቦ እንደነበር ቦርዱ አስታውሷል። ይህን ተከትሎም በክልሉ በሰባት ምርጫ ክልሎች በድጋሚ የመራጮች ምዝገባ ተከናውኗል ብሏል ቦርዱ። የመራጮች ምዝገባ የተካሄደውም ቦርዱ ባሰማራው አጣሪ ቡድን ውሳኔ ላይ መስረት በማድረግ መሆኑም ተገልጿል። መስከረም 20 2014 ዓ.ም. በሶማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዚሁ ዕለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመሆን ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል። በዚህ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት 7.6 ሚሊዮን ሕዝብ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቋል። በፀጥታ ችግር፣ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዩ ግድፈቶች፣ በመራጮች ምዝገባ ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ የድምፅ መስጫው ቀን በአንዳንድ ክልሎች የምርጫ ክልሎች እንዲራዘም መወሰኑ ይታወቃል። | ተጨማሪ ሁለት ፓርቲዎች በሶማሌ ክልል ከሚደረገው ምርጫ እራሳቸውን አገለሉ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሶማሌ ክልል ተሳታፊ የነበሩ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አስታወቁ። በሶማሌ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት እጩዎችን አቅርበው የነበሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የነፃነትና የእኩልነት ፓርቲ (ነዕፓ) ከመጪው ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል። ከሁለቱ ፓርቲዎች በተጨማሪ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) መስከረም 20 ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ እንደማይሳተፍ ማስታወቁ ይታወሳል። ኦብነግ በምርጫው አልሳተፍም ያለው፤ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ መፍትሄ ባለማግኘቱ እንደሆነ፣ የኦብነግ የአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብዱላሂ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ኢዜማ እና ነዕፓ በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ ሂደት እንዲሁም ከአጠቃላይ የምርጫ ሕግ እና ሥርዓት ጋር በተያያዘ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረብናቸው ቅሬታዎች ሊፈቱ ባለመቻላቸው እራሳችንን ከምርጫው አግልለናል ብለዋል። ሁለቱ ፓርቲዎች፤ ከዚህ በፊት ተሰርቆ የነበረው የምርጫ ቁሳቁስ በአዲስ እንዲተካ የጠየቅን ቢሆንም አሁን ግን ቀድሞ ተዘርፎ በነበረው ካርድ ወደ ምርጫ በመገባቱ ምርጫው ተዓማኒነት አይኖረውም" ብለዋል በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ። ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲዎቹ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መዋቅር ከመንግሥት መዋቅር ጋር የተዋሀደ በመሆኑ የምርጫውን ፍትሀዊነት እና ተዓማኒነት ያሳጣል የሚሉ እና ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር ከምርጫው እራሳቸውን ማግለላቸውን ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ መስከረም 20 የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ ትናንት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ምርጫ ባልተደረገበት የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ በነበረበት ወቅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቱታ ቀርቦ እንደነበር ቦርዱ አስታውሷል። ይህን ተከትሎም በክልሉ በሰባት ምርጫ ክልሎች በድጋሚ የመራጮች ምዝገባ ተከናውኗል ብሏል ቦርዱ። የመራጮች ምዝገባ የተካሄደውም ቦርዱ ባሰማራው አጣሪ ቡድን ውሳኔ ላይ መስረት በማድረግ መሆኑም ተገልጿል። መስከረም 20 2014 ዓ.ም. በሶማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዚሁ ዕለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመሆን ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል። በዚህ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት 7.6 ሚሊዮን ሕዝብ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቋል። በፀጥታ ችግር፣ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዩ ግድፈቶች፣ በመራጮች ምዝገባ ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ የድምፅ መስጫው ቀን በአንዳንድ ክልሎች የምርጫ ክልሎች እንዲራዘም መወሰኑ ይታወቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58640081 |
3politics
| የትግራይ ኃይሎች አላማጣና ኮረምን መቆጣጠራቸው ተነገረ | የትግራይ ኃይሎች በደቡባዊ ትግራይ የምትገኘውን ኮረም ከተማን መቆጣጠራቸው ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ። ክልሉ ከጦርነቱ በፊት የነበረ ግዛቶችን በሙሉ ለማስመለስ እየተካሄደ ነው የተባለውም ጦርነት ወደ ደቡብ ክፍል መቀጠሉንም ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል። ሮይተርስ የህወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው ረዳን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የትግራይ ኃይሎች ከመቀለ በስተደቡብ በኩል 170 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ኮረም ከተማ መቆጣጠራቸውን ነው። ሰኞ ዕለት አመሻሽ ላይ የወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በደቡባዊ ትግራይ ዋነኛዋ ከተማ የሆነችውና ከኮረም 20 ኪሎሜትር ርቀት የምትገኘውን አላማጣንም መቆጣጠራቸው እየተነገረ ነው። ሁለት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአላማጣ ነዋሪዎች የትግራይ ኃይሎች ከትናንት ምሽት አምስት ሰዓት ጀምሮ የአላማጣ ከተማን መቆጣጠራቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የዓይን እማኞቹ እንደሚሉት ከከተማ ወጣ ብሎ በሶስት የገጠር መንደሮችም ከፍተኛ የሆነ ውጊያ መስማታቸውን አስረድተዋል። ከአይን እማኞቹ በተጨማሪ የትግራይ ኃይል ተዋጊዎችም ኮረምና አላማጣ ከተሞችን እንደተቆጣጠሩ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በአላማጣ ከተማ የስልክ አገልግሎት የሚሰራ ሲሆን፤ በከተማዋም መረጋጋት እየታየ እንደሆነና በርካታዎችም በጎዳናዎች ወጥተው ደስታቸውን እየገለፁ እንደሆነ አኚሁ እማኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት እነዚህ ከተሞች በትግራይ ኃይሎች ስር ቁጥጥር ስለመሆናቸው የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ከሮይተርስ የኮረም ከተማ በማን ቁጥጥር ስር ነው ያለችው ተብሎ የቀረበላቸውን ጥያቄ ቀጥታ ባይመልሱም "የተኩስ አቁም አውጀናል" የሚል የጽሁፍ መልዕከት ልከዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮቹን ከመቀለ እንዳስወጣና የተናጠል ተኩስ አቁም እንዳወጀ ይታወሳል። በወቅቱም ህወሓት የተኩስ አቁሙን "ቀልድ ነው" ብሎ ነበር። ሮይተርስ የኮረምን በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋል በግል ባያረጋግጥም በአዲስ አበባ የሚገኙና የኮረም የቀድሞ ነዋሪ ከሆኑ ሰው ውጊያ እንደነበር ሰምቷል። በአሁኑ ወቅት ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ቢቋረጥም የእኚህ የቀድሞ ነዋሪ የቤተሰብ አባል የሆኑ ግለሰብ ውጊያውን ሸሽተው ስልክ ወዳለበት ቦታ ደርሰው ነግረውኛል ብለዋል። በትግራይ ክልል ጦርነቱ የተነሳው በማዕከላዊ መንግሥትና በክልሉ አስተዳዳሪ ህወሓት መካከል ከስምንት ወራት በፊት ነበር። የማዕከላዊ መንግሥቱ ከሦስት ሳምንታት በኋላ መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ድል መቀዳጀቱን በማወጅ ውጊያው ቆሟል ብሎ ነበር። ህወሓት በበኩሉ ውጊያውን እንደቀጠለ በተደጋጋሚ ሲናገር ነበር። ህወሓት የክልሉን መዲናን ጨምሮ በርካታ የክልሉ ግዛቶችን ቢቆጣጠርም በምዕራብና በደቡብ በኩል ያሉ ግዛቶች በአማራ ክልል ኃይሎች በመያዛቸው ጦርነቱ መፋፋሙ እየተነገረ ነው። ህወሃትና የአማራ ክልል ከሰሞኑ ምን አሉ? የህወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው እንደሚናገሩት የትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት የነበራት ወሰን እንዲከበርና ሰዎችና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ የትራንስፖርት መንገዶች ክፍት እንዲሆኑ በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ አስነብቧል። ከሰሞኑ ህወሓት ምዕራብ ትግራይ የሚላቸውን ግዛቶች በተመለከተ የአማራ ክልል ቀደም ሲል የተወሰዱብኝ አካባቢዎች ናቸው በማለት የሚነሳው ጥያቄ ተቀባይነት የሌላቸውና የአማራ አካባቢዎች ናቸው የሚል ምላሽ ተሰጥቷል። የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ "ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠለምትና ራያ በራሳቸው መስዋዕትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃችኋለን" በማለት አስፍሯል። ህወሓት በበኩሉ የትግራይ መንግሥት በሚል ባወጣው መግለጫ "በትግራይ መሬት እና የትግራይ ክልል ያሉ የአማራ ልዩ ኃይል ይሁኑ ሚሊሻዎችና ታጣቂዎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ" ብሏል። ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ገልጿል። የአማራ ክልል መንግሥት "የአማራን ሕዝብ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ደም ለማቃባት በሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሕዝቡን እያነሳሳሱ ይገኛሉ። የአማራ ሚሊሻዎችንም ወደ ትግራይ መሬት እያስጠጉ ነው" ብሏል። የአማራ ክልል በበኩሉ "ለህልውና የማስከበር ዘመቻ" በሚልም የክልሉ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በከፈታቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥሮችም ነዋሪዎች የተቻላቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀርቧል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር በትናንትናው ዕለት "የህልውና ዘመቻ" ብለው የጠሩትን እንዲደግፉ ለሕዝቡ ጥሪ አቅርበዋል። "ኢትዮጵያውያንና የአማራ ተወላጆች በአሁኑ ጊዜ ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት አውጆብን የህልውና ትግል በማካሄድ ላይ እንገኛለን ይህንን ዘመቻ በቻላችሁት ሁሉ እንድትደግፉ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ" በማለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። አሜሪካ የውጊያው መቀጠል ያሳደረባት ስጋት የአሜሪካ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ቃለ አቀባዩ ኔድ ፕራይስ በኩል በሰጠው መግለጫ በምዕራብ ትግራይ የቀጠለው ውጊያ ሪፖርቶች ስጋት እንዳጫሩባቸው ገልጸዋል። የውጊያዎች መቀጠል በክልሉ ያሉ በረሃብ የተጎዱ ነዋሪዎችን ለመድረስ የሚደረገውን የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያደናቅፈውም ቃለ አቀባዩ ተናግረዋል። ቃለ አቀባዩ የትግራይ መከላከያ ኃይል፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና የአማራ ልዩ ኃይል ለንፁሃኑ ሕዝብ ጥቅምና የአገሪቱን አንድነት ለመጠበቅ በስምምነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጠይቀዋል። ሁሉም የታጠቁ አካላት ንፁሃንን መጠበቅን ጨምሮ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተጣለባቸውን የሰብዓዊ ሕግጋዊ ግዴታ እንዲወጡም አሳስበዋል፥። በዚህም መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ መብቶችን የጣሱና ሰብዓዊ መብት ጥሰትን የፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ ይገባል ተብሏል። "ከዚህ ቀደም ደጋግመን እንዳልነው የኢትዮጵያን ውስጣዊ ወሰኖችን በኃይል ለመቀየር መሞከር ተቀባይነት የለውም። እንዲህ አይነት ጉዳዮችን የመሰሉ ብሔራዊ ጥያቄዎች ሊፈቱ የሚገቡት በሕዝቡ ነው። ሕዝቡ ብሔራዊ ውይይትና መግባባት ላይ ሲደርስ ነው። በጠመንጃ አፈሙዝ አይደለም" ብለዋል። በክልሉ ያለው ቀውስና የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት በትግራይ ክልል የተነሳው ጦርነት 2 ሚሊዮን ነዋሪውን ከክልሉ ሲያፈናቅል 400 ሺህ ደግሞ ለረሃብ ተጋልጠዋል። በያዝነው ሳምንት ሰኞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል የላካቸው ሰብዓዊ እርዳታ ጭነት መቀለ መግባታቸው ተገልጿል። በሁለት ሳምንት ውስጥ ለመጀሪያ ጊዜ የደረሰው ይህ እርዳታ በ50 የጭነት መኪኖች የተጓጓዘ ነው። በመቀለ የደረሰው እርዳታ 900 ሜትሪክ ቶን ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁስ ቢሆንም በክልሉ ካለው ችግር አንፃር ይህ ቁጥር በእጥፍ ማደግ አለበት ተብሏል። ከአራት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ በሚፈልግባት ትግራይ 10 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብና 150 ሺህ ሊትር ነዳጅ በየሳምንቱ መድረስ አለበት በማለት ድርጅቱ አፅንኦት ሰጥቷል። በትግራይ ያሉ ዋነኛ መንገዶች የተዘጉ ሲሆን ሁለት ድልድዮችም ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። መቀለ በትግራይ ኃይሎች ከተያዘች ጀምሮ መብራት የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ባንክና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል። ህወሓት ማዕከላዊው መንግሥት እርዳታን እያገደ ነው በሚል የሚወቅስ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ መሰረተ ልማቶችን እየገነባሁ ነው ብሏል። በትግራይ ክልል ከግንቦት 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት በረራዎች የተቋረጡ ቢሆንም መንግሥት ከሰሞኑ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ለሚፈልጉ ሁሉ ልዩ ፈቃድ እንደሚሰጥና በረራዎችም ከሰኔ 28/2013 ዓ.ም እንደሚጀመሩ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ሁኔታ የፈቀደውን የሰብዓዊ እርዳታ በረራ አለመከልከሉንና በአሁኑም ወቅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም መንገደኞችን ወደ ትግራይ ክልል ለማጓጓዝ ሁለት በረራዎች እንዲፈቀዱለት መጠየቁን ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ወታደሮቹን ከመዲናዋ መቀለ እንዳስወጣ ቢገልፅም ህወሓት በበኩሉ መቀለን በኃይል እንደተቆጣጠረ ተናግሯል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን በኩል ኢትዮጵያ የተኩስ አቁሙን ለማወጅ የወሰነችበት ሁኔታም ከሰሞኑ ተገልጿል። ከዚህም መካከል አብዛኛዎቹ የህወሓት የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች በመገደላቸውና በመታሰራቸው እንዲሁም የቀሩትን ጥቂት የህወሓት አመራሮች ለመያዝ ሲባል ጦርነቱን መቀጠል አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው ተብሏል። በክልሉ ያሉ ነዋሪዎች የግብርና ወቅታቸውን እንዳይስተጓጎል፣ የረድዔት ድርጅቶች የበርካቶችን ህይወት እንዲያድኑ እድል ለመስጠት እንዲሁም የግጭቱ የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ የትግራይ ሕዝብ ሰላም የሚያስፈልገው በመሆኑ እና ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ የሚፈልግ በመሆኑ ከጠቀሷቸው ምክንያቶች ናቸው። ህወሓት በስምምነት ላይ የተደረሰ የተኩስ አቁም እንደሚቀበል ያስታወቀ ሲሆን ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ከክልሉ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ኃይሎች ወጥተው ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚጠይቀው ይገኝበታል። ባለፉት ወራት ጦርነቱን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ተፈጽመዋል የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እንዲሁም ቴሌኮም፣ መብራትና የአውሮፕላን በረራን ጨምሮ የተቋረጡ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ጠይቋል። | የትግራይ ኃይሎች አላማጣና ኮረምን መቆጣጠራቸው ተነገረ የትግራይ ኃይሎች በደቡባዊ ትግራይ የምትገኘውን ኮረም ከተማን መቆጣጠራቸው ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ። ክልሉ ከጦርነቱ በፊት የነበረ ግዛቶችን በሙሉ ለማስመለስ እየተካሄደ ነው የተባለውም ጦርነት ወደ ደቡብ ክፍል መቀጠሉንም ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል። ሮይተርስ የህወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው ረዳን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የትግራይ ኃይሎች ከመቀለ በስተደቡብ በኩል 170 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ኮረም ከተማ መቆጣጠራቸውን ነው። ሰኞ ዕለት አመሻሽ ላይ የወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በደቡባዊ ትግራይ ዋነኛዋ ከተማ የሆነችውና ከኮረም 20 ኪሎሜትር ርቀት የምትገኘውን አላማጣንም መቆጣጠራቸው እየተነገረ ነው። ሁለት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአላማጣ ነዋሪዎች የትግራይ ኃይሎች ከትናንት ምሽት አምስት ሰዓት ጀምሮ የአላማጣ ከተማን መቆጣጠራቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የዓይን እማኞቹ እንደሚሉት ከከተማ ወጣ ብሎ በሶስት የገጠር መንደሮችም ከፍተኛ የሆነ ውጊያ መስማታቸውን አስረድተዋል። ከአይን እማኞቹ በተጨማሪ የትግራይ ኃይል ተዋጊዎችም ኮረምና አላማጣ ከተሞችን እንደተቆጣጠሩ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በአላማጣ ከተማ የስልክ አገልግሎት የሚሰራ ሲሆን፤ በከተማዋም መረጋጋት እየታየ እንደሆነና በርካታዎችም በጎዳናዎች ወጥተው ደስታቸውን እየገለፁ እንደሆነ አኚሁ እማኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት እነዚህ ከተሞች በትግራይ ኃይሎች ስር ቁጥጥር ስለመሆናቸው የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ከሮይተርስ የኮረም ከተማ በማን ቁጥጥር ስር ነው ያለችው ተብሎ የቀረበላቸውን ጥያቄ ቀጥታ ባይመልሱም "የተኩስ አቁም አውጀናል" የሚል የጽሁፍ መልዕከት ልከዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮቹን ከመቀለ እንዳስወጣና የተናጠል ተኩስ አቁም እንዳወጀ ይታወሳል። በወቅቱም ህወሓት የተኩስ አቁሙን "ቀልድ ነው" ብሎ ነበር። ሮይተርስ የኮረምን በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋል በግል ባያረጋግጥም በአዲስ አበባ የሚገኙና የኮረም የቀድሞ ነዋሪ ከሆኑ ሰው ውጊያ እንደነበር ሰምቷል። በአሁኑ ወቅት ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ቢቋረጥም የእኚህ የቀድሞ ነዋሪ የቤተሰብ አባል የሆኑ ግለሰብ ውጊያውን ሸሽተው ስልክ ወዳለበት ቦታ ደርሰው ነግረውኛል ብለዋል። በትግራይ ክልል ጦርነቱ የተነሳው በማዕከላዊ መንግሥትና በክልሉ አስተዳዳሪ ህወሓት መካከል ከስምንት ወራት በፊት ነበር። የማዕከላዊ መንግሥቱ ከሦስት ሳምንታት በኋላ መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ድል መቀዳጀቱን በማወጅ ውጊያው ቆሟል ብሎ ነበር። ህወሓት በበኩሉ ውጊያውን እንደቀጠለ በተደጋጋሚ ሲናገር ነበር። ህወሓት የክልሉን መዲናን ጨምሮ በርካታ የክልሉ ግዛቶችን ቢቆጣጠርም በምዕራብና በደቡብ በኩል ያሉ ግዛቶች በአማራ ክልል ኃይሎች በመያዛቸው ጦርነቱ መፋፋሙ እየተነገረ ነው። ህወሃትና የአማራ ክልል ከሰሞኑ ምን አሉ? የህወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው እንደሚናገሩት የትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት የነበራት ወሰን እንዲከበርና ሰዎችና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ የትራንስፖርት መንገዶች ክፍት እንዲሆኑ በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ አስነብቧል። ከሰሞኑ ህወሓት ምዕራብ ትግራይ የሚላቸውን ግዛቶች በተመለከተ የአማራ ክልል ቀደም ሲል የተወሰዱብኝ አካባቢዎች ናቸው በማለት የሚነሳው ጥያቄ ተቀባይነት የሌላቸውና የአማራ አካባቢዎች ናቸው የሚል ምላሽ ተሰጥቷል። የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ "ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠለምትና ራያ በራሳቸው መስዋዕትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃችኋለን" በማለት አስፍሯል። ህወሓት በበኩሉ የትግራይ መንግሥት በሚል ባወጣው መግለጫ "በትግራይ መሬት እና የትግራይ ክልል ያሉ የአማራ ልዩ ኃይል ይሁኑ ሚሊሻዎችና ታጣቂዎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ" ብሏል። ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ገልጿል። የአማራ ክልል መንግሥት "የአማራን ሕዝብ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ደም ለማቃባት በሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሕዝቡን እያነሳሳሱ ይገኛሉ። የአማራ ሚሊሻዎችንም ወደ ትግራይ መሬት እያስጠጉ ነው" ብሏል። የአማራ ክልል በበኩሉ "ለህልውና የማስከበር ዘመቻ" በሚልም የክልሉ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በከፈታቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥሮችም ነዋሪዎች የተቻላቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀርቧል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር በትናንትናው ዕለት "የህልውና ዘመቻ" ብለው የጠሩትን እንዲደግፉ ለሕዝቡ ጥሪ አቅርበዋል። "ኢትዮጵያውያንና የአማራ ተወላጆች በአሁኑ ጊዜ ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት አውጆብን የህልውና ትግል በማካሄድ ላይ እንገኛለን ይህንን ዘመቻ በቻላችሁት ሁሉ እንድትደግፉ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ" በማለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። አሜሪካ የውጊያው መቀጠል ያሳደረባት ስጋት የአሜሪካ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ቃለ አቀባዩ ኔድ ፕራይስ በኩል በሰጠው መግለጫ በምዕራብ ትግራይ የቀጠለው ውጊያ ሪፖርቶች ስጋት እንዳጫሩባቸው ገልጸዋል። የውጊያዎች መቀጠል በክልሉ ያሉ በረሃብ የተጎዱ ነዋሪዎችን ለመድረስ የሚደረገውን የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያደናቅፈውም ቃለ አቀባዩ ተናግረዋል። ቃለ አቀባዩ የትግራይ መከላከያ ኃይል፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና የአማራ ልዩ ኃይል ለንፁሃኑ ሕዝብ ጥቅምና የአገሪቱን አንድነት ለመጠበቅ በስምምነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጠይቀዋል። ሁሉም የታጠቁ አካላት ንፁሃንን መጠበቅን ጨምሮ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተጣለባቸውን የሰብዓዊ ሕግጋዊ ግዴታ እንዲወጡም አሳስበዋል፥። በዚህም መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ መብቶችን የጣሱና ሰብዓዊ መብት ጥሰትን የፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ ይገባል ተብሏል። "ከዚህ ቀደም ደጋግመን እንዳልነው የኢትዮጵያን ውስጣዊ ወሰኖችን በኃይል ለመቀየር መሞከር ተቀባይነት የለውም። እንዲህ አይነት ጉዳዮችን የመሰሉ ብሔራዊ ጥያቄዎች ሊፈቱ የሚገቡት በሕዝቡ ነው። ሕዝቡ ብሔራዊ ውይይትና መግባባት ላይ ሲደርስ ነው። በጠመንጃ አፈሙዝ አይደለም" ብለዋል። በክልሉ ያለው ቀውስና የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት በትግራይ ክልል የተነሳው ጦርነት 2 ሚሊዮን ነዋሪውን ከክልሉ ሲያፈናቅል 400 ሺህ ደግሞ ለረሃብ ተጋልጠዋል። በያዝነው ሳምንት ሰኞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል የላካቸው ሰብዓዊ እርዳታ ጭነት መቀለ መግባታቸው ተገልጿል። በሁለት ሳምንት ውስጥ ለመጀሪያ ጊዜ የደረሰው ይህ እርዳታ በ50 የጭነት መኪኖች የተጓጓዘ ነው። በመቀለ የደረሰው እርዳታ 900 ሜትሪክ ቶን ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁስ ቢሆንም በክልሉ ካለው ችግር አንፃር ይህ ቁጥር በእጥፍ ማደግ አለበት ተብሏል። ከአራት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ በሚፈልግባት ትግራይ 10 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብና 150 ሺህ ሊትር ነዳጅ በየሳምንቱ መድረስ አለበት በማለት ድርጅቱ አፅንኦት ሰጥቷል። በትግራይ ያሉ ዋነኛ መንገዶች የተዘጉ ሲሆን ሁለት ድልድዮችም ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። መቀለ በትግራይ ኃይሎች ከተያዘች ጀምሮ መብራት የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ባንክና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል። ህወሓት ማዕከላዊው መንግሥት እርዳታን እያገደ ነው በሚል የሚወቅስ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ መሰረተ ልማቶችን እየገነባሁ ነው ብሏል። በትግራይ ክልል ከግንቦት 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት በረራዎች የተቋረጡ ቢሆንም መንግሥት ከሰሞኑ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ለሚፈልጉ ሁሉ ልዩ ፈቃድ እንደሚሰጥና በረራዎችም ከሰኔ 28/2013 ዓ.ም እንደሚጀመሩ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ሁኔታ የፈቀደውን የሰብዓዊ እርዳታ በረራ አለመከልከሉንና በአሁኑም ወቅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም መንገደኞችን ወደ ትግራይ ክልል ለማጓጓዝ ሁለት በረራዎች እንዲፈቀዱለት መጠየቁን ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ወታደሮቹን ከመዲናዋ መቀለ እንዳስወጣ ቢገልፅም ህወሓት በበኩሉ መቀለን በኃይል እንደተቆጣጠረ ተናግሯል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን በኩል ኢትዮጵያ የተኩስ አቁሙን ለማወጅ የወሰነችበት ሁኔታም ከሰሞኑ ተገልጿል። ከዚህም መካከል አብዛኛዎቹ የህወሓት የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች በመገደላቸውና በመታሰራቸው እንዲሁም የቀሩትን ጥቂት የህወሓት አመራሮች ለመያዝ ሲባል ጦርነቱን መቀጠል አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው ተብሏል። በክልሉ ያሉ ነዋሪዎች የግብርና ወቅታቸውን እንዳይስተጓጎል፣ የረድዔት ድርጅቶች የበርካቶችን ህይወት እንዲያድኑ እድል ለመስጠት እንዲሁም የግጭቱ የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ የትግራይ ሕዝብ ሰላም የሚያስፈልገው በመሆኑ እና ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ የሚፈልግ በመሆኑ ከጠቀሷቸው ምክንያቶች ናቸው። ህወሓት በስምምነት ላይ የተደረሰ የተኩስ አቁም እንደሚቀበል ያስታወቀ ሲሆን ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ከክልሉ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ኃይሎች ወጥተው ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚጠይቀው ይገኝበታል። ባለፉት ወራት ጦርነቱን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ተፈጽመዋል የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እንዲሁም ቴሌኮም፣ መብራትና የአውሮፕላን በረራን ጨምሮ የተቋረጡ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ጠይቋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57816164 |
0business
| ሮማን አብራሞቪች፡ ከማደጎ እስከ ቢሊየነርነት | ገና በሦስት ዓመቱ ወላጆቹን በሞት የተነጠቀው ዛሬ ላይ ከዓለማችን እጅግ ከናጠጡ ባለጸጎች መካከል ተጠቃሹ ነው፤ ሮማን አብራሞቪች። ሮማን አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያለው የጠበቀ ግንኙነት የገነባውን ገናና ስምና ንግድ እያሳጣው ይገኛል። ''እርግጠኛ ሰዎች ለሦስት ወይም አራት ቀናት እኔ ላይ ትኩረት ያደርጉ እና ከዛ ያልፋል። እኔ ላይ ትኩረት አያደርጉም። ማን እንደሆንኩኝ ቶሎ ይረሳሉ። እኔ ደግሞ ይሄ በጣም ነው የሚስማማኝ'' ብሎ ነበር ቢሊየነሩ የለንደኑን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቡድን ቼልሲን በገዛ ወቅት። ነገር ግን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ዓለም ሁሉ የሚያወራው ስለዚህ ቢሊየነር ሆኗል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በአብራሞቪች ንብረት ላይ እግድ ጥሏል። ይህ እግድ ቼልሲ እግር ኳስ ክለብ እና መኖሪያ ቤቶቹን ይጨምራል። ከንብረት እግዱ በተጨማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ)መንግሥት የጉዞ እገዳም ጥሎበታል። የዩኬ መንግሥት ይህንን ያደረግኩት አብራሞቪች በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈጸሙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የቀረበ ትስስር ስላለው ነው ብሏል። አብራሞቪች ስመ ጥር የንግድ ሰው ለመሆን ብዙ ፈተናዎችን አልፏል። ገና ከጨቅላ እድሜው ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ ነው ዓለማችን ላይ ተጽእኖ መፍጠር ከሚችሉ ቢሊየነሮች መካከል ተጠቃሽ መሆን የቻለው። ከወላጅ አልባነት ወደ ቢሊየነርነት ሮማን አብራሞቪች እአአ 1966 በደቡብ ምዕራባዊ ሩሲያ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ሳራቶቭ በተባለች ከተማ ነበር የተወለደው። አብራሞቪች ገና የአንድ ዓመት ልጅ ሳለ ነበር ወላጅ እናቱ ኤእሪ በደም መመረዝ ምክንያት ሕይወቷ ያለፈው። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ አባቱ በግንባታ ሥራ ላይ ባጋጠመው አደጋ ሕይወቱ አለፈ። ከዚህ በኋላ አብራሞቪች እድገቱ የአየሩ ሁኔታ እጅግ ቀዝቃዛ እና ሕይወት ከባድ በሆነች የሩሲያ ክፍል ውስጥ በዘመዶች እጅ ሆነ። "እውነቱን ለመናገር ልጅነቴ በጣም መጥፎ ነበር አልልም። በልጅነታችን ነገሮችን መለየት ላይ እስከዚህም ነን። አንዱ ህጻን ካሮት ይበላል፤ ሌላኛው ደግሞ ከረሜላ ይበላል። ሁለቱም ለልጆች ጣፋጭ ናቸው። በልጅነታችን እነዚህን ልዩነቶች አናስተውላቸውም'' ብሎ ነበር አብራሞቪች ከጋርዲያን ጋር ቆይታ ባደረገ ወቅት። በ16 ዓመቱ ትምህርቱን በማቋረጥ በመካኒክነት የሥራ ሲሆን ሞስኮ ውስጥ ደግሞ ከፕላስቲክ የተሰሩ የህጻናት መጫወቻዎችን ይሸጥ ነበር። የሶቪየት ሕብረት መከላከያ ኃይልንም ተቀላቅሎ ነበር። የወቅቱ የሶቪየት ሕብረት መሪ የነበሩት ሚኻኤል ጎርባቾቭ ለሥራ ፈጣሪዎች የሚመች አስተዳደር መዘርጋታቸውን ተከትሎ አብራሞቪች ሽቶ በመሸጥ ጠቀም ያለ ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ። የሶቪየት ሕብረት መበተንን ተከትሎ የነዳጅ ኩባንያዎች ከመንግሥት እጅ ወጥተው ለባለሀብቶች መሸጥ ተጀመረ። ገና በሀያዎቹ አጋማሽ የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረው አብራሞቪች አጋጣሚውን ከመጠቀም አልቦዘነም። በተጭበረበረ ነው በተባለ የጨረታ ሂደት አብራሞቪች 'ሲብኔፍት' የተባለውን የነዳጅ ኩባንያ በአውሮፓውያኑ 1995 ላይ ከመንግሥት በ250 ሚሊየን ዶላር ገዛ። ከአስር ዓመታት በኋላ ማለትም እአአ 2005 ላይ መልሶ ይህንኑ ኩባንያ ለመንግሥት በ13 ቢሊየን ዶላር ሸጠው። ምንም እንኳን የአብራሞቪች ጠበቆች ቢሊየነሩ የነዳጅ ድርጅቱን በሚገዛበት ወቅት ምንም አይነት ሕገ ወጥ ነገር አልፈጸመም ብለው ቢከራከሩም፤ 2012 ላይ በአንድ የዩኬ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ግን አብራሞቪች እራሱ የኩባንያውን ግዢ ለማቀላጠፍ ክፍያ መፈጸሙን አምኗል። በ1990ዎቹ አካባቢ ደግሞ በሩሲያ የአልሙኒየም ንግድ ዘርፍን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍትጊያ ነበር። ''በየሦስት ቀኑ የሆነ ሰው ይገደል ነበር'' ይላል አብራሞቪች። ግድያው የሚፈጸመው በተፎካካሪ የአልሙኒየም ነጋዴዎች ላይ ነበር። ይህንን ያስተዋለው አብራሞቪች የራሱንና የቤተሰቦቹን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲል ከዚህ ንግድ እራሱን በሂደት አግልሏል። ይሁን እንጂ ባልተረጋጋ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ሆኖ እንኳ አብራሞቪች ብዙ ቢሊዮን ዶላሮችን መሰብሰብ ችሏል። ጉዞ ወደ ፖለቲካ የሩሲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቦሪስ ዬልሲን ጥሩ ወዳጁ ነበሩ። እንዲያውም በአንድ ወቅት በሞስኮ የፖለቲካ ዓለም ውስጥ ተሳትፎው ጠንክሮ በክሬምሊን መኖሪያ ቤት እንዲሰጠው ተደርጎም ነበር። 1999 ላይ ፕሬዝዳንት ቦሪስ ዬልሲን ከሥልጣናቸው ሲወርዱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትና የቀድሞው የሩሲያ የስለላ ተቋም ኬጂቢ ሰላይ ቭላድሚር ፑቲን ቦሪስ ዬልሲንን እንዲተኩ ከደገፏቸው ሰዎች መካከል አብራሞቪች አንዱ ነበሩ። ፑቲን ሥልጣን በያዙ በመጀመሪያዎቹ ወራት የሶቪየት ሕብረት መፍረስን ተከትሎ ቢሊየኖችን መሰብሰብ የቻሉ ባለሃብቶች ላይ ትኩረት አድርገው ነበር። ለፑፒን አጋርነታቸውን ማሳየት ያልቻሉት ከአገር የወጡ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደርጓል። አብራሞቪች ከፑቲን ጎን መሰለፍን መርጧል። እንደውም እአአ 2000 ላይ አብራሞቪች በሰሜን ምሥራቃዊ ሩሲያ የተጎዳ የሚባለው ቹኮትካ ግዛት አስተዳዳሪ ሆኖ ተሹሞ ነበር። አብራሞቪች የራሱን ገንዘብ በመጠቀም ዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማድረጉን ተከትሎ ከፍተኛ ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በ2008 ላይ በገዛ ፈቃዱ ከሥስልጣኑ ወርዷል። ሥልጣን ይበቃኝ ቢልም፤ የንግድ ሥራውን ግን አቀላጥፎ ቀጥሏል። መኪኖችን፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ውድ የጥበብ ሥራዎችን በመሰብሰብም ይታወቃል። እግር ኳስና አብራሞቪች በአውሮፓውያኑ 2003 ዝምተኛውና አይናፋር ነው የሚባለው አብራሞቪች የእንግሊዙን ቼልሲ የእግር ኳስ ክለብ በ140 ሚሊዮን ፓዎንድ በመግዛት በእግር ኳስ ወዳጆች ዘንድ ዝናው ናኘ። አብራሞቪች ቼልሲን ከገዛ በኋላ ቡድኑ አምስት ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለ ሲሆን፣ ሁለት ቻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም አምስት የኤፍኤ ዋንጫዎችን አሸንፏል። የዩኬ መንግሥት ማዕቀብ ከመጣሉ 8 ቀናት አስቀድሞ አብራሞቪች ቼልሲን ለሽያጭ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። "አንድ ቀን በአካል በስታምፎርድ ብሪጅ ተገኝቼ እሰናበታችኋለሁ" ሲል መልዕክቱን ለቼልሲ ደጋፊዎች አስተላልፏል። አብራሞቪች በለንድን የእግር ኳስ ክለብ ብቻ ሳይሆን ከ150 ሚሊዮን ፓዎንድ በላይ የሚገመት ባለ15 ክፍል የተንጣለለ መኖሪያ ቤት አለው። ሦስት ጊዜ ትዳሩን የፈታው አብራሞቪች፤ በዓለማችን ግዙፍ ከሚባሉ ቅንጡ የመዝናኛ መርከቦች መካከል የሚዘረዘሩት ሶላሪስ እና ኢክሊፕስ የተባሉት የግሉ ናቸው። የአብራሞቪች አጠቃላይ ሀብት 13.7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን፣ በዓለማችን 128ኛው ሀብታም ሰውም ነው ሲል ብሉምበርግ ብሏል። ፎርብስ ግን የአብራሞቪች አጠቃላይ ሀብት ከ12.3 ቢሊየን እንደማይበልጥና በዓለማችን ካሉ ባለሀብቶች አንጻር 142ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል። | ሮማን አብራሞቪች፡ ከማደጎ እስከ ቢሊየነርነት ገና በሦስት ዓመቱ ወላጆቹን በሞት የተነጠቀው ዛሬ ላይ ከዓለማችን እጅግ ከናጠጡ ባለጸጎች መካከል ተጠቃሹ ነው፤ ሮማን አብራሞቪች። ሮማን አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያለው የጠበቀ ግንኙነት የገነባውን ገናና ስምና ንግድ እያሳጣው ይገኛል። ''እርግጠኛ ሰዎች ለሦስት ወይም አራት ቀናት እኔ ላይ ትኩረት ያደርጉ እና ከዛ ያልፋል። እኔ ላይ ትኩረት አያደርጉም። ማን እንደሆንኩኝ ቶሎ ይረሳሉ። እኔ ደግሞ ይሄ በጣም ነው የሚስማማኝ'' ብሎ ነበር ቢሊየነሩ የለንደኑን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቡድን ቼልሲን በገዛ ወቅት። ነገር ግን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ዓለም ሁሉ የሚያወራው ስለዚህ ቢሊየነር ሆኗል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በአብራሞቪች ንብረት ላይ እግድ ጥሏል። ይህ እግድ ቼልሲ እግር ኳስ ክለብ እና መኖሪያ ቤቶቹን ይጨምራል። ከንብረት እግዱ በተጨማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ)መንግሥት የጉዞ እገዳም ጥሎበታል። የዩኬ መንግሥት ይህንን ያደረግኩት አብራሞቪች በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈጸሙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የቀረበ ትስስር ስላለው ነው ብሏል። አብራሞቪች ስመ ጥር የንግድ ሰው ለመሆን ብዙ ፈተናዎችን አልፏል። ገና ከጨቅላ እድሜው ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ ነው ዓለማችን ላይ ተጽእኖ መፍጠር ከሚችሉ ቢሊየነሮች መካከል ተጠቃሽ መሆን የቻለው። ከወላጅ አልባነት ወደ ቢሊየነርነት ሮማን አብራሞቪች እአአ 1966 በደቡብ ምዕራባዊ ሩሲያ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ሳራቶቭ በተባለች ከተማ ነበር የተወለደው። አብራሞቪች ገና የአንድ ዓመት ልጅ ሳለ ነበር ወላጅ እናቱ ኤእሪ በደም መመረዝ ምክንያት ሕይወቷ ያለፈው። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ አባቱ በግንባታ ሥራ ላይ ባጋጠመው አደጋ ሕይወቱ አለፈ። ከዚህ በኋላ አብራሞቪች እድገቱ የአየሩ ሁኔታ እጅግ ቀዝቃዛ እና ሕይወት ከባድ በሆነች የሩሲያ ክፍል ውስጥ በዘመዶች እጅ ሆነ። "እውነቱን ለመናገር ልጅነቴ በጣም መጥፎ ነበር አልልም። በልጅነታችን ነገሮችን መለየት ላይ እስከዚህም ነን። አንዱ ህጻን ካሮት ይበላል፤ ሌላኛው ደግሞ ከረሜላ ይበላል። ሁለቱም ለልጆች ጣፋጭ ናቸው። በልጅነታችን እነዚህን ልዩነቶች አናስተውላቸውም'' ብሎ ነበር አብራሞቪች ከጋርዲያን ጋር ቆይታ ባደረገ ወቅት። በ16 ዓመቱ ትምህርቱን በማቋረጥ በመካኒክነት የሥራ ሲሆን ሞስኮ ውስጥ ደግሞ ከፕላስቲክ የተሰሩ የህጻናት መጫወቻዎችን ይሸጥ ነበር። የሶቪየት ሕብረት መከላከያ ኃይልንም ተቀላቅሎ ነበር። የወቅቱ የሶቪየት ሕብረት መሪ የነበሩት ሚኻኤል ጎርባቾቭ ለሥራ ፈጣሪዎች የሚመች አስተዳደር መዘርጋታቸውን ተከትሎ አብራሞቪች ሽቶ በመሸጥ ጠቀም ያለ ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ። የሶቪየት ሕብረት መበተንን ተከትሎ የነዳጅ ኩባንያዎች ከመንግሥት እጅ ወጥተው ለባለሀብቶች መሸጥ ተጀመረ። ገና በሀያዎቹ አጋማሽ የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረው አብራሞቪች አጋጣሚውን ከመጠቀም አልቦዘነም። በተጭበረበረ ነው በተባለ የጨረታ ሂደት አብራሞቪች 'ሲብኔፍት' የተባለውን የነዳጅ ኩባንያ በአውሮፓውያኑ 1995 ላይ ከመንግሥት በ250 ሚሊየን ዶላር ገዛ። ከአስር ዓመታት በኋላ ማለትም እአአ 2005 ላይ መልሶ ይህንኑ ኩባንያ ለመንግሥት በ13 ቢሊየን ዶላር ሸጠው። ምንም እንኳን የአብራሞቪች ጠበቆች ቢሊየነሩ የነዳጅ ድርጅቱን በሚገዛበት ወቅት ምንም አይነት ሕገ ወጥ ነገር አልፈጸመም ብለው ቢከራከሩም፤ 2012 ላይ በአንድ የዩኬ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ግን አብራሞቪች እራሱ የኩባንያውን ግዢ ለማቀላጠፍ ክፍያ መፈጸሙን አምኗል። በ1990ዎቹ አካባቢ ደግሞ በሩሲያ የአልሙኒየም ንግድ ዘርፍን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍትጊያ ነበር። ''በየሦስት ቀኑ የሆነ ሰው ይገደል ነበር'' ይላል አብራሞቪች። ግድያው የሚፈጸመው በተፎካካሪ የአልሙኒየም ነጋዴዎች ላይ ነበር። ይህንን ያስተዋለው አብራሞቪች የራሱንና የቤተሰቦቹን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲል ከዚህ ንግድ እራሱን በሂደት አግልሏል። ይሁን እንጂ ባልተረጋጋ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ሆኖ እንኳ አብራሞቪች ብዙ ቢሊዮን ዶላሮችን መሰብሰብ ችሏል። ጉዞ ወደ ፖለቲካ የሩሲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቦሪስ ዬልሲን ጥሩ ወዳጁ ነበሩ። እንዲያውም በአንድ ወቅት በሞስኮ የፖለቲካ ዓለም ውስጥ ተሳትፎው ጠንክሮ በክሬምሊን መኖሪያ ቤት እንዲሰጠው ተደርጎም ነበር። 1999 ላይ ፕሬዝዳንት ቦሪስ ዬልሲን ከሥልጣናቸው ሲወርዱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትና የቀድሞው የሩሲያ የስለላ ተቋም ኬጂቢ ሰላይ ቭላድሚር ፑቲን ቦሪስ ዬልሲንን እንዲተኩ ከደገፏቸው ሰዎች መካከል አብራሞቪች አንዱ ነበሩ። ፑቲን ሥልጣን በያዙ በመጀመሪያዎቹ ወራት የሶቪየት ሕብረት መፍረስን ተከትሎ ቢሊየኖችን መሰብሰብ የቻሉ ባለሃብቶች ላይ ትኩረት አድርገው ነበር። ለፑፒን አጋርነታቸውን ማሳየት ያልቻሉት ከአገር የወጡ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደርጓል። አብራሞቪች ከፑቲን ጎን መሰለፍን መርጧል። እንደውም እአአ 2000 ላይ አብራሞቪች በሰሜን ምሥራቃዊ ሩሲያ የተጎዳ የሚባለው ቹኮትካ ግዛት አስተዳዳሪ ሆኖ ተሹሞ ነበር። አብራሞቪች የራሱን ገንዘብ በመጠቀም ዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማድረጉን ተከትሎ ከፍተኛ ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በ2008 ላይ በገዛ ፈቃዱ ከሥስልጣኑ ወርዷል። ሥልጣን ይበቃኝ ቢልም፤ የንግድ ሥራውን ግን አቀላጥፎ ቀጥሏል። መኪኖችን፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ውድ የጥበብ ሥራዎችን በመሰብሰብም ይታወቃል። እግር ኳስና አብራሞቪች በአውሮፓውያኑ 2003 ዝምተኛውና አይናፋር ነው የሚባለው አብራሞቪች የእንግሊዙን ቼልሲ የእግር ኳስ ክለብ በ140 ሚሊዮን ፓዎንድ በመግዛት በእግር ኳስ ወዳጆች ዘንድ ዝናው ናኘ። አብራሞቪች ቼልሲን ከገዛ በኋላ ቡድኑ አምስት ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለ ሲሆን፣ ሁለት ቻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም አምስት የኤፍኤ ዋንጫዎችን አሸንፏል። የዩኬ መንግሥት ማዕቀብ ከመጣሉ 8 ቀናት አስቀድሞ አብራሞቪች ቼልሲን ለሽያጭ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። "አንድ ቀን በአካል በስታምፎርድ ብሪጅ ተገኝቼ እሰናበታችኋለሁ" ሲል መልዕክቱን ለቼልሲ ደጋፊዎች አስተላልፏል። አብራሞቪች በለንድን የእግር ኳስ ክለብ ብቻ ሳይሆን ከ150 ሚሊዮን ፓዎንድ በላይ የሚገመት ባለ15 ክፍል የተንጣለለ መኖሪያ ቤት አለው። ሦስት ጊዜ ትዳሩን የፈታው አብራሞቪች፤ በዓለማችን ግዙፍ ከሚባሉ ቅንጡ የመዝናኛ መርከቦች መካከል የሚዘረዘሩት ሶላሪስ እና ኢክሊፕስ የተባሉት የግሉ ናቸው። የአብራሞቪች አጠቃላይ ሀብት 13.7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን፣ በዓለማችን 128ኛው ሀብታም ሰውም ነው ሲል ብሉምበርግ ብሏል። ፎርብስ ግን የአብራሞቪች አጠቃላይ ሀብት ከ12.3 ቢሊየን እንደማይበልጥና በዓለማችን ካሉ ባለሀብቶች አንጻር 142ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60899537 |
0business
| ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ከስምምነት ደረሱ | ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ እና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማቃለል ምርታቸውን ለማሳደግ ተስማሙ። በሁለት ዓመት ተኩል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ዋጋዎች ከጨመሩ በኋላ የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) አባላት እና እንደ ሩሲያ ያሉ ከድርጅቱ ውጭ ያሉ አገራት ከነሐሴ ጀምሮ አቅርቦትን ያሳድጋሉ። እርምጃው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይም ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሏል። የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በዚህ ዓመት በ43 በመቶ ገደማ ጨምሮ በበርሜል ወደ 74 ዶላር ከፍ ብሏል። ባለፈው ዓመት ኦፔክ እና አጋሮቻቸው በወረርሽኙ የተነሳ የፍላጎት ማሽቆልቆል በመኖሩ እና ዋጋው በመቀነሱ ከምርታቸው በቀን 10 ሚሊዮን በርሜል ቀንሰው ነበር። ይሁን እንጂ በዚህ ዓመት የዓለም ምጣኔ ሃብት እያንሰራራ በመሆኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። ይህም በአንዳንድ አገራት የዋጋ ግሽበት እንዲጨምር አስተዋጽኦ በማድረጉ እና በዓለም የኢኮኖሚ መሻሻል ላይ እንቅፋት እንዳይሆን አስግቷል። የነዳጅ አምራቾች ዋጋ ለመቀነስ ፍላጎት ቢያሳዩም በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በሐምሌ ወር መጀመሪያ ዕቅዱን እንዲደናቀፍ ምክንያት ሆኗል። በሪያድ እና በሞስኮ የቀረበውን ተጨማሪ ነዳጅ የማምረት ዕቅድ ፍላጎት አቡዳቢ ውድቅ አድርጋ ነበር። በቅርብ አጋሮች መካከል ያልተለመደ ውዝግብ ከ50 በመቶ በላይ የነዳጅ አቅርቦቶችን የሚቆጣጠረውን ኦፔክና አጋሮቹ መረጋጋት ላይ ጥያቄ አስነስቷል። በአዲሱ ስምምነት መሠረት ኦፔክ እና አጋሮቹ ገበያውን ለማረጋጋት ከነሐሴ እስከ ታህሳስ 2021 ድረስ በቀን ተጨማሪ ሁለት ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለማምረት ተስማምተዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ፣ ኩዌት እና ኢራቅን ጨምሮ በርካታ አባል ሃገራት ከግንቦት 2022 ጀምሮ ከፍተኛ የምርት ኮታ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። ባለፈው ዓመት ወደ ሥራ የገባው የነዳጅ ምርት ቅነሳ እስከ መስከረም 2022 ድረስ ያበቃል ብሏል። የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ አባላቱ "ገንቢ" እና "መግባባት" ላይ ደርሰዋል ብለዋል። "ወረርሽኙ እስካ አሁን በቁጥጥር ስር ባይውልም በመላው ዓለም በክትባት ምክንያት እንደ መኪኖች እና የአውሮፕላን ነዳጅ በመጨመሩ ምርታችን እያገገመ መሆኑን እያየን ነው" ብለዋል። "ኃላፊነታችንን መወጣት እና የዓለም ኢኮኖሚ እንዲረጋጋ ማድረግ በጣም አስፈላጊያችን ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ | ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ከስምምነት ደረሱ ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ እና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማቃለል ምርታቸውን ለማሳደግ ተስማሙ። በሁለት ዓመት ተኩል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ዋጋዎች ከጨመሩ በኋላ የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) አባላት እና እንደ ሩሲያ ያሉ ከድርጅቱ ውጭ ያሉ አገራት ከነሐሴ ጀምሮ አቅርቦትን ያሳድጋሉ። እርምጃው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይም ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሏል። የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በዚህ ዓመት በ43 በመቶ ገደማ ጨምሮ በበርሜል ወደ 74 ዶላር ከፍ ብሏል። ባለፈው ዓመት ኦፔክ እና አጋሮቻቸው በወረርሽኙ የተነሳ የፍላጎት ማሽቆልቆል በመኖሩ እና ዋጋው በመቀነሱ ከምርታቸው በቀን 10 ሚሊዮን በርሜል ቀንሰው ነበር። ይሁን እንጂ በዚህ ዓመት የዓለም ምጣኔ ሃብት እያንሰራራ በመሆኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። ይህም በአንዳንድ አገራት የዋጋ ግሽበት እንዲጨምር አስተዋጽኦ በማድረጉ እና በዓለም የኢኮኖሚ መሻሻል ላይ እንቅፋት እንዳይሆን አስግቷል። የነዳጅ አምራቾች ዋጋ ለመቀነስ ፍላጎት ቢያሳዩም በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በሐምሌ ወር መጀመሪያ ዕቅዱን እንዲደናቀፍ ምክንያት ሆኗል። በሪያድ እና በሞስኮ የቀረበውን ተጨማሪ ነዳጅ የማምረት ዕቅድ ፍላጎት አቡዳቢ ውድቅ አድርጋ ነበር። በቅርብ አጋሮች መካከል ያልተለመደ ውዝግብ ከ50 በመቶ በላይ የነዳጅ አቅርቦቶችን የሚቆጣጠረውን ኦፔክና አጋሮቹ መረጋጋት ላይ ጥያቄ አስነስቷል። በአዲሱ ስምምነት መሠረት ኦፔክ እና አጋሮቹ ገበያውን ለማረጋጋት ከነሐሴ እስከ ታህሳስ 2021 ድረስ በቀን ተጨማሪ ሁለት ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለማምረት ተስማምተዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ፣ ኩዌት እና ኢራቅን ጨምሮ በርካታ አባል ሃገራት ከግንቦት 2022 ጀምሮ ከፍተኛ የምርት ኮታ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። ባለፈው ዓመት ወደ ሥራ የገባው የነዳጅ ምርት ቅነሳ እስከ መስከረም 2022 ድረስ ያበቃል ብሏል። የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ አባላቱ "ገንቢ" እና "መግባባት" ላይ ደርሰዋል ብለዋል። "ወረርሽኙ እስካ አሁን በቁጥጥር ስር ባይውልም በመላው ዓለም በክትባት ምክንያት እንደ መኪኖች እና የአውሮፕላን ነዳጅ በመጨመሩ ምርታችን እያገገመ መሆኑን እያየን ነው" ብለዋል። "ኃላፊነታችንን መወጣት እና የዓለም ኢኮኖሚ እንዲረጋጋ ማድረግ በጣም አስፈላጊያችን ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-57884491 |
3politics
| ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ የተገደሉባት የቻድ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? | የሟቹ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ መጨረሻ አነሳሳቸውን የሚያስታውስ ነው። ዴቢ በ1990 (እአአ) በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ነበር ስልጣን ከሄስኔ ሃበሬ የቀሙት። በተመሳሳይም ፕሬዝዳንት ዴቢ ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚፈልጉት አማጽያን ጉዳት ደርሶባቸው ህይወታቸው አለፈ። ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚታገሉት አማጽያን እጅ ሞትን ተቀበሉ። ዴቢ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላም ጦር ሜዳ እየተገኙ ወታደሮቻቸውን ይጎበኛሉ። "ተዋጊው መሪ" በመባል የሚታወቁት ዴቢ ነሐሴ 2020 ከገዢው ከፓትሪዮቲክ ሳልቬሽን ሙቭመንት ፓርቲ 'ማርሻል ኦፍ ቻድ' የሚል ማዕረግ ተሰጣቸው። ሠራዊቱ በመንግሥታዊው 'ቴሌ ቻድ' ቴሌቪዥን በሰጠው መግለጫ ዴቢ "በመጨረሻ በጦር ሜዳ ተገኝተው የአገሪቱን አንድነት ሲያስጠብቁ አልፈዋል" ብሏል። "በጦር ሜዳ ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ተከትሎ የቻድ ማርሻል ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ህይወታቸው ማሉን ለቻዳውያን ስናሳውቅ በታላቅ ሀዘን ነው።" ዴቢ "ከሊቢያ ከመጡ አሸባሪ ቡድኖች ጋር የተካሄደ ውጊያ በጀግንነት ሲመሩ እንደነበር" እና ወደ ዋና ከተማዋ ንጃሜና ህክምና ሲያቀኑ ህይወታቸው ማለፉን አክሏል። ቱቡ ሚዲያ በትዊተር ገጹ እንደዘገበው ዴቢ በሰሜን ንጃሜና በምትገኘው ካኔም ግዛት ከፍሮንት ቼንጅ ኤንድ ኮንኮርድ ኢን ቻድ (ፋክት) ጋር በነበረ ግጭት ነው የቆሰሉት። ወታደር ስልጣኑን ይቆጣጠራል ዴቢ አገሪቱን በኃይል መርተዋል። ተቺዎቻቸውን እና ተቀናቃኞቻቸውን ያለ ርህራሄ አፍነዋል። ለምሳሌ ቻድ በ2018 ከተሞከረው የመፈንቅለ መንግሥት ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትር አልነበራትም። ታኅሣሥ 2020 ይፋ የተደረገው አዲስ ሕገ-መንግሥት የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታን ቢፈጥርም ዴቢ እስከተገደሉበት ጊዜ ማንም አልተሾመበትም። የቅርቡ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የተቃናቃኞቻቸውን ጥያቄ "የዲሞክራሲ ሥርዓት ማለት ሥርዓት አልበኝነት አይደለም" በማለት ዴቢ ውድቅ አደርገዋል። ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ላይ ዘመዶቻቸውን እና የሚቀርቧቸውን በመሾም ስልጣን ዘመናቸውነ ሲያራዝሙ ቆዩ። ልጃቸው ጄኔራል ማሐማት ኢድሪስ ዴቢ የፕሬዚዳንታዊው ጥበቃ ኃላፊ ነበሩ። የአገሪቱ አመራር ቦታ በፕሬዚዳንቱ ዘመዶች በመታጠሩ ለዴቢ የሚሆን የፖለቲካ ተተኪ የለም ማለት ነው። የዴቢን ሞት ተከትሎ ሠራዊቱ ስልጣኑን መቆጣጠሩ አያስደንቅም። ሠራዊቱ እንደገለጸው ፓርላማውና መንግሥት አስተዳደሩ መበተኑንና በመሐማት ዴቢ የሚመራ 15 አባላት ያሉት የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤት "የአገሪቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ" መሾሙን አስታውቋል። አዲስ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ወታደራዊው ቡድን ጁንታ ለ18 ወራት አገሪቱን ያስተዳድራል። ሕገ መንግሥቱ ተሰርዞ በመሐማት ዴቢ በሚተላለፍ የሽግግር ቻርተር ይተካል። ወታደራዊ ኃይል በአገር አቀፍ ደረጃ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት የሚቆይ የሰዓት እላፊ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል። መሐማት ኢድሪስ ዴቢ ማሐማት ከ2014 ጀምሮ የፕሬዚዳንታዊ ጥበቃ ኃላፊ፣ የመንግሥት ተቋማት የደኅንነት አገልግሎቶች ዋና ዳይሬክቶሬት ሆነው አገልግለዋል። በ2013 በማሊ የቻድ ኃይሎች ምክትል ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን አዲሱን ኃላፊነት በመረከብ ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው በፊት ከፈረንሳይ ኃይሎች ጎን በተለያዩ ተልዕኮዎች ላይ ተሳትፈዋል ተብሏል። ማሐማት ከአማጽያን ጋር በምዕራባዊው የካኔም ግዛት በተደረገው ፍልሚያ አባታቸው ሲቆስሉ አብረዋቸው ነበሩ። "ጄኔራል ካካ" በመባል የሚታወቁት ማሐማትም ከአንዳንድ ወንድሞቹ በተቃራኒ ብልህነት እና ታዋቂነትን በማሳየት ዝና አላቸው። ልክ እንደ አባታቸው በጦርነት ከጥቃት የተረፉ ወታደር ናቸው። "ፕሬዚዳንቱ [ኢድሪስ ዴቢ] ከታዋቂ ቻዳውያን እና ከሚግቧቧቸው መንግሥታት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር ማሐማት እንዲገናኙ አድርገዋል። ለሥልጣን አንዲበቁም በአባታቸው በሚሰጣቸው መንገድ ነበር" ሲል ጁን እፍሪክ ዘግቧል። ሟቹ ዴቢ ብዙ ወንድ ልጆች ነበሯቸው። አንዳንዶቹም በመንግሥታቸው ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። በማሐማት እና በአንዳንድ ወንድሞቹ መካከል ውዝግብ ሊፈጠር ይችላል። ተቃዋሚዎች የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤቱን ውድቅ አድርገዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሌህ ኬብዛቦ እና የተቃዋሚ ፓርቲው ፍሪደምስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት መሐመድ አህመድ አልሃቦ በበኩላቸው የሽግግር መንግሥቱ በብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲመራ መጠየቃቸውን 'ሌ ጆርናል ደ ቻድ' ዘግቧል። ተቃዋሚዎች የተዳከሙ እና የተከፋፈሉ በመሆናቸው ለወታደራዊው ጁንታ ከፍተኛ ተግዳሮት የመሆን ዕድል የላቸውም። ለአማጽያን የሞራል ማሻሻያ በካኔም ጦርነት ከባድ ኪሳራ እንደደረሰባቸው የተዘገበው አማጽያኑ የዴቢ ሞት ሁኔታውን ሊያሳምርላቸው ይችላል። ሠራዊቱ ከአማጽያኑ ጋር በካኔም በተደረገው ውጊያ ከ300 በላይ አማጽያን የተገደሉ ሲሆን 150 ደግሞ ቆስለዋል። የአማጽያኑ መሪ ማሐማት መሃዲ አሊ ከፈረንሳዩ አርኤፍአይ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የደረሰባቸው ኪሳራ እውነት መሆኑን አምነዋል። "ያልተለመደው ዓይነት ግጭት ነበር። ከሁኔታዎች አንጻር ታክቲካዊ ማፈግፈግ አደረግን" ያሉት መሪው የቻድ ጦር በፈረንሣይ አየር ኃይል የተደገፈ መሆኑን ቢገልጹም ፓሪስ ውድቅ አደርጋዋለች። አማጺው ከ2016 ጀምሮ ከደቡብ ሊቢያ እየተነሳ ጥቃት ያደርስ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ወደ ንጃሜና ለማቅናት ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ቡድኑ በሁለት ቀናቱ የካኔም ውጊያ 15 ከፍተኛ የቻድ ወታደራዊ መኮንኖችን ገድያለሁ ወይም አቁስያለሁ ብሏል። ኪሳራ ቢደርስበትም ከ1,500 በላይ ተዋጊዎችን እንዳሉት የሚዘገበው የፋክት አማጽያን ቻድ በዴቢ ሞት በምታዝነበት በዚህ ወቅት አዳዲስ ጥቃቶችን ሊያደርስ ይችላል። የዴቢ ሞት ለቻድ ታጠቂ ቡድኖች የመሰባሰቢያ ጥሪ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ሌላኛው አማጺ ቡድን ከአገሪቱ ሠራዊት ጋር የሚፋለመውን አማጺ ያወደሰ ሲሆን ሁሉም የቻድ አማጺያን ቡድኖች በአንድ ተሰባስበው የዴቢን አገዛዝ እንዲከስልጣን እንዲያወርዱ ጠይቋል። ቀጣናዊ የፀረ-ሽምቅ አንቅስቃሴዎች የዴቢ ሞት በሳሀል እና በቻድ ሐይቅ አካባቢ በጂሃዳዊ አማጽያን ላይ የቻድን መንግሥት ወታደራዊ ዘመቻ መቀጠል ጥርጣሬ ውስጥ ጥሎታል። ቻድ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ በማሰማራት አገራቱን እና የፈረንሣይን በአልቃይዳ እና በኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ታጣቂዎች ላይ የምታደርገውን ውጊያ እየረዱ ነው። የቻድ ወታደሮች ቦኮ ሃራምን እና ኢስላሚክ ስቴት በምዕራብ አፍሪካ በቻድ አቅራቢያ ከሚገኙት ናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ካሜሩን እና ቻድ ጋር በመተባበር ላይ ይገኛሉ። ዴቢ በክልላዊ የፀረ-ሽምቅ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ የቻድን ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ከፍ ያደረገ ሲሆን ከምዕራቡ ዓለም በተለይም ከፈረንሳይ፣ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ወታደራዊ እና የገንዘብ ድጋፍን እንድታገኝ አድርጓል። ለምሳሌም 5,200 የወታደሮች በማሊ ቢሰማሩም የኦፕሬሽን ባርካኔ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫው ቻድ ነው። የፋክት አማጽያን ንጃሜናን ኢላማ ያደረጉ ሲሆን ዴቢንም ገድለዋል። ወታደራዊው ምክር ቤት በአገር ውስጥ በሚካሄደው አመጽ ላይ በማተኮር የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቀንስ ስለመሆኑ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። በነሐሴ ወር 2020 በማሊ የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በጭፍን መደገፏን ከሚገልጹ መረጃዎች አንፃር ፈረንሳይ ቻድ ውስጥ ለሠራዊቱ ስልጣን መያዝ የምትሰጠው ምላሽ ትኩረትን የሚስብ ነው። | ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ የተገደሉባት የቻድ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? የሟቹ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ መጨረሻ አነሳሳቸውን የሚያስታውስ ነው። ዴቢ በ1990 (እአአ) በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ነበር ስልጣን ከሄስኔ ሃበሬ የቀሙት። በተመሳሳይም ፕሬዝዳንት ዴቢ ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚፈልጉት አማጽያን ጉዳት ደርሶባቸው ህይወታቸው አለፈ። ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚታገሉት አማጽያን እጅ ሞትን ተቀበሉ። ዴቢ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላም ጦር ሜዳ እየተገኙ ወታደሮቻቸውን ይጎበኛሉ። "ተዋጊው መሪ" በመባል የሚታወቁት ዴቢ ነሐሴ 2020 ከገዢው ከፓትሪዮቲክ ሳልቬሽን ሙቭመንት ፓርቲ 'ማርሻል ኦፍ ቻድ' የሚል ማዕረግ ተሰጣቸው። ሠራዊቱ በመንግሥታዊው 'ቴሌ ቻድ' ቴሌቪዥን በሰጠው መግለጫ ዴቢ "በመጨረሻ በጦር ሜዳ ተገኝተው የአገሪቱን አንድነት ሲያስጠብቁ አልፈዋል" ብሏል። "በጦር ሜዳ ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ተከትሎ የቻድ ማርሻል ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ህይወታቸው ማሉን ለቻዳውያን ስናሳውቅ በታላቅ ሀዘን ነው።" ዴቢ "ከሊቢያ ከመጡ አሸባሪ ቡድኖች ጋር የተካሄደ ውጊያ በጀግንነት ሲመሩ እንደነበር" እና ወደ ዋና ከተማዋ ንጃሜና ህክምና ሲያቀኑ ህይወታቸው ማለፉን አክሏል። ቱቡ ሚዲያ በትዊተር ገጹ እንደዘገበው ዴቢ በሰሜን ንጃሜና በምትገኘው ካኔም ግዛት ከፍሮንት ቼንጅ ኤንድ ኮንኮርድ ኢን ቻድ (ፋክት) ጋር በነበረ ግጭት ነው የቆሰሉት። ወታደር ስልጣኑን ይቆጣጠራል ዴቢ አገሪቱን በኃይል መርተዋል። ተቺዎቻቸውን እና ተቀናቃኞቻቸውን ያለ ርህራሄ አፍነዋል። ለምሳሌ ቻድ በ2018 ከተሞከረው የመፈንቅለ መንግሥት ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትር አልነበራትም። ታኅሣሥ 2020 ይፋ የተደረገው አዲስ ሕገ-መንግሥት የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታን ቢፈጥርም ዴቢ እስከተገደሉበት ጊዜ ማንም አልተሾመበትም። የቅርቡ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የተቃናቃኞቻቸውን ጥያቄ "የዲሞክራሲ ሥርዓት ማለት ሥርዓት አልበኝነት አይደለም" በማለት ዴቢ ውድቅ አደርገዋል። ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ላይ ዘመዶቻቸውን እና የሚቀርቧቸውን በመሾም ስልጣን ዘመናቸውነ ሲያራዝሙ ቆዩ። ልጃቸው ጄኔራል ማሐማት ኢድሪስ ዴቢ የፕሬዚዳንታዊው ጥበቃ ኃላፊ ነበሩ። የአገሪቱ አመራር ቦታ በፕሬዚዳንቱ ዘመዶች በመታጠሩ ለዴቢ የሚሆን የፖለቲካ ተተኪ የለም ማለት ነው። የዴቢን ሞት ተከትሎ ሠራዊቱ ስልጣኑን መቆጣጠሩ አያስደንቅም። ሠራዊቱ እንደገለጸው ፓርላማውና መንግሥት አስተዳደሩ መበተኑንና በመሐማት ዴቢ የሚመራ 15 አባላት ያሉት የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤት "የአገሪቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ" መሾሙን አስታውቋል። አዲስ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ወታደራዊው ቡድን ጁንታ ለ18 ወራት አገሪቱን ያስተዳድራል። ሕገ መንግሥቱ ተሰርዞ በመሐማት ዴቢ በሚተላለፍ የሽግግር ቻርተር ይተካል። ወታደራዊ ኃይል በአገር አቀፍ ደረጃ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት የሚቆይ የሰዓት እላፊ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል። መሐማት ኢድሪስ ዴቢ ማሐማት ከ2014 ጀምሮ የፕሬዚዳንታዊ ጥበቃ ኃላፊ፣ የመንግሥት ተቋማት የደኅንነት አገልግሎቶች ዋና ዳይሬክቶሬት ሆነው አገልግለዋል። በ2013 በማሊ የቻድ ኃይሎች ምክትል ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን አዲሱን ኃላፊነት በመረከብ ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው በፊት ከፈረንሳይ ኃይሎች ጎን በተለያዩ ተልዕኮዎች ላይ ተሳትፈዋል ተብሏል። ማሐማት ከአማጽያን ጋር በምዕራባዊው የካኔም ግዛት በተደረገው ፍልሚያ አባታቸው ሲቆስሉ አብረዋቸው ነበሩ። "ጄኔራል ካካ" በመባል የሚታወቁት ማሐማትም ከአንዳንድ ወንድሞቹ በተቃራኒ ብልህነት እና ታዋቂነትን በማሳየት ዝና አላቸው። ልክ እንደ አባታቸው በጦርነት ከጥቃት የተረፉ ወታደር ናቸው። "ፕሬዚዳንቱ [ኢድሪስ ዴቢ] ከታዋቂ ቻዳውያን እና ከሚግቧቧቸው መንግሥታት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር ማሐማት እንዲገናኙ አድርገዋል። ለሥልጣን አንዲበቁም በአባታቸው በሚሰጣቸው መንገድ ነበር" ሲል ጁን እፍሪክ ዘግቧል። ሟቹ ዴቢ ብዙ ወንድ ልጆች ነበሯቸው። አንዳንዶቹም በመንግሥታቸው ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። በማሐማት እና በአንዳንድ ወንድሞቹ መካከል ውዝግብ ሊፈጠር ይችላል። ተቃዋሚዎች የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤቱን ውድቅ አድርገዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሌህ ኬብዛቦ እና የተቃዋሚ ፓርቲው ፍሪደምስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት መሐመድ አህመድ አልሃቦ በበኩላቸው የሽግግር መንግሥቱ በብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲመራ መጠየቃቸውን 'ሌ ጆርናል ደ ቻድ' ዘግቧል። ተቃዋሚዎች የተዳከሙ እና የተከፋፈሉ በመሆናቸው ለወታደራዊው ጁንታ ከፍተኛ ተግዳሮት የመሆን ዕድል የላቸውም። ለአማጽያን የሞራል ማሻሻያ በካኔም ጦርነት ከባድ ኪሳራ እንደደረሰባቸው የተዘገበው አማጽያኑ የዴቢ ሞት ሁኔታውን ሊያሳምርላቸው ይችላል። ሠራዊቱ ከአማጽያኑ ጋር በካኔም በተደረገው ውጊያ ከ300 በላይ አማጽያን የተገደሉ ሲሆን 150 ደግሞ ቆስለዋል። የአማጽያኑ መሪ ማሐማት መሃዲ አሊ ከፈረንሳዩ አርኤፍአይ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የደረሰባቸው ኪሳራ እውነት መሆኑን አምነዋል። "ያልተለመደው ዓይነት ግጭት ነበር። ከሁኔታዎች አንጻር ታክቲካዊ ማፈግፈግ አደረግን" ያሉት መሪው የቻድ ጦር በፈረንሣይ አየር ኃይል የተደገፈ መሆኑን ቢገልጹም ፓሪስ ውድቅ አደርጋዋለች። አማጺው ከ2016 ጀምሮ ከደቡብ ሊቢያ እየተነሳ ጥቃት ያደርስ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ወደ ንጃሜና ለማቅናት ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ቡድኑ በሁለት ቀናቱ የካኔም ውጊያ 15 ከፍተኛ የቻድ ወታደራዊ መኮንኖችን ገድያለሁ ወይም አቁስያለሁ ብሏል። ኪሳራ ቢደርስበትም ከ1,500 በላይ ተዋጊዎችን እንዳሉት የሚዘገበው የፋክት አማጽያን ቻድ በዴቢ ሞት በምታዝነበት በዚህ ወቅት አዳዲስ ጥቃቶችን ሊያደርስ ይችላል። የዴቢ ሞት ለቻድ ታጠቂ ቡድኖች የመሰባሰቢያ ጥሪ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ሌላኛው አማጺ ቡድን ከአገሪቱ ሠራዊት ጋር የሚፋለመውን አማጺ ያወደሰ ሲሆን ሁሉም የቻድ አማጺያን ቡድኖች በአንድ ተሰባስበው የዴቢን አገዛዝ እንዲከስልጣን እንዲያወርዱ ጠይቋል። ቀጣናዊ የፀረ-ሽምቅ አንቅስቃሴዎች የዴቢ ሞት በሳሀል እና በቻድ ሐይቅ አካባቢ በጂሃዳዊ አማጽያን ላይ የቻድን መንግሥት ወታደራዊ ዘመቻ መቀጠል ጥርጣሬ ውስጥ ጥሎታል። ቻድ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ በማሰማራት አገራቱን እና የፈረንሣይን በአልቃይዳ እና በኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ታጣቂዎች ላይ የምታደርገውን ውጊያ እየረዱ ነው። የቻድ ወታደሮች ቦኮ ሃራምን እና ኢስላሚክ ስቴት በምዕራብ አፍሪካ በቻድ አቅራቢያ ከሚገኙት ናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ካሜሩን እና ቻድ ጋር በመተባበር ላይ ይገኛሉ። ዴቢ በክልላዊ የፀረ-ሽምቅ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ የቻድን ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ከፍ ያደረገ ሲሆን ከምዕራቡ ዓለም በተለይም ከፈረንሳይ፣ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ወታደራዊ እና የገንዘብ ድጋፍን እንድታገኝ አድርጓል። ለምሳሌም 5,200 የወታደሮች በማሊ ቢሰማሩም የኦፕሬሽን ባርካኔ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫው ቻድ ነው። የፋክት አማጽያን ንጃሜናን ኢላማ ያደረጉ ሲሆን ዴቢንም ገድለዋል። ወታደራዊው ምክር ቤት በአገር ውስጥ በሚካሄደው አመጽ ላይ በማተኮር የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቀንስ ስለመሆኑ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። በነሐሴ ወር 2020 በማሊ የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በጭፍን መደገፏን ከሚገልጹ መረጃዎች አንፃር ፈረንሳይ ቻድ ውስጥ ለሠራዊቱ ስልጣን መያዝ የምትሰጠው ምላሽ ትኩረትን የሚስብ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/56828901 |
5sports
| ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፍ እድላቸው ምን ያህል ነው? | በካሜሮን እዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ያደርጋል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈትን ያስተናገዱት ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋቸውን ከቡርኪና ፋሶ ጋር ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ። ዋልያዎቹ በመጀመሪያው ጨዋታቸው በኬፕ ቬርድ 1 ለ 0፤ በሁለተኛው ግጥሚያ ደግሞ በአዘጋጇ ካሜሩን 4 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል። ለመሆኑ ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፈ እድላቸውም ምን ያህል ነው? መልሱ - ጠባብ ነው። ዋልያዎቹ ሁለት ጊዜ ተሸንፈው 4 የጎል እዳን በመያዝ በምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ቡርኪና ፋሶ በውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ አዘጋጇን 1ለ0 ስትመራ ቆይታ ተከታትሎ በተቆጠሩባት ሁለት የፍጹም ቅጣት ምቶች በካሜሮን 2 ለ 1 ተሸንፋለች። ቡርኪና ፋሶ በቀጣይ የምትጋጠመው ከኬፕ ቬርድ ነው። ኬፕ ቬርድን 1 ለ 0 በማሸነፍ በምድብ ሀ ኬፕ ቬርድን በጎል ልዩነት በመብለጥ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። የምድቡን ሁለቱንም ጨዋታዎች ያሸነፈችው ካሜሮን በአንደኝነት እየመራች ነው። ዋልያዎቹ ያለባቸውን 4 የግብ እዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ቡርኪና ፋሶን 5 ለ 0 እና ከዚያ በላይ በሆነ ውጤት አሸንፈው፤ የኬፕ ቬርድ ቡድን በካሜሮን የማይበገሩ አናብስት መሸነፍን መጠበቅ አለባቸው። ነገር ግን በእግር ኳስ ሜዳ የሚከሰተውን መተንበይ ባይቻልም ዋልያዎቹ የምድቡ ሁለተኛ በሆነችው ቡርኪና ፋሶ ላይ በርካታ ጎሎችን አስቆጥረው ማሸነፍ የዋዛ አይሆንላቸውም። በፈረንጆቹ 2013 በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ኢትዮጵያ እና ቡርኪና ፋሶ በአንድ ምድብ ተደልድለው እንደነበረ ይታወሳል። በዚህ ውድድርም ቡርኪና ፋሶ ዋልያዎቹን 4 ለ 0 አሸንፈው እንደነበር ይታወሳል። ምርጥ ሦስተኛ? የአፍሪካ ዋንጫ 24 ብሔራዊ ቡድኖችን እያሳተፈ ይገኛል። ይህ ማለት እያንዳንዳቸው አራት ቡድኖችን ያቀፉ ስድስት ምድቦች አሉት ማለት ነው። ከእነዚህ መካከል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን የሚይዙ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ ሲያልፉ፤ አራት ምርጥ ሦስተኛ ቡድኖችም ቀጣዩን የ16ቱን ዙር ይቀላቀላሉ። ዋልዮቹም ከምድባቸው ምርጥ ሦስተኛ ሆኖ ለመጨረስ ቡርኪና ፋሶን አሸንፈው የኬፕ ቬርድ በካሜሮን መሸነፍን መጠበቅ አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪም ዋልያዎቹ ከሌሎች ምድቦች ምርጥ ሦስተኛ ሆኖ የመጨረስ እድል ያላቸውን አገራት ውጤት መጠበቅ ግድ ይላቸዋል። | ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፍ እድላቸው ምን ያህል ነው? በካሜሮን እዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ያደርጋል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈትን ያስተናገዱት ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋቸውን ከቡርኪና ፋሶ ጋር ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ። ዋልያዎቹ በመጀመሪያው ጨዋታቸው በኬፕ ቬርድ 1 ለ 0፤ በሁለተኛው ግጥሚያ ደግሞ በአዘጋጇ ካሜሩን 4 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል። ለመሆኑ ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፈ እድላቸውም ምን ያህል ነው? መልሱ - ጠባብ ነው። ዋልያዎቹ ሁለት ጊዜ ተሸንፈው 4 የጎል እዳን በመያዝ በምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ቡርኪና ፋሶ በውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ አዘጋጇን 1ለ0 ስትመራ ቆይታ ተከታትሎ በተቆጠሩባት ሁለት የፍጹም ቅጣት ምቶች በካሜሮን 2 ለ 1 ተሸንፋለች። ቡርኪና ፋሶ በቀጣይ የምትጋጠመው ከኬፕ ቬርድ ነው። ኬፕ ቬርድን 1 ለ 0 በማሸነፍ በምድብ ሀ ኬፕ ቬርድን በጎል ልዩነት በመብለጥ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። የምድቡን ሁለቱንም ጨዋታዎች ያሸነፈችው ካሜሮን በአንደኝነት እየመራች ነው። ዋልያዎቹ ያለባቸውን 4 የግብ እዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ቡርኪና ፋሶን 5 ለ 0 እና ከዚያ በላይ በሆነ ውጤት አሸንፈው፤ የኬፕ ቬርድ ቡድን በካሜሮን የማይበገሩ አናብስት መሸነፍን መጠበቅ አለባቸው። ነገር ግን በእግር ኳስ ሜዳ የሚከሰተውን መተንበይ ባይቻልም ዋልያዎቹ የምድቡ ሁለተኛ በሆነችው ቡርኪና ፋሶ ላይ በርካታ ጎሎችን አስቆጥረው ማሸነፍ የዋዛ አይሆንላቸውም። በፈረንጆቹ 2013 በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ኢትዮጵያ እና ቡርኪና ፋሶ በአንድ ምድብ ተደልድለው እንደነበረ ይታወሳል። በዚህ ውድድርም ቡርኪና ፋሶ ዋልያዎቹን 4 ለ 0 አሸንፈው እንደነበር ይታወሳል። ምርጥ ሦስተኛ? የአፍሪካ ዋንጫ 24 ብሔራዊ ቡድኖችን እያሳተፈ ይገኛል። ይህ ማለት እያንዳንዳቸው አራት ቡድኖችን ያቀፉ ስድስት ምድቦች አሉት ማለት ነው። ከእነዚህ መካከል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን የሚይዙ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ ሲያልፉ፤ አራት ምርጥ ሦስተኛ ቡድኖችም ቀጣዩን የ16ቱን ዙር ይቀላቀላሉ። ዋልዮቹም ከምድባቸው ምርጥ ሦስተኛ ሆኖ ለመጨረስ ቡርኪና ፋሶን አሸንፈው የኬፕ ቬርድ በካሜሮን መሸነፍን መጠበቅ አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪም ዋልያዎቹ ከሌሎች ምድቦች ምርጥ ሦስተኛ ሆኖ የመጨረስ እድል ያላቸውን አገራት ውጤት መጠበቅ ግድ ይላቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60020563 |
0business
| ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ? | የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከጅማሮው በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ አንድ ዓመት አስቆጠሩ። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው በድንገት አልፎ ከተገኘ በኋላ፤ በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ኢንጅነሩ ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራው እንደደረሰበት ማሳወቁ ይታወሳል። መኪናቸው ውስጥ የተገኘውም ሽጉጥ የኢንጂነሩ እንደነበር በምርመራው አረጋግጫለሁ ብሏል። •ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? •ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ የግድቡ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱት ኢንጅነር ስመኘው ሞት፣ በርካቶችን ያስደነገጠ እና ኃገሪቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የህዳሴ ግድብ ከየት ይደርሳል? የሚል ስጋትን የፈጠረም ነበር። በኢንጅነር ስመኘው ቦታ የተተኩት የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፤ ''አንድ ሰው በግሉ የሚቻለውን ያክል ነው አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው እንጂ የጀመረውን ሁሉ ይጨርሳል ማለት አይደለም'' በማለት የቀድሞውን የፕሮጀክቱን መሪ ያስታውሳሉ። አክለውም ''ህዳሴ ግድብ የህዝብ ነው። እኔም አሻራዬን ትቼ ላልፍ እችላለሁ የኢንጅነር ስመኘውን አስተዋጽኦንም እንዲሁ ነው የምመለከተው'' ይላሉ። የቀድሞው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሪ ከሞቱ በኋላ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የህዳሴ ግድብ አፈጻጸም እንዴት ነው? ምን ተለወጠ? ምን ችግር አጋጠመው? ከኢንጅነር ክፍሌ ጋር ቆይታ አድርገናል። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮጀክቱ ለምን ዘገየ? ኢንጅነር ክፍሌ ፕሮጀክቱ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ባይሄድም በአሁኑም ወቅት ህዝብ እና መንግሥት ለአባይ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዳላቋረጡ ይናገራሉ። በዋናነት ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ሁለት ፈተናዎች አሉ የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ የመጀመሪያው ከስነ-ምድር (Geology) ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገልጻሉ። የአባይ ወንዝ የሚሄድበት መሬት ሥሩ ጠንካራ ነው ተብሎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው፤ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ ግን መሬቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን እንደቀረና መሬቱን ቆፍሮ በኮንክሪት የመሙላቱ ሥራ ብዙ ጊዜ መውሰዱን ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ለህዳሴ ግድብ መዘግየት እንደ ሁለተኛ ምክንያትነት የሚጠቅሱት ደግሞ ከብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የተያያዘ ነው። እንደ ኢንጅነር ክፍሌ ከሆነ መንግሥት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ግንባታው ሲገባ በተቻለ መጠን በግድቡ ላይ ሃገር በቀል ተቋማት አስተዋጽኦዋቸውን እንዲያበረክቱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነበር። በዚሁ መንፈስ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሥራውን እንዲያከናውን በንዑስ ተቋራጭነት እንዲሰራ መወሰኑን ያስረዳሉ። ተቋሙ የኤክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን የመገንባት አቅምም ሆነ ልምድ ስለሌለው የግንባታ ስራውን ወደፊት ማስኬድ አልቻለም ብለዋል። "ፕሮጀክቱ ላይ ብዙ ቢሊየን ብር ቢፈስም፤ መልክ አልያዘም" ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የሲቪል ሥራው ወደ 84 በመቶ በላይ ቢጠናቀቅም፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው 28 በመቶ የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ወደ ስልሳ ስምንት በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። መጋቢት 10፣ 2011ዓ.ም በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት፣ ከሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በነበረው የውይይት መድረክ የግድቡ የግንባታ ቡድን ተወካይ አቶ ኤርሚያስ ውብሸት የግድቡ የሲቪል ሥራ 85 በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ 25በመቶ እና የብረታ ብረት ስራ 13 መድረሱንና በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 66.24 በመቶ ደርሷል ብለዋል። መንግሥት ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን ውል ካቋረጠ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እና ልምድ ላላቸው ለአዳዲስ ተቋራጮች በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ተግባርም ተከናውኗል ። በግንባታ ስራው ተሰማርተው የሚገኙት ስድስትተቋራጮች እንደሆነ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ከእነዚህም መካከል የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቻይና ኩባንያዎች ይገኙበታል ይላሉ። በውይይት መድረኩ ላይም እንደተጠቀሰው ከተቋራጮቹም መካከል ሲጂጂሲ፣ ሳይኖ ሃይድሮ፣ ቮይት፣ ጂኦ ሃይድሮ ፍራንስና ኤክሲዲ ይገኙበታል በማለት በስም ይዘረዝራሉ። •ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? እንደ ተርባይን ያሉ ከውሃ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግንባታዎች ከፍተኛ ልምድ የሚጠይቁ ሥራዎች መሆናቸውን ኢንጅነር ክፍሌ ገልፀው አዳዲሶቹ ተቋራጮች የግንባታ ሥራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየሠሩ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሳሊኒ ቅሬታ እና የፕሮጀክቱ ክንውን የሲቪል ሥራውን ለማከናወን ኮንትራት ወስዶ ሲሰራ የቆየው የጣሊያኑ ሳሊኒ ከግንባታ ክፍያ መዘግየት ጋር ተያይዞ ቅሬታዎችን ሲያሰማ ነበር። ኢንጅነር ክፍሌ እንደሚሉት ሳሊኒ ያነሳቸው ቅሬታዎች አግባብነት ከተጠና በኋላ መንግሥት እና ሳሊኒ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል ይላሉ። "ሳሊኒ ሲያነሳው የነበረው ቅሬታ 'ፕሮጀክቱ የዘገየው እኔ በፈጠርኩት ችግር አይደለም። ሜቴክ የሚጠበቅበትን የተርባይን እና ሌሎች ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ብረቶችን በወቅቱ ማቅረብ ቢችል ኖሮ ሥራውን በሰዓቱ ማጠናቀቅ እችል ነበር። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ለኪሳራ ተጋልጫለሁ' የሚል ነበር" በማለት ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ሳሊኒ በዚህ ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ መንግሥት ካሳ እንዲከፍለው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። •ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ " ከሳሊኒ ጋር ያለው ጉዳይ አልተፈታም። በመንግሥት የተወሰደው እርምጃ በዚህ የመዘግየት ምክንያት ኪሳራ ደርሶበት አስጊ የሆነ የገንዘብ ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ሳሊኒ ይገባኛል የሚለው ጥያቄ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በታሳቢነት 124 ሚሊዮን ብር እንዲከፈለው ተወስኗል። ይህ የተወሰነው ስራውን ከማስቀጠል አንፃር ነው። የሳሊኒ ያቀረበው የኪሳራ ይገባኛል ካሳ ሙሉ በሙሉ መቀበል ማለት አይደለም። እየታየ እንዲሁም እየተጠና ነው። እውነት ይህ ሁሉ ኪሳራ ይደርስበታል ለሚለውም በዝርዝር እየታየ ነው"ይላሉ ኢንጅነር ክፍሌ። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ሳሊኒ ብቻ ሳይሆን ጉዳቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "እውነት ለመናገር ህዝቡ በግንባታው ሞራሉ ተነክቷል። ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ በማስመልከት ለህዝብ የሚሰጠው መረጃ የተሳሳተ ነበር። እውነቱ ተደብቆ ቆይቶ በአንዴ እውነቱ ሲገለጥ ህዝቡ ማዘኑ አልቀረም" ይላሉ። ፕሮጀክቱ በተጀመረበት ወቅት በአራት ዓመት ውስጥ በሁለት ተርባይኖች አማካኝነት ኃይል ማመንጨት ይጀምራል መባሉን እና በሰባት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደነበረ ኢንጅነር ክፍሌ ያስታውሳሉ። ይህን መሰል ግዙፍ ፕሮጀክት በሰባት ዓመታት ውሰጥ መጨረስ ይቻላል ተብሎ መጀመሩ በራሱ ስህተት ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ሜቴክ "የሚጠበቅበትን በወቅቱ ማድረግ ቢችል ኖሮ ቢያንስ በ2009 ላይ ኃይል ማመንጨት መጀመር ይቻል ነበር" ይላሉ። ከሁለት አመታት በኋላ ኃይል የማመንጨት ጅማሮ እቅድ እንዳለ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ በአራት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ግንባታው ሙሉ በሙሉ የማጠናቀቅ እቅድም እንደተያዘ ይናገራሉ። ነገር ግን ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አልደበቁም። በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ ሁሉም ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ማለት ሳይሆን በመጀመሪያ ግድቡ ውሃ የሚሞላበት ሁኔታ ላይ የታችኛው የተፋሰስ ሃገራትን ማወያየት ዋናው ስራ እንደሆነ ይናገራሉ። "ተርባይኖቹ በሙሉ አቅም ኃይል የሚያመነጩት በግድቡ ውሃ መሙላት ላይ ተሞርኩዞ ነው። የተርባይኖቹ ስራ ግን ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ ታቅዷል" ይላሉ። የፕሮጀክቱ ተጨማሪ ወጪ ሃሳብ ሆኗል? የዚህ ፕሮጀክት ወጪ ከህዝብ ከሚሰበሰበው እና መንግሥት ከሚመድበው በጀት ሲሆን፤ መንግሥት ተጨማሪ በጀት እየመደበ የግንባታ ሥራው እንዲቀጥል እያደረገ መሆኑንም ይናገራሉ። ህዝቡም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቅሰዋል። የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና ከግንባታው መጓተት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ወጪ ፕሮጀክቱን እንደጎዳው የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ "ህዝብ እና መንግሥት አሁንም ፕሮጀክቱን ከግብ ማድረስ ያለስለሰ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ" ተናግረዋል። | ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ? የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከጅማሮው በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ አንድ ዓመት አስቆጠሩ። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው በድንገት አልፎ ከተገኘ በኋላ፤ በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ኢንጅነሩ ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራው እንደደረሰበት ማሳወቁ ይታወሳል። መኪናቸው ውስጥ የተገኘውም ሽጉጥ የኢንጂነሩ እንደነበር በምርመራው አረጋግጫለሁ ብሏል። •ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? •ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ የግድቡ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱት ኢንጅነር ስመኘው ሞት፣ በርካቶችን ያስደነገጠ እና ኃገሪቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የህዳሴ ግድብ ከየት ይደርሳል? የሚል ስጋትን የፈጠረም ነበር። በኢንጅነር ስመኘው ቦታ የተተኩት የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፤ ''አንድ ሰው በግሉ የሚቻለውን ያክል ነው አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው እንጂ የጀመረውን ሁሉ ይጨርሳል ማለት አይደለም'' በማለት የቀድሞውን የፕሮጀክቱን መሪ ያስታውሳሉ። አክለውም ''ህዳሴ ግድብ የህዝብ ነው። እኔም አሻራዬን ትቼ ላልፍ እችላለሁ የኢንጅነር ስመኘውን አስተዋጽኦንም እንዲሁ ነው የምመለከተው'' ይላሉ። የቀድሞው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሪ ከሞቱ በኋላ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የህዳሴ ግድብ አፈጻጸም እንዴት ነው? ምን ተለወጠ? ምን ችግር አጋጠመው? ከኢንጅነር ክፍሌ ጋር ቆይታ አድርገናል። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮጀክቱ ለምን ዘገየ? ኢንጅነር ክፍሌ ፕሮጀክቱ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ባይሄድም በአሁኑም ወቅት ህዝብ እና መንግሥት ለአባይ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዳላቋረጡ ይናገራሉ። በዋናነት ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ሁለት ፈተናዎች አሉ የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ የመጀመሪያው ከስነ-ምድር (Geology) ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገልጻሉ። የአባይ ወንዝ የሚሄድበት መሬት ሥሩ ጠንካራ ነው ተብሎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው፤ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ ግን መሬቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን እንደቀረና መሬቱን ቆፍሮ በኮንክሪት የመሙላቱ ሥራ ብዙ ጊዜ መውሰዱን ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ለህዳሴ ግድብ መዘግየት እንደ ሁለተኛ ምክንያትነት የሚጠቅሱት ደግሞ ከብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የተያያዘ ነው። እንደ ኢንጅነር ክፍሌ ከሆነ መንግሥት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ግንባታው ሲገባ በተቻለ መጠን በግድቡ ላይ ሃገር በቀል ተቋማት አስተዋጽኦዋቸውን እንዲያበረክቱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነበር። በዚሁ መንፈስ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሥራውን እንዲያከናውን በንዑስ ተቋራጭነት እንዲሰራ መወሰኑን ያስረዳሉ። ተቋሙ የኤክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን የመገንባት አቅምም ሆነ ልምድ ስለሌለው የግንባታ ስራውን ወደፊት ማስኬድ አልቻለም ብለዋል። "ፕሮጀክቱ ላይ ብዙ ቢሊየን ብር ቢፈስም፤ መልክ አልያዘም" ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የሲቪል ሥራው ወደ 84 በመቶ በላይ ቢጠናቀቅም፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው 28 በመቶ የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ወደ ስልሳ ስምንት በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። መጋቢት 10፣ 2011ዓ.ም በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት፣ ከሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በነበረው የውይይት መድረክ የግድቡ የግንባታ ቡድን ተወካይ አቶ ኤርሚያስ ውብሸት የግድቡ የሲቪል ሥራ 85 በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ 25በመቶ እና የብረታ ብረት ስራ 13 መድረሱንና በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 66.24 በመቶ ደርሷል ብለዋል። መንግሥት ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን ውል ካቋረጠ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እና ልምድ ላላቸው ለአዳዲስ ተቋራጮች በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ተግባርም ተከናውኗል ። በግንባታ ስራው ተሰማርተው የሚገኙት ስድስትተቋራጮች እንደሆነ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ከእነዚህም መካከል የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቻይና ኩባንያዎች ይገኙበታል ይላሉ። በውይይት መድረኩ ላይም እንደተጠቀሰው ከተቋራጮቹም መካከል ሲጂጂሲ፣ ሳይኖ ሃይድሮ፣ ቮይት፣ ጂኦ ሃይድሮ ፍራንስና ኤክሲዲ ይገኙበታል በማለት በስም ይዘረዝራሉ። •ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? እንደ ተርባይን ያሉ ከውሃ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግንባታዎች ከፍተኛ ልምድ የሚጠይቁ ሥራዎች መሆናቸውን ኢንጅነር ክፍሌ ገልፀው አዳዲሶቹ ተቋራጮች የግንባታ ሥራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየሠሩ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሳሊኒ ቅሬታ እና የፕሮጀክቱ ክንውን የሲቪል ሥራውን ለማከናወን ኮንትራት ወስዶ ሲሰራ የቆየው የጣሊያኑ ሳሊኒ ከግንባታ ክፍያ መዘግየት ጋር ተያይዞ ቅሬታዎችን ሲያሰማ ነበር። ኢንጅነር ክፍሌ እንደሚሉት ሳሊኒ ያነሳቸው ቅሬታዎች አግባብነት ከተጠና በኋላ መንግሥት እና ሳሊኒ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል ይላሉ። "ሳሊኒ ሲያነሳው የነበረው ቅሬታ 'ፕሮጀክቱ የዘገየው እኔ በፈጠርኩት ችግር አይደለም። ሜቴክ የሚጠበቅበትን የተርባይን እና ሌሎች ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ብረቶችን በወቅቱ ማቅረብ ቢችል ኖሮ ሥራውን በሰዓቱ ማጠናቀቅ እችል ነበር። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ለኪሳራ ተጋልጫለሁ' የሚል ነበር" በማለት ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ሳሊኒ በዚህ ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ መንግሥት ካሳ እንዲከፍለው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። •ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ " ከሳሊኒ ጋር ያለው ጉዳይ አልተፈታም። በመንግሥት የተወሰደው እርምጃ በዚህ የመዘግየት ምክንያት ኪሳራ ደርሶበት አስጊ የሆነ የገንዘብ ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ሳሊኒ ይገባኛል የሚለው ጥያቄ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በታሳቢነት 124 ሚሊዮን ብር እንዲከፈለው ተወስኗል። ይህ የተወሰነው ስራውን ከማስቀጠል አንፃር ነው። የሳሊኒ ያቀረበው የኪሳራ ይገባኛል ካሳ ሙሉ በሙሉ መቀበል ማለት አይደለም። እየታየ እንዲሁም እየተጠና ነው። እውነት ይህ ሁሉ ኪሳራ ይደርስበታል ለሚለውም በዝርዝር እየታየ ነው"ይላሉ ኢንጅነር ክፍሌ። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ሳሊኒ ብቻ ሳይሆን ጉዳቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "እውነት ለመናገር ህዝቡ በግንባታው ሞራሉ ተነክቷል። ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ በማስመልከት ለህዝብ የሚሰጠው መረጃ የተሳሳተ ነበር። እውነቱ ተደብቆ ቆይቶ በአንዴ እውነቱ ሲገለጥ ህዝቡ ማዘኑ አልቀረም" ይላሉ። ፕሮጀክቱ በተጀመረበት ወቅት በአራት ዓመት ውስጥ በሁለት ተርባይኖች አማካኝነት ኃይል ማመንጨት ይጀምራል መባሉን እና በሰባት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደነበረ ኢንጅነር ክፍሌ ያስታውሳሉ። ይህን መሰል ግዙፍ ፕሮጀክት በሰባት ዓመታት ውሰጥ መጨረስ ይቻላል ተብሎ መጀመሩ በራሱ ስህተት ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ሜቴክ "የሚጠበቅበትን በወቅቱ ማድረግ ቢችል ኖሮ ቢያንስ በ2009 ላይ ኃይል ማመንጨት መጀመር ይቻል ነበር" ይላሉ። ከሁለት አመታት በኋላ ኃይል የማመንጨት ጅማሮ እቅድ እንዳለ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ በአራት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ግንባታው ሙሉ በሙሉ የማጠናቀቅ እቅድም እንደተያዘ ይናገራሉ። ነገር ግን ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አልደበቁም። በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ ሁሉም ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ማለት ሳይሆን በመጀመሪያ ግድቡ ውሃ የሚሞላበት ሁኔታ ላይ የታችኛው የተፋሰስ ሃገራትን ማወያየት ዋናው ስራ እንደሆነ ይናገራሉ። "ተርባይኖቹ በሙሉ አቅም ኃይል የሚያመነጩት በግድቡ ውሃ መሙላት ላይ ተሞርኩዞ ነው። የተርባይኖቹ ስራ ግን ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ ታቅዷል" ይላሉ። የፕሮጀክቱ ተጨማሪ ወጪ ሃሳብ ሆኗል? የዚህ ፕሮጀክት ወጪ ከህዝብ ከሚሰበሰበው እና መንግሥት ከሚመድበው በጀት ሲሆን፤ መንግሥት ተጨማሪ በጀት እየመደበ የግንባታ ሥራው እንዲቀጥል እያደረገ መሆኑንም ይናገራሉ። ህዝቡም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቅሰዋል። የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና ከግንባታው መጓተት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ወጪ ፕሮጀክቱን እንደጎዳው የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ "ህዝብ እና መንግሥት አሁንም ፕሮጀክቱን ከግብ ማድረስ ያለስለሰ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ" ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-49027549 |
0business
| ህንድ አሜሪካን ይጎዳል የተባለ የንግድ ታሪፍ ልታስተዋውቅ ነው | ህንድ ከእሁድ ጀምሮ የለውዝና የአፕል ምርቶችን ጨምሮ 28 የአሜሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ታሪፍ ልታስተዋውቅ መሆኑን ገልፃለች። አዲሱ ታሪፍ ህንድ የብረትና አሉሚኒየም ምርቶችን ወደ አሜሪካ በምትልክበት ወቅት ለጫነችባት ከፍተኛ ግብር ምላሽ ነው ተብሏል። አሜሪካ ግብሩን ዝቅ አድርጊ ብትባል በእምቢተኝነቷ ቀጥላለች። በዚህ ወር ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ለህንድ በንግዱ ዘርፍ የምታደርግላትን የተለየ ጥቅማጥቅም እንደምታቆም ገልፀው ነበር። •ኢሳያስን ለመጣል'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት በምላሹም ህንድ እስከ 120% የሚደርስ ታሪፍ በአሜሪካ ምርቶች እንደሚጫን በባለፈው አመት ህንድ አስታውቃ የነበረ ቢሆንም በውይይቶች ምክንያት አተገባበሩ ዘግይቶ ነበር። በባለፈው አርብ ግን የህንድ የገንዘብ ሚኒስትር ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲባል ውሳኔው ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል። በአሜሪካና በህንድ ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት በባለፈው አመት 142 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ይህም ከአስራ ሰባት አመት በፊት ከነበረው ቁጥር ጋር ሲወዳደር ሰባት እጥፍ ነው ተብሏል። ነገር ግን 5.6 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው የህንድ ወጪ ንግድ አሜሪካ ከቀረጥ ነፃ አድርጋላት የነበረ ሲሆን አሜሪካ ይህንን የንግድ ግንኙነት ማቆሟ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ተፅእኖ ሊያደርስ እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ። •የትራምፕ እና የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካህን እሰጣገባ የትራምፕ አስተዳደር "ኢፍትሐዊ" የንግድ ስርአትን ለማስተካከል በሚል እንቅስቃሴያቸው ነው እንዲህ አይነት የንግድ መጠቃቀም ግንኙነት እንዲቀሩ ያደረጉት። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ ኃገራት ያለው የንግድ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን በባለፈው አመትም ህንድ ለዚህ ምላሽ የሚሆን የታሪፍ ጫናን አስተዋውቃለች። ትራምፕ በበኩላቸው ህንድ ከኢራን ነዳጅ እንዲሁም ከሩሲያ ኤስ 400 ሚሳይል ለመግዛት የያዘችውን እቅድ የማታቆም ከሆነ ማእቀብ ይጣልባታል ሲሉ አስፈራርተዋል። •የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን? የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራሃማንያም ጃይሻንካርና አቻቸው ማይክ ፖምፔዮ ጃፓን በሚካሄደው የጂ-20 ጉባኤ ላይ የሚወያየዩ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል። | ህንድ አሜሪካን ይጎዳል የተባለ የንግድ ታሪፍ ልታስተዋውቅ ነው ህንድ ከእሁድ ጀምሮ የለውዝና የአፕል ምርቶችን ጨምሮ 28 የአሜሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ታሪፍ ልታስተዋውቅ መሆኑን ገልፃለች። አዲሱ ታሪፍ ህንድ የብረትና አሉሚኒየም ምርቶችን ወደ አሜሪካ በምትልክበት ወቅት ለጫነችባት ከፍተኛ ግብር ምላሽ ነው ተብሏል። አሜሪካ ግብሩን ዝቅ አድርጊ ብትባል በእምቢተኝነቷ ቀጥላለች። በዚህ ወር ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ለህንድ በንግዱ ዘርፍ የምታደርግላትን የተለየ ጥቅማጥቅም እንደምታቆም ገልፀው ነበር። •ኢሳያስን ለመጣል'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት በምላሹም ህንድ እስከ 120% የሚደርስ ታሪፍ በአሜሪካ ምርቶች እንደሚጫን በባለፈው አመት ህንድ አስታውቃ የነበረ ቢሆንም በውይይቶች ምክንያት አተገባበሩ ዘግይቶ ነበር። በባለፈው አርብ ግን የህንድ የገንዘብ ሚኒስትር ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲባል ውሳኔው ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል። በአሜሪካና በህንድ ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት በባለፈው አመት 142 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ይህም ከአስራ ሰባት አመት በፊት ከነበረው ቁጥር ጋር ሲወዳደር ሰባት እጥፍ ነው ተብሏል። ነገር ግን 5.6 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው የህንድ ወጪ ንግድ አሜሪካ ከቀረጥ ነፃ አድርጋላት የነበረ ሲሆን አሜሪካ ይህንን የንግድ ግንኙነት ማቆሟ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ተፅእኖ ሊያደርስ እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ። •የትራምፕ እና የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካህን እሰጣገባ የትራምፕ አስተዳደር "ኢፍትሐዊ" የንግድ ስርአትን ለማስተካከል በሚል እንቅስቃሴያቸው ነው እንዲህ አይነት የንግድ መጠቃቀም ግንኙነት እንዲቀሩ ያደረጉት። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ ኃገራት ያለው የንግድ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን በባለፈው አመትም ህንድ ለዚህ ምላሽ የሚሆን የታሪፍ ጫናን አስተዋውቃለች። ትራምፕ በበኩላቸው ህንድ ከኢራን ነዳጅ እንዲሁም ከሩሲያ ኤስ 400 ሚሳይል ለመግዛት የያዘችውን እቅድ የማታቆም ከሆነ ማእቀብ ይጣልባታል ሲሉ አስፈራርተዋል። •የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን? የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራሃማንያም ጃይሻንካርና አቻቸው ማይክ ፖምፔዮ ጃፓን በሚካሄደው የጂ-20 ጉባኤ ላይ የሚወያየዩ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-48652222 |
3politics
| የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ በወታደራዊው ኃይል ተቃውሞ ሦስት ሰዎች ተገደሉ | በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመደገፍና ወታደራዊ ኃይሉን በመቃወም አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተኮሱት ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሐኪሞች ኮሚቴ አስታወቀ። ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣን እንዲመለሱ በዋና መዲናዋ ካርቱም እና በሌሎች ከተሞች አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል። የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተቃዋሚዎች ላይ ተኩሰዋል መባሉን ሀሰት ነው ብሏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ሌሎች ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችም ለጉዳት እንደተዳረጉ ተናግረዋል። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት ጀነራል አብደል ፈታህ ቡርሃን የሲቪል አስተዳደሩን የበተኑት በዚህ ሳምንት ነበር። ጀነራሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጁ ሲሆን "መፈንቅለ መንግሥቱን ያደረኩት በአገሪቷ የእርስ በርስ ጦርነትንና ፖለቲካዊ ሽኩቻን ለማስወገድ ነው" ብለዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ውግዘትን አስከትሏል። ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን በመቃወም አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የሱዳንን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ እንዲሁም "ወታደራዊ አገዛዝ አንፈልግም" በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። በካርቱም 'የሬዚስታንስ' ኮሚቴ አባል የሆኑት ሻህን አል ሻህፍ "ሰዎች ሰላማዊ ናቸው። ምንም እንኳን ከጸጥታ ኃይሎች ጥይት ቢተኮስባቸውም ተቃውሞው በሰላማዊ መንገድ ይቀጥላል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሁን ላይ ጀነራል ቡርሃን ሁሉንም ደጋፊዎቹን እንዳጣ ተረድተናል ሲሉም ሻህን አክለዋል። " ይህ አንድ ሰው ያካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ነው ። የሚደግፈው ማንም የለም" ብለዋል ሻህን። ገለልተኛ የሆነው የሱዳን ሴንትራል ሐኪሞች ኮሚቴ በኦምዱርማን በተቃዋሚዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን በተቃዋሚዎች ላይ ጥይት ተተኩሷል መባሉን ሀሰት ነው ያለ ሲሆን የተወሰኑ ተቃዋሚዎች ፖሊስ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል ሲል ከሷል። በዚህ ሳምንት ብቻ በተቃዋሚዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በነበረ ግጭት ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የሱዳን ባለሥልጣናት የኢንተርኔትና ሌሎች የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎቶችን ያቋረጡ ሲሆን የእንቅስቃሴ ገደብም ጥለዋል። እአአ 2019 አገሪቷን ለረዥም ዓመታት የመሩት ኦማር ሀሰን አል ባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ባሳለፍነው ሰኞ መፈንቅለ መንግሥቱ እስከሚካሄድ ድረስ የሲቪልና ወታደራዊ ኃይሎች ሥልጣን በመጋራት ሱዳንን ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል። | የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ በወታደራዊው ኃይል ተቃውሞ ሦስት ሰዎች ተገደሉ በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመደገፍና ወታደራዊ ኃይሉን በመቃወም አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተኮሱት ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሐኪሞች ኮሚቴ አስታወቀ። ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣን እንዲመለሱ በዋና መዲናዋ ካርቱም እና በሌሎች ከተሞች አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል። የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተቃዋሚዎች ላይ ተኩሰዋል መባሉን ሀሰት ነው ብሏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ሌሎች ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችም ለጉዳት እንደተዳረጉ ተናግረዋል። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት ጀነራል አብደል ፈታህ ቡርሃን የሲቪል አስተዳደሩን የበተኑት በዚህ ሳምንት ነበር። ጀነራሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጁ ሲሆን "መፈንቅለ መንግሥቱን ያደረኩት በአገሪቷ የእርስ በርስ ጦርነትንና ፖለቲካዊ ሽኩቻን ለማስወገድ ነው" ብለዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ውግዘትን አስከትሏል። ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን በመቃወም አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የሱዳንን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ እንዲሁም "ወታደራዊ አገዛዝ አንፈልግም" በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። በካርቱም 'የሬዚስታንስ' ኮሚቴ አባል የሆኑት ሻህን አል ሻህፍ "ሰዎች ሰላማዊ ናቸው። ምንም እንኳን ከጸጥታ ኃይሎች ጥይት ቢተኮስባቸውም ተቃውሞው በሰላማዊ መንገድ ይቀጥላል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሁን ላይ ጀነራል ቡርሃን ሁሉንም ደጋፊዎቹን እንዳጣ ተረድተናል ሲሉም ሻህን አክለዋል። " ይህ አንድ ሰው ያካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ነው ። የሚደግፈው ማንም የለም" ብለዋል ሻህን። ገለልተኛ የሆነው የሱዳን ሴንትራል ሐኪሞች ኮሚቴ በኦምዱርማን በተቃዋሚዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን በተቃዋሚዎች ላይ ጥይት ተተኩሷል መባሉን ሀሰት ነው ያለ ሲሆን የተወሰኑ ተቃዋሚዎች ፖሊስ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል ሲል ከሷል። በዚህ ሳምንት ብቻ በተቃዋሚዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በነበረ ግጭት ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የሱዳን ባለሥልጣናት የኢንተርኔትና ሌሎች የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎቶችን ያቋረጡ ሲሆን የእንቅስቃሴ ገደብም ጥለዋል። እአአ 2019 አገሪቷን ለረዥም ዓመታት የመሩት ኦማር ሀሰን አል ባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ባሳለፍነው ሰኞ መፈንቅለ መንግሥቱ እስከሚካሄድ ድረስ የሲቪልና ወታደራዊ ኃይሎች ሥልጣን በመጋራት ሱዳንን ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59066441 |
3politics
| በአገር ውስጥ ጉዳይ የተወጠሩት ባይደን ስብሰባ ለመሳተፍ አውሮፓ ገቡ | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 2.75 ትሪሊየን ዶላር የሃገር ውስጥ አጀንዳቸውን በዋሽንግተን በመተው ለሁለት ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች አውሮፓ ገብተዋል። ባይደን በዩናይትድ ኪንግደም የአየር ንብረት ኮንፈረንስ ላይ ለሌሎች የዓለም መሪዎች የአካባቢ ጥበቃ ዕቅዳቸውን ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። የተሰሚነት ደረጃቸው እየቀነሰ የመጣው ባይደን፤ የስልጣን ዘመናቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ፕሬዚዳንቱ ራሳቸው ተናግረዋል ። ባይደን ለጂ20 ስብሰባ ዓርብ ጠዋት ሮም ደርሰዋል። በስብሰባው የዓለም ዝቅተኛ የግብር መጠን ዋነኛ አጀንዳ ይሆናል። ካቶሊክ የሆኑት ሁለተኛው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አርብ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋርም በቫቲካን ይገናኛሉ። ቀጥሎ እሁድ ምሽት ለተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት (COP26) ኮንፈረንስ ወደ ግላስጎው ስኮትላንድ ያመራሉ። ባይደን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት ከወጡ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመዋጋት ተመልሳለች የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ይፈልጋሉ ። ባይደን ከዋይት ሃውስ ወደ ሮም ከማቅናታቸው በፊት ለወራት የውዝግብ ውጤት የሆነውን የወጪ ቅነሳ ዕቅድን ይፋ አድርገዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራሲ አሁንም እንደሚሠራ በሁለቱ ጉባኤዎች ወቅት ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። "የተቀረው ዓለም መስራት እንችል እንደሆነ ይጠራጠራል" ማለታቸው አንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የባይደን የወጪ ዕቅዱ ምን ይዟል? 555 ቢሊዮን ዶላር፡ ታዳሽ ኃይልን ለሚጠቀሙ እና ዝቅተኛ ልቀትን ለሚያመነጬ በግብር ማበረታቻ መስጠት። 400 ቢሊዮን ዶላር፡ ለሦስት እና አራት ዓመት ህጻናት ነጻ ትምህርት። 150 ቢሊዮን ዶላር፡ አንድ ሚሊዮን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ባይደን በአንድ ትሪሊየን ዶላር የመሠረተ ልማት ፓኬጅ ዙሪያ ዲሞክራቶችን ለማሰባሰብ መጀመሪያ እየሞከሩ ነው። ይህም ቀደም ብሎ በሴኔቱ ጸድቋል ። አረንጓዴው ወጪ በ2030 የአሜሪካን የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ፣ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አዲስ የግብር እፎይታ ለመስጠት እና በአሜሪካ ቤቶች ላይ የፀሐይ ፓነሎች መትከልን አቅዷል። በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ ያላቸው አካላት ሕጉን በጽሁፍ ለማየትም በመጠየቃቸው የተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት 1,684 ገጾች ያሉትን ሰነድ ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ በመሠረተ ልማት ረቂቅ ህግ ላይ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ድምጽ አይሰጥም። ባይደን ረቡዕ ወደ ዋሽንግተን የሚመለሱ ይሆናል። የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አሁንም ቢሆን ባይደን ከሮም በስልክ ሕግ አውጭውን ለማግባባት ሊሞክሩ ይችላሉ ብለዋል ። እንደ ሪልክሊርፖሊቲክስ ከሆነ የፕሬዝዳንቱ የሥራ ተቀባይነት ደረጃ አማካይ ወደ 42.5 በመቶ ዝቅ ብሏል። | በአገር ውስጥ ጉዳይ የተወጠሩት ባይደን ስብሰባ ለመሳተፍ አውሮፓ ገቡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 2.75 ትሪሊየን ዶላር የሃገር ውስጥ አጀንዳቸውን በዋሽንግተን በመተው ለሁለት ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች አውሮፓ ገብተዋል። ባይደን በዩናይትድ ኪንግደም የአየር ንብረት ኮንፈረንስ ላይ ለሌሎች የዓለም መሪዎች የአካባቢ ጥበቃ ዕቅዳቸውን ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። የተሰሚነት ደረጃቸው እየቀነሰ የመጣው ባይደን፤ የስልጣን ዘመናቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ፕሬዚዳንቱ ራሳቸው ተናግረዋል ። ባይደን ለጂ20 ስብሰባ ዓርብ ጠዋት ሮም ደርሰዋል። በስብሰባው የዓለም ዝቅተኛ የግብር መጠን ዋነኛ አጀንዳ ይሆናል። ካቶሊክ የሆኑት ሁለተኛው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አርብ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋርም በቫቲካን ይገናኛሉ። ቀጥሎ እሁድ ምሽት ለተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት (COP26) ኮንፈረንስ ወደ ግላስጎው ስኮትላንድ ያመራሉ። ባይደን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት ከወጡ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመዋጋት ተመልሳለች የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ይፈልጋሉ ። ባይደን ከዋይት ሃውስ ወደ ሮም ከማቅናታቸው በፊት ለወራት የውዝግብ ውጤት የሆነውን የወጪ ቅነሳ ዕቅድን ይፋ አድርገዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራሲ አሁንም እንደሚሠራ በሁለቱ ጉባኤዎች ወቅት ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። "የተቀረው ዓለም መስራት እንችል እንደሆነ ይጠራጠራል" ማለታቸው አንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የባይደን የወጪ ዕቅዱ ምን ይዟል? 555 ቢሊዮን ዶላር፡ ታዳሽ ኃይልን ለሚጠቀሙ እና ዝቅተኛ ልቀትን ለሚያመነጬ በግብር ማበረታቻ መስጠት። 400 ቢሊዮን ዶላር፡ ለሦስት እና አራት ዓመት ህጻናት ነጻ ትምህርት። 150 ቢሊዮን ዶላር፡ አንድ ሚሊዮን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ባይደን በአንድ ትሪሊየን ዶላር የመሠረተ ልማት ፓኬጅ ዙሪያ ዲሞክራቶችን ለማሰባሰብ መጀመሪያ እየሞከሩ ነው። ይህም ቀደም ብሎ በሴኔቱ ጸድቋል ። አረንጓዴው ወጪ በ2030 የአሜሪካን የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ፣ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አዲስ የግብር እፎይታ ለመስጠት እና በአሜሪካ ቤቶች ላይ የፀሐይ ፓነሎች መትከልን አቅዷል። በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ ያላቸው አካላት ሕጉን በጽሁፍ ለማየትም በመጠየቃቸው የተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት 1,684 ገጾች ያሉትን ሰነድ ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ በመሠረተ ልማት ረቂቅ ህግ ላይ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ድምጽ አይሰጥም። ባይደን ረቡዕ ወደ ዋሽንግተን የሚመለሱ ይሆናል። የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አሁንም ቢሆን ባይደን ከሮም በስልክ ሕግ አውጭውን ለማግባባት ሊሞክሩ ይችላሉ ብለዋል ። እንደ ሪልክሊርፖሊቲክስ ከሆነ የፕሬዝዳንቱ የሥራ ተቀባይነት ደረጃ አማካይ ወደ 42.5 በመቶ ዝቅ ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/59074461 |
0business
| በዓመት 2ሚሊዮን ብር የሚያስከፍለው ትምህርት ቤት ጥቁሮችን ይቅርታ ጠየቀ | የኢትን ትምህርት ቤት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኝና በትምህርት ጥራቱ የገነነ ሥመ ጥር እንዲሁም ውድ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት የአሁኑን ጠቅላይ ሚኒትር ቦሪስ ጆንሰንን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦችና ሌሎች ሥመ ጥር ፖለቲከኞች ተምረውበታል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ታዲያ ለመጀመርያው የትምህርት ቤቱ ጥቁር ተማሪ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ደራሲ ዲሊቤ ኦኒያማ ከኢትን ኮሌጅ ለመመረቅ የመጀመርያው ጥቁር ነው፡፡ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ማትሪክ) የወሰደው እንደ አውሮፓዊያኑ በ1969 ዓ. ም ነበር፡፡ በኢትን ኮሌጅ ተማሪ ሳለ ይደርስበት የነበረው ዘረኝነት በተመለከተ መጽሐፍ ጽፎ አሳትሞ ነበር፡፡ ይህን በማድረጉም ትምህርት ቤቱ ‹‹እኔ ዘንድ ዝር እንዳትል›› በሚል ለረዥም ዘመን አግዶት ቆይቷል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሳይመን ሄንደርሰን "ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ነገሮች ከዚያ በኋላ ተሻሽለዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ ይቀረናል" ብለዋል፡፡ ‹‹ከኛ ትምህርት ቤት የወጡ ጥቁሮች ተማሪ ሳሉ በዘረኝነት ችግር ይደርስባቸው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ ይህን መቀበልና ማሻሻል ይኖርብናል፡፡›› ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ዲሊቤ ኦኒያማንም ቢሆን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በአካል አግኝቼው ወደ ተማረበት ትምህርት ቤት ጋብዤው ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለቢቢሲ። ዝነኛው ደራሲ ኦኒይማን ለቢቢሲ እንደተናገረው ‹‹አሁን እሱን ይቅርታ መጠየቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ስለ ኢተን ያለኝ አመለካከትንም አይቀይረውም፡፡›› ብለዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ደራሲ በየቀኑ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ዘረኝነትን ያስተናግድ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል፡፡ ‹‹ለምንድነው ጥቁር የሆንከው፣ ጸጉርህ ውስጥ ምን ያህል ዝንብና ቅማል ነው ያለው? እናትህ ለመሆኑ አፍንጫዋ ውስጥ አጥንት አለ?›› ይሉኝ ነበር ሲል ይደርስበት የነበረውን ዘረኝነት ጠቅሷል፡፡ ኦኒያማን በትምህርቱ ደከም ሲል ወይም በስፖርት የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ መምህራኑ ‹‹ይህ በዘሩ ምክንያት የመጣ ነው›› ይሉት እንደነበር ያስታውሳል፡፡ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ባመጣ ጊዜ ደግሞ ‹‹እንዴት ጥቁር ሆነው እንዲህ አይነት ውጤት አገኘህ፤ ኮርጀህ መሆን አለበት›› ይሉታል፡፡ ትምህርት ቤቱን ከለቀቀ በኋላ በዚያ ትምህርት ቤት የገጠመውን ሁሉ ጽፎ በማሳተሙ ነበር በ1972 ትምህርት ቤቱ ደብዳቤ የላከለት፡፡ መጽሐፍ በመጻፉም መቼም ቢሆን የተማረበትን ትምህርት ቤት ዳግም መጎብኘት እንደማይችል የሚገልጽ ደብዳቤ ነበር የተላከለት፡፡ አሁን የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ይቅርታ ያሉት የጆርጅ ፍሎይድን በነጭ ፖሊስ ግድያ ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ከተቀጣጠለ በኋላ ነው፡፡ በእንግሊዝ ባለፉት ሳምንታት ሁለት ግዙፍ ኩባንያዎች በተመሳሳይ ጥቁሮችን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ ባሪያ ያመላልሱ ለነበሩ የመርከብ ድርጅቶች የመድን ዋስትና ይሰጥ የነበረው ሎይድስ ኦፍ ሎንደን ኩባንያ በባሪያ ንግድ ላይ ለነበረው ሚና ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ቢራ ጠማቂው ግሪን ኪንግ የኩባንያው መስራች ድሮ በካሪቢያን በባሪያዎች ጉልበት ላይ ላደረሰው መከራ ይቅርታ ጠይቋል፡፡. ኢተን ትምህርት ቤት በንጉሥ ሄነሪ ስድስተኛ የተመሰረተ ሲሆን ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ በ1440 የሆነ ነው፡፡ በኢተን የትምህርት ጥራት የላቀ ሲሆን አሁን እዚያ ለመማር በዓመት 50ሺህ ዶላር ክፍያን ይጠይቃል፡፡ | በዓመት 2ሚሊዮን ብር የሚያስከፍለው ትምህርት ቤት ጥቁሮችን ይቅርታ ጠየቀ የኢትን ትምህርት ቤት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኝና በትምህርት ጥራቱ የገነነ ሥመ ጥር እንዲሁም ውድ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት የአሁኑን ጠቅላይ ሚኒትር ቦሪስ ጆንሰንን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦችና ሌሎች ሥመ ጥር ፖለቲከኞች ተምረውበታል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ታዲያ ለመጀመርያው የትምህርት ቤቱ ጥቁር ተማሪ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ደራሲ ዲሊቤ ኦኒያማ ከኢትን ኮሌጅ ለመመረቅ የመጀመርያው ጥቁር ነው፡፡ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ማትሪክ) የወሰደው እንደ አውሮፓዊያኑ በ1969 ዓ. ም ነበር፡፡ በኢትን ኮሌጅ ተማሪ ሳለ ይደርስበት የነበረው ዘረኝነት በተመለከተ መጽሐፍ ጽፎ አሳትሞ ነበር፡፡ ይህን በማድረጉም ትምህርት ቤቱ ‹‹እኔ ዘንድ ዝር እንዳትል›› በሚል ለረዥም ዘመን አግዶት ቆይቷል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሳይመን ሄንደርሰን "ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ነገሮች ከዚያ በኋላ ተሻሽለዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ ይቀረናል" ብለዋል፡፡ ‹‹ከኛ ትምህርት ቤት የወጡ ጥቁሮች ተማሪ ሳሉ በዘረኝነት ችግር ይደርስባቸው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ ይህን መቀበልና ማሻሻል ይኖርብናል፡፡›› ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ዲሊቤ ኦኒያማንም ቢሆን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በአካል አግኝቼው ወደ ተማረበት ትምህርት ቤት ጋብዤው ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለቢቢሲ። ዝነኛው ደራሲ ኦኒይማን ለቢቢሲ እንደተናገረው ‹‹አሁን እሱን ይቅርታ መጠየቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ስለ ኢተን ያለኝ አመለካከትንም አይቀይረውም፡፡›› ብለዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ደራሲ በየቀኑ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ዘረኝነትን ያስተናግድ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል፡፡ ‹‹ለምንድነው ጥቁር የሆንከው፣ ጸጉርህ ውስጥ ምን ያህል ዝንብና ቅማል ነው ያለው? እናትህ ለመሆኑ አፍንጫዋ ውስጥ አጥንት አለ?›› ይሉኝ ነበር ሲል ይደርስበት የነበረውን ዘረኝነት ጠቅሷል፡፡ ኦኒያማን በትምህርቱ ደከም ሲል ወይም በስፖርት የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ መምህራኑ ‹‹ይህ በዘሩ ምክንያት የመጣ ነው›› ይሉት እንደነበር ያስታውሳል፡፡ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ባመጣ ጊዜ ደግሞ ‹‹እንዴት ጥቁር ሆነው እንዲህ አይነት ውጤት አገኘህ፤ ኮርጀህ መሆን አለበት›› ይሉታል፡፡ ትምህርት ቤቱን ከለቀቀ በኋላ በዚያ ትምህርት ቤት የገጠመውን ሁሉ ጽፎ በማሳተሙ ነበር በ1972 ትምህርት ቤቱ ደብዳቤ የላከለት፡፡ መጽሐፍ በመጻፉም መቼም ቢሆን የተማረበትን ትምህርት ቤት ዳግም መጎብኘት እንደማይችል የሚገልጽ ደብዳቤ ነበር የተላከለት፡፡ አሁን የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ይቅርታ ያሉት የጆርጅ ፍሎይድን በነጭ ፖሊስ ግድያ ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ከተቀጣጠለ በኋላ ነው፡፡ በእንግሊዝ ባለፉት ሳምንታት ሁለት ግዙፍ ኩባንያዎች በተመሳሳይ ጥቁሮችን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ ባሪያ ያመላልሱ ለነበሩ የመርከብ ድርጅቶች የመድን ዋስትና ይሰጥ የነበረው ሎይድስ ኦፍ ሎንደን ኩባንያ በባሪያ ንግድ ላይ ለነበረው ሚና ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ቢራ ጠማቂው ግሪን ኪንግ የኩባንያው መስራች ድሮ በካሪቢያን በባሪያዎች ጉልበት ላይ ላደረሰው መከራ ይቅርታ ጠይቋል፡፡. ኢተን ትምህርት ቤት በንጉሥ ሄነሪ ስድስተኛ የተመሰረተ ሲሆን ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ በ1440 የሆነ ነው፡፡ በኢተን የትምህርት ጥራት የላቀ ሲሆን አሁን እዚያ ለመማር በዓመት 50ሺህ ዶላር ክፍያን ይጠይቃል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-53148768 |
5sports
| ደራርቱ ቱሉ፡ ከ30 ዓመት በፊት ለአፍሪካ ሴቶች የተተከለ የድል ችቦ | ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ነግሳ ከቆየች ድፍን 30 ዓመታት ተቆጠሩ። ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ገብታ መኖር የጀመረችው የባርሴሎና ኦሊምፒክን ተከትሎ ነው። በባርሴሎና ደግሞ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንም ፈር የቀደደ ድል ነበር ያስመዘገበችው። ሳቂታዋ ደራርቱ በሩጫው ሜዳ ብቻ ሳይሆን በስፖርት አስተዳደርም ስሟ በበጎ ይነሳል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት፣ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ በምክት ፕሬዝዳንትነት እና በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ደግሞ ኢትዮጵያን ወክላ የምክር ቤቱ አባል የሆነችው ደራርቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቃለ ምልልስ ባርሴሎናን አስታውሳለች። ሩጫ እንዴት ጀመርሽ? ሩጫ የጀመርኩት በቆጂ ትምህርት ቤት እያለሁ ነው። ሩጫ እወድ ነበር። እረኛም ስለሆንኩኝ ከብትም ለመመለስ ስሄድ፣ ውሃም ስቀዳ፣ ጎረቤትም ስላክ ገበያም ስላክ ሁሌ በሩጫ ነው። ውሃ ስቀዳ ትንሿን ገንቦዬን ተሸክሜ እሮጥ ነበር። ከሩጫ ጎን ለጎን ደግሞ ፈረስ መጋለብ እወድ ነበር። ትምህርት ቤት ውስጥ ሩጫ የጀመርኩት በ15 ዓመቴ ነበር። ሩጫ እና ፈረስ ግልቢያ የኔ መዝናኛዎች ናቸው። በሩጫ እታወቃለሁ ብዬ ሳይሆን እንዲሁ ስለምወድ ነበር የምሮጠው። እግዚአብሔር ፈቅዶ ደግሞ እንጀራዬ አደረገው። በሩጫ ለመጀመርያ ግዜ መወዳደር የጀመርሽው የት ነው? ለምን? ሩጫን የጀመርኩት አርሲ ውስጥ በትንሿ በቆጂ ከተማ በትምህርት ቤቴ ነው። በትምህርት ቤት ውስጥ ለስፖርት ክፍለ ጊዜ፣ ለማርክ ሲባል የተለያዩ ስፖርቶችን እንሰራ እና እንጫወት ነበር። በዚያውም በውድድሮች ላይ መሳተፍ ጀመርኩኝ። ለትምህርት ቤት፣ ለወረዳ፣ ለአውራጃ ከዚያ ለክፍለ አገር ለመወዳደር በቃሁ። እኤአ በ1992 ኦሊምፒክ ላይ ስትሳተፊ ምን ተሰማሽ? እስካሁንም ድረስ ለባርሴሎና ኦሊምፒክ ያለኝ ስሜት ትልቅ ነው። ምክንያቱም እስካሁንም ከአገሬ ሕዝብ እንዲሁም ከዓለም ማኅበረሰብ ጋር ያስተዋወቀኝ ውድድር ነው። ከእኔ መታወቅ፣ ከእኔ ደስታ በላይ ደግሞ በባርሴሎና ኦሊምፒክ ላይ የእኔ ማሸነፍ ለኢትዮጵያ ሴቶች በር ከፋች በመሆኑ በጣም ደስ ይለኛል። ሁልጊዜም የምደሰትበት ነው። ለካ ሴቶችም ከሰሩ፣ ወደ ስፖርቱ መድረክ ከመጡ በእንደዚህ ዓይነት የአደባባይ ውድድሮች ላይ ማሸነፍ ይችላሉ ብለው የኢትዯጵያ ሴት አትሌቶች ተነሱ። በዚያ ነው እስካሁን ድረስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ሴቶች የበረከቱት። ስለዚህ የባርሴሎና ድል ለእኔ ሁለት ስሜት፣ ሁለት ደስታ አለው። ባርሴሎና ላይ በወቅቱ ስትሳተፊ አሸንፋለሁ የሚል የራስ መተማመን ነበረሽ? እንዲህ ዓይነት ዝግጁነት ነበረሽ? ከዚያ በፊት በተወሰኑ ውድድሮች ላይ ተሳትፌአለሁ። ኦሊምፒክ ግን የመጀመሪያዬ ነበር። ባርሴሎናን እንደ ማንኛውም ውድድር ነበር ያየሁት። ምክንያቱም በዚያን ወቅት ኦሊምፒክ ከሌሎች ውድድሮች ምን ያህል እንደሚለይ ለይቼ ስለማላውቅ እንደማንኛውም ውድድር ነበር ያየሁት። ነገር ግን የውድድሩን ትልቅነት የሚያውቁት፣ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው አሰልጣኜ አስፈላጊውን ልምምድ አድርገን በከፍተኛ ሁኔታ ነበር ያዘጋጁን። በወቅቱ ምንም ዓይነት የፍርሃት ስሜት አልነበረኝም፤ ምክንያቱም በእድሜ ልጅ ነበርኩ። የመጀመሪያዬ የኦሊሎምፒክ ውድድርም ስለሆነ መሸነፍና ማሸነፉ ብዙም አላስጨነቀኝም። ግን ጥሩ አቋም ላይ ነበርኩኝ። ከዚያ ውድድር በፊት ጃፓን ቶኪዮ ላይ ተወዳድሬ ነበር ስምንተኛ ነበር የወጣሁት። ስለዚህ ባርሴሎና ላይ እንደ ቶኪዮው መጨረሻ ላይ ሄደሽ እንዳትቆሚ ከፊት ከሚሄዱት ጋር እግር በእግር እየተከተልሽ ሂጂ ተብዬ ነበር። በወቅቱ 10 ሺህ ማጣሪያ ነበረው። እዚያ ላይ ፉክክሩን ስታዬ ምን ነበር ስሜትሽ? ጥሩ አቋም ላይ ስለነበርኩኝ፣ ጥሩ ስለተዘጋጀሁኝ ማጣሪያውም ፍጻሜውም አልከበደኝም። አሰልጣኜ በቂ ልምምድ እና ዝግጅት እንድሰራ በማድጋቸው ብዙ አልተቸገርኩም። ሌላው ደግሞ አብረውን የሚወዳደሩትን ብዙዎቹን አላውቃቸውም ነበር። እኔ የማውቀው ሁለት አትሌቶችን ብቻ ነበር። ሌሎቹን አላውቃቸውም። እናም ብዙ አልከበደኝም። በወቅቱ በተካሄዱት የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድር መካከል ምን ታደርጊ በር? (ሳቅ) አሰልጣኜ ዓለም አቀፍ አሰልጣኝ ናቸው። እርሳቸው ከውድድር በፊት ምን እንደምንሰራ፣ በውድድር መካከል ደግሞ ምን እንደምናደርግ ያውቃሉ። የረዥም ጊዜ ውድድር ፕሮግራም ምን እነደሆነ፣ በዚያ መካከል ደግሞ በማጣሪያ እና በፍጻሜ መካከል ደግሞ ያለውን ስለሚያውቁ እርሳቸው የሚሰጡንን ልምምድ ነበር የምንሰራው። እንግዲህ አሁን ብዙ አላስታውስም ግን እርሳቸው የሚሰጡንን ስሰራ ደስተኛ ሆኜ ነበር የምሰራው። ግን ከማጣሪያው በኋላ ለፍጻሜውም አልተጨናነኩም ነበር። ከውድድር በፊት የምታደርጊው የተለየ ነገር አለ? ሌላ ጊዜ አንደማደርገው ልምምዴን ከቁርስ በፊት ወይንም ደግሞ በኋላ ልሰራ እችላለሁ። ከሰራሁም በኋላ ደግሞ እተኛለሁ። ስለዚህ እበላለሁ፣ እጠጣለሁ፣ ከዚያ ደግሞ አርፋለሁ። ከዚያ ውጪ የተለመደው ምግብ፣ የተለመደው እረፍት፣ የተለመደውን ልምምድ ነው ያደረግኩት። ማታ ራሱ ማሟሟቂያ ሰዓቴ እስኪደረስ ድረስ ስታዲየም ውስጥ መተኛቴ ትዝ እለኛል። ማማሟቂያ ሜዳ ላይ በጣም ጥሩ እንቅልፍ መተኛቴ ትዝ ይለኛል። ትዝ ይለኛል አሰልጣኜ ነበረ የቀሰቀሱኝ። ብዙ ነገር ስለባርሴሎና ይረሳኛል ይህ ግን አይረሳኝም። ስለ ፍጻሜው ውድድር ትዝ የሚልሽ ነገር ምንድን ነው? ሳስብ የነበረው አሰልጣኜ ልክ የቶኪዮው ዓይነት ነገር እንዳይገጥመኝ የመከሩኝን ነበር። እሱም ተጠንቅቀሽ ሩጪ፣ ከከበደሽ በራስሸ ጊዜ ሩጪ፣ እንዳትደነዝዢ ነበር ያሉኝ። እርሳቸውም እነዳሉኝ፣ ቀስ እያልኩ ነበር ዙሩን የሄድኩት። ምክንያቱም እርሳቸው ልጆቹ ፈጥነው የሚሄዱብሽ ከሆነ ራስሽን ጠብቀሽ ሂጂ ብለውኝ ነበር። ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤለና ሜየር አስር ዙር ሲቀር ነበር የሄደችው እና እኔ ቀረት ብዬ ቀስ ብዬ ነበር የደረስኩባት። ምክንያቱም እኔ አሰልጣኜን በጣም አከብራለሁ። በጣም እወዳቸዋለሁ። የሚሉኝንም ስለምሰማ እና ቃላቸውን ስለማከብር እርሳቸው የመከሩኝን ነበር እያሰብኩ ስሮጥ የነበረው። ከሦስት፣ ከአራት ዙር በኋላ ነበር የደረስኩባቸው። ልክ አሰልጣኜ የመከሩኝን ነበረ የማደርገው። ስታሸንፊ ምን ተሰማሽ? በወቅቱ የስፔኗ ባርሴሎና በጣም ሞቃት ነበረች፣ በዚያ ሙቀት ቲሸርት ደርቤ ነበር ስሮጥ የነበረው። ነገር ግን አቋሜ ጥሩ ነበረ። ልክ 400 ሜትር ሲቀር እንደምወጣ እና በአጨራረስ እንደማሸንፋቸው ነበር የማስበው እና ጥሩ ስሜት ነበር የተሰማኝ። ደስታውም ወደር አልነበረውም። ውድድሩን በአሸናፊነት ካጠናቀቅሽ በኋላ ከኤላና ሜየር ጋር ደስታችሁን በጋራ ነበር የገለጻችሁት፤ ለምን? ይሄማ ሁል ጊዜ የሚደረግ ነገር ነው። ምክንያቱም አሸንፈን ሁለታችንም አንደኛ እና ሁለተኛ ነው የወጣነው። አንደኛው ሁለታችንም ከአፍሪካ ነበርን። ሁለተኛው ደግሞ አፓርታይድ ያበቃበት ወቅት ነበር። ደቡበን አፍሪካውያን በዚያን ጊዜ ከአፓርታይድ ሥርዓት ማብቃት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ኦሊምፒክ ስለነበር በጋራ ደስታችንን ገለጽን። ከኤሌና ጋር ባንተዋወቅም እንግዲህ ስፖርት ለእህትማማችንት፣ ለሰላም፣ ለፍቅር የሚለው እዚያ ሜዳ ላይ ታየ ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ነበር ደስታችንን ነው የገለጽነው ማለት ነው። ከድል በኋላ በአገር ቤት የነበረው አቀባበል ምን ይመስል ነበር? (ሳቅ) በጣም የተለየ ነበር። በጣም በጣም የተለየ እና እስከዛሬም ድረስ ልዩ ስሜት የሚፈጥርብኝ አቀባበል ነበር። ቤተሰቤ፣ ፌዴሬሽናችን፣ አገራችን፣ መሥሪያ ቤቴ (ማረሚያ ቤቶች)፣ ጓደኞቼ ሁሉም በአጠቃላይ እንደ አገር ጀግና ነበር የተቀበሉኝ። እና ሁሌም በጣም በጣም ሁሌም የማይረሳ አቀባበል ነው ያደረጉልኝ። በጣም ነበር ደስ ያለኝ። በተጨማሪም እኔ ወታደር ስለሆንኩ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ያገኘሁበትም ነው። በወቅቱ ከፍተኛ ገንዘብ የተሸለምኩበት፣ እንደገና ደግሞ በአገሬ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያወቀኝ፣ እና ብቻ ለእኔ ልዩ ነበር ያ ጊዜ። አሸናፊነትሽ ጥሎ ያለፈው ነገር ምንድን ነው? እንዴት እታወሳለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ? (ሳቅ) እንግዲህ ጥሎ ያለፈው እንደገለጽኩት ከሕዝበ ጋር ያስተዋወቀኝ ይህ የባርሴሎና ድል ነው። ሁለተኛ ደግሞ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ምሳሌ መሆኔ የእኔ ውርስ [ሌጋሲ] ነው ብዬ አስባለሁ። የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ በመሆንሽ እና ለአገርሽ እና ለአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ውጤት ማስመዝገብሽ ምን ስሜት ፈጥሮብሽ ነበር? (ሳቅ) እንግዲህ ባርሴሎና የመጀመሪያዬ ይሁን አንጂ ብዙ ውድድሮችን አድርጌያለሁ። ከአገር አቋራጭ ጀመሮ የተለያዩ ውድድሮችን አሸንፌያለሁ። ብዙ የተለየ ነገር አይሰማኝም። እንዲያውም ምንድን ነው አሁን ከአትሌትነት ወጥቼ ወደ ስፖርት አመራርነት ስመጣ እና በቅርቡ ደግሞ ከአሜሪካ ኦሪገን በድል ስንመለስ ልክ የባርሴሎናው እና የሲድኒው ጊዜ ድል ነው ትዝ ያለኝ። በሩጫ ዘመኔ እንደዚህ ዓይነት አቀባበል ሲደረግ ማየቴ በጣም ነው ያስደሰተኝ። ምከንያቱም አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ነው እንደዚህ ዓይነት ዕድል የሚሰጠው። እኔ ያሳለፍኩባቸው ጊዜያት ወርቃማ ናቸው። ምክንያቱም ያለውንም ጊዜ በደንብ ነበር የተጠቀምኩበት። በጣም ነው ደስ የሚለኝ። በጣም በጣም ወርቃማ ጊዜያት ነበሩ። ለእኔም ለቤተሰቤም ልዩ ጊዜ ነበር። የዛሬ 30 ዓመትን ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስታውሰው በጣም ደስ ይለኛል። ሦስት የቤተሰቦችሽ አባልም በሩጫው ዘርፍ ውጤታማ አትሌቶች ናቸው። ቤተሰቦችሽ በሩጫው ውጤታማ የመሆናቸው ሚስጥሩ ምንድን ነው? (ረዥም ሳቅ) ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ምንም የተለየ ምስጢር የለውም። አንዱ ደግሞ ወደዚህ እስከመጣሁ ድረስ እኔ በጣም ሥራዬን አክባሪ ነኝ። ታታሪ ነኝ። የሚጠበቅብኝን በሚገባ እሰራለሁ። ልምምዴን በደንብ እሰራለሁ። አንድ ሰው ሥራው በእግዚአብሔር እንዲባረክልት በተቻለ መጠን መልፋት፣ መጣር አለበት። ከዚያ ደግሞ ባለው ዕምነት እግዚአብሔር ጥረቱን እንዲባርክለት ፀሎት ማድረግ አለበት። ዋናው ጠንክሮ መስራት፣ መታገስ፣ ለሥራ ያለን ፍቅር ማሳየት ነው። ይኸው ነው ሌላ የተለየ ነገር የለውም። የስፖርት ቡድንን ለመቀላቀል ብለሽ ለእናትሽ ሳትናገሪ መሄድሽ እውነት ነው? ከዛሬ 35 ዓመት በፊት እኔ ሩጫ ስጀምር አገር ቤት የነበረው አመለካከት፣ ሴት ልጅ ረዥም ቀሚስ ለብሳ፣ በሥነ ሥርዓት ትምህርቷን ተምራ፣ ትዳርም የምትይዝ ከሆነ በሥርዓቱ ተድራ ቤተሰብ ትመሠርታለች እንጂ በቁምጣ መታየት ነውር ነው። ስለዚህ እናቴም እንደ አንድ እናት ጥሩ ልጅ ሆኜ፣ ጨዋ ልጅ ሆኜ እንዳድግ ትፈልጋለች። ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከወንድ ጋር መሮጥ፣ በቁምጣ መሮጥ፣ እንደ ባለጌ ልጅ፣ ሥነ ምግባር እንደ ሌላት ልጅ ያስቆጥራል። ስለዚህ ለእናቴ ፍላጎቴን ብነግራት ስለማትፈቅድልኝ ለአባቴ እና ለእህቶቼ፣ ለአክስቶቼ ነግሬ ነበር የመጣሁት። በዚያው ወቅት ባርሴሎና ከሩጫ ሜዳው ውጪ ምን ተሰማሽ? ከተማውን ጎበኘሽ? (ሳቅ) በዚያ ወቅት ምንም አላየሁም። ምክንያቱም ሁልጊዜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች፣ አሁንም ድረስ የምናደርገው የግል ውድድር ካልሆነ በስተቀር፣ አገር ወክለን ስንሄድ ውድድራችን እና ልምምዳችን ላይ ነው የምናተኩረው። ውድድር የጨረሰ ውድድር ያልጨረሰውን መደገፍ ማበረታታት እንጂ እንደዚህ ከተማ የመዞር፣ ገበያ የመሄድ ብዙም ልምድ የለንም። እስከዛሬ ድረስም የኢትዮጵያን አትሌቶች፣ አንዱ የማመሰግንበት ነገር ይሄ ነው። ስለዚህም የዚያን ጊዜ ባርሴሎናን ተዘዋውሬ አላየኋትም። ነገር ግን የማስታውሰው ልምምድ በምሰራበት ወቅት፣ የልምምድ ስታዲየም መኖሩ፣ ምግብ ቤቶቹ 24 ሰዓት ክፍት መሆናቸው እርሱ እርሱ ለእኔ ይገርመኝ ነበር። የሚስተናገደው ሰው ብዛት ይገርመኝ ነበር። በቁርስ ሰዓት፣ በምሳ ሰዓት በእራት ሰዓት ሰዉ አይቀንስም እና ወጪ ወራጁ መብዛቱ ይገርመኝ ነበር። በወቅቱ ከተማዋን ተዘዋውሬ ባላያትም የባርሴሎና ኦሊምፒክ ለእኔ አሁንም ድረስ የተለየ ነው። ከባርሴሎና በኋላ ከኤለና ሜየር ጋር ግንኙነታችሁ ቀጥሏል? እርሷ ናት ከእኔ ቀድማ ሩጫ ያቆመችው። ሩጫ እስክታቆም ድረስ እንገናኝ ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ በአጋጣሚ እንገናኝ ነበር። የደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክተሬት ሲሰጠኝ የክብር እንግዳ ሆና መጥታ ተገናኝተናል። ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘነው ያኔ ነው። | ደራርቱ ቱሉ፡ ከ30 ዓመት በፊት ለአፍሪካ ሴቶች የተተከለ የድል ችቦ ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ነግሳ ከቆየች ድፍን 30 ዓመታት ተቆጠሩ። ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ገብታ መኖር የጀመረችው የባርሴሎና ኦሊምፒክን ተከትሎ ነው። በባርሴሎና ደግሞ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንም ፈር የቀደደ ድል ነበር ያስመዘገበችው። ሳቂታዋ ደራርቱ በሩጫው ሜዳ ብቻ ሳይሆን በስፖርት አስተዳደርም ስሟ በበጎ ይነሳል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት፣ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ በምክት ፕሬዝዳንትነት እና በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ደግሞ ኢትዮጵያን ወክላ የምክር ቤቱ አባል የሆነችው ደራርቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቃለ ምልልስ ባርሴሎናን አስታውሳለች። ሩጫ እንዴት ጀመርሽ? ሩጫ የጀመርኩት በቆጂ ትምህርት ቤት እያለሁ ነው። ሩጫ እወድ ነበር። እረኛም ስለሆንኩኝ ከብትም ለመመለስ ስሄድ፣ ውሃም ስቀዳ፣ ጎረቤትም ስላክ ገበያም ስላክ ሁሌ በሩጫ ነው። ውሃ ስቀዳ ትንሿን ገንቦዬን ተሸክሜ እሮጥ ነበር። ከሩጫ ጎን ለጎን ደግሞ ፈረስ መጋለብ እወድ ነበር። ትምህርት ቤት ውስጥ ሩጫ የጀመርኩት በ15 ዓመቴ ነበር። ሩጫ እና ፈረስ ግልቢያ የኔ መዝናኛዎች ናቸው። በሩጫ እታወቃለሁ ብዬ ሳይሆን እንዲሁ ስለምወድ ነበር የምሮጠው። እግዚአብሔር ፈቅዶ ደግሞ እንጀራዬ አደረገው። በሩጫ ለመጀመርያ ግዜ መወዳደር የጀመርሽው የት ነው? ለምን? ሩጫን የጀመርኩት አርሲ ውስጥ በትንሿ በቆጂ ከተማ በትምህርት ቤቴ ነው። በትምህርት ቤት ውስጥ ለስፖርት ክፍለ ጊዜ፣ ለማርክ ሲባል የተለያዩ ስፖርቶችን እንሰራ እና እንጫወት ነበር። በዚያውም በውድድሮች ላይ መሳተፍ ጀመርኩኝ። ለትምህርት ቤት፣ ለወረዳ፣ ለአውራጃ ከዚያ ለክፍለ አገር ለመወዳደር በቃሁ። እኤአ በ1992 ኦሊምፒክ ላይ ስትሳተፊ ምን ተሰማሽ? እስካሁንም ድረስ ለባርሴሎና ኦሊምፒክ ያለኝ ስሜት ትልቅ ነው። ምክንያቱም እስካሁንም ከአገሬ ሕዝብ እንዲሁም ከዓለም ማኅበረሰብ ጋር ያስተዋወቀኝ ውድድር ነው። ከእኔ መታወቅ፣ ከእኔ ደስታ በላይ ደግሞ በባርሴሎና ኦሊምፒክ ላይ የእኔ ማሸነፍ ለኢትዮጵያ ሴቶች በር ከፋች በመሆኑ በጣም ደስ ይለኛል። ሁልጊዜም የምደሰትበት ነው። ለካ ሴቶችም ከሰሩ፣ ወደ ስፖርቱ መድረክ ከመጡ በእንደዚህ ዓይነት የአደባባይ ውድድሮች ላይ ማሸነፍ ይችላሉ ብለው የኢትዯጵያ ሴት አትሌቶች ተነሱ። በዚያ ነው እስካሁን ድረስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ሴቶች የበረከቱት። ስለዚህ የባርሴሎና ድል ለእኔ ሁለት ስሜት፣ ሁለት ደስታ አለው። ባርሴሎና ላይ በወቅቱ ስትሳተፊ አሸንፋለሁ የሚል የራስ መተማመን ነበረሽ? እንዲህ ዓይነት ዝግጁነት ነበረሽ? ከዚያ በፊት በተወሰኑ ውድድሮች ላይ ተሳትፌአለሁ። ኦሊምፒክ ግን የመጀመሪያዬ ነበር። ባርሴሎናን እንደ ማንኛውም ውድድር ነበር ያየሁት። ምክንያቱም በዚያን ወቅት ኦሊምፒክ ከሌሎች ውድድሮች ምን ያህል እንደሚለይ ለይቼ ስለማላውቅ እንደማንኛውም ውድድር ነበር ያየሁት። ነገር ግን የውድድሩን ትልቅነት የሚያውቁት፣ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው አሰልጣኜ አስፈላጊውን ልምምድ አድርገን በከፍተኛ ሁኔታ ነበር ያዘጋጁን። በወቅቱ ምንም ዓይነት የፍርሃት ስሜት አልነበረኝም፤ ምክንያቱም በእድሜ ልጅ ነበርኩ። የመጀመሪያዬ የኦሊሎምፒክ ውድድርም ስለሆነ መሸነፍና ማሸነፉ ብዙም አላስጨነቀኝም። ግን ጥሩ አቋም ላይ ነበርኩኝ። ከዚያ ውድድር በፊት ጃፓን ቶኪዮ ላይ ተወዳድሬ ነበር ስምንተኛ ነበር የወጣሁት። ስለዚህ ባርሴሎና ላይ እንደ ቶኪዮው መጨረሻ ላይ ሄደሽ እንዳትቆሚ ከፊት ከሚሄዱት ጋር እግር በእግር እየተከተልሽ ሂጂ ተብዬ ነበር። በወቅቱ 10 ሺህ ማጣሪያ ነበረው። እዚያ ላይ ፉክክሩን ስታዬ ምን ነበር ስሜትሽ? ጥሩ አቋም ላይ ስለነበርኩኝ፣ ጥሩ ስለተዘጋጀሁኝ ማጣሪያውም ፍጻሜውም አልከበደኝም። አሰልጣኜ በቂ ልምምድ እና ዝግጅት እንድሰራ በማድጋቸው ብዙ አልተቸገርኩም። ሌላው ደግሞ አብረውን የሚወዳደሩትን ብዙዎቹን አላውቃቸውም ነበር። እኔ የማውቀው ሁለት አትሌቶችን ብቻ ነበር። ሌሎቹን አላውቃቸውም። እናም ብዙ አልከበደኝም። በወቅቱ በተካሄዱት የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድር መካከል ምን ታደርጊ በር? (ሳቅ) አሰልጣኜ ዓለም አቀፍ አሰልጣኝ ናቸው። እርሳቸው ከውድድር በፊት ምን እንደምንሰራ፣ በውድድር መካከል ደግሞ ምን እንደምናደርግ ያውቃሉ። የረዥም ጊዜ ውድድር ፕሮግራም ምን እነደሆነ፣ በዚያ መካከል ደግሞ በማጣሪያ እና በፍጻሜ መካከል ደግሞ ያለውን ስለሚያውቁ እርሳቸው የሚሰጡንን ልምምድ ነበር የምንሰራው። እንግዲህ አሁን ብዙ አላስታውስም ግን እርሳቸው የሚሰጡንን ስሰራ ደስተኛ ሆኜ ነበር የምሰራው። ግን ከማጣሪያው በኋላ ለፍጻሜውም አልተጨናነኩም ነበር። ከውድድር በፊት የምታደርጊው የተለየ ነገር አለ? ሌላ ጊዜ አንደማደርገው ልምምዴን ከቁርስ በፊት ወይንም ደግሞ በኋላ ልሰራ እችላለሁ። ከሰራሁም በኋላ ደግሞ እተኛለሁ። ስለዚህ እበላለሁ፣ እጠጣለሁ፣ ከዚያ ደግሞ አርፋለሁ። ከዚያ ውጪ የተለመደው ምግብ፣ የተለመደው እረፍት፣ የተለመደውን ልምምድ ነው ያደረግኩት። ማታ ራሱ ማሟሟቂያ ሰዓቴ እስኪደረስ ድረስ ስታዲየም ውስጥ መተኛቴ ትዝ እለኛል። ማማሟቂያ ሜዳ ላይ በጣም ጥሩ እንቅልፍ መተኛቴ ትዝ ይለኛል። ትዝ ይለኛል አሰልጣኜ ነበረ የቀሰቀሱኝ። ብዙ ነገር ስለባርሴሎና ይረሳኛል ይህ ግን አይረሳኝም። ስለ ፍጻሜው ውድድር ትዝ የሚልሽ ነገር ምንድን ነው? ሳስብ የነበረው አሰልጣኜ ልክ የቶኪዮው ዓይነት ነገር እንዳይገጥመኝ የመከሩኝን ነበር። እሱም ተጠንቅቀሽ ሩጪ፣ ከከበደሽ በራስሸ ጊዜ ሩጪ፣ እንዳትደነዝዢ ነበር ያሉኝ። እርሳቸውም እነዳሉኝ፣ ቀስ እያልኩ ነበር ዙሩን የሄድኩት። ምክንያቱም እርሳቸው ልጆቹ ፈጥነው የሚሄዱብሽ ከሆነ ራስሽን ጠብቀሽ ሂጂ ብለውኝ ነበር። ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤለና ሜየር አስር ዙር ሲቀር ነበር የሄደችው እና እኔ ቀረት ብዬ ቀስ ብዬ ነበር የደረስኩባት። ምክንያቱም እኔ አሰልጣኜን በጣም አከብራለሁ። በጣም እወዳቸዋለሁ። የሚሉኝንም ስለምሰማ እና ቃላቸውን ስለማከብር እርሳቸው የመከሩኝን ነበር እያሰብኩ ስሮጥ የነበረው። ከሦስት፣ ከአራት ዙር በኋላ ነበር የደረስኩባቸው። ልክ አሰልጣኜ የመከሩኝን ነበረ የማደርገው። ስታሸንፊ ምን ተሰማሽ? በወቅቱ የስፔኗ ባርሴሎና በጣም ሞቃት ነበረች፣ በዚያ ሙቀት ቲሸርት ደርቤ ነበር ስሮጥ የነበረው። ነገር ግን አቋሜ ጥሩ ነበረ። ልክ 400 ሜትር ሲቀር እንደምወጣ እና በአጨራረስ እንደማሸንፋቸው ነበር የማስበው እና ጥሩ ስሜት ነበር የተሰማኝ። ደስታውም ወደር አልነበረውም። ውድድሩን በአሸናፊነት ካጠናቀቅሽ በኋላ ከኤላና ሜየር ጋር ደስታችሁን በጋራ ነበር የገለጻችሁት፤ ለምን? ይሄማ ሁል ጊዜ የሚደረግ ነገር ነው። ምክንያቱም አሸንፈን ሁለታችንም አንደኛ እና ሁለተኛ ነው የወጣነው። አንደኛው ሁለታችንም ከአፍሪካ ነበርን። ሁለተኛው ደግሞ አፓርታይድ ያበቃበት ወቅት ነበር። ደቡበን አፍሪካውያን በዚያን ጊዜ ከአፓርታይድ ሥርዓት ማብቃት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ኦሊምፒክ ስለነበር በጋራ ደስታችንን ገለጽን። ከኤሌና ጋር ባንተዋወቅም እንግዲህ ስፖርት ለእህትማማችንት፣ ለሰላም፣ ለፍቅር የሚለው እዚያ ሜዳ ላይ ታየ ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ነበር ደስታችንን ነው የገለጽነው ማለት ነው። ከድል በኋላ በአገር ቤት የነበረው አቀባበል ምን ይመስል ነበር? (ሳቅ) በጣም የተለየ ነበር። በጣም በጣም የተለየ እና እስከዛሬም ድረስ ልዩ ስሜት የሚፈጥርብኝ አቀባበል ነበር። ቤተሰቤ፣ ፌዴሬሽናችን፣ አገራችን፣ መሥሪያ ቤቴ (ማረሚያ ቤቶች)፣ ጓደኞቼ ሁሉም በአጠቃላይ እንደ አገር ጀግና ነበር የተቀበሉኝ። እና ሁሌም በጣም በጣም ሁሌም የማይረሳ አቀባበል ነው ያደረጉልኝ። በጣም ነበር ደስ ያለኝ። በተጨማሪም እኔ ወታደር ስለሆንኩ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ያገኘሁበትም ነው። በወቅቱ ከፍተኛ ገንዘብ የተሸለምኩበት፣ እንደገና ደግሞ በአገሬ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያወቀኝ፣ እና ብቻ ለእኔ ልዩ ነበር ያ ጊዜ። አሸናፊነትሽ ጥሎ ያለፈው ነገር ምንድን ነው? እንዴት እታወሳለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ? (ሳቅ) እንግዲህ ጥሎ ያለፈው እንደገለጽኩት ከሕዝበ ጋር ያስተዋወቀኝ ይህ የባርሴሎና ድል ነው። ሁለተኛ ደግሞ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ምሳሌ መሆኔ የእኔ ውርስ [ሌጋሲ] ነው ብዬ አስባለሁ። የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ በመሆንሽ እና ለአገርሽ እና ለአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ውጤት ማስመዝገብሽ ምን ስሜት ፈጥሮብሽ ነበር? (ሳቅ) እንግዲህ ባርሴሎና የመጀመሪያዬ ይሁን አንጂ ብዙ ውድድሮችን አድርጌያለሁ። ከአገር አቋራጭ ጀመሮ የተለያዩ ውድድሮችን አሸንፌያለሁ። ብዙ የተለየ ነገር አይሰማኝም። እንዲያውም ምንድን ነው አሁን ከአትሌትነት ወጥቼ ወደ ስፖርት አመራርነት ስመጣ እና በቅርቡ ደግሞ ከአሜሪካ ኦሪገን በድል ስንመለስ ልክ የባርሴሎናው እና የሲድኒው ጊዜ ድል ነው ትዝ ያለኝ። በሩጫ ዘመኔ እንደዚህ ዓይነት አቀባበል ሲደረግ ማየቴ በጣም ነው ያስደሰተኝ። ምከንያቱም አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ነው እንደዚህ ዓይነት ዕድል የሚሰጠው። እኔ ያሳለፍኩባቸው ጊዜያት ወርቃማ ናቸው። ምክንያቱም ያለውንም ጊዜ በደንብ ነበር የተጠቀምኩበት። በጣም ነው ደስ የሚለኝ። በጣም በጣም ወርቃማ ጊዜያት ነበሩ። ለእኔም ለቤተሰቤም ልዩ ጊዜ ነበር። የዛሬ 30 ዓመትን ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስታውሰው በጣም ደስ ይለኛል። ሦስት የቤተሰቦችሽ አባልም በሩጫው ዘርፍ ውጤታማ አትሌቶች ናቸው። ቤተሰቦችሽ በሩጫው ውጤታማ የመሆናቸው ሚስጥሩ ምንድን ነው? (ረዥም ሳቅ) ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ምንም የተለየ ምስጢር የለውም። አንዱ ደግሞ ወደዚህ እስከመጣሁ ድረስ እኔ በጣም ሥራዬን አክባሪ ነኝ። ታታሪ ነኝ። የሚጠበቅብኝን በሚገባ እሰራለሁ። ልምምዴን በደንብ እሰራለሁ። አንድ ሰው ሥራው በእግዚአብሔር እንዲባረክልት በተቻለ መጠን መልፋት፣ መጣር አለበት። ከዚያ ደግሞ ባለው ዕምነት እግዚአብሔር ጥረቱን እንዲባርክለት ፀሎት ማድረግ አለበት። ዋናው ጠንክሮ መስራት፣ መታገስ፣ ለሥራ ያለን ፍቅር ማሳየት ነው። ይኸው ነው ሌላ የተለየ ነገር የለውም። የስፖርት ቡድንን ለመቀላቀል ብለሽ ለእናትሽ ሳትናገሪ መሄድሽ እውነት ነው? ከዛሬ 35 ዓመት በፊት እኔ ሩጫ ስጀምር አገር ቤት የነበረው አመለካከት፣ ሴት ልጅ ረዥም ቀሚስ ለብሳ፣ በሥነ ሥርዓት ትምህርቷን ተምራ፣ ትዳርም የምትይዝ ከሆነ በሥርዓቱ ተድራ ቤተሰብ ትመሠርታለች እንጂ በቁምጣ መታየት ነውር ነው። ስለዚህ እናቴም እንደ አንድ እናት ጥሩ ልጅ ሆኜ፣ ጨዋ ልጅ ሆኜ እንዳድግ ትፈልጋለች። ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከወንድ ጋር መሮጥ፣ በቁምጣ መሮጥ፣ እንደ ባለጌ ልጅ፣ ሥነ ምግባር እንደ ሌላት ልጅ ያስቆጥራል። ስለዚህ ለእናቴ ፍላጎቴን ብነግራት ስለማትፈቅድልኝ ለአባቴ እና ለእህቶቼ፣ ለአክስቶቼ ነግሬ ነበር የመጣሁት። በዚያው ወቅት ባርሴሎና ከሩጫ ሜዳው ውጪ ምን ተሰማሽ? ከተማውን ጎበኘሽ? (ሳቅ) በዚያ ወቅት ምንም አላየሁም። ምክንያቱም ሁልጊዜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች፣ አሁንም ድረስ የምናደርገው የግል ውድድር ካልሆነ በስተቀር፣ አገር ወክለን ስንሄድ ውድድራችን እና ልምምዳችን ላይ ነው የምናተኩረው። ውድድር የጨረሰ ውድድር ያልጨረሰውን መደገፍ ማበረታታት እንጂ እንደዚህ ከተማ የመዞር፣ ገበያ የመሄድ ብዙም ልምድ የለንም። እስከዛሬ ድረስም የኢትዮጵያን አትሌቶች፣ አንዱ የማመሰግንበት ነገር ይሄ ነው። ስለዚህም የዚያን ጊዜ ባርሴሎናን ተዘዋውሬ አላየኋትም። ነገር ግን የማስታውሰው ልምምድ በምሰራበት ወቅት፣ የልምምድ ስታዲየም መኖሩ፣ ምግብ ቤቶቹ 24 ሰዓት ክፍት መሆናቸው እርሱ እርሱ ለእኔ ይገርመኝ ነበር። የሚስተናገደው ሰው ብዛት ይገርመኝ ነበር። በቁርስ ሰዓት፣ በምሳ ሰዓት በእራት ሰዓት ሰዉ አይቀንስም እና ወጪ ወራጁ መብዛቱ ይገርመኝ ነበር። በወቅቱ ከተማዋን ተዘዋውሬ ባላያትም የባርሴሎና ኦሊምፒክ ለእኔ አሁንም ድረስ የተለየ ነው። ከባርሴሎና በኋላ ከኤለና ሜየር ጋር ግንኙነታችሁ ቀጥሏል? እርሷ ናት ከእኔ ቀድማ ሩጫ ያቆመችው። ሩጫ እስክታቆም ድረስ እንገናኝ ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ በአጋጣሚ እንገናኝ ነበር። የደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክተሬት ሲሰጠኝ የክብር እንግዳ ሆና መጥታ ተገናኝተናል። ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘነው ያኔ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c891j8lrn81o |
3politics
| ባይደን እና ፑቲን በዩክሬን ጉዳይ 'ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ' ፍለጋ ሊወያዩ ነው | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዚህ ወር ለሁለተኛ ጊዜ ሊወያዩ ነው። መሪዎቹ ሐሙስ ዕለት በስልክ ይነጋገራሉ ተብሏል። እንደዋይት ሐውስ ባለሥልጣን ከሆነ ፕሬዝዳንቶቹ በአገሮቹ መካከል በቀጣይ ስለሚደረጉ የፀጥታ ውይይቶች እና በአውሮፓ ባለው ሁኔታ ላይ ይወያያሉ። ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ጦር ያሰፈረችው ሩሲያ አገሪቱን ለመውረር አላቀድኩም ስትል አስተባብላለች። ሩሲያ ወታደሮቿ በቦታው ለልምምድ መገኘታቸውን ጠቅሳ ጦሯን በአገሯ በነጻነት የማንቀሳቀስ መብት እንዳላት ተናግራለች። ለጉዳዩ የጋራ ምላሽን ለመስጠት ከሐሙሱ ውይይት በፊት አሜሪካ፣ የአውሮፓ መሪዎችን አማክራለች ሲል የዋይት ሐውስ መግለጫ አስታውቋል። የዩክሬን የደኅንነት ባለሥልጣናት ከ100 ሺህ የሚበልጡ የሩሲያ ወታደሮች ወደሚጋሩት ድንበር መላካቸውን ገልጸዋል። ዩክሬን ጥቃት ከደረሰባት ፑቲንን "አይተውት የማያውቁት" ማዕቀብ እንደሚጠብቃቸው አሜሪካ ዝታለች። አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደገለጹት ባይደን ለሩሲያ አቻው "ዲፕሎማሲያዊ መንገድ" የሚያቀርቡ ቢሆንም በድንበር ላይ ያለው የሩሲያ ጦር መጠናከር "በጣም ያሳስባቸዋል" ብለዋል። ሩሲያ "ዩክሬን ላይ ተጨማሪ ወረራ" ከፈጸመች አሜሪካ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ባይደን ለፑቲንን ይነግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪን ጋር ረቡዕ ዕለት ተነጋግረዋል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዳሉት ብሊንከን "ሩሲያ በዩክሬን ድንበሮች ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ዩናይትድ ስቴትስ በመቃወም ለዩክሬን ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ በድጋሚ ገልጸዋል።" በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በስልክ ባደረጉት ውይይት ባይደን ለዩክሬን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ባትሆንም ከሕብረቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት። ሩሲያ በበኩሏ ኔቶ ወደ ምሥራቅ እንደማይንቀሳቀስ እና የጦር መሳሪያ ዩክሬንን ጨምሮ ወደ የትኛውም የጎረቤት አገር እንደማይላክ በሕጋዊ መንገድ ዋስትና እንደምትፈልግ ተናግራለች። የኔቶ ዋና ፀሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ በበኩላቸው የዩክሬን የሕብረቱ አባልነት የኔቶ እና የኪየቭ ጉዳይ ነው ሲሉ አበክረው ገልጸዋል። "ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ማንኛውም ውይይት የአውሮፓ ደኅንነት የተመሰረተባቸውን ዋና መርሆች በማክበር መሆን አለበት" ሲሉ ቀደም ብለው ተናግረዋል። የሊቱዌኒያው ፕሬዝዳንት ጊታናስ ናውሴዳ ደግሞ አሁን ያለውን ሁኔታ ምናልባትም "በ30 ዓመታት ውስጥ ከታዩት እጅግ አደገኛው" ሲሉ ገልጸውታል። የሩሲያ ባለሥልጣናት በአውሮፓውያኑ ጥር 10 ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር በጄኔቫ ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘዋል። በዕለቱ ከፑቲን ጋር ይገናኙ እንደሆነ የተጠየቁት ባይደን "እስቲ እናያለን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ሆኖም በጄኔቫ በሚደረገው ድርድር ላይ ይገኛሉ ተብሎ አይጠበቅም። | ባይደን እና ፑቲን በዩክሬን ጉዳይ 'ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ' ፍለጋ ሊወያዩ ነው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዚህ ወር ለሁለተኛ ጊዜ ሊወያዩ ነው። መሪዎቹ ሐሙስ ዕለት በስልክ ይነጋገራሉ ተብሏል። እንደዋይት ሐውስ ባለሥልጣን ከሆነ ፕሬዝዳንቶቹ በአገሮቹ መካከል በቀጣይ ስለሚደረጉ የፀጥታ ውይይቶች እና በአውሮፓ ባለው ሁኔታ ላይ ይወያያሉ። ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ጦር ያሰፈረችው ሩሲያ አገሪቱን ለመውረር አላቀድኩም ስትል አስተባብላለች። ሩሲያ ወታደሮቿ በቦታው ለልምምድ መገኘታቸውን ጠቅሳ ጦሯን በአገሯ በነጻነት የማንቀሳቀስ መብት እንዳላት ተናግራለች። ለጉዳዩ የጋራ ምላሽን ለመስጠት ከሐሙሱ ውይይት በፊት አሜሪካ፣ የአውሮፓ መሪዎችን አማክራለች ሲል የዋይት ሐውስ መግለጫ አስታውቋል። የዩክሬን የደኅንነት ባለሥልጣናት ከ100 ሺህ የሚበልጡ የሩሲያ ወታደሮች ወደሚጋሩት ድንበር መላካቸውን ገልጸዋል። ዩክሬን ጥቃት ከደረሰባት ፑቲንን "አይተውት የማያውቁት" ማዕቀብ እንደሚጠብቃቸው አሜሪካ ዝታለች። አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደገለጹት ባይደን ለሩሲያ አቻው "ዲፕሎማሲያዊ መንገድ" የሚያቀርቡ ቢሆንም በድንበር ላይ ያለው የሩሲያ ጦር መጠናከር "በጣም ያሳስባቸዋል" ብለዋል። ሩሲያ "ዩክሬን ላይ ተጨማሪ ወረራ" ከፈጸመች አሜሪካ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ባይደን ለፑቲንን ይነግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪን ጋር ረቡዕ ዕለት ተነጋግረዋል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዳሉት ብሊንከን "ሩሲያ በዩክሬን ድንበሮች ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ዩናይትድ ስቴትስ በመቃወም ለዩክሬን ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ በድጋሚ ገልጸዋል።" በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በስልክ ባደረጉት ውይይት ባይደን ለዩክሬን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ባትሆንም ከሕብረቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት። ሩሲያ በበኩሏ ኔቶ ወደ ምሥራቅ እንደማይንቀሳቀስ እና የጦር መሳሪያ ዩክሬንን ጨምሮ ወደ የትኛውም የጎረቤት አገር እንደማይላክ በሕጋዊ መንገድ ዋስትና እንደምትፈልግ ተናግራለች። የኔቶ ዋና ፀሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ በበኩላቸው የዩክሬን የሕብረቱ አባልነት የኔቶ እና የኪየቭ ጉዳይ ነው ሲሉ አበክረው ገልጸዋል። "ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ማንኛውም ውይይት የአውሮፓ ደኅንነት የተመሰረተባቸውን ዋና መርሆች በማክበር መሆን አለበት" ሲሉ ቀደም ብለው ተናግረዋል። የሊቱዌኒያው ፕሬዝዳንት ጊታናስ ናውሴዳ ደግሞ አሁን ያለውን ሁኔታ ምናልባትም "በ30 ዓመታት ውስጥ ከታዩት እጅግ አደገኛው" ሲሉ ገልጸውታል። የሩሲያ ባለሥልጣናት በአውሮፓውያኑ ጥር 10 ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር በጄኔቫ ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘዋል። በዕለቱ ከፑቲን ጋር ይገናኙ እንደሆነ የተጠየቁት ባይደን "እስቲ እናያለን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ሆኖም በጄኔቫ በሚደረገው ድርድር ላይ ይገኛሉ ተብሎ አይጠበቅም። | https://www.bbc.com/amharic/news-59825257 |
0business
| በሩሲያዊው አሌክሴ መታሰር ምክንያት የ11 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ሊቋረጥ ይችላል ተባለ | ሩሲያና አውሮፓን የሚያስተሳስረው ንግድ በዋዛ የሚታይ አይደለም። አውሮፓ 40 ከመቶ ጋዝ የምታገኘው ከሩሲያ ነው። አሁን ደግሞ እጅግ ግዙፉ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ከሩሲያዋ ኪንጊሴፐን እስከ ግራስዋልድ ጀርመን ድረስ የሚዘረጋ ነው። ይህ ፕሮጀክት በርካታ አገራትን የሚያቋርጥና በባልቲክ ባህር ስምጥ ተቀብሮ የሚያልፍ ውስብስብ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ጀርመንን የሩሲያ የኢኮኖሚ እስረኛ ሊያደርጋት ይችላል የሚለው ስጋት ገና ከፕሮጀክቱ መጠንሰስ ጀምሮ ሲነገር የነበረ ነው። አሁን ደግሞ ጀርመንና ሩሲያ በአሌክሴ ናቫልንሊ ጉዳይ እየተነታረኩ ነው የሚገኙት። በርካታ አገራት ጀርመን በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንደትጥል እየገፏፏት ይገኛሉ። በተለይም ከሩሲያ እስከ ጀርመን እየተዘረጋ ያለውን ዘመናዊ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ሥራ እንዲቋረጥ እንድታደርግ ነው በዋናነት ግፊቱ እየበረታ ያለው። "ኖርድ ስትሪም 2" የሚል ስም የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት በአውሮፓ እጅግ ግዙፍ ከሆኑት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው። በአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባላት፣ አባል አገራት በሩሲያ ላይ ማናቸውን ዓይነት ማዕቀብ በመጣል ጫና እንዲፈጥሩ ጥሪ አድርገዋል። አሌክሴ ናቫልኒ በሩሲያ ከተመረዘ በኋላ በጀርመን ሕክምና አድርጎ ወደ አገሩ ሲመለስ በፕሬዚዳንት ፑቲን ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ እስር ቤት መወሰዱ አይዘነጋም። አሜሪካ በዚህ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ፕሮጀክት ላይ ቀደም ብላ ማዕቀብ ጥላለች። ማዕቀቡ የተጣለው ቧንቧዎቹን እየቀበረ ባለው የሩሲያ ግዙፍ መርከብ ላይ ነው። አሜሪካ በተደጋጋሚ እንደምትለው ይህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ሩሲያ በአውሮፓ ላይ የሚኖራትን ተጽእኖ ፈጣሪነት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። የአሜሪካ ግምጃ ቤት ማዕቀብ የጣለባት የሩሲያ መርከብ ፎርቹና የምትባለዋ ስትሆን ይህ ማዕቀብ የተጣለው ትራምፕ ሥልጣን ሊለቁ በነበሩባቸው የመጨረሻ ቀናት ነው። ሆኖም ይህን ማዕቀብ ጆ ባይደንም የሚደግፉት እንጂ የሚቀለብሱት አይሆንም ተብሏል። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ስምምነት ለአውሮፓ መጥፎ ስምምነት ነው ሲሉም ነበር። በቅርቡ ሥልጣን የሚለቁት የጀመርኗ መራሂት መንግሥት አንጌላ መርከል በማዕቀቡ ጉዳይ ተጠይቀው ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ፕሮጀክቱ ሩሲያ ለጀርመን የምትልከውን የጋዝ መጠን በእጥፍ እንደሚጨምር እጅግ ቁልፍ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው ሆኖም መንግሥታቸው ጉዳዩን ከባይደን አስተዳደር ጋር እንደሚመክርበት ተናግረዋል። ይህን የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ 2ሺህ 460 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 94 ከመቶ ተጠናቋል። ሥራው በ2019 መጨረሻ ላይ ለአንድ ዓመት የቆመው በአሜሪካ ማዕቀብ የተነሳ ነበር። ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ ዋናው የቧንቧዎቹን መቅበር ሥራ የሚሰራው ኩባንያ ሥራውን ለማቆም ተገዶ ነበር። ባለፈው ወር ግን ፎርቹና መርከብ በጀርመን የውሀ አካል ሥር የመቅበሩን ሥራ ጨርሳ በዴንማርክ ውስጥ ሥራውን ለመቀጠል በዝጅግጀት ላየዕ ነበረች። ሆኖም ማዕቀቡ ሥራውን እንዲቆም አስደርጓታል። አሁን ፎርቹና መርከብ በባልቲክ ባህር ላይ ነው የምትገኘው። የ44 ዓመቱ የፑቲን ተቺ አሌክሴ ናቫልኒ ኖቪቾክ በሚባል የነርቭ መርዝ ከተመረዘ በኋላ ሕይወቱ በተአምር የተረፈችው የጀርመን ሐኪሞች ባደረጉለት ርብርብ ነው። ሆኖም ማገገሙን ተከትሎ ወደ እናት አገሩ ሩሲያ በድፍረት ለመመለስ መወሰኑ ብዙዎችን አስደንቋል። በርካታ ጋዜጠኞች እሱ በተሳፈረባት አውሮፕላን አብረውት ወደ ሩሲያ የተጓዙ ሲሆን እንደተፈራውም ከበርሊን ሩሲያ እንደገባ በቁጥጥር ሥር ውሏል። የሱን መታሰር ተከትሎ በርካታ አገራት ቁጣቸውን በሩሲያ ላይ ሰንዝረዋል። የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ የአሌክሴ መታሰር በጀርመንና በሩሲያ መካከል ችግር የሚፈጥር ነው ካሉ በኋላ በዚህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት ላይም የራሱ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁመው ነበር። በዚህ ሳምንት ሃይኮ ማስ ወደ ዋሺንግተን ተጉዘው አቻቸውን አንቶኒ ብሊንከንን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። | በሩሲያዊው አሌክሴ መታሰር ምክንያት የ11 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ሊቋረጥ ይችላል ተባለ ሩሲያና አውሮፓን የሚያስተሳስረው ንግድ በዋዛ የሚታይ አይደለም። አውሮፓ 40 ከመቶ ጋዝ የምታገኘው ከሩሲያ ነው። አሁን ደግሞ እጅግ ግዙፉ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ከሩሲያዋ ኪንጊሴፐን እስከ ግራስዋልድ ጀርመን ድረስ የሚዘረጋ ነው። ይህ ፕሮጀክት በርካታ አገራትን የሚያቋርጥና በባልቲክ ባህር ስምጥ ተቀብሮ የሚያልፍ ውስብስብ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ጀርመንን የሩሲያ የኢኮኖሚ እስረኛ ሊያደርጋት ይችላል የሚለው ስጋት ገና ከፕሮጀክቱ መጠንሰስ ጀምሮ ሲነገር የነበረ ነው። አሁን ደግሞ ጀርመንና ሩሲያ በአሌክሴ ናቫልንሊ ጉዳይ እየተነታረኩ ነው የሚገኙት። በርካታ አገራት ጀርመን በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንደትጥል እየገፏፏት ይገኛሉ። በተለይም ከሩሲያ እስከ ጀርመን እየተዘረጋ ያለውን ዘመናዊ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ሥራ እንዲቋረጥ እንድታደርግ ነው በዋናነት ግፊቱ እየበረታ ያለው። "ኖርድ ስትሪም 2" የሚል ስም የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት በአውሮፓ እጅግ ግዙፍ ከሆኑት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው። በአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባላት፣ አባል አገራት በሩሲያ ላይ ማናቸውን ዓይነት ማዕቀብ በመጣል ጫና እንዲፈጥሩ ጥሪ አድርገዋል። አሌክሴ ናቫልኒ በሩሲያ ከተመረዘ በኋላ በጀርመን ሕክምና አድርጎ ወደ አገሩ ሲመለስ በፕሬዚዳንት ፑቲን ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ እስር ቤት መወሰዱ አይዘነጋም። አሜሪካ በዚህ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ፕሮጀክት ላይ ቀደም ብላ ማዕቀብ ጥላለች። ማዕቀቡ የተጣለው ቧንቧዎቹን እየቀበረ ባለው የሩሲያ ግዙፍ መርከብ ላይ ነው። አሜሪካ በተደጋጋሚ እንደምትለው ይህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ሩሲያ በአውሮፓ ላይ የሚኖራትን ተጽእኖ ፈጣሪነት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። የአሜሪካ ግምጃ ቤት ማዕቀብ የጣለባት የሩሲያ መርከብ ፎርቹና የምትባለዋ ስትሆን ይህ ማዕቀብ የተጣለው ትራምፕ ሥልጣን ሊለቁ በነበሩባቸው የመጨረሻ ቀናት ነው። ሆኖም ይህን ማዕቀብ ጆ ባይደንም የሚደግፉት እንጂ የሚቀለብሱት አይሆንም ተብሏል። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ስምምነት ለአውሮፓ መጥፎ ስምምነት ነው ሲሉም ነበር። በቅርቡ ሥልጣን የሚለቁት የጀመርኗ መራሂት መንግሥት አንጌላ መርከል በማዕቀቡ ጉዳይ ተጠይቀው ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ፕሮጀክቱ ሩሲያ ለጀርመን የምትልከውን የጋዝ መጠን በእጥፍ እንደሚጨምር እጅግ ቁልፍ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው ሆኖም መንግሥታቸው ጉዳዩን ከባይደን አስተዳደር ጋር እንደሚመክርበት ተናግረዋል። ይህን የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ 2ሺህ 460 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 94 ከመቶ ተጠናቋል። ሥራው በ2019 መጨረሻ ላይ ለአንድ ዓመት የቆመው በአሜሪካ ማዕቀብ የተነሳ ነበር። ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ ዋናው የቧንቧዎቹን መቅበር ሥራ የሚሰራው ኩባንያ ሥራውን ለማቆም ተገዶ ነበር። ባለፈው ወር ግን ፎርቹና መርከብ በጀርመን የውሀ አካል ሥር የመቅበሩን ሥራ ጨርሳ በዴንማርክ ውስጥ ሥራውን ለመቀጠል በዝጅግጀት ላየዕ ነበረች። ሆኖም ማዕቀቡ ሥራውን እንዲቆም አስደርጓታል። አሁን ፎርቹና መርከብ በባልቲክ ባህር ላይ ነው የምትገኘው። የ44 ዓመቱ የፑቲን ተቺ አሌክሴ ናቫልኒ ኖቪቾክ በሚባል የነርቭ መርዝ ከተመረዘ በኋላ ሕይወቱ በተአምር የተረፈችው የጀርመን ሐኪሞች ባደረጉለት ርብርብ ነው። ሆኖም ማገገሙን ተከትሎ ወደ እናት አገሩ ሩሲያ በድፍረት ለመመለስ መወሰኑ ብዙዎችን አስደንቋል። በርካታ ጋዜጠኞች እሱ በተሳፈረባት አውሮፕላን አብረውት ወደ ሩሲያ የተጓዙ ሲሆን እንደተፈራውም ከበርሊን ሩሲያ እንደገባ በቁጥጥር ሥር ውሏል። የሱን መታሰር ተከትሎ በርካታ አገራት ቁጣቸውን በሩሲያ ላይ ሰንዝረዋል። የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ የአሌክሴ መታሰር በጀርመንና በሩሲያ መካከል ችግር የሚፈጥር ነው ካሉ በኋላ በዚህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት ላይም የራሱ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁመው ነበር። በዚህ ሳምንት ሃይኮ ማስ ወደ ዋሺንግተን ተጉዘው አቻቸውን አንቶኒ ብሊንከንን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55761773 |
3politics
| በሊባኖስ ጉዳት ባደረሰው ፍንዳታ የተቆጡ ተቃዋሚዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ጥቃት ፈጸሙ | ሊባኖስ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ፈንድቶ ሞትና ጉዳት ካደረሰ በኋላ ተቃዋሚዎች በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤት ላይ ጥቃት ፈጸሙ። እሁድ ዕለት በደረሰው ነዳጅ ፍንዳታ 27 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 79 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ይህንን ተከትሎም በርካታ ተቃዋሚዎች ናጂብ ሚካቲ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠይቀዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤትም ላይ ድንጋይ በመወርወር ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። ሚካቲ የተቃዋሚዎቹን ሐዘን እንደተረዱ የገለጹ ሲሆን "ተቀባይነት የሌለው ጥፋት" ያሉትን የተቃዋሚዎቹን ድርጊት አውግዘዋል። የአገሪቱ ሠራዊት እንዳስታወቀው የነዳጅ ማጠራቀሚያው ፍንዳታ ያጋጠመው በአካር ክልል ወታደሮች ከጥቁር ገበያ ነጋዴዎች የያዙትን ነዳጅ ሲያስተላልፉ ነበር። የፍንዳታው መንስኤ እስካሁን ግልጽ አይደለም፤ ነገር ግን በወቅቱ በነዳጅ ማጠራቀሚያው አካባቢ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው እንደነበር ጦሩ አስታውቋል። "ጦሩ ቤንዚኑን እያከፋፈለ እንደሆነ ሰማን፤ ሰዎችም ነዳጁን በጀሪካን ለመቅዳት ሲጎርፉ ነበር" ስትል እስማኤል የተባለ ወንድሟ በአደጋው ክፉኛ የተጎዳባት ማረዋ አል ሼይክ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግራለች። ማርዋ አክላም ፍንዳታው የተከሰተው አንድ ሰው ላይተር ሲጠቀም እንደሆነ ከዓይን ምስክሮች መስማቷን ገልጻ፤ "ሌሎች ደግሞ 'በአካባቢው ተኩስ ነበር' ብለዋል" ብላለች። "ሟቾቹ የዚህ ግድየለሽ መንግሥት ሰለባዎች ናቸው" ብላለች ማርዋ። ከአንድ ዓመት በፊት በቤይሩት የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ አስተዳደራቸው ሥልጣን የለቀውና በፖለቲካ አለመግባባት ምክንያት በሌላ ያልተተኩት፤ ነገር ግን አገሪቷን በባለአደራነት የሚያስተዳድሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ዲያብ "ፍንዳታው አሳዛኝ አደጋ ነው" በማለት ሰኞ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ እንዲውል አውጀዋል። ጦሩ በበኩሉ የአደጋውን መንስዔ እያጣራሁ ነው ብሏል። በአል ቴሊል የነዳጅ ማጠራቀሚያው የነበረበትን ቦታ ባለቤትም በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጦሩ አክሏል። የአካባቢው ነዋሪዎችም የግለሰቡ ቤት በእሳት እንዳቃጠሉት ተገልጿል። በሊባኖስ የነዳጅ እጥረት ያለ ሲሆን፤ በዓለም በከባድ የምጣኔ ሐብት ቀውስ እየተፈተኑ ካሉ አገራት አንዷ ናት። የአገሪቷ ገንዘብ የመግዛት አቅም ባለፉት ሁለት ዓመታት ወድቋል። ይህም በአገሪቷ ያለውን ግሽበት ከነበረበት የበለጠ አባብሶታል። ባለፈው ሳምንት የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በማጋጠሙ የነዳጅ ድጎማዎችን ለማቆም ወስኗል። መንግሥት በበኩሉ የነዳጅ ዋጋ መለወጥ የለበትም ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል። የፀጥታ አካላትም በነዳጅ ማደያዎችና በግለሰብ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች የተከማቸ ነው ያሉትን ነዳጅ ቅዳሜ እለት ማከፋፈል ጀምረዋል። አብዛኞቹ ሊባኖሳውያን በግል ጀኔሬተር (ኃይል ማመንጫ) ላይ ጥገኛ በመሆናቸው የነዳጅ እጥረቱ በርካታ ሰዎችና ተቋማት በቀን ለሁለት ሰዓታት ያህል ብቻ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። እሁድ ዕለት ባጋጠመው ፍንዳታ የተጎዱ ሰዎችን የሚያክሙ አንዳንድ ሆስፒታሎችም መደበኛ የነዳጅ አቅርቦት ከሌለ ለመዝጋት ሊገደዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። | በሊባኖስ ጉዳት ባደረሰው ፍንዳታ የተቆጡ ተቃዋሚዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ጥቃት ፈጸሙ ሊባኖስ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ፈንድቶ ሞትና ጉዳት ካደረሰ በኋላ ተቃዋሚዎች በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤት ላይ ጥቃት ፈጸሙ። እሁድ ዕለት በደረሰው ነዳጅ ፍንዳታ 27 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 79 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ይህንን ተከትሎም በርካታ ተቃዋሚዎች ናጂብ ሚካቲ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠይቀዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤትም ላይ ድንጋይ በመወርወር ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። ሚካቲ የተቃዋሚዎቹን ሐዘን እንደተረዱ የገለጹ ሲሆን "ተቀባይነት የሌለው ጥፋት" ያሉትን የተቃዋሚዎቹን ድርጊት አውግዘዋል። የአገሪቱ ሠራዊት እንዳስታወቀው የነዳጅ ማጠራቀሚያው ፍንዳታ ያጋጠመው በአካር ክልል ወታደሮች ከጥቁር ገበያ ነጋዴዎች የያዙትን ነዳጅ ሲያስተላልፉ ነበር። የፍንዳታው መንስኤ እስካሁን ግልጽ አይደለም፤ ነገር ግን በወቅቱ በነዳጅ ማጠራቀሚያው አካባቢ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው እንደነበር ጦሩ አስታውቋል። "ጦሩ ቤንዚኑን እያከፋፈለ እንደሆነ ሰማን፤ ሰዎችም ነዳጁን በጀሪካን ለመቅዳት ሲጎርፉ ነበር" ስትል እስማኤል የተባለ ወንድሟ በአደጋው ክፉኛ የተጎዳባት ማረዋ አል ሼይክ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግራለች። ማርዋ አክላም ፍንዳታው የተከሰተው አንድ ሰው ላይተር ሲጠቀም እንደሆነ ከዓይን ምስክሮች መስማቷን ገልጻ፤ "ሌሎች ደግሞ 'በአካባቢው ተኩስ ነበር' ብለዋል" ብላለች። "ሟቾቹ የዚህ ግድየለሽ መንግሥት ሰለባዎች ናቸው" ብላለች ማርዋ። ከአንድ ዓመት በፊት በቤይሩት የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ አስተዳደራቸው ሥልጣን የለቀውና በፖለቲካ አለመግባባት ምክንያት በሌላ ያልተተኩት፤ ነገር ግን አገሪቷን በባለአደራነት የሚያስተዳድሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ዲያብ "ፍንዳታው አሳዛኝ አደጋ ነው" በማለት ሰኞ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ እንዲውል አውጀዋል። ጦሩ በበኩሉ የአደጋውን መንስዔ እያጣራሁ ነው ብሏል። በአል ቴሊል የነዳጅ ማጠራቀሚያው የነበረበትን ቦታ ባለቤትም በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጦሩ አክሏል። የአካባቢው ነዋሪዎችም የግለሰቡ ቤት በእሳት እንዳቃጠሉት ተገልጿል። በሊባኖስ የነዳጅ እጥረት ያለ ሲሆን፤ በዓለም በከባድ የምጣኔ ሐብት ቀውስ እየተፈተኑ ካሉ አገራት አንዷ ናት። የአገሪቷ ገንዘብ የመግዛት አቅም ባለፉት ሁለት ዓመታት ወድቋል። ይህም በአገሪቷ ያለውን ግሽበት ከነበረበት የበለጠ አባብሶታል። ባለፈው ሳምንት የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በማጋጠሙ የነዳጅ ድጎማዎችን ለማቆም ወስኗል። መንግሥት በበኩሉ የነዳጅ ዋጋ መለወጥ የለበትም ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል። የፀጥታ አካላትም በነዳጅ ማደያዎችና በግለሰብ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች የተከማቸ ነው ያሉትን ነዳጅ ቅዳሜ እለት ማከፋፈል ጀምረዋል። አብዛኞቹ ሊባኖሳውያን በግል ጀኔሬተር (ኃይል ማመንጫ) ላይ ጥገኛ በመሆናቸው የነዳጅ እጥረቱ በርካታ ሰዎችና ተቋማት በቀን ለሁለት ሰዓታት ያህል ብቻ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። እሁድ ዕለት ባጋጠመው ፍንዳታ የተጎዱ ሰዎችን የሚያክሙ አንዳንድ ሆስፒታሎችም መደበኛ የነዳጅ አቅርቦት ከሌለ ለመዝጋት ሊገደዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58223897 |
0business
| ሮበርት ሙጋቤ በባንካቸው ውስጥ ያልተናዘዙት አስር ሚሊዮን ዶላር ተገኘ | የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስር ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችም በመዲናዋ ሐራሬ ትተው ማለፋቸውን የሃገሪቱ የመንግሥት ጋዜጣ 'ሔራልድ' ዘግቧል። ባለፈው ዓመት መስከረም በዘጠና አምስት ዓመታቸው ያረፉት ሙጋቤ ለገንዘቡም ሆነ ለቀሪው ንብረታቸው ወራሽ ማን እንደሆነ ኑዛዜ ባለማስቀመጣቸው የመንግሥት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ሆኗል። ይህንን ጉዳይ ለመወሰን ስብሰባ ተቀምጠው ነበር። •ሮበርት ሙጋቤ የሞቱት "በካንሰር" ነው ተባለ •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ልጅ ቦና ቺኮዎሬ በጥቅምት ወር ላይ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በፃፈችው ደብዳቤ አስር ሚሊዮን ዶላር በሃገሪቱ ባንክ፣ በሌሎች ገጠራማ ቦታዎች ካሏቸው ቤቶች በተጨማሪ ደግሞ አራት ቤቶች በሐራሬ እንዳላቸውም መጥቀሷን ሔራልድ ልጃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። አስር መኪኖችም እንዳላቸው ጋዜጣው ጨምሮ አትቷል። •ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው ዚምባብዌ ነፃ ከወጣችበት ጀምሮ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሃገሪቱን የመሩት ሙጋቤ ከስልጣን የተነሱት ከሁለት ዓመታት በፊት ነው። ሙጋቤ አራት ልጆችም ትተው ነው ይህችን ዓለም የተሰናበቱት። በዚምባብዌ ህግ መሰረት ባለቤታቸው እንዲሁም ልጆቻቸው ሃብታቸውን የሚወርሱ ይሆናል። | ሮበርት ሙጋቤ በባንካቸው ውስጥ ያልተናዘዙት አስር ሚሊዮን ዶላር ተገኘ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስር ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችም በመዲናዋ ሐራሬ ትተው ማለፋቸውን የሃገሪቱ የመንግሥት ጋዜጣ 'ሔራልድ' ዘግቧል። ባለፈው ዓመት መስከረም በዘጠና አምስት ዓመታቸው ያረፉት ሙጋቤ ለገንዘቡም ሆነ ለቀሪው ንብረታቸው ወራሽ ማን እንደሆነ ኑዛዜ ባለማስቀመጣቸው የመንግሥት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ሆኗል። ይህንን ጉዳይ ለመወሰን ስብሰባ ተቀምጠው ነበር። •ሮበርት ሙጋቤ የሞቱት "በካንሰር" ነው ተባለ •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ልጅ ቦና ቺኮዎሬ በጥቅምት ወር ላይ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በፃፈችው ደብዳቤ አስር ሚሊዮን ዶላር በሃገሪቱ ባንክ፣ በሌሎች ገጠራማ ቦታዎች ካሏቸው ቤቶች በተጨማሪ ደግሞ አራት ቤቶች በሐራሬ እንዳላቸውም መጥቀሷን ሔራልድ ልጃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። አስር መኪኖችም እንዳላቸው ጋዜጣው ጨምሮ አትቷል። •ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው ዚምባብዌ ነፃ ከወጣችበት ጀምሮ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሃገሪቱን የመሩት ሙጋቤ ከስልጣን የተነሱት ከሁለት ዓመታት በፊት ነው። ሙጋቤ አራት ልጆችም ትተው ነው ይህችን ዓለም የተሰናበቱት። በዚምባብዌ ህግ መሰረት ባለቤታቸው እንዲሁም ልጆቻቸው ሃብታቸውን የሚወርሱ ይሆናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-50640487 |
3politics
| ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ ደካማ ነው አሉ | የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ወጪ ንግድ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ “ደካማ” ነው ሲሉ ተቹ። አርብ ዕለት የጸደቀው የዋጋ ገደብ የሩሲያን ድፍድፍ ነዳጅ የሚገዙ አገራት በበርሜል ከ60 ዶላር በላይ እንዳይከፍሉ ለማድረግ ያለመ ነው። ሩሲያ በነዳጅ ምርቶች ወጪ ንግድ ላይ የተጣለውን የዋጋ ገደብ እንደማትቀበል አሳውቃለች። በመጪው ሰኞ ተግባራዊ የሚሆነው የዋጋ ጣሪያ ምዕራባውያን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ ጋር ተያይዞ እያደረጉት ያለው ጫና አካል ነው። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ የዋጋ ጣሪያውን የምዕራባውያንን ደካማ አቋም ያንጸባረቀ ነው ሲሉ ተችተዋል። የሩሲያ ምጣኔ ኃብትም ላይ የረባ የሚባል ጫናም አያሳርፍም፤ ጉዳትም አያደርስም ብለዋል። “ሩሲያ ሆን ብላ የዓለምን የገበያ ስርዓት በማወክ በሁሉም የአለም ሃገራት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሳለች” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። “በአሁኑ ወቅት ጠንከርና ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች ጥቅም ላይ የሚውሉበት ነው” ሲሉም አክለዋል። የዋጋ ጣሪያው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት የገንዘብ አቅም ለማዳከም አልሟል። ይህንንም ፕሮፖዛል ያቀረቡት በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የቡድን ሰባት አገራት (አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን እና የአውሮፓ ህብረት) ናቸው። የቡድን ሰባት አገራት ባወጡት የጋራ መግለጫ የአውሮፓ ህብረት እና አውስትራሊያ እርምጃው የተወሰደው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከምታካሂደው ወራራ ትርፍ እንዳታገኝ ለማድረግ ነው ማለታቸው ሰፍሯል። ቅዳሜ ዕለት የክሬምሊን ቃለ አባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ለዚህ እርምጃ ዝግጁ መሆናቸውን ቢያሳውቁም አገራቸው የዋጋ ጣሪያውን አትቀበለውም ብለዋል ። የሩሲያ ነዳጅ ላይ የሚደረገው የምዕራባውያኑ ጫና ሞስኮ ላይ ተጽእኖ ቢኖረውም፣ በአሁኑ ወቅት የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ ቀዳሚ ገዢዎች በሆኑት እንደ ሕንድ እና ቻይና ባሉ ገበያዎች ይካካሳል ተብሏል። የዋጋ ጣሪያው ስምምነት ተግባራዊ የሚሆነው የአውሮፓ ህብረት በባህር በሚገባው የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ ላይ የተጣለው እገዳ ተፈጻሚ በሚሆንበት በተመሳሳይ ዕለት ነው። አዲሱ የዋጋ ጣሪያ እርምጃ በዓለም ዙሪያ ያለውን የነዳጅ ወጪ ንግድ ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ነው። በቡድን 7 አማካኝነት የቀረበውን የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ውሳኔን የፈረሙ አገራት በባሕር በኩል የሚያስገቡትን ነዳጅ መግዛት የሚችሉት በስምምነቱ በተቀመጠው ወይም ከዚያ በታች በሆነ ዋጋ ነው። የዩክሬን ምዕራባውያን አጋሮች በዋጋ ጣሪያው ስምምነት ላይ ያልፈረሙ አገራት የሩሲያን ነዳጅ ለሚያደርሱላቸው ተሽከርካሪዎች የሚሰጠውን መድህን እንደሚከለክሉ ገልጸዋል። ይህም ሩሲያ ነዳጇን ከተቀመጠው ዋጋ በላይ እንዳትሸጥ የሚያደርግ ነው። | ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ ደካማ ነው አሉ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ወጪ ንግድ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ “ደካማ” ነው ሲሉ ተቹ። አርብ ዕለት የጸደቀው የዋጋ ገደብ የሩሲያን ድፍድፍ ነዳጅ የሚገዙ አገራት በበርሜል ከ60 ዶላር በላይ እንዳይከፍሉ ለማድረግ ያለመ ነው። ሩሲያ በነዳጅ ምርቶች ወጪ ንግድ ላይ የተጣለውን የዋጋ ገደብ እንደማትቀበል አሳውቃለች። በመጪው ሰኞ ተግባራዊ የሚሆነው የዋጋ ጣሪያ ምዕራባውያን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ ጋር ተያይዞ እያደረጉት ያለው ጫና አካል ነው። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ የዋጋ ጣሪያውን የምዕራባውያንን ደካማ አቋም ያንጸባረቀ ነው ሲሉ ተችተዋል። የሩሲያ ምጣኔ ኃብትም ላይ የረባ የሚባል ጫናም አያሳርፍም፤ ጉዳትም አያደርስም ብለዋል። “ሩሲያ ሆን ብላ የዓለምን የገበያ ስርዓት በማወክ በሁሉም የአለም ሃገራት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሳለች” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። “በአሁኑ ወቅት ጠንከርና ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች ጥቅም ላይ የሚውሉበት ነው” ሲሉም አክለዋል። የዋጋ ጣሪያው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት የገንዘብ አቅም ለማዳከም አልሟል። ይህንንም ፕሮፖዛል ያቀረቡት በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የቡድን ሰባት አገራት (አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን እና የአውሮፓ ህብረት) ናቸው። የቡድን ሰባት አገራት ባወጡት የጋራ መግለጫ የአውሮፓ ህብረት እና አውስትራሊያ እርምጃው የተወሰደው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከምታካሂደው ወራራ ትርፍ እንዳታገኝ ለማድረግ ነው ማለታቸው ሰፍሯል። ቅዳሜ ዕለት የክሬምሊን ቃለ አባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ለዚህ እርምጃ ዝግጁ መሆናቸውን ቢያሳውቁም አገራቸው የዋጋ ጣሪያውን አትቀበለውም ብለዋል ። የሩሲያ ነዳጅ ላይ የሚደረገው የምዕራባውያኑ ጫና ሞስኮ ላይ ተጽእኖ ቢኖረውም፣ በአሁኑ ወቅት የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ ቀዳሚ ገዢዎች በሆኑት እንደ ሕንድ እና ቻይና ባሉ ገበያዎች ይካካሳል ተብሏል። የዋጋ ጣሪያው ስምምነት ተግባራዊ የሚሆነው የአውሮፓ ህብረት በባህር በሚገባው የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ ላይ የተጣለው እገዳ ተፈጻሚ በሚሆንበት በተመሳሳይ ዕለት ነው። አዲሱ የዋጋ ጣሪያ እርምጃ በዓለም ዙሪያ ያለውን የነዳጅ ወጪ ንግድ ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ነው። በቡድን 7 አማካኝነት የቀረበውን የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ውሳኔን የፈረሙ አገራት በባሕር በኩል የሚያስገቡትን ነዳጅ መግዛት የሚችሉት በስምምነቱ በተቀመጠው ወይም ከዚያ በታች በሆነ ዋጋ ነው። የዩክሬን ምዕራባውያን አጋሮች በዋጋ ጣሪያው ስምምነት ላይ ያልፈረሙ አገራት የሩሲያን ነዳጅ ለሚያደርሱላቸው ተሽከርካሪዎች የሚሰጠውን መድህን እንደሚከለክሉ ገልጸዋል። ይህም ሩሲያ ነዳጇን ከተቀመጠው ዋጋ በላይ እንዳትሸጥ የሚያደርግ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c1ve0drlrzvo |
0business
| የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው ተባለ | ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የፋይናንስ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው። ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የመክፈል አቅሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ነው። በገንዘብ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ለምሳሌ የቻይናው ኤክዚም ባንክ እሰጣለው ብሎ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህም ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ከመስጠት የታቀበው የብድር መጠን 339 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስቴር የቻይና ትብብር ዳይሬክተር ደምሱ ለማ ናቸው። ነገር ግን የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ በማቅማማት ላይ ያለ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም አይደለም። ሰኔ ወር ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር የታተመ አንድ ሰነድ እንዳመለከተው የውጭ አበዳሪዎች አስከ መጋቢት መጨረሻ ድረስ 11 ቢሊዮን ዶላር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) ለምሳሌ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ይለቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ይህን እስከአሁን ተግባራዊ አላደረገም። ሚኒስቴሩ በሰነዱ ከጠቀሳቸው ሌሎች አበዳሪ ተቋሟት አንዱ ግዙፉ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሲሆን ተቋሙ 2.7 ቢሊዮን ዶላር እስከ አሁን ለኢትዮጵያ አለቀቀም። ከውጭ አበዳሪዎች ትልቅ የምትባለው ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አልለቀቀችም። ከላይ ከተጠቀሱት አበዳሪዎች ሌላ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ሌሎች የንግድ ባንኮች ይገኙበታል። ይህ የውጭ አበዳሪዎች ተጨማሪ ብድር ለኢትዮጵያ ለመልቀቅ አለመፍቀዳቸው አገሪቱ ላይ እየተካሄዱ ያሉ መጠነ ሰፊ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ሊያስተጓጉል እንደሚችል ይገመታል። በውጭ ብድር ተጠቃሚ እየሆኑ ከቆዩት ፕሮጀክቶች መካከል እርሻ፣ ትራንስፖርት፣ ኮሚዩኒኬሽን፣ አውራ ጎዳናዎች እና የባቡር ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። እነዚህ በድምሩ 675 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኙ ፕሮጀክቶች ናቸው። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ ከሐምሌ 2020 እስከ መጋቢት 2021 ያለውን የሚያመላክት አሐዝ ነው። አሁን የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ገንዘብ ለማበደር ታቅበው ሁኔታውን ቆም ብለው እያጤኑት የሚገኙት አገሪቱ የብድር እፎይታን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንግግር የጀመረች በመሆኑ ነው። ባለፈው ሐምሌ ወር የአይኤምኤፍ ቃል አቀባይ ጌሪ ራይስ በኢትዮጵያ የብድር ጉዳይ ላይ አንድ ከሚቴ በፍጥነት እንዲቋቋም ጥሪ አድርገው ነበር። ይህም ከቡድን 20 እና ከፓሪስ ክለብ አበዳሪዎች ዘንድ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የብድር እፎይታ ጥያቄ እንዲመለከት ነበር። መንግሥት የብድር መመለሻ እፎይታ ለማግኘት ንግግር መጀመሩ ስህተት አይደለም ይላሉ ባለሙያዎች። በተለይም የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ ብዙ አገራት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል ብለዋል። በጉዳዩ ላይ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ እንደሚሉት "ኢትዮጵያ ኮቪድን አልፈጠረችውም፡፡ … ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ጊዜን መጠየቃቸው ምክንያታዊ አይደለም ማለት አልችልም" ሲሉ የኢትዮጵያን የብድር እፎይታ ጥያቄ አግባብነት ደግፈዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ የተበደረችው ዕዳ እስከ መጋቢት ወር ብቻ 29 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም የጥቅል አገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) 27 ከመቶ የያዘ ነው። | የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው ተባለ ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የፋይናንስ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው። ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የመክፈል አቅሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ነው። በገንዘብ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ለምሳሌ የቻይናው ኤክዚም ባንክ እሰጣለው ብሎ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህም ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ከመስጠት የታቀበው የብድር መጠን 339 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስቴር የቻይና ትብብር ዳይሬክተር ደምሱ ለማ ናቸው። ነገር ግን የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ በማቅማማት ላይ ያለ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም አይደለም። ሰኔ ወር ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር የታተመ አንድ ሰነድ እንዳመለከተው የውጭ አበዳሪዎች አስከ መጋቢት መጨረሻ ድረስ 11 ቢሊዮን ዶላር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) ለምሳሌ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ይለቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ይህን እስከአሁን ተግባራዊ አላደረገም። ሚኒስቴሩ በሰነዱ ከጠቀሳቸው ሌሎች አበዳሪ ተቋሟት አንዱ ግዙፉ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሲሆን ተቋሙ 2.7 ቢሊዮን ዶላር እስከ አሁን ለኢትዮጵያ አለቀቀም። ከውጭ አበዳሪዎች ትልቅ የምትባለው ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አልለቀቀችም። ከላይ ከተጠቀሱት አበዳሪዎች ሌላ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ሌሎች የንግድ ባንኮች ይገኙበታል። ይህ የውጭ አበዳሪዎች ተጨማሪ ብድር ለኢትዮጵያ ለመልቀቅ አለመፍቀዳቸው አገሪቱ ላይ እየተካሄዱ ያሉ መጠነ ሰፊ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ሊያስተጓጉል እንደሚችል ይገመታል። በውጭ ብድር ተጠቃሚ እየሆኑ ከቆዩት ፕሮጀክቶች መካከል እርሻ፣ ትራንስፖርት፣ ኮሚዩኒኬሽን፣ አውራ ጎዳናዎች እና የባቡር ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። እነዚህ በድምሩ 675 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኙ ፕሮጀክቶች ናቸው። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ ከሐምሌ 2020 እስከ መጋቢት 2021 ያለውን የሚያመላክት አሐዝ ነው። አሁን የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ገንዘብ ለማበደር ታቅበው ሁኔታውን ቆም ብለው እያጤኑት የሚገኙት አገሪቱ የብድር እፎይታን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንግግር የጀመረች በመሆኑ ነው። ባለፈው ሐምሌ ወር የአይኤምኤፍ ቃል አቀባይ ጌሪ ራይስ በኢትዮጵያ የብድር ጉዳይ ላይ አንድ ከሚቴ በፍጥነት እንዲቋቋም ጥሪ አድርገው ነበር። ይህም ከቡድን 20 እና ከፓሪስ ክለብ አበዳሪዎች ዘንድ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የብድር እፎይታ ጥያቄ እንዲመለከት ነበር። መንግሥት የብድር መመለሻ እፎይታ ለማግኘት ንግግር መጀመሩ ስህተት አይደለም ይላሉ ባለሙያዎች። በተለይም የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ ብዙ አገራት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል ብለዋል። በጉዳዩ ላይ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ እንደሚሉት "ኢትዮጵያ ኮቪድን አልፈጠረችውም፡፡ … ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ጊዜን መጠየቃቸው ምክንያታዊ አይደለም ማለት አልችልም" ሲሉ የኢትዮጵያን የብድር እፎይታ ጥያቄ አግባብነት ደግፈዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ የተበደረችው ዕዳ እስከ መጋቢት ወር ብቻ 29 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም የጥቅል አገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) 27 ከመቶ የያዘ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-58246656 |
3politics
| እስራኤል-ጋዛ፡ ኔታንያሁ የሃማስ ታጣቂዎች ለዓመታት ወደ ኋላ ተመልሰዋል አሉ | እስራኤል በጋዛ ያደረገችው የዘጠኝ ቀናት ድብደባ የሃማስ ታጣቂዎችን በበርካታ ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ተናገሩ። የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት አሁንም ጋብ አላለም። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ወደ ደቡባዊ እስራኤል በተኮሱት ሮኬት ሁለት የውጭ አገር የእርሻ ሠራተኞች ተገድለዋል። እስራኤልም በጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባ ቀጥላለች። በዌስት ባንክ በራማላህ አቅራቢያ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ ሦስት ፍልስጥኤማዊያን በእስራኤል ፖሊሶች ተገድለዋል። ግጭቱ እንዲቆም የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችም ያን ያህል ውጤት አላመጡም። ፈረንሳይ ከግብጽ እና ጆርዳን ጋር በመተባበር ግጭቱን ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ ሃሳብ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አቅርባለች። አገራቱ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል እርዳታ እንዲገባ ለመፍቀድ ወደ ጋዛ የሚወስደውን ድንበር የከፈተች ቢሆንም ከፍልስጤም ወታደሮች ሮኬቶች በመተኮሱ በድጋሜ ድንበሩ ተዘግቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ምንድን ነው ያሉት? ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ "ጋዛን የሚያስተዳድረው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኑ ሃማስ ያልተጠበቀ ዱብ ዳ አጋጥሞታል፤ ይህ ዘመቻም በእስራኤል ዜጎች ዘንድ መረጋጋት እስከሚመጣ ድረስ ይቀጥላል" ብለዋል። እንደ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በጋዛ ቢያንስ 215 ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚህ መካከል 100 የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት ናቸው። የጤና አገልግሎት ተቋም እንዳለው በእስራኤል ደግሞ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 12 ሰዎች ተገድለዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል በጋዛ ከተገደሉት መካከል ቢያንስ 150 የሚሆኑት ታጣቂዎች እንደሆኑ አስታውቃለች። ይሁን እንጅ ሃማስ በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት በአሃዝ አልጠቀሰም። ግጭቱ ከተከሰተ ጀምሮ እስራኤል ሁለቱ የፍልስጤም ታጣቂዎች ክንፍ 120 ሺህ የሚደርሱ ሮኬቶች በጋዛ እንደነበራቸው ግምቷን አስቀምጣለች። ታጣቂዎቹ ከማክሰኞ ዕለት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ 3 ሺህ 300 የሚሆኑ ሮኬቶችን እስራኤል ላይ ተኩሰዋል። ከእነዚህ መካከል ከ450 እስከ 500 የሚደርሱት ከታለመው ሳይደርሱ በአጭር ቀርተው በጋዛ ጉዳት ማድረሳቸውን የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በዌስት ባንክ የተፈጠረው ምንድን ነው? በዌስት ባንክ እና በምስራቅ እየሩሳሌም ያሉ በርካታ ፍልስጥኤማዊያን እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ በመቃወም አድማ መትተዋል። በእስራኤል የሚገኙና የእስራኤል አረቦች በብዛት በሚኖሩባቸው እንደ ሃይፋ ያሉ አካባቢዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። የሕዝብ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል። በተለያዩ አካባቢዎችም ግጭቶች ነበሩ። በዌስት ባንክ ከተማ ራማላህ ሰላማዊ ባልሆነው ተቃውሞ ወቅት መተኮሳቸውን የእስራኤል ፖሊስ ተናግሯል። በአካባቢው የነበሩ ሦስት ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሄብሮን ወታደሮችን ለማጥቃት የሞከረ ሌላ ፍልስጤማዊ መገደሉንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በእየሩሳሌም የደማስቆ መግቢያም ግጭቶች የነበሩ ሲሆን የእስራኤል ወታደሮች በርካቶችን አስረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድርጅት- ኦቻ በጋዛ 52 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከእነዚህ መካከል 47 ሺህ የሚሆኑት ወደ ተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች መሸሻቸውን አስታውቋል። ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በኒውዮርክ በቅርቡ በተደረገው ስብሰባ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ በድጋሚ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ቀርቷል። ፈረንሳይ ያቀረበችው የመፍትሔ ሃሳብ የተዘጋጀው ከግብፁ መሪ አብደል ፈታህ አል ሲሲ እና ከጆርዳኑ ንጉስ አብዱላህ ሁለተኛ ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ወቅት መሆኑን አስታውቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም የጸጥታው ምክር ቤት የተኩስ አቁም ጥሪ የሚያቀርብ የጋራ መግለጫ ለማውጣት የተደረጉ ጥረቶች ላይ ሳትስማማ ቀርታለች። አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች ኃያላን ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ግብጽ እስራኤልና ሃማስን ለማሸማገል እንደምትፈልግ ገልጻለች። ይሁን እንጅ እስራኤል ሃማስን እና እስላማዊ ጅሃድን ለማጥፋት ጥቃት መፈፀሟን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። በተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም አምባሳደር ሪያድ ማንሱር የጸጥታው ምክር ቤት ወጥ አቋም አለማሳየቱን "አሳፋሪ" ብለውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ የቱርኩ ፕሬዚደንትን ሬሲብ ታይፕ ኤርዶዋንን ስለ እስራኤል ተናግረዋል ባለችው 'ጸረ አይሁዳውያን' ንግግር ከሳለች። ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው በፍልስጥኤማውያን ላይ በምትፈጽመው ጥቃት እስራኤልን ከሰዋል። በቅርቡም "ይህ ተፈጥሯቸው ነው" በማለት "እስራኤል ገዳይ ናት" በማለት 'ጸረ አይሁዳውያን' ተደርጎ በስፋት የሚታይ ንግግር ተናግረዋል። የአሜሪካ የፕሬዚደንት የታይፕ ኤርዶዋንን ንግግር በጥብቅ አውግዛለች። ፕሬዚደንት ኤርዶዋንና ሌሎች የቱርክ መሪዎች ተጨማሪ ግጭት ሊቀሰቅስ ከሚችል መሰል ንግግርም እንዲታቀቡ አሳስባለች። ግጭቱን የቀሰቀሰው ምንድን ነው? በእስራኤልና በሃማስ መካከል የተከሰተው ግጭት የተነሳው በፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን ፖሊስ መካከል በምሥራቅ እየሩሳሌም ቅዱስ ሥፍራ ለቀናት በተፈጠረ ግጭት ነው። ሥፍራው በሙስሊሞችም ክብር የሚሰጠው ሲሆን ሃራም አል ሻሪፍ እያሉ ይጠሩታል። አይሁዳውያን ደግሞ የተራራው ቤተ መቅደስ ይሉታል። ሃማስ እስራኤል ፖሊሶቿን ከአካባቢውና በርካታ ሙስሊሞች ከሚኖሩበት የአረቦች ግዛት ሼክ ጃራህ እንድታነሳ ትፈልጋለች። ሼክ ጃራህ በርካታ የፍልስጥኤም ቤተሰቦች በአይሁድ ነዋሪዎች የተገደሉበት ነው። ሃማስ ለዚህ ጥያቄው መልስ ሳያገኝ ቀረ። ከዚያም ሮኬት መተኮስ ጀመረ። በእርግጥ የፍልስጤማውያን ቁጣ ለሳምንታት በእየሩሳሌም በነበረው ውጥረት ታምቆ የቆየ ነበር። ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮም ከፖሊሶች ጋር ግቶች ነበሩ። ከዚያም እስራኤል እአአ1967 በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት፤ ምስራቅ እየሩሳሌምን በተቆጣጠረችበትና 'የእየሩሳሌም ቀን' ተብሎ በሚጠራው ዓመታዊ በዓል ላይ ሌላ ችግር ተቆሰቆሰ። ግጭቱ ለዓመታት የነበረ ይሁን እንጅ የሰሞኑ ግጭት መነሻ ግን ይኸው ነው። ለሁለቱም ወገኖች ሃይማኖታዊና ብሔራዊ መሠረት ያላት የከተማዋ እጣ ፈንታም ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጤም ግጭት ላይ የወደቀ ነው። እስራኤል እአአ በ1980 ምሥራቅ እየሩሳሌምና ጠቅላላ ከተማዋን እአአ በ2017 ዋና መዲናዋ አድርጋለች። ነገር ግን ይህ በአብዛኛው አገራት እውቅና አልተሰጠውም። ፍልስጤም ደግሞ እመሰርተዋለሁ ብላ ላሰበችው ለራሷ አገር ዋና መዲናነት የምሥራቃዊ እየሩሳሌም ግማሹ ክፍል ይገባኛል ትላለች። | እስራኤል-ጋዛ፡ ኔታንያሁ የሃማስ ታጣቂዎች ለዓመታት ወደ ኋላ ተመልሰዋል አሉ እስራኤል በጋዛ ያደረገችው የዘጠኝ ቀናት ድብደባ የሃማስ ታጣቂዎችን በበርካታ ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ተናገሩ። የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት አሁንም ጋብ አላለም። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ወደ ደቡባዊ እስራኤል በተኮሱት ሮኬት ሁለት የውጭ አገር የእርሻ ሠራተኞች ተገድለዋል። እስራኤልም በጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባ ቀጥላለች። በዌስት ባንክ በራማላህ አቅራቢያ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ ሦስት ፍልስጥኤማዊያን በእስራኤል ፖሊሶች ተገድለዋል። ግጭቱ እንዲቆም የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችም ያን ያህል ውጤት አላመጡም። ፈረንሳይ ከግብጽ እና ጆርዳን ጋር በመተባበር ግጭቱን ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ ሃሳብ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አቅርባለች። አገራቱ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል እርዳታ እንዲገባ ለመፍቀድ ወደ ጋዛ የሚወስደውን ድንበር የከፈተች ቢሆንም ከፍልስጤም ወታደሮች ሮኬቶች በመተኮሱ በድጋሜ ድንበሩ ተዘግቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ምንድን ነው ያሉት? ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ "ጋዛን የሚያስተዳድረው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኑ ሃማስ ያልተጠበቀ ዱብ ዳ አጋጥሞታል፤ ይህ ዘመቻም በእስራኤል ዜጎች ዘንድ መረጋጋት እስከሚመጣ ድረስ ይቀጥላል" ብለዋል። እንደ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በጋዛ ቢያንስ 215 ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚህ መካከል 100 የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት ናቸው። የጤና አገልግሎት ተቋም እንዳለው በእስራኤል ደግሞ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 12 ሰዎች ተገድለዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል በጋዛ ከተገደሉት መካከል ቢያንስ 150 የሚሆኑት ታጣቂዎች እንደሆኑ አስታውቃለች። ይሁን እንጅ ሃማስ በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት በአሃዝ አልጠቀሰም። ግጭቱ ከተከሰተ ጀምሮ እስራኤል ሁለቱ የፍልስጤም ታጣቂዎች ክንፍ 120 ሺህ የሚደርሱ ሮኬቶች በጋዛ እንደነበራቸው ግምቷን አስቀምጣለች። ታጣቂዎቹ ከማክሰኞ ዕለት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ 3 ሺህ 300 የሚሆኑ ሮኬቶችን እስራኤል ላይ ተኩሰዋል። ከእነዚህ መካከል ከ450 እስከ 500 የሚደርሱት ከታለመው ሳይደርሱ በአጭር ቀርተው በጋዛ ጉዳት ማድረሳቸውን የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በዌስት ባንክ የተፈጠረው ምንድን ነው? በዌስት ባንክ እና በምስራቅ እየሩሳሌም ያሉ በርካታ ፍልስጥኤማዊያን እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ በመቃወም አድማ መትተዋል። በእስራኤል የሚገኙና የእስራኤል አረቦች በብዛት በሚኖሩባቸው እንደ ሃይፋ ያሉ አካባቢዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። የሕዝብ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል። በተለያዩ አካባቢዎችም ግጭቶች ነበሩ። በዌስት ባንክ ከተማ ራማላህ ሰላማዊ ባልሆነው ተቃውሞ ወቅት መተኮሳቸውን የእስራኤል ፖሊስ ተናግሯል። በአካባቢው የነበሩ ሦስት ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሄብሮን ወታደሮችን ለማጥቃት የሞከረ ሌላ ፍልስጤማዊ መገደሉንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በእየሩሳሌም የደማስቆ መግቢያም ግጭቶች የነበሩ ሲሆን የእስራኤል ወታደሮች በርካቶችን አስረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድርጅት- ኦቻ በጋዛ 52 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከእነዚህ መካከል 47 ሺህ የሚሆኑት ወደ ተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች መሸሻቸውን አስታውቋል። ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በኒውዮርክ በቅርቡ በተደረገው ስብሰባ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ በድጋሚ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ቀርቷል። ፈረንሳይ ያቀረበችው የመፍትሔ ሃሳብ የተዘጋጀው ከግብፁ መሪ አብደል ፈታህ አል ሲሲ እና ከጆርዳኑ ንጉስ አብዱላህ ሁለተኛ ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ወቅት መሆኑን አስታውቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም የጸጥታው ምክር ቤት የተኩስ አቁም ጥሪ የሚያቀርብ የጋራ መግለጫ ለማውጣት የተደረጉ ጥረቶች ላይ ሳትስማማ ቀርታለች። አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች ኃያላን ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ግብጽ እስራኤልና ሃማስን ለማሸማገል እንደምትፈልግ ገልጻለች። ይሁን እንጅ እስራኤል ሃማስን እና እስላማዊ ጅሃድን ለማጥፋት ጥቃት መፈፀሟን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። በተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም አምባሳደር ሪያድ ማንሱር የጸጥታው ምክር ቤት ወጥ አቋም አለማሳየቱን "አሳፋሪ" ብለውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ የቱርኩ ፕሬዚደንትን ሬሲብ ታይፕ ኤርዶዋንን ስለ እስራኤል ተናግረዋል ባለችው 'ጸረ አይሁዳውያን' ንግግር ከሳለች። ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው በፍልስጥኤማውያን ላይ በምትፈጽመው ጥቃት እስራኤልን ከሰዋል። በቅርቡም "ይህ ተፈጥሯቸው ነው" በማለት "እስራኤል ገዳይ ናት" በማለት 'ጸረ አይሁዳውያን' ተደርጎ በስፋት የሚታይ ንግግር ተናግረዋል። የአሜሪካ የፕሬዚደንት የታይፕ ኤርዶዋንን ንግግር በጥብቅ አውግዛለች። ፕሬዚደንት ኤርዶዋንና ሌሎች የቱርክ መሪዎች ተጨማሪ ግጭት ሊቀሰቅስ ከሚችል መሰል ንግግርም እንዲታቀቡ አሳስባለች። ግጭቱን የቀሰቀሰው ምንድን ነው? በእስራኤልና በሃማስ መካከል የተከሰተው ግጭት የተነሳው በፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን ፖሊስ መካከል በምሥራቅ እየሩሳሌም ቅዱስ ሥፍራ ለቀናት በተፈጠረ ግጭት ነው። ሥፍራው በሙስሊሞችም ክብር የሚሰጠው ሲሆን ሃራም አል ሻሪፍ እያሉ ይጠሩታል። አይሁዳውያን ደግሞ የተራራው ቤተ መቅደስ ይሉታል። ሃማስ እስራኤል ፖሊሶቿን ከአካባቢውና በርካታ ሙስሊሞች ከሚኖሩበት የአረቦች ግዛት ሼክ ጃራህ እንድታነሳ ትፈልጋለች። ሼክ ጃራህ በርካታ የፍልስጥኤም ቤተሰቦች በአይሁድ ነዋሪዎች የተገደሉበት ነው። ሃማስ ለዚህ ጥያቄው መልስ ሳያገኝ ቀረ። ከዚያም ሮኬት መተኮስ ጀመረ። በእርግጥ የፍልስጤማውያን ቁጣ ለሳምንታት በእየሩሳሌም በነበረው ውጥረት ታምቆ የቆየ ነበር። ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮም ከፖሊሶች ጋር ግቶች ነበሩ። ከዚያም እስራኤል እአአ1967 በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት፤ ምስራቅ እየሩሳሌምን በተቆጣጠረችበትና 'የእየሩሳሌም ቀን' ተብሎ በሚጠራው ዓመታዊ በዓል ላይ ሌላ ችግር ተቆሰቆሰ። ግጭቱ ለዓመታት የነበረ ይሁን እንጅ የሰሞኑ ግጭት መነሻ ግን ይኸው ነው። ለሁለቱም ወገኖች ሃይማኖታዊና ብሔራዊ መሠረት ያላት የከተማዋ እጣ ፈንታም ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጤም ግጭት ላይ የወደቀ ነው። እስራኤል እአአ በ1980 ምሥራቅ እየሩሳሌምና ጠቅላላ ከተማዋን እአአ በ2017 ዋና መዲናዋ አድርጋለች። ነገር ግን ይህ በአብዛኛው አገራት እውቅና አልተሰጠውም። ፍልስጤም ደግሞ እመሰርተዋለሁ ብላ ላሰበችው ለራሷ አገር ዋና መዲናነት የምሥራቃዊ እየሩሳሌም ግማሹ ክፍል ይገባኛል ትላለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-57167680 |
3politics
| አንዳንድ ነጥቦች አዲስ ስለሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን | ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ይህንን ሂደት የሚመራና የሚያስተባብር አካል ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። የተለያዩ አላማዎችን አንግበው በፖለቲካው መድረኩ ላይ ያሉ ኃይሎችና ልሂቃን እንዲሁም ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችና ሐሳቦችን መሠረት በማድረግ እንዲቀራረቡ በማድረግ ለአገራዊ አንድነት ገንቢ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አገራዊ ምክክሩ አውንታዊ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለአስርታት ምላሽ ሳያገኙ መግባባት ያልተደረሰባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮችን በማንሳት ታላላቅና ተከታታይ አገራዊ ምክክሮችን አሳታፊ በሆነ መንገድ በማካሄድ መግባባትን መገንባት ዋነኛ አላማው ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቡዕ ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም ያጸደቀው እና ላለፉት ሁለት ወራት ሲረቀቅ ብሎም ውይይቶች ሲደረጉበት የቆየው "የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን" አዋጅ መነጋጋሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ቢያንስ ሁለት ጊዜ መሠረታዊ ማሻሻያዎችን ያለፈው አዋጁ በርካታ አስተያየቶችና ትችቶችን ሲያስተናግድ ቆይቶ ነው ወደ ሥራ እንዲገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀው። በቀድሞው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአሁኑ የፍትሕ ሚኒስቴር አርቃቂነት፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መሪነት እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ስላለው አዲሱ ኮሚሽን አንዳንድ ነጥቦች። የኮሚሽነሮች ሹመት በአዋጁ የዜሮ ረቂቅ ላይ ሰባት ኮሚሽነሮች ይሾሙለታል ተብሎ የተጠቀሰ ሲሆን ቀጥሎም ተሻሽሎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ላይ የኮሚሽነሮች ቁጥር ወደ 11 ከፍ ተደርጓል። የመጀመሪያው ረቂቅ ዋና ኮሚሽነር እና ሌሎች ኮሚሽነሮች የሰላም ሚኒስቴር ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበራት ጥቆማ በመቀበል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያቀርብ ያወሳ ነበር። በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በመወያየት ዕጩዎቹን ለተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ያሾማሉ ሲል የመጀመሪያው ረቂቅ ያትት ነበር። ነገር ግን የጸደቀው አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት የዕጩ ኮሚሽነሮችን ጥቆማ ከሕዝብ፣ ከሲቪል ማኅበራት እና ከፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚቀበል እና አፈ ጉባኤው ለምክር ቤቱ ዕጩ ኮሚሽነሮችን እንደሚያቀርብ ያትታል። "ምክንያቱም የዕጩዎችን ጥቆማ መቀበል እና ለምክር ቤቱ አቅርቦ የማሾም ሥልጣን የአፈ ጉባኤው እና የጽህፈት ቤታቸው ሲሆን ይህ የኮሚሽነሮቹ ገለልተኝነት የተሻለ እንዲሆን ያደርጋል" ሲል የጸደቀው የውሳኔ ሃሳብ ይጠቅሳል። በቅድሚያ በረቂቅ ሕጉ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ሥልጣን ሊሰጥ የነበረው ሐሳብም በመጨረሻ ውድቅ ተደርጎ የአፈ ጉባኤው ሥልጣን አንዲሆን ተደርጓል። የኮሚሽነሮቹ መብቶች በአዋጁ አንቀጽ 15 መሰረት በኮሚሽነርነት የሚሾሙት አባላት ያለመከሰስ መብት አግኝተዋል። እንዲሁም "የኮሚሽነሮች ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ለመንግሥት ከፍተኛ ተሿሚዎች በተፈቀደው ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም አግባብ ይፈፀማል" ሲል አዋጁ ያስቀምጣል። በኮሚሽኑ ሥራ ላይ ድምጽ የመስጠት ብሎም ለሥራቸው የሚያስፈልጉ ሰነዶቸን እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን የማግኘት እና የመመልከት መብት አላቸው። ይህንንም በሥራ ላይ ያገኙትን ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ስለ ኮሚሽኑ ሥራዎች ኮሚሽኑ በጀቱ በመንግሥት የሚመደብ ሲሆን የመንግሥትን የፋይናንስ አስተዳደር መርሆዎችን መሰረት በማድረግ በበጀቱ ላይ ሙሉ ነጻነት እንደሚኖረው አዋጁ ያደርጋል። ኮሚሽነሮቹ አባል የሆኑበት ምክር ቤት ዋናውን የኮሚሽኑን ሥራዎች የሚያከናውን ይሆናል። ምክር ቤቱ ለምክክር የሚሆኑ አጀንዳዎችን መምረጥ፣ ከኮሚቴዎችም ሆነ ከሕዝብ የሚገኙ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግሥት ማቅረብ፣ ለኮሚሽኑ እንቅስቃሴ የሚያስፈለጉ የውስጥ ደንብ እና መመሪያዎችን ማውጣትን ጨምሮ መሠረታዊ የአስተዳዳራዊ ተግባራትን ጨምሮ በበላይነት ይመራል። በሕብረተሰቦች መካከል የሚታዩ መሠረታዊ ልዩነቶች ምክንያቶችን በመለየት እና ለውይይትም ርዕሰ ጉዳዮችን በመለየት ምክክር እንዲደረግባቸው የሚለየው ይሔው ኮሚሽን ነው። እንዲሁም እነዚህ ምክክሮች "ብቃት ባለው ገለልተኛ በሆነ አካል የሚመሩ፤ ያለመግባባት መንስኤዎችን በትክክል የሚዳስስ አጀንዳ ላይ የሚያተኩ፣ ግልጽ ብሎም ለማስፈጸም የሚያስችሉ ውጤታማ አገራዊ ውይይትን የሚያስተናግድ ሥርዓትን የመዘርጋት" ሥልጣንም ተሰጥቶታል። የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ በአዋጁ ዜሮ ረቂቅ ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ እድሜ ይኖረዋል የተባለው ኮሚሽኑ በአንድ ዓመት ከፍ ብሎ የሦስት ዓመት የቆይታ ዘመን እንዲኖረውም ተደርጓል። ነገር ግን እንዳስፈላጊነቱ በተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል እና እድሜው መሰላት የሚጀምረው ኮሚሽነሮቹ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ መሆኑም በአዋጁ ተካቷል። ዋና መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ በክልሎች ቅርንጫፎች ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል። የኮሚሽኑ ሥልጣን ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ አላማ መንግሥታዊ በሆኑም ሆነ ባልሆኑ ተቋማት የተደረጉ የምክክር ሂደቶችን እና የተገኙ ውጤቶችን በማጥናት በቀጣይ ለሚያካሂዳቸው አገራዊ ውይይቶች በግብአትነት እንደሚጠቀም አዋጁ ያስረዳል። በልሂቃኖች መካከል አገራዊ ጉዳዮችን አስመልከቶ ያሉ ልዩነቶችን የመለየት፣ ምክክሮችን የማሳለጥ እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚወከሉ ተሳታፊዎች ያሉባቸውን የምክክር ስብሰባዎችን ያካሂዳል። ኮሚሸኑ ተወካዮችን የመምረጥ ብሎም ኮሚሽነሮቹ እነዚህን ምክክሮችን የመምራት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። እንዲሁም የምክክር አጀንዳዎችን፣ የምክክሮቹን ሂደት፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረ ሐሳቦችን ተግባር ላይ ሊውሉ ስለሚችሉበት መንገድ ሪፖርቶችን በማሰናዳት ለመንግሥት እና ለሕዝብ የማቅረብ ግዴታም ተጥሎበታል። መንግሥት ምክረ ሐሳቦችን እንዲተገብር የማገዝ ብሎም ተግባራዊነታቸውን የመከታተል ሥልጣንም አግኝቷል። | አንዳንድ ነጥቦች አዲስ ስለሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ይህንን ሂደት የሚመራና የሚያስተባብር አካል ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። የተለያዩ አላማዎችን አንግበው በፖለቲካው መድረኩ ላይ ያሉ ኃይሎችና ልሂቃን እንዲሁም ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችና ሐሳቦችን መሠረት በማድረግ እንዲቀራረቡ በማድረግ ለአገራዊ አንድነት ገንቢ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አገራዊ ምክክሩ አውንታዊ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለአስርታት ምላሽ ሳያገኙ መግባባት ያልተደረሰባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮችን በማንሳት ታላላቅና ተከታታይ አገራዊ ምክክሮችን አሳታፊ በሆነ መንገድ በማካሄድ መግባባትን መገንባት ዋነኛ አላማው ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቡዕ ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም ያጸደቀው እና ላለፉት ሁለት ወራት ሲረቀቅ ብሎም ውይይቶች ሲደረጉበት የቆየው "የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን" አዋጅ መነጋጋሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ቢያንስ ሁለት ጊዜ መሠረታዊ ማሻሻያዎችን ያለፈው አዋጁ በርካታ አስተያየቶችና ትችቶችን ሲያስተናግድ ቆይቶ ነው ወደ ሥራ እንዲገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀው። በቀድሞው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአሁኑ የፍትሕ ሚኒስቴር አርቃቂነት፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መሪነት እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ስላለው አዲሱ ኮሚሽን አንዳንድ ነጥቦች። የኮሚሽነሮች ሹመት በአዋጁ የዜሮ ረቂቅ ላይ ሰባት ኮሚሽነሮች ይሾሙለታል ተብሎ የተጠቀሰ ሲሆን ቀጥሎም ተሻሽሎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ላይ የኮሚሽነሮች ቁጥር ወደ 11 ከፍ ተደርጓል። የመጀመሪያው ረቂቅ ዋና ኮሚሽነር እና ሌሎች ኮሚሽነሮች የሰላም ሚኒስቴር ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበራት ጥቆማ በመቀበል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያቀርብ ያወሳ ነበር። በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በመወያየት ዕጩዎቹን ለተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ያሾማሉ ሲል የመጀመሪያው ረቂቅ ያትት ነበር። ነገር ግን የጸደቀው አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት የዕጩ ኮሚሽነሮችን ጥቆማ ከሕዝብ፣ ከሲቪል ማኅበራት እና ከፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚቀበል እና አፈ ጉባኤው ለምክር ቤቱ ዕጩ ኮሚሽነሮችን እንደሚያቀርብ ያትታል። "ምክንያቱም የዕጩዎችን ጥቆማ መቀበል እና ለምክር ቤቱ አቅርቦ የማሾም ሥልጣን የአፈ ጉባኤው እና የጽህፈት ቤታቸው ሲሆን ይህ የኮሚሽነሮቹ ገለልተኝነት የተሻለ እንዲሆን ያደርጋል" ሲል የጸደቀው የውሳኔ ሃሳብ ይጠቅሳል። በቅድሚያ በረቂቅ ሕጉ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ሥልጣን ሊሰጥ የነበረው ሐሳብም በመጨረሻ ውድቅ ተደርጎ የአፈ ጉባኤው ሥልጣን አንዲሆን ተደርጓል። የኮሚሽነሮቹ መብቶች በአዋጁ አንቀጽ 15 መሰረት በኮሚሽነርነት የሚሾሙት አባላት ያለመከሰስ መብት አግኝተዋል። እንዲሁም "የኮሚሽነሮች ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ለመንግሥት ከፍተኛ ተሿሚዎች በተፈቀደው ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም አግባብ ይፈፀማል" ሲል አዋጁ ያስቀምጣል። በኮሚሽኑ ሥራ ላይ ድምጽ የመስጠት ብሎም ለሥራቸው የሚያስፈልጉ ሰነዶቸን እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን የማግኘት እና የመመልከት መብት አላቸው። ይህንንም በሥራ ላይ ያገኙትን ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ስለ ኮሚሽኑ ሥራዎች ኮሚሽኑ በጀቱ በመንግሥት የሚመደብ ሲሆን የመንግሥትን የፋይናንስ አስተዳደር መርሆዎችን መሰረት በማድረግ በበጀቱ ላይ ሙሉ ነጻነት እንደሚኖረው አዋጁ ያደርጋል። ኮሚሽነሮቹ አባል የሆኑበት ምክር ቤት ዋናውን የኮሚሽኑን ሥራዎች የሚያከናውን ይሆናል። ምክር ቤቱ ለምክክር የሚሆኑ አጀንዳዎችን መምረጥ፣ ከኮሚቴዎችም ሆነ ከሕዝብ የሚገኙ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግሥት ማቅረብ፣ ለኮሚሽኑ እንቅስቃሴ የሚያስፈለጉ የውስጥ ደንብ እና መመሪያዎችን ማውጣትን ጨምሮ መሠረታዊ የአስተዳዳራዊ ተግባራትን ጨምሮ በበላይነት ይመራል። በሕብረተሰቦች መካከል የሚታዩ መሠረታዊ ልዩነቶች ምክንያቶችን በመለየት እና ለውይይትም ርዕሰ ጉዳዮችን በመለየት ምክክር እንዲደረግባቸው የሚለየው ይሔው ኮሚሽን ነው። እንዲሁም እነዚህ ምክክሮች "ብቃት ባለው ገለልተኛ በሆነ አካል የሚመሩ፤ ያለመግባባት መንስኤዎችን በትክክል የሚዳስስ አጀንዳ ላይ የሚያተኩ፣ ግልጽ ብሎም ለማስፈጸም የሚያስችሉ ውጤታማ አገራዊ ውይይትን የሚያስተናግድ ሥርዓትን የመዘርጋት" ሥልጣንም ተሰጥቶታል። የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ በአዋጁ ዜሮ ረቂቅ ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ እድሜ ይኖረዋል የተባለው ኮሚሽኑ በአንድ ዓመት ከፍ ብሎ የሦስት ዓመት የቆይታ ዘመን እንዲኖረውም ተደርጓል። ነገር ግን እንዳስፈላጊነቱ በተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል እና እድሜው መሰላት የሚጀምረው ኮሚሽነሮቹ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ መሆኑም በአዋጁ ተካቷል። ዋና መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ በክልሎች ቅርንጫፎች ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል። የኮሚሽኑ ሥልጣን ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ አላማ መንግሥታዊ በሆኑም ሆነ ባልሆኑ ተቋማት የተደረጉ የምክክር ሂደቶችን እና የተገኙ ውጤቶችን በማጥናት በቀጣይ ለሚያካሂዳቸው አገራዊ ውይይቶች በግብአትነት እንደሚጠቀም አዋጁ ያስረዳል። በልሂቃኖች መካከል አገራዊ ጉዳዮችን አስመልከቶ ያሉ ልዩነቶችን የመለየት፣ ምክክሮችን የማሳለጥ እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚወከሉ ተሳታፊዎች ያሉባቸውን የምክክር ስብሰባዎችን ያካሂዳል። ኮሚሸኑ ተወካዮችን የመምረጥ ብሎም ኮሚሽነሮቹ እነዚህን ምክክሮችን የመምራት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። እንዲሁም የምክክር አጀንዳዎችን፣ የምክክሮቹን ሂደት፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረ ሐሳቦችን ተግባር ላይ ሊውሉ ስለሚችሉበት መንገድ ሪፖርቶችን በማሰናዳት ለመንግሥት እና ለሕዝብ የማቅረብ ግዴታም ተጥሎበታል። መንግሥት ምክረ ሐሳቦችን እንዲተገብር የማገዝ ብሎም ተግባራዊነታቸውን የመከታተል ሥልጣንም አግኝቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59822579 |
0business
| በህንድ በመጠጥ መመረዝ የበርካቶች ህይወት አለፈ | በህንድ በመጠጥ መመረዝ የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። ግለሰቦቹ በህገወጥ መንገድ የተመረተ አልኮል በመጠጣታቸው ህይወታቸው ማለፉን የሰሜን ህንዷ ግዛት ፑንጃብ ኃላፊዎች አስረድተዋል። በትናንትናው ዕለት ፖሊስ አካባቢውን በመቆጣጠር ህገወጥ የተባለውን መጠጥ የያዘ ሲሆን መጠጡን ያመርታሉ የተባሉ 25 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የሟቾችም ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው ተብሏል። በህንድ በመጠጥ መመረዝ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሲሞቱ አዲስ አይደለም፤ በተደጋጋሚም የሚከሰት ችግር ነው ተብሏል። በየአመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህንዳውያን በጓዳ ጎድጓዳው ንፅህናው ባልተጠበቀ መልኩ የሚጠመቁ መጠጦችን በመጠጣት ህይወታቸው ያልፋል። በተለይም በገጠሯ ህንድ ታዋቂ ስም ያላቸውን መጠጦች ከመግዛት ይልቅ በህገ ወጥ መንገድ የተመረቱና ዋጋቸው ርካሽ የሆኑ መጠጦችን ይገዛሉ፤ በዚህም በርካቶች መመረዛቸው ሪፖርት ይደረጋል። መጠጥ ጠማቂዎች ሜታኖል የሚባለው ንጥረ ነገር ይጨምሩበታል። ይህ ንጥረ- ነገር ከፍተኛ መርዛማነት ያለው ሲሆን የመጠጡን ጥንካሬም ለመጨመርም ነው ሜታኖልን የሚጨምሩበት ተብሏል። በትንሽም መጠን ቢሆን ይህ ንጥረ ነገር ከተወሰደ አይነ ስውርነት፣ የጉበት ህመም እንዲሁም ባስ ሲል ሞት እንደሚያስከትልም ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዚህ ሳምንት አርብም የፑንጃብ ግዛት አስተዳዳሪ ሚኒስትር አማሪንደር ሲንግ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ላይ ምርመራ እንዲጀመር አዘዋል። በርካታ ሪፖርቶች እንደሚያስረዱት መጠጡ በከፍተኛ መጠን እንደተጠመቀና ጎዳናዎች ላይ ላሉ የካፌ ባለቤቶች እንደተሸጠና የአካባቢው ማህበረሰብም መጠጡን ማግኘቱ ተገልጿል። ከሰሞኑም በሕንድ ውስጥ በምትገኘው አንድራ ፕራዴሽ ግዛት የመጠጥ መሸጫ ሱቆች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርከት ባለ አልኮል የተሰራ ሳኒታይዘር የጠጡ ቢያንስ አስር ግለሰቦች ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል። የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ እንደተናገሩት ሰዎቹ ሕይወታቸው ሊያልፍ የቻለው ሳኒታይዘሩን ከውሃ እና ከለስላሳ መጠጦች ጋር ቀላቅለው በመጠጣታቸው ነው። | በህንድ በመጠጥ መመረዝ የበርካቶች ህይወት አለፈ በህንድ በመጠጥ መመረዝ የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። ግለሰቦቹ በህገወጥ መንገድ የተመረተ አልኮል በመጠጣታቸው ህይወታቸው ማለፉን የሰሜን ህንዷ ግዛት ፑንጃብ ኃላፊዎች አስረድተዋል። በትናንትናው ዕለት ፖሊስ አካባቢውን በመቆጣጠር ህገወጥ የተባለውን መጠጥ የያዘ ሲሆን መጠጡን ያመርታሉ የተባሉ 25 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የሟቾችም ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው ተብሏል። በህንድ በመጠጥ መመረዝ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሲሞቱ አዲስ አይደለም፤ በተደጋጋሚም የሚከሰት ችግር ነው ተብሏል። በየአመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህንዳውያን በጓዳ ጎድጓዳው ንፅህናው ባልተጠበቀ መልኩ የሚጠመቁ መጠጦችን በመጠጣት ህይወታቸው ያልፋል። በተለይም በገጠሯ ህንድ ታዋቂ ስም ያላቸውን መጠጦች ከመግዛት ይልቅ በህገ ወጥ መንገድ የተመረቱና ዋጋቸው ርካሽ የሆኑ መጠጦችን ይገዛሉ፤ በዚህም በርካቶች መመረዛቸው ሪፖርት ይደረጋል። መጠጥ ጠማቂዎች ሜታኖል የሚባለው ንጥረ ነገር ይጨምሩበታል። ይህ ንጥረ- ነገር ከፍተኛ መርዛማነት ያለው ሲሆን የመጠጡን ጥንካሬም ለመጨመርም ነው ሜታኖልን የሚጨምሩበት ተብሏል። በትንሽም መጠን ቢሆን ይህ ንጥረ ነገር ከተወሰደ አይነ ስውርነት፣ የጉበት ህመም እንዲሁም ባስ ሲል ሞት እንደሚያስከትልም ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዚህ ሳምንት አርብም የፑንጃብ ግዛት አስተዳዳሪ ሚኒስትር አማሪንደር ሲንግ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ላይ ምርመራ እንዲጀመር አዘዋል። በርካታ ሪፖርቶች እንደሚያስረዱት መጠጡ በከፍተኛ መጠን እንደተጠመቀና ጎዳናዎች ላይ ላሉ የካፌ ባለቤቶች እንደተሸጠና የአካባቢው ማህበረሰብም መጠጡን ማግኘቱ ተገልጿል። ከሰሞኑም በሕንድ ውስጥ በምትገኘው አንድራ ፕራዴሽ ግዛት የመጠጥ መሸጫ ሱቆች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርከት ባለ አልኮል የተሰራ ሳኒታይዘር የጠጡ ቢያንስ አስር ግለሰቦች ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል። የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ እንደተናገሩት ሰዎቹ ሕይወታቸው ሊያልፍ የቻለው ሳኒታይዘሩን ከውሃ እና ከለስላሳ መጠጦች ጋር ቀላቅለው በመጠጣታቸው ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-53627129 |
2health
| ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ "ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው" አሉ | በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ "ኦቫል" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣ አውሮፕላንና ሆስፒታል ባሉ መሰባሰብን በሚጠይቁ ከበር መለስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ቦታዎች ላይ ግን ክትባት የተከተቡትም ቢሆኑ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ላገኙ ሰዎች የኮቪድ ክልከላዎች እንዲነሱላቸው በባይደን አስተዳደር ላይ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንት ባይደን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ፋይዘር ያመረተውን ከትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ ፍቃድ ከተሰጠ በኃላ ነው። አሁን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተሰምቷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅም ግዴታቸ እንዳልሆነ አስታውቋል። በቲውተር ገጻቸው ያልተከተቡ ሰዎች 'ማስክ' ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ባይደን "ህጉ ቀላል ነው መከተብ ወይም እስከትከተቡ ጭምብል ማደረግ። ምርጫው የእናንተ ነው" ብለዋል። በአሜሪካ 35 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን የ ጆ ባይደን አስተዳደር ይሄ ቁጥር እስከ ሀምሌ ደረስ በእጥፍ አሳድጎ 70 በመቶ ለማደረስ አቅዷል። | ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ "ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው" አሉ በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ "ኦቫል" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣ አውሮፕላንና ሆስፒታል ባሉ መሰባሰብን በሚጠይቁ ከበር መለስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ቦታዎች ላይ ግን ክትባት የተከተቡትም ቢሆኑ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ላገኙ ሰዎች የኮቪድ ክልከላዎች እንዲነሱላቸው በባይደን አስተዳደር ላይ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንት ባይደን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ፋይዘር ያመረተውን ከትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ ፍቃድ ከተሰጠ በኃላ ነው። አሁን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተሰምቷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅም ግዴታቸ እንዳልሆነ አስታውቋል። በቲውተር ገጻቸው ያልተከተቡ ሰዎች 'ማስክ' ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ባይደን "ህጉ ቀላል ነው መከተብ ወይም እስከትከተቡ ጭምብል ማደረግ። ምርጫው የእናንተ ነው" ብለዋል። በአሜሪካ 35 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን የ ጆ ባይደን አስተዳደር ይሄ ቁጥር እስከ ሀምሌ ደረስ በእጥፍ አሳድጎ 70 በመቶ ለማደረስ አቅዷል። | https://www.bbc.com/amharic/57111329 |
5sports
| ለንደን ማራቶን፡ አትሌት ሹራ ቂጣታ ከኬንያዊው ኪፕቾጌ የማራቶን ድል እንዲነጥቅ የረዳው ምንድን ነው? | ኤሉድ ኪፕቾጌን ለማሸነፍ እንዴት ያለ ወኔ ይበቃ ይሆን? ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የሮጠውን ብርቱ አትሌት ለማሸነፍ ምን ሲደረግ ይቻላል? ጥብቅ ልምምድ ወይስ ተሰጥኦ? ለለንደን ማራቶን አሸናፊው ሹራ ቂጣታ ግን ጥሩ ቁርስ በቂ ነው። ባለፈው ዓመት በዩኬ ዋና ከተማ አራተኛ በመሆን ነው ያጠናቀቀው። ያኔ ኬኒያዊው ኪፕቾጌ ነው ያሸነፈው። በወቅቱ ሹራ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ባዶ ሆዱን መሮጡን፣ ለቁርስ ፍራፍሬ ብቻ መመገቡን ገልጾ ነበር። ሹራ በወቅቱ 35 ኪሎ ሜትሮች ከሮጠ በኋላ የተሰማውን ሲያሰፍር "ሆዴ ከጀርባዬ ጋር የተጣበቀ መስሎኝ ነበር፤ ሞርሙሮኝ ነበር" ብሏል። በዚህ ዓመት ከስህተቱ የተማረው ሹራ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ጥሩ ምግብ ወሳስዷል። ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ " ሁሉንም ነገር ተመግቤያለሁ" ብሏል። "ሾርባ፣ ዳቦ፣ እንቁላል እና እርጎ ወስጃለሁ፤ አቅም የሚሆነኝንና ውድድሩን በጥሩ ጉልበት መፎካከር የሚያስችለኝን ሁሉ ወስጃለሁ።" ውድድሩ ደግሞ ከ2014 ጀምሮ በማራቶኑ መስክ አልበገር ያለውን ኬንያዊ ማንበርከክን ያካተተ ነበር። ኪፕቾጌ የዋዛ አትሌት አይደለም። በኦሎምፒክ መንደር ስሙ በደማቅ ተጽፏል። የዓለም ክብረ ወሰን በእጁ ነው። የ35 ዓመቱ ኪፕቾጌ በለንደን ለአምስተኛ ጊዜ ድልን ለመቀዳጀት ጉልበቱን አበርትቶ ሞራሉን አደርጅቶ ነው የተገኘው። የዓለም መገናኛ ብዙኃንም ስሙን ደጋግመው ያነሳሉ። ምስሉን ደጋግመው ያሳያሉ። ጋዜጦች የፊት ገጻቸው ላይ አትመውታል። ለንደን ለኪፕቾጌ፣ ኪፕቾጌም ለለንደን መሃላ ያላቸው ይመስላል። ኪፕቾጌና ለንደን ግን ያላቸው ቃል ኪዳን ፈረሰ። መፍረስ ብቻ ሳይሆን ስምንተኛ ወጣ። ከፊት የፈለጉት ከኋላ አገኙት። በኋላም ጆሮውን አሞት እንደነበር አስረዳ። ለረዥም ርቀት ሩጫ እርጥበታማ አየርና ቅዝቃዜ ምቹ አይደለም። ሹራ የገባበት ሰዓትም፣ ሁለት ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ41 ሰከንድ የሚያሳየው ይህንኑ ነው። ሹራ ግን እንደውም አየሩ ረድቶኛል ሲል ያምናል። እኤአ ከ2013 ወዲህ የለንደን ማራቶንን ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ሹራ "ሲዘንብ በጣም ደስ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በከባድ ዝናብ ውስጥ ነው ልምምድ ስሰራ የነበረው" ይላል። "አንድ ቀን ሶደሬ ለልምምድ ሄድኩኝ፣ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ከተማው በጎርፍ ተጥለቅልቋል። አሰልጣኜ እኔን ለማዳን መምጣት ሁሉ ነበረበት" ሲል የነበረውን የልምምድ ሁኔታም ያስታውሳል። "የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲከሰት፣ ቤት አልተቀመጥኩም። ለአምስት ወራት ያህል ከአሰልጣኜ ጋር ልምምድ ስሰራ ነበር። ይህን ድል ኪፕቾጌን ማሸነፌ ልዩ አያደርገውም፤ ጠንክሬ መስራቴ ነው ልዩ የሚያደርገው።" ቀነኒሳ በቀለ ባጋጠመው ጉዳት የተነሳ ከውድድሩ መውጣቱን ካሳወቀ በኋላ በኪፕቾጌና በቀነኒሳ መካከል ይኖራል ተብሎ የታሰበው ፍልሚያ ሳይሳካ ቀረ። ስለዚህ ማንም የቀነኒሳን አገር ልጅ፣ ሹራን ከኪፕቾጌ ጋር አነጻጽሮ ለማወዳደርና የዜና ፍጆታ ለማድረግ ፍላጎት አላሳየም። ሹራም ቢሆን "ሁሉም ትኩረቱ የነበረው ኪፕቾጌ እና ቀነኒሳ ላይ ነበር፤ እኔን ዞርም ብሎ ያየኝ አልነበረም" ሲል ይገልጻል። "ለራሴ ለዓለም ሌላ ሻምፒዮን መኖሩን አሳያለሁ ብዬ ነገርኩት፤ እናም ይህ ስሜት ነው እስከመጨረሻው ድረስ በራስ መተማመንና በሙሉ አቅም እንድቀጥል የረዳኝ።" ሹራ በበርካታ የስፖርቱ አድናቂዎች ዘንድ የሚታወቅ ስም አይደለም። ነገር ግን በለንደን ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል፣ በ2018 ደግሞ በኒውዮርክ ሁለት ሰዓት ከአራት ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በመግባት የራሱን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል። በዙሪያው ያሉ አትሌቶች የ24 ዓመቱን ሹራ ዝምተኛ ግን በራስ መተማመን ያለው ሲሉ ይገልፁታል። የሹራ ወኪል ሁሴን ማኬ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ፤ " በጣም መልካም፣ የሚፈልገውን የሚያውቅ፣ ቤተሰቡን የሚያስቀድም ሰው ነው። እናም የእርሱ ምርጥ ነገሩ በራስ መተማመኑ ነው" ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። "በለንደን በራሱ በብርቱ ተማምኖ ነበር፤ እናም ወደ ውድድር ሲገባ ውድድሩ ውስጥ ስላሉት አትሌቶች ግድ አልሰጠውም፤ ያም አሁን ላገኘው ሻምፒዮናነት ረድቶታል። ተስፋ አደርጋለሁ በዚሁ ይቀጥላል።" ሹራ አትሌቲክስን የተዋወቀው በትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ኋላም እኤአ ከ2015 ጀምሮ አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ በአዲስ አበባ እያሰለጠኑት ይገኛሉ። "በጣም ደፋር አትሌት ነው፤ እናም ሁልጊዜ አቅሙን እስከቻለ ድረስ ይጠቀማል" ይላሉ አሰልጣኙ። አሰልጣኝ ሃጂ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ ቀናት ሲቀራቸው የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው በምርመራ በመረጋገጡ ድሉን በአካል ተገኝተው ለማጣጣም አልታደሉም። ቢቢሲ ሹራን እንዴት ማሰልጠን እንደጀመሩ ሲጠይቃቸው "ሹራ ከመጣበት አካባቢ የሆነ ሰው ከኔ ጋር አብሮ ይሮጥ ነበር። እናም እኔ ወዳለሁበት ካምፕ አምጥቶት እስቲ እየው አለኝ። ሞከርነው፤ ጥሩ ነበር ግን ፅናቱንና ፍጥነቱን ማሻሻል ነበረበት" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ። "በሶስት ወር ውስጥ፣ በጣም በርካታ ነገር አሻሻለ፤ እናም የመጀመሪያውን ማራቶን እንዲካፈል ወደ ሻንጋይ ላክነው።" ሹራ የተገኘው ሰባት ልጆች ካሏቸው ገበሬ ቤተሰቦች ነው። "ትምህርት በጣም እወድ ነበር፤ ዶክተር አልያም ፓይለት ነበር መሆን የምፈልገው። ነገር ግን ከድሃ ቤተሰብ ስለሆነ የተገኘሁት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ትምህርቴን ማቋረጥ ነበረብኝ" በማለት ልጅነቱን ያስታውሳል። "አንድ ቀን ዝነኛ እሆናለሁ፤ አለምን እዞራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለ እርሱ እና ስለድሉ በትዊተር ሰሌዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ መጻፋቸውን በመግለጽ፤ "አስቤ የማላውቀውን ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት" ይላል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ሹራ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ለሁለት አስርታት ያጣችውን ድል መመለስ ይፈልጋል። "ለአገሬ እና ለልጆቼ ጥሩ ትዝታ እንዲሆን የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት እፈልጋለሁ። ከዚያም 'አባታችን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አሸናፊ ነው' ይላሉ።" | ለንደን ማራቶን፡ አትሌት ሹራ ቂጣታ ከኬንያዊው ኪፕቾጌ የማራቶን ድል እንዲነጥቅ የረዳው ምንድን ነው? ኤሉድ ኪፕቾጌን ለማሸነፍ እንዴት ያለ ወኔ ይበቃ ይሆን? ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የሮጠውን ብርቱ አትሌት ለማሸነፍ ምን ሲደረግ ይቻላል? ጥብቅ ልምምድ ወይስ ተሰጥኦ? ለለንደን ማራቶን አሸናፊው ሹራ ቂጣታ ግን ጥሩ ቁርስ በቂ ነው። ባለፈው ዓመት በዩኬ ዋና ከተማ አራተኛ በመሆን ነው ያጠናቀቀው። ያኔ ኬኒያዊው ኪፕቾጌ ነው ያሸነፈው። በወቅቱ ሹራ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ባዶ ሆዱን መሮጡን፣ ለቁርስ ፍራፍሬ ብቻ መመገቡን ገልጾ ነበር። ሹራ በወቅቱ 35 ኪሎ ሜትሮች ከሮጠ በኋላ የተሰማውን ሲያሰፍር "ሆዴ ከጀርባዬ ጋር የተጣበቀ መስሎኝ ነበር፤ ሞርሙሮኝ ነበር" ብሏል። በዚህ ዓመት ከስህተቱ የተማረው ሹራ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ጥሩ ምግብ ወሳስዷል። ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ " ሁሉንም ነገር ተመግቤያለሁ" ብሏል። "ሾርባ፣ ዳቦ፣ እንቁላል እና እርጎ ወስጃለሁ፤ አቅም የሚሆነኝንና ውድድሩን በጥሩ ጉልበት መፎካከር የሚያስችለኝን ሁሉ ወስጃለሁ።" ውድድሩ ደግሞ ከ2014 ጀምሮ በማራቶኑ መስክ አልበገር ያለውን ኬንያዊ ማንበርከክን ያካተተ ነበር። ኪፕቾጌ የዋዛ አትሌት አይደለም። በኦሎምፒክ መንደር ስሙ በደማቅ ተጽፏል። የዓለም ክብረ ወሰን በእጁ ነው። የ35 ዓመቱ ኪፕቾጌ በለንደን ለአምስተኛ ጊዜ ድልን ለመቀዳጀት ጉልበቱን አበርትቶ ሞራሉን አደርጅቶ ነው የተገኘው። የዓለም መገናኛ ብዙኃንም ስሙን ደጋግመው ያነሳሉ። ምስሉን ደጋግመው ያሳያሉ። ጋዜጦች የፊት ገጻቸው ላይ አትመውታል። ለንደን ለኪፕቾጌ፣ ኪፕቾጌም ለለንደን መሃላ ያላቸው ይመስላል። ኪፕቾጌና ለንደን ግን ያላቸው ቃል ኪዳን ፈረሰ። መፍረስ ብቻ ሳይሆን ስምንተኛ ወጣ። ከፊት የፈለጉት ከኋላ አገኙት። በኋላም ጆሮውን አሞት እንደነበር አስረዳ። ለረዥም ርቀት ሩጫ እርጥበታማ አየርና ቅዝቃዜ ምቹ አይደለም። ሹራ የገባበት ሰዓትም፣ ሁለት ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ41 ሰከንድ የሚያሳየው ይህንኑ ነው። ሹራ ግን እንደውም አየሩ ረድቶኛል ሲል ያምናል። እኤአ ከ2013 ወዲህ የለንደን ማራቶንን ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ሹራ "ሲዘንብ በጣም ደስ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በከባድ ዝናብ ውስጥ ነው ልምምድ ስሰራ የነበረው" ይላል። "አንድ ቀን ሶደሬ ለልምምድ ሄድኩኝ፣ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ከተማው በጎርፍ ተጥለቅልቋል። አሰልጣኜ እኔን ለማዳን መምጣት ሁሉ ነበረበት" ሲል የነበረውን የልምምድ ሁኔታም ያስታውሳል። "የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲከሰት፣ ቤት አልተቀመጥኩም። ለአምስት ወራት ያህል ከአሰልጣኜ ጋር ልምምድ ስሰራ ነበር። ይህን ድል ኪፕቾጌን ማሸነፌ ልዩ አያደርገውም፤ ጠንክሬ መስራቴ ነው ልዩ የሚያደርገው።" ቀነኒሳ በቀለ ባጋጠመው ጉዳት የተነሳ ከውድድሩ መውጣቱን ካሳወቀ በኋላ በኪፕቾጌና በቀነኒሳ መካከል ይኖራል ተብሎ የታሰበው ፍልሚያ ሳይሳካ ቀረ። ስለዚህ ማንም የቀነኒሳን አገር ልጅ፣ ሹራን ከኪፕቾጌ ጋር አነጻጽሮ ለማወዳደርና የዜና ፍጆታ ለማድረግ ፍላጎት አላሳየም። ሹራም ቢሆን "ሁሉም ትኩረቱ የነበረው ኪፕቾጌ እና ቀነኒሳ ላይ ነበር፤ እኔን ዞርም ብሎ ያየኝ አልነበረም" ሲል ይገልጻል። "ለራሴ ለዓለም ሌላ ሻምፒዮን መኖሩን አሳያለሁ ብዬ ነገርኩት፤ እናም ይህ ስሜት ነው እስከመጨረሻው ድረስ በራስ መተማመንና በሙሉ አቅም እንድቀጥል የረዳኝ።" ሹራ በበርካታ የስፖርቱ አድናቂዎች ዘንድ የሚታወቅ ስም አይደለም። ነገር ግን በለንደን ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል፣ በ2018 ደግሞ በኒውዮርክ ሁለት ሰዓት ከአራት ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በመግባት የራሱን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል። በዙሪያው ያሉ አትሌቶች የ24 ዓመቱን ሹራ ዝምተኛ ግን በራስ መተማመን ያለው ሲሉ ይገልፁታል። የሹራ ወኪል ሁሴን ማኬ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ፤ " በጣም መልካም፣ የሚፈልገውን የሚያውቅ፣ ቤተሰቡን የሚያስቀድም ሰው ነው። እናም የእርሱ ምርጥ ነገሩ በራስ መተማመኑ ነው" ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። "በለንደን በራሱ በብርቱ ተማምኖ ነበር፤ እናም ወደ ውድድር ሲገባ ውድድሩ ውስጥ ስላሉት አትሌቶች ግድ አልሰጠውም፤ ያም አሁን ላገኘው ሻምፒዮናነት ረድቶታል። ተስፋ አደርጋለሁ በዚሁ ይቀጥላል።" ሹራ አትሌቲክስን የተዋወቀው በትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ኋላም እኤአ ከ2015 ጀምሮ አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ በአዲስ አበባ እያሰለጠኑት ይገኛሉ። "በጣም ደፋር አትሌት ነው፤ እናም ሁልጊዜ አቅሙን እስከቻለ ድረስ ይጠቀማል" ይላሉ አሰልጣኙ። አሰልጣኝ ሃጂ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ ቀናት ሲቀራቸው የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው በምርመራ በመረጋገጡ ድሉን በአካል ተገኝተው ለማጣጣም አልታደሉም። ቢቢሲ ሹራን እንዴት ማሰልጠን እንደጀመሩ ሲጠይቃቸው "ሹራ ከመጣበት አካባቢ የሆነ ሰው ከኔ ጋር አብሮ ይሮጥ ነበር። እናም እኔ ወዳለሁበት ካምፕ አምጥቶት እስቲ እየው አለኝ። ሞከርነው፤ ጥሩ ነበር ግን ፅናቱንና ፍጥነቱን ማሻሻል ነበረበት" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ። "በሶስት ወር ውስጥ፣ በጣም በርካታ ነገር አሻሻለ፤ እናም የመጀመሪያውን ማራቶን እንዲካፈል ወደ ሻንጋይ ላክነው።" ሹራ የተገኘው ሰባት ልጆች ካሏቸው ገበሬ ቤተሰቦች ነው። "ትምህርት በጣም እወድ ነበር፤ ዶክተር አልያም ፓይለት ነበር መሆን የምፈልገው። ነገር ግን ከድሃ ቤተሰብ ስለሆነ የተገኘሁት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ትምህርቴን ማቋረጥ ነበረብኝ" በማለት ልጅነቱን ያስታውሳል። "አንድ ቀን ዝነኛ እሆናለሁ፤ አለምን እዞራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለ እርሱ እና ስለድሉ በትዊተር ሰሌዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ መጻፋቸውን በመግለጽ፤ "አስቤ የማላውቀውን ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት" ይላል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ሹራ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ለሁለት አስርታት ያጣችውን ድል መመለስ ይፈልጋል። "ለአገሬ እና ለልጆቼ ጥሩ ትዝታ እንዲሆን የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት እፈልጋለሁ። ከዚያም 'አባታችን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አሸናፊ ነው' ይላሉ።" | https://www.bbc.com/amharic/54546131 |
0business
| የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለምን ተስተጓጎለ? | በመላው ሃገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎችና በትልቅነቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ተስተጓጉሎ የነበረውን አገልግሎት አስተካክሎ መደበኛ አገልግሎቱን መስጠት እንደጀመረ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የአብሥራ ከበደ ለቢቢሲ ገለፁ። • በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ • የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ? ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ተገልጋዮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ22 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችና ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፈው ሳምንት አርብ ጀምሮ ሲስተሙ የመዘግየት ችግር እንዳጋጠመውና ሙሉ በሙሉ ተስተጓጉሎ እንደነበር አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ባሳለፍነው እሁድ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሶ የኤትኤም ማሽኖች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። ይኽው አገልግሎት እንደገና ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በድጋሚ መስተጓጎል ገጥሞት የነበረ ቢሆንም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። "በአጠቃላይ ለአንድ ቀን ተኩል ያህል ነበር አገልግሎቱ የተቋረጠው" የሚሉት ኃላፊው አገልግሎቱ ከተስተካከለ በኋላ በየቅርንጫፎቹ የደንበኞች ቁጥር ጨምሮ ነበር ይላሉ። ስለ ሲስተሙ መጨናነቅ የተጠየቁት አቶ የአብሥራ "እንዲህ ነው ተብሎ የሚገለፅ ነገር የለም፤ ግን ቴክኖሎጂ በባህሪው ድንገት የሚፈጠሩ ችግሮችን ያስተናግዳል" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የሲስተም መጨናነቅ በባንኩ ውስጥ አሊያም በውጭ በሚፈጠሩ የኢንተርኔትና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሊፈጠር እንደሚችል የሚያስረዱት ኃላፊው፤ አሁን ያጋጠመው ችግር ግን በራሱ በባንኩ ሲስተም መጨናነቅ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ባንኩ ለሚመጡት 10 ዓመታት የሚያገለግል ዘመናዊ የመረጃ ቋት ያለው ቢሆንም ያጋጠመው እክል አንዳንድ ጊዜ በቴክኖሎጂ ላይ በሚፈጠሩ ጊዜያዊ ችግሮች ነው። በነበረው መስተጓጎል የደረሰውን ኪሳራ አስመልክተን ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ የአብሥራ "ባንኩ የደንበኞች አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ነበር እንጂ፤ ባጋጠመው መስተጓል ያጋጠመው ኪሳራ ስሌት ውስጥ አልገባም"ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የደንበኞች ቁጥር በጨመረ ቁጥርም እንዲህ ዓይነት መጨናነቆች እንዳይከሰቱ ባንኩ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ፣ የኢንተርኔት፣ ሲቢኢ ብር፣ በካርድ አገልግሎት ክፍያ መፈፀሚያ ማቅረቡን በመግለፅ ደንበኞች ሳይንገላቱና ሳይደክሙ አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁመዋል። እንደ አማራጭ የቀረቡት መንገዶች ከኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነትና ፍጥነት በርካቶች የሚማረሩበት ነው። እንዲያም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱ ጉዳዩን የከፋ ያደርገዋል። በመሆኑም እነዚህ ንግድ ባንክ ያስቀመጣቸው አማራጭ አገልግሎቶች የበለጠ ጫናው ላይ አይወድቁም ወይ? ስንል ለኃላፊው ጥያቄ አንስተን ነበር። ኃላፊውም ችግሮች መኖራቸውን አምነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት ሃገሪቱ ውስጥ ያለውን እንዲሁም የራሱንም መሠረተ ልማት አጣምሮ እንደሚጠቀም ገልፀዋል። በዚህ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ደንበኞች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል። "እስካሁን ከ5 ሚሊዮን በላይ የኤትኤም ካርድ ተጠቃሚዎች እና ከ2 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎች አሉ" የሚሉት ኃላፊው በኢትዮጵያ ካለው የሕዝብ ብዛት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ በአገሪቱ የሚፈጠሩ ክፍተቶቹን ባንኩ እየሞላ አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመው መስተጓጎል ተፈታ ካለ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ተጠቃሚዎችና የባንኩ ሠራተኞችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ባደረግነው ሙከራ የነበረው ችግር መፈታቱን የገለጹ ሲሆን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሲስተም ዘገምተኛ መሆን እንዳለ ገልጸዋል። ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊው እንደነገሩን... • ከ22 ሚሊየን በላይ ደንበኞች አሉት • የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 542 ቢሊየን ብር ደርሷል • አጠቃላይ ሃብቱ ከ660 ቢሊየን ብር በላይ ነው • ከ5 ሚሊየን በላይ የኤ ቲ ኤም ካርድ ተጠቃሚዎች አሉት • ከ2 ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን ያስተናግዳል • 38 ሺህ ሠራተኞች አሉት • ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት • የደበኞች ቁጥር በየዓመቱ በ2 እና 3ሚሊየን ብልጫ ያሳያል። | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለምን ተስተጓጎለ? በመላው ሃገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎችና በትልቅነቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ተስተጓጉሎ የነበረውን አገልግሎት አስተካክሎ መደበኛ አገልግሎቱን መስጠት እንደጀመረ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የአብሥራ ከበደ ለቢቢሲ ገለፁ። • በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ • የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ? ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ተገልጋዮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ22 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችና ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፈው ሳምንት አርብ ጀምሮ ሲስተሙ የመዘግየት ችግር እንዳጋጠመውና ሙሉ በሙሉ ተስተጓጉሎ እንደነበር አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ባሳለፍነው እሁድ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሶ የኤትኤም ማሽኖች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። ይኽው አገልግሎት እንደገና ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በድጋሚ መስተጓጎል ገጥሞት የነበረ ቢሆንም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። "በአጠቃላይ ለአንድ ቀን ተኩል ያህል ነበር አገልግሎቱ የተቋረጠው" የሚሉት ኃላፊው አገልግሎቱ ከተስተካከለ በኋላ በየቅርንጫፎቹ የደንበኞች ቁጥር ጨምሮ ነበር ይላሉ። ስለ ሲስተሙ መጨናነቅ የተጠየቁት አቶ የአብሥራ "እንዲህ ነው ተብሎ የሚገለፅ ነገር የለም፤ ግን ቴክኖሎጂ በባህሪው ድንገት የሚፈጠሩ ችግሮችን ያስተናግዳል" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የሲስተም መጨናነቅ በባንኩ ውስጥ አሊያም በውጭ በሚፈጠሩ የኢንተርኔትና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሊፈጠር እንደሚችል የሚያስረዱት ኃላፊው፤ አሁን ያጋጠመው ችግር ግን በራሱ በባንኩ ሲስተም መጨናነቅ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ባንኩ ለሚመጡት 10 ዓመታት የሚያገለግል ዘመናዊ የመረጃ ቋት ያለው ቢሆንም ያጋጠመው እክል አንዳንድ ጊዜ በቴክኖሎጂ ላይ በሚፈጠሩ ጊዜያዊ ችግሮች ነው። በነበረው መስተጓጎል የደረሰውን ኪሳራ አስመልክተን ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ የአብሥራ "ባንኩ የደንበኞች አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ነበር እንጂ፤ ባጋጠመው መስተጓል ያጋጠመው ኪሳራ ስሌት ውስጥ አልገባም"ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የደንበኞች ቁጥር በጨመረ ቁጥርም እንዲህ ዓይነት መጨናነቆች እንዳይከሰቱ ባንኩ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ፣ የኢንተርኔት፣ ሲቢኢ ብር፣ በካርድ አገልግሎት ክፍያ መፈፀሚያ ማቅረቡን በመግለፅ ደንበኞች ሳይንገላቱና ሳይደክሙ አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁመዋል። እንደ አማራጭ የቀረቡት መንገዶች ከኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነትና ፍጥነት በርካቶች የሚማረሩበት ነው። እንዲያም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱ ጉዳዩን የከፋ ያደርገዋል። በመሆኑም እነዚህ ንግድ ባንክ ያስቀመጣቸው አማራጭ አገልግሎቶች የበለጠ ጫናው ላይ አይወድቁም ወይ? ስንል ለኃላፊው ጥያቄ አንስተን ነበር። ኃላፊውም ችግሮች መኖራቸውን አምነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት ሃገሪቱ ውስጥ ያለውን እንዲሁም የራሱንም መሠረተ ልማት አጣምሮ እንደሚጠቀም ገልፀዋል። በዚህ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ደንበኞች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል። "እስካሁን ከ5 ሚሊዮን በላይ የኤትኤም ካርድ ተጠቃሚዎች እና ከ2 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎች አሉ" የሚሉት ኃላፊው በኢትዮጵያ ካለው የሕዝብ ብዛት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ በአገሪቱ የሚፈጠሩ ክፍተቶቹን ባንኩ እየሞላ አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመው መስተጓጎል ተፈታ ካለ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ተጠቃሚዎችና የባንኩ ሠራተኞችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ባደረግነው ሙከራ የነበረው ችግር መፈታቱን የገለጹ ሲሆን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሲስተም ዘገምተኛ መሆን እንዳለ ገልጸዋል። ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊው እንደነገሩን... • ከ22 ሚሊየን በላይ ደንበኞች አሉት • የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 542 ቢሊየን ብር ደርሷል • አጠቃላይ ሃብቱ ከ660 ቢሊየን ብር በላይ ነው • ከ5 ሚሊየን በላይ የኤ ቲ ኤም ካርድ ተጠቃሚዎች አሉት • ከ2 ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን ያስተናግዳል • 38 ሺህ ሠራተኞች አሉት • ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት • የደበኞች ቁጥር በየዓመቱ በ2 እና 3ሚሊየን ብልጫ ያሳያል። | https://www.bbc.com/amharic/news-49260745 |
3politics
| የአውሮፓ ሕብረት የአውሮፕላን እስርን ተከትሎ በቤላሩስ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ | የአውሮፓ ሕብረት የቤላሩስ አየር መንገድ በአውሮፓ ሰማይ ላይ እንዳይበር ለማድረግ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ። ሕብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው እሁድ ዕለት በበረራ ላይ የነበረ አውሮፕላን አንድ ጋዜጠኛን ለመያዝ ሲል አቅጣጫውን እንዲለውጥ ተገዶ ሚንስክ እንዲያርፍ መደረጉን ተከትሎ ነው። በብራስልስ በተካሄደው ስብሰባ የ27ቱ አባል አገራት መሪዎች የአውሮፓ ሕብረት አየር መንገዶችም በቤላሩስ ሰማይ ላይ ድርሽ እንዳይሉ ተናግረዋል። ሕብረቱ ሌሎች ተጨማሪ ምጣኔ ሃብታዊ ማዕቀቦችን እንደሚጥልም አስታውቋል። የ26 ዓመቱ ሮማን ፕሮታሴቪች ከግሪክ ወደ ሊቱያኒያ እየበረረ ሳለ ነበር አውሮፕላኑ ውስጥ ቦምብ ሊኖር ይችላል በሚል አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ለውጦ ሚንስክ እንዲያርፍ የተገደደው። ይህንን ተከትሎ ምዕራባውያን አገራት ቤላሩስን በራየንኤር አውሮፕላን ጠለፋ ከሰዋል። አሁን ላይ የወጣ ተንቀሳቃሽ ምሥል ጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች በምንስክ አየር ማረፊያ ከተያዘበት ጊዜ አንስቶ ያለ ፈቃዱና ጫና ተደርጎበት ምሥሉ መቀረጹን ያሳያል። ሰኞ ዕለት በወጣው በዚሁ ተንቀሳቃሽ ምሥል ጋዜጠኛው በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና በቤላሩስ ግዛት የተከሰሰበትን ወንጀል እንደሠራ ተናዟል። ይሁን እንጅ የአገሪቷን ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪን ጨምሮ የመብት ተሟጋቾች ጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች ስህተቱን እንዲያምን ጫና ተደርጎበታል ሲሉ ተንቀሳቃሽ ምሥሉን ተችተዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የቤላሩስ ባለሥልጣናት ድርጊት "አስደንጋጭ ነው፤ በፖለቲካ ልዩነት እና በፕሬስ ነጻነት ላይ የተፈጸመ አሳፋሪ ጥቃት ነው" ብለዋል። የጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች አባት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ልጃቸው ድብደባ ሊፈጸምበት እንደሚችል ሰግተዋል። አባት ድሚትሪ ፕሮታሴቪች ሰኞ ዕለት ለቢቢሲ ሲናገሩ ልጃቸው "በገዛ አገሩ ባለሥልጠናት እንዴት እንደሚያዝ በጣም ተጨንቄያለሁ" ብለዋል። "እንደሚወጣው ተስፋ እናደርጋለን። ሁኔታው ለማሰብም ያስፈራል። ድብደባ እና እንግልት ሊደርስበት ይችላል። በጣም ነው የሰጋነው" ሲሉ ተናግረዋል። ድሚትሪ አክለውም " በጣም ደንግጠናል ፤ ተበሳጭተናልም። እንዲህ ዓይነት ነገር በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያውም በአውሮፓ እምብርት ላይ መፈፀም አይገባውም ነበር" ብለዋል። የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ ሁሉም የዓለም ማሕበረሰብ በባለሥልጣናቱ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጫና እንደሚያሳድር ተስፋ አለን ብለዋል ዲሚትሪ። ጫናውም እንደሚሰራና ባለሥልጣናቱ የሰሩት ተግባር ትልቅ ስህተት እንደሆነ እንደሚገነዘቡም ተስፋ እንደሚያደርጉ አባት ዲሚትሪ ገልጸዋል። ጋዜጠኛው ማነው? የ26 ዓመቱ ጋዜጠኛ ከቤላሩስ የወጣው እአአ በ2019 ነው። ኔክስታ ለተባለው መገናኛ ብዙኃን የቤላሩስም የ2020 ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ዘግቧል። ኔክስታ በዋነኛነት በቴሌግራም የሚሠራጭ መገናኛ ብዙኃን ሲሆን፤ በትዊተር እና በዩቲዩብ ላይም ይገኛል። በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላም የቤላሩስን የተቃውሞ ድምጽ በማሰማት ከፍተኛ ሚና አለው። ጋዜኛው ከምርጫ ዘገባው በኋላ ቤላሩስ ከሳዋለች። ቤላሩስ ውስጥ በሽብርተኝነት ስለተፈረጀ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተቃዋሚዋ ስቪትና ቲካንቫክያ ተናግረዋል። ተቃዋሚዋ በምርጫው ማሸነፋቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ግን ከቤላሩስ መንግሥት ሸሽተው ሊቱዋንያ ለመሸሸግ ተገደዋል። | የአውሮፓ ሕብረት የአውሮፕላን እስርን ተከትሎ በቤላሩስ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ የአውሮፓ ሕብረት የቤላሩስ አየር መንገድ በአውሮፓ ሰማይ ላይ እንዳይበር ለማድረግ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ። ሕብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው እሁድ ዕለት በበረራ ላይ የነበረ አውሮፕላን አንድ ጋዜጠኛን ለመያዝ ሲል አቅጣጫውን እንዲለውጥ ተገዶ ሚንስክ እንዲያርፍ መደረጉን ተከትሎ ነው። በብራስልስ በተካሄደው ስብሰባ የ27ቱ አባል አገራት መሪዎች የአውሮፓ ሕብረት አየር መንገዶችም በቤላሩስ ሰማይ ላይ ድርሽ እንዳይሉ ተናግረዋል። ሕብረቱ ሌሎች ተጨማሪ ምጣኔ ሃብታዊ ማዕቀቦችን እንደሚጥልም አስታውቋል። የ26 ዓመቱ ሮማን ፕሮታሴቪች ከግሪክ ወደ ሊቱያኒያ እየበረረ ሳለ ነበር አውሮፕላኑ ውስጥ ቦምብ ሊኖር ይችላል በሚል አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ለውጦ ሚንስክ እንዲያርፍ የተገደደው። ይህንን ተከትሎ ምዕራባውያን አገራት ቤላሩስን በራየንኤር አውሮፕላን ጠለፋ ከሰዋል። አሁን ላይ የወጣ ተንቀሳቃሽ ምሥል ጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች በምንስክ አየር ማረፊያ ከተያዘበት ጊዜ አንስቶ ያለ ፈቃዱና ጫና ተደርጎበት ምሥሉ መቀረጹን ያሳያል። ሰኞ ዕለት በወጣው በዚሁ ተንቀሳቃሽ ምሥል ጋዜጠኛው በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና በቤላሩስ ግዛት የተከሰሰበትን ወንጀል እንደሠራ ተናዟል። ይሁን እንጅ የአገሪቷን ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪን ጨምሮ የመብት ተሟጋቾች ጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች ስህተቱን እንዲያምን ጫና ተደርጎበታል ሲሉ ተንቀሳቃሽ ምሥሉን ተችተዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የቤላሩስ ባለሥልጣናት ድርጊት "አስደንጋጭ ነው፤ በፖለቲካ ልዩነት እና በፕሬስ ነጻነት ላይ የተፈጸመ አሳፋሪ ጥቃት ነው" ብለዋል። የጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች አባት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ልጃቸው ድብደባ ሊፈጸምበት እንደሚችል ሰግተዋል። አባት ድሚትሪ ፕሮታሴቪች ሰኞ ዕለት ለቢቢሲ ሲናገሩ ልጃቸው "በገዛ አገሩ ባለሥልጠናት እንዴት እንደሚያዝ በጣም ተጨንቄያለሁ" ብለዋል። "እንደሚወጣው ተስፋ እናደርጋለን። ሁኔታው ለማሰብም ያስፈራል። ድብደባ እና እንግልት ሊደርስበት ይችላል። በጣም ነው የሰጋነው" ሲሉ ተናግረዋል። ድሚትሪ አክለውም " በጣም ደንግጠናል ፤ ተበሳጭተናልም። እንዲህ ዓይነት ነገር በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያውም በአውሮፓ እምብርት ላይ መፈፀም አይገባውም ነበር" ብለዋል። የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ ሁሉም የዓለም ማሕበረሰብ በባለሥልጣናቱ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጫና እንደሚያሳድር ተስፋ አለን ብለዋል ዲሚትሪ። ጫናውም እንደሚሰራና ባለሥልጣናቱ የሰሩት ተግባር ትልቅ ስህተት እንደሆነ እንደሚገነዘቡም ተስፋ እንደሚያደርጉ አባት ዲሚትሪ ገልጸዋል። ጋዜጠኛው ማነው? የ26 ዓመቱ ጋዜጠኛ ከቤላሩስ የወጣው እአአ በ2019 ነው። ኔክስታ ለተባለው መገናኛ ብዙኃን የቤላሩስም የ2020 ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ዘግቧል። ኔክስታ በዋነኛነት በቴሌግራም የሚሠራጭ መገናኛ ብዙኃን ሲሆን፤ በትዊተር እና በዩቲዩብ ላይም ይገኛል። በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላም የቤላሩስን የተቃውሞ ድምጽ በማሰማት ከፍተኛ ሚና አለው። ጋዜኛው ከምርጫ ዘገባው በኋላ ቤላሩስ ከሳዋለች። ቤላሩስ ውስጥ በሽብርተኝነት ስለተፈረጀ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተቃዋሚዋ ስቪትና ቲካንቫክያ ተናግረዋል። ተቃዋሚዋ በምርጫው ማሸነፋቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ግን ከቤላሩስ መንግሥት ሸሽተው ሊቱዋንያ ለመሸሸግ ተገደዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57230080 |
2health
| ኢትዮጵያ፡ ‘የማይናገሩት’ እና ‘የማይነገርለት’ የተንሰራፋው የወጣቶች ጭንቀት | በብዙ ምክንያቶች ማንነቷ እንዲታወቅ አትፈልግም። እኛም እንዳትታወቅ በሚል ‘ቅድስት’ በሚል ስም እንጠራታለን። ቅድስት ዘንድሮ ነው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናዋን የወሰደችው። ከቢቢሲ ጋር ዛሬ ያገናኛት ጉዳይ ግን የተከሰተው ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ገና አስረኛ ክፍል እያለች። “አንድ እኛ ትምህርት ቤት ከሚማር ልጅ ጋር የዐይን ፍቅር ይዞኝ ነበር” ስትል ትጀምራለች። አፍላ ፍቅር። በጓደኞቿ ግፊት ፈራ ተባ እያለች ‘የልቤን’ ያለችውን ነገረችው። ምላሹ ግን የልቧን አላደረሰውም። አዘነች። ተከፋች። የማዘን እና የመከፋቱ ጉዳይ መልከ ብዙ ነው። “አንዳንዴ ለምን ለጓደኞቼ ነገርኳቸው? እላለሁ” ትላለች። ጓደኞቿ እሷን ሲያዩ ርዕሰ ጉዳይ የሚሆነው የእሷ ‘የፍቅር ጥያቄ’ ሆኗል። ጓደኞቿ እሱን ሲያዩም ርዕስ የሚሆነው አሁንም የእሷ ‘የፍቅር ጥያቄ’ ነው። ጭንቀቱ ትምህርት ቤት ተወልዶ ቤት ድረስ ዘለቀ። “ቤተሰቦቼ ስለጉዳዩ አያውቁም” ትላለች። ቤተሰቦቿ የማያውቁትን ጉዳይ ግን የቤተሰቡ አባል አደረገችው። ስታጠናም አልጋ ላይ ተጋድማም ስለ ‘ትምህርት ቤቱ ልጅ’ ብቻ ሆነ ሃሳቧ። እንዳሁኑ አይሁን እንጂ ሌላም ሃሳብ ነበረባት። በትምህርቷ ጥሩ የምትባል ናት። ቤተሰቦቿም ለትልቅ ደረጃ የሚጠብቋት። በትምህርት ጥሩ ራመድ ካለ ቤተሰብም ነው የተገኘችው። በተለይ አባት ዲግሪውን አንድ ሁለት ሦስት እያሉ ደራርበውታል። ለዚህም ነው አባት የእኔን መንገድ ትከተላለች ብለው የሚኮሩባት ጭምር የሆነችው። ይህ በቀጥታም ሆነ በዘወርዋራ ትምህርትሽ ላይ አተኩሪ የሚል ግፊ ነበረው። ለእሷ ግን ሌላ የምታብሰለስለው ሌላ ምትጨነቅበት ጉዳይ ሆነባት። የምትወደውን ልጅ ማጣቷን እና ቤተሰቦቿ በሚፈልጓት ደረጃ አለመራመዷ ያስጨንቋት ገቡ። ቤትም ትምህርት ቤትም የሚያሳስቧት ነገሮች ሆኑ። ከቤት ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት ደግሞ ቤት ለምትለው ቅድስት ሌላ ማምለጫ መንገድ ጠፋ። “ሌላ ሰው የሆንኩ ያህል ተሰማኝ። የሚያስደስተኝ ነገር አጣሁ። እንቅልፍ በዓይኔ አልዞር አለ። ሌላ ሰው ሆንኩኝ” ትላለች። በዚህ ጊዜ ትንሽ እረፍት የሚሰጣት ‘የእኔ’ ከምትላቸው ጓደኞቿ ጋር መሆን ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም አይሳካም። እሷ ብዙም እንድትወጣ አይፈቀድላትም። ጓደኞቿ ቤታቸው ሲሄዱ ደግሞ የልባቸውን ለማውራት አይመቻቸውም። በዚህ ውጣ ውረድ ሳምንታት ከነፉ። ቤተሰቦቿ ሳይሰሙ መፍትሔ ያመጡልኛል ያለቻቸውን መንገዶች አማተረች። መፍትሔ የለም። መጽሐፍትን አነበበች። መፍትሔ የለም። ዩቲዩብ ላይ ተጣደች። አሁንም መፍትሔ የለም። * * * የመጨረሻው መፍትሔ ወደ ህክምና ማዕከል ለመሄድ ሆነ። ይህም ግን ቀላል ውሳኔ አልነበረም። ለቤተሰብ ሳይናገሩ ህክምና መሄድ ከባድ ነው። ብዙ መዘዞችም አሉት። ብዙ ጥያቄ ያስከትላል። እሷ ደግሞ አንኳን ለብዙ ለአንድም ጥያቄ መልስ የላትም። ያለቤተሰብ ሐኪም ዘንድ መሄድ የድጋፍ ማጣት ስሜት ይፈጥራል። ለተማሪ ደግሞ ሌላ ፈተና አለው - ገንዘብ አለማግኘት። ‘ቁጥጥር ለሚበዛባት’ ቅድስት ከትምህርት ቤት ቀርቶ ሐኪም ዘንድ መሔድ በራሱ ከባድ ነበር። አውጥታ አውርዳ ግን አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰች። ለብቻዋ ወደ ህክምና መሔድ። “እኔም የሚሰጠኝን [የኪስ ገንዘብ] አጠራቅሜ ጓደኞቼም ሰጥተውኝ ሐኪም ቤት ሄድኩኝ” ትላለች። ሐኪሙ ጭንቀት እንዳለባት ነገራት። አሁን ወደ አቶ ብርሃኑ ራቦ እናቅና። አቶ ብርሃኑ የሞሽን የማማከር እና የሥልጠና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው። “በብዙ ፀሐፊዎች ወይም ፈላስፋዎች አረዳድ ውጥረት ወይም ጭንቀት ሰው አሁን ያለበት እና በመድረሻው መካከል ያለው ርቀት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ በሚፈጠር ተስፋ ማጣት የሚከሰት ነው ይላሉ” ሲሉ ይገልጻሉ። ቅድስት ስላሳለፈችበት የሕይወት መስመር ለአቶ ብርሃኑ ስናጫውታቸውም “ውጥረት ወይም ጭንቀት በተለይ ዕድሜያቸው 20 እና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ዘንድ እየጨመረ ነው። ቤተሰብ፣ መምህራን እና ማኅበረሰቡ ሳያውቁ ስር እየሰደደ እየተሰቃዩበት ነው። ማንም ስለማይረዳቸውም በራሳቸው መንገድ መፍትሔ ለመፈለግ ይጥራሉ” ብለዋል። ምክንያቱ ምን ይሆን ሲባሉ መልከ ብዙ መሆኑን ይጠቁማሉ ባለሙያው። አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ችግሮች ፍርሃት እንዲያድርባቸውና ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋቸዋል። “ጤና፣ ችግር፣ የሠላም እጦት ችግር አለ። የሰዎችን ሞት መስማት ኖርማል (የተለመደ) ሆኗል” የሚሉት አማካሪው አቶ ብርሃኑ፣ ስለዚህ ወጣቶች ተስፋ የማይታያቸው በጣም የሚጨነቁ እና ውጥረት ውስጥ የሚገቡ ሆነዋል ሲሉ ያስረዳሉ። ማን ከጎኔ አለ ሳይባል ስለዘረኝነት፣ ስለሃይማኖት. . . ጦርነት ይወራል። ወጣቶችን እና ህጻናትና ሳያማክል መኖራቸውን እንኳን ከግምት ሳይገባ ይወራል። ትርፉ ልጆችን መጉዳት ነው ሲሉ አቶ ብርሃኑ ያስረዳሉ። በተጨማሪ ደግሞ የቴክኖሎጂ በረከት የትዬ ለሌ ነው። ከህጻን እስከ አዋቂ መዳፍ ላይ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ . . . በቀላሉ የሚገኝበት ዘመን ነው። የሚታጨደው በረከት ግን መልካሙም ብቻ አይደለም። እንክርዳዱም ጥቂት አይደለም። አቶ ብርሃኑ ሩብ ክፍለ ዘመን በማማከር እና በማሠልጠን አሳልፈዋል። ዓመት ዓመትን ሲተካ በጭንቀት እና ድባቴ የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር መናሩን ይናገራሉ። ምክንያቱን ለማወቅ ደግሞ አነስተኛ ጥናት አከናውነዋል። “ዘመኑ ሰዎች የማይረኩበት። በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ ነገሮች የፈጣሪን ህላዌ ራሱ የሚጠራጠሩበት፤ ‘ፈጣሪ እያለ ለምን ይሔ ሆነ?’ የሚል ሊመልሷቸው የማይችሏቸው ጥያቄዎች ውስጥ የመግባት ዕድል አለ።” “ቤተሰብ፣ እናት እና አባት እያለኝ ለምን ይሔ ደረሰብኝ? ለምን ይሔ ሆነብኝ? መንግሥት እያለ ለምን ይሔ ሆነ?” እያሉ ከሚተማመኑበት ነገር እየራቁ ሲሄዱ መፍትሔ፣ ረዳት እና አቅም የማጣት ሁኔታ ይመጣል። “በተስፋ ከመሞላት ወደ ተስፋ መቁረጥ ይሄዳሉ።” መፍትሔ የሚሉት ደግሞ ከባህል፣ ከእምነት እና ከእሴት የወጡ ነገሮችን ማድረግ ነው። “በመቀጠል በራሳቸውም በሌላውም ላይ መጨከን ነው” ይላሉ። በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ ራሳቸውን እንደሚያጠፉ ተናግረው ራሳቸውን ያጠፉ መኖራቸውን አስታውሰው “ይህ አስደንጋጭ ነው” ሲሉ አቶ ብርሃኑ ያስረዳሉ። “ሞትን የመሰለ ከባድ ነገር በቀጠሮ ወስነህ ስታደርገው ውጥረታችን እና ጭንቀታችን በሰው፣ በምድር እና በሰማይ ተስፋ መቁረጣችን ምን ያህል እንደሆነ በትክክል ይገለጻል። ልጆችን ተሰናብቶ ወደ ሞት መሄድ ወደየት እየሄድን እንደሆነ ያሳያል” ሲሉ ያክላሉ። “እንደተከታታይ ፊልም በላያችን ላይ የሚመላለሰው ጦርነት፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳቱን እንጂ ሥነልቦናዊ አደጋው ታስቦ እየተሠራበት አይደለም” ይላሉ። ይህም ልጆች ተስፋ እንዲቆርጡ፣ ነገን እንዳያስቡ፣ እንዳያልሙ፣ የሰውነት ክብርን እና ሰብዓዊነትን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል በሚል ይገልጻሉ። “የሰብዓዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ በኢኮኖሚው ላይ ተደምሮ የምንይዘው የምንጨብጠው አጥተናል” በማለት የእለት ከዕለት ሕይወት ጫናም የእራሱ አሉታዊ ውጤት አለው ይላሉ። “የመኖር ትርጉም ሲያጣባቸው የማያውቁትን ዓለም መሞትን ወደ መምረጥ ይሄዳሉ” የሚሉት አቶ ብርሃኑ “ከዚህ አንጻር እንደባለሙያ የሚያሳስበን ትኩረት ማጣት ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ይህ ‘ጊዜ ቦንብ’ ነው የሚሉት አቶ ብርሃኑ ያውም ‘ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ’ ይላሉ። ቤተሰብ በሙሉ ቴክኖሎጂ ላይ ተጥዶ ሰው አፍ ለአፍ የማይነጋገርበት ሁኔታ እያደገ ነው። ሰው ችግሩን የሚነግረው ለሚሰማው ለሚያዳምጠው ነው። ወላጆች የራሳቸውን ችግር ለማለፍ ወይም ዓላማቸውን ለማሳካት እንጂ ልጆችን ለመስማት ጊዜ የላቸውም። “ወላጆች ልጆቻቸውን፣ መምህራን የተማሪዎቻቸው ችግር ከማዳመጥ የራሳቸውን ችግር ነው የሚያሰላስሉት። ‘እኔ ለመግባችሁ ስሯሯጥ’ በሚል የልጆቹን ችግር እንደምቾት እና ድሎት ነው የሚያዩት” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። ልጆቹ ችግራቸውን ያጠራቅሙና ከወላጆች። ከመመህራን እና ከማኅበረሰቡ ደብቀው በራሳቸው መንገድ ለመፍታት ይሞክራሉ። ያውም “ጥሩ ባልሆነ፣ በማይመከር እና ችግሩን በሚያባበስ መልኩ ለመፍታት ይሯሯጣሉ።” “ይህንን አድርገው ሲያቅታቸው ደግሞ ራሳቸውን ይጠላሉ፣ እንቅለፍ ያጣሉ። እያደረ ፍርሃት ውስጥ ይከታቸዋል። ሁሉም እያወቀበቸው መሆኑን ከፍተኛ እርምጃ ይወስዳሉ” ይላሉ። የቅድስት ወላጆች ልጃቸው ያላትን ለውጥ መከታተል ነበረባቸው። ለእሷም ከባድ ቢሆንም ችግሩን ለቤተሰቦቿ ማሳወቅ የተሻለ ቀላል ያደርግላት ነበር። “እነዲህ ዓይነት ነገር በብዛት ያጋጥማል። ከትንንሽ ልጆች ጀምሮ በማይታወቅ ድባቴ ውስጥ ያሉ አሉ” ይላሉ ባለሙያው። ስለ ቅድስት ያጫወትናቸው አቶ ብርሃኑ እሳቸውም በርካታ ተመሳሳይ ታሪክ እንደሚያውቁ ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱን አውግተውናል። “አንድ በጣም ጎበዝ ወጣት ነበር። በጥሩ ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ነው። ዩኒቨርሲቲ ሲገባ ችግሩን የሚሰማው ስለሌለ ይጨነቅ ጀመረ። ቤተሰቡ ለእሱ ያላቸው ግምት ትልቅ በመሆኑ፣ ትምህርቱን መከታታል አልቻለም። በኋላም ትምህርቱን አቋረጠ። ወላጆቹ ይህን ሁሉ አያውቁም።” ነጻ አገልግሎትም የሚሰጡት አቶ ብርሃኑ ተማሪው ቢሯቸው ሲደርስ ፊታቸውን አላዞሩበትም። “እና ተገቢውን ድጋፍ ሰጥተነው ወደ ትምህርቱ ተመልሶ ዓላማው እንዲያሳካ እገዛ አደረግንለት” ሲሉ ያስታውሳሉ። “ብዙ ወላጅ ልጆቼ ጥሩ ናቸው። ጎበዝ እና ሥነ ምግባር ያላቸው ናቸው ይላሉ እንጂ ብዙ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ድባቴ ውስጥ ነው ያሉት።” “በአገራችን ብዙ ነገር ተስፋ የሚያስቀርጥ ይሆንባቸዋል። ወላጆች ትልልቅ ርዕሶችን ቤት እና መኪና ውስጥ ያወራሉ። ቲቪው እና ስልካቸው የሚዘገንን መረጃ ይሰጣል። ልጆቹ ትምህርት ቤት ሌላ፣ ቤት ሌላ ናቸው። ጓደኞቻው ጋርም ሌላ ናቸው። በዚህ ምክንያትም የተለያየ ስብዕና ያዳብራሉ” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። ለአቶ ብርሃኑ እነዚህን ከፍተኛ ችግሮች በአነስተኛ ድርጅቶች ብቻ መፍታት ከባድ ነው። “ከቁስ እና ኢኮኖሚው በላይም በዘመቻ ከምንም በላይ መሠራት አለበት ብለን የምናምነው የሰው አዕምሮ ላይ ነው” ይላሉ። ይህ ሕብረተሰቡ እና መንግሥት ኃላፊነት ነው። ወጣቶች ደግሞ ሌላ ኃላፊነት አለባቸው። “ወጣቶች እውቀት ላይ ትኩረት ያድረጉ። አካላዊ እንቅስቃሴ አለባቸው። ከዲጂታል ይልቅ መጽሐፎችን በእጅ ይዞ እያገላበጡ ማንበብ። በተቻለ መጠንም ከቴክኖሎጂ ጋር የሚቆዩበትን ጊዜ መቀነስ አለባቸው” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። በተጨማሪም በቀን ስንት ሰዓት ማየት እንዳለባቸው መለየት እና ከቻሉ በሳምንት አንድ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ከቴክኖሎጂ ውጪ መሆን ያስፈልጋል። ከተፈጥሮ ጋር መገናኘት፣ ስፖርት መስራት፣ በበጎ አድራጎት መሳተፍ እና ህይወታቸውን በተቻለ መጠን መንፈሳዊ ማድረግ እንደሚያስፈለግ ባለሙያው አጥብቀው ይመክራሉ። “ዘመኑ ፈጣን ነው። ይህን ሊታደግ የሚችል ፈጣሪ እንዳላቸው በማየት ለሕይወታቸው ቅርጽ መስጠት። በሕይወት ክህሎት ሥልጠናዎች እንዲሳተፉ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለይ ደግሞ ወጣቶች የትምህርት፣ የሥራ እና ሌሎች መከወን ያለባቸው ነገሮች መብዛት ሳይሆን ለበርካቶች የጭንቀት ምንጭ የሚሆነው፣ እያንዳንዱን ሥራ በጊዜ አለመሥራት መሆኑን እንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህ ወላጆች እና ልጆች ያላቸውን ጊዜ እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው መልመድ ይገባል የሚሉት አቶ ብርሃኑ “የሰዓት አስተዳርን ከቤት ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።” ወደተነሳንበት ታሪክ እንመለስ። አሁን ቅድስት በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ህክምናዋን በደንብ ተከታትላለች። “ሐኪም ቤት ደርሼ የተመለስኩ ቀን ነው የሆነ ነገር የቀለለኝ” ስትል ታስታውሳለች። “ቤት የደረስኩት ፈገግ ብዬ ነበር። ከረዥም ጊዜ በኋለ ጥሩ እንቅልፍም ተኛሁኝ” ብላለች። ሕክምናውም ቢሆን ግን መዘዝ ነበረው። በተለይ ቤተሰብ ሳያውቅ መድኃኒት ደብቆ መዋጥ ፈተና ነው። አንዴ ወስና የገባችበት በመሆኑ ግን ተወጣችው። ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግባት በመዘጋጀት ላይ ትገኛለች። ቤተሰቦቿ እንደሚጠብቋት በትምህርቷ መግፋት ትፈልጋለች። ያውም አባቷ በሚፈልጉት የትምህርት ዘርፍ ነው መቀጠል የምትፈልገው። አባት እና ልጅ በአንድ የትምህርት መስክ ሊጓዙ ነው። አሁንም ግን ከስጋት ነጻ አይደለችም። ጉዳዩን ለቤተሰቦቿ አለመንገሯ ያሳስባታል። ቢያውቁስ የሚል ስጋት አለባት። ግን ከቀድሞው የተሻለ ጥንካሬ ስላላት ምንም ቢመጣ ከቤተሰቦቿ ጋር እንደምታልፈው ታምናለች። | ኢትዮጵያ፡ ‘የማይናገሩት’ እና ‘የማይነገርለት’ የተንሰራፋው የወጣቶች ጭንቀት በብዙ ምክንያቶች ማንነቷ እንዲታወቅ አትፈልግም። እኛም እንዳትታወቅ በሚል ‘ቅድስት’ በሚል ስም እንጠራታለን። ቅድስት ዘንድሮ ነው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናዋን የወሰደችው። ከቢቢሲ ጋር ዛሬ ያገናኛት ጉዳይ ግን የተከሰተው ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ገና አስረኛ ክፍል እያለች። “አንድ እኛ ትምህርት ቤት ከሚማር ልጅ ጋር የዐይን ፍቅር ይዞኝ ነበር” ስትል ትጀምራለች። አፍላ ፍቅር። በጓደኞቿ ግፊት ፈራ ተባ እያለች ‘የልቤን’ ያለችውን ነገረችው። ምላሹ ግን የልቧን አላደረሰውም። አዘነች። ተከፋች። የማዘን እና የመከፋቱ ጉዳይ መልከ ብዙ ነው። “አንዳንዴ ለምን ለጓደኞቼ ነገርኳቸው? እላለሁ” ትላለች። ጓደኞቿ እሷን ሲያዩ ርዕሰ ጉዳይ የሚሆነው የእሷ ‘የፍቅር ጥያቄ’ ሆኗል። ጓደኞቿ እሱን ሲያዩም ርዕስ የሚሆነው አሁንም የእሷ ‘የፍቅር ጥያቄ’ ነው። ጭንቀቱ ትምህርት ቤት ተወልዶ ቤት ድረስ ዘለቀ። “ቤተሰቦቼ ስለጉዳዩ አያውቁም” ትላለች። ቤተሰቦቿ የማያውቁትን ጉዳይ ግን የቤተሰቡ አባል አደረገችው። ስታጠናም አልጋ ላይ ተጋድማም ስለ ‘ትምህርት ቤቱ ልጅ’ ብቻ ሆነ ሃሳቧ። እንዳሁኑ አይሁን እንጂ ሌላም ሃሳብ ነበረባት። በትምህርቷ ጥሩ የምትባል ናት። ቤተሰቦቿም ለትልቅ ደረጃ የሚጠብቋት። በትምህርት ጥሩ ራመድ ካለ ቤተሰብም ነው የተገኘችው። በተለይ አባት ዲግሪውን አንድ ሁለት ሦስት እያሉ ደራርበውታል። ለዚህም ነው አባት የእኔን መንገድ ትከተላለች ብለው የሚኮሩባት ጭምር የሆነችው። ይህ በቀጥታም ሆነ በዘወርዋራ ትምህርትሽ ላይ አተኩሪ የሚል ግፊ ነበረው። ለእሷ ግን ሌላ የምታብሰለስለው ሌላ ምትጨነቅበት ጉዳይ ሆነባት። የምትወደውን ልጅ ማጣቷን እና ቤተሰቦቿ በሚፈልጓት ደረጃ አለመራመዷ ያስጨንቋት ገቡ። ቤትም ትምህርት ቤትም የሚያሳስቧት ነገሮች ሆኑ። ከቤት ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት ደግሞ ቤት ለምትለው ቅድስት ሌላ ማምለጫ መንገድ ጠፋ። “ሌላ ሰው የሆንኩ ያህል ተሰማኝ። የሚያስደስተኝ ነገር አጣሁ። እንቅልፍ በዓይኔ አልዞር አለ። ሌላ ሰው ሆንኩኝ” ትላለች። በዚህ ጊዜ ትንሽ እረፍት የሚሰጣት ‘የእኔ’ ከምትላቸው ጓደኞቿ ጋር መሆን ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም አይሳካም። እሷ ብዙም እንድትወጣ አይፈቀድላትም። ጓደኞቿ ቤታቸው ሲሄዱ ደግሞ የልባቸውን ለማውራት አይመቻቸውም። በዚህ ውጣ ውረድ ሳምንታት ከነፉ። ቤተሰቦቿ ሳይሰሙ መፍትሔ ያመጡልኛል ያለቻቸውን መንገዶች አማተረች። መፍትሔ የለም። መጽሐፍትን አነበበች። መፍትሔ የለም። ዩቲዩብ ላይ ተጣደች። አሁንም መፍትሔ የለም። * * * የመጨረሻው መፍትሔ ወደ ህክምና ማዕከል ለመሄድ ሆነ። ይህም ግን ቀላል ውሳኔ አልነበረም። ለቤተሰብ ሳይናገሩ ህክምና መሄድ ከባድ ነው። ብዙ መዘዞችም አሉት። ብዙ ጥያቄ ያስከትላል። እሷ ደግሞ አንኳን ለብዙ ለአንድም ጥያቄ መልስ የላትም። ያለቤተሰብ ሐኪም ዘንድ መሄድ የድጋፍ ማጣት ስሜት ይፈጥራል። ለተማሪ ደግሞ ሌላ ፈተና አለው - ገንዘብ አለማግኘት። ‘ቁጥጥር ለሚበዛባት’ ቅድስት ከትምህርት ቤት ቀርቶ ሐኪም ዘንድ መሔድ በራሱ ከባድ ነበር። አውጥታ አውርዳ ግን አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰች። ለብቻዋ ወደ ህክምና መሔድ። “እኔም የሚሰጠኝን [የኪስ ገንዘብ] አጠራቅሜ ጓደኞቼም ሰጥተውኝ ሐኪም ቤት ሄድኩኝ” ትላለች። ሐኪሙ ጭንቀት እንዳለባት ነገራት። አሁን ወደ አቶ ብርሃኑ ራቦ እናቅና። አቶ ብርሃኑ የሞሽን የማማከር እና የሥልጠና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው። “በብዙ ፀሐፊዎች ወይም ፈላስፋዎች አረዳድ ውጥረት ወይም ጭንቀት ሰው አሁን ያለበት እና በመድረሻው መካከል ያለው ርቀት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ በሚፈጠር ተስፋ ማጣት የሚከሰት ነው ይላሉ” ሲሉ ይገልጻሉ። ቅድስት ስላሳለፈችበት የሕይወት መስመር ለአቶ ብርሃኑ ስናጫውታቸውም “ውጥረት ወይም ጭንቀት በተለይ ዕድሜያቸው 20 እና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ዘንድ እየጨመረ ነው። ቤተሰብ፣ መምህራን እና ማኅበረሰቡ ሳያውቁ ስር እየሰደደ እየተሰቃዩበት ነው። ማንም ስለማይረዳቸውም በራሳቸው መንገድ መፍትሔ ለመፈለግ ይጥራሉ” ብለዋል። ምክንያቱ ምን ይሆን ሲባሉ መልከ ብዙ መሆኑን ይጠቁማሉ ባለሙያው። አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ችግሮች ፍርሃት እንዲያድርባቸውና ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋቸዋል። “ጤና፣ ችግር፣ የሠላም እጦት ችግር አለ። የሰዎችን ሞት መስማት ኖርማል (የተለመደ) ሆኗል” የሚሉት አማካሪው አቶ ብርሃኑ፣ ስለዚህ ወጣቶች ተስፋ የማይታያቸው በጣም የሚጨነቁ እና ውጥረት ውስጥ የሚገቡ ሆነዋል ሲሉ ያስረዳሉ። ማን ከጎኔ አለ ሳይባል ስለዘረኝነት፣ ስለሃይማኖት. . . ጦርነት ይወራል። ወጣቶችን እና ህጻናትና ሳያማክል መኖራቸውን እንኳን ከግምት ሳይገባ ይወራል። ትርፉ ልጆችን መጉዳት ነው ሲሉ አቶ ብርሃኑ ያስረዳሉ። በተጨማሪ ደግሞ የቴክኖሎጂ በረከት የትዬ ለሌ ነው። ከህጻን እስከ አዋቂ መዳፍ ላይ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ . . . በቀላሉ የሚገኝበት ዘመን ነው። የሚታጨደው በረከት ግን መልካሙም ብቻ አይደለም። እንክርዳዱም ጥቂት አይደለም። አቶ ብርሃኑ ሩብ ክፍለ ዘመን በማማከር እና በማሠልጠን አሳልፈዋል። ዓመት ዓመትን ሲተካ በጭንቀት እና ድባቴ የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር መናሩን ይናገራሉ። ምክንያቱን ለማወቅ ደግሞ አነስተኛ ጥናት አከናውነዋል። “ዘመኑ ሰዎች የማይረኩበት። በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ ነገሮች የፈጣሪን ህላዌ ራሱ የሚጠራጠሩበት፤ ‘ፈጣሪ እያለ ለምን ይሔ ሆነ?’ የሚል ሊመልሷቸው የማይችሏቸው ጥያቄዎች ውስጥ የመግባት ዕድል አለ።” “ቤተሰብ፣ እናት እና አባት እያለኝ ለምን ይሔ ደረሰብኝ? ለምን ይሔ ሆነብኝ? መንግሥት እያለ ለምን ይሔ ሆነ?” እያሉ ከሚተማመኑበት ነገር እየራቁ ሲሄዱ መፍትሔ፣ ረዳት እና አቅም የማጣት ሁኔታ ይመጣል። “በተስፋ ከመሞላት ወደ ተስፋ መቁረጥ ይሄዳሉ።” መፍትሔ የሚሉት ደግሞ ከባህል፣ ከእምነት እና ከእሴት የወጡ ነገሮችን ማድረግ ነው። “በመቀጠል በራሳቸውም በሌላውም ላይ መጨከን ነው” ይላሉ። በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ ራሳቸውን እንደሚያጠፉ ተናግረው ራሳቸውን ያጠፉ መኖራቸውን አስታውሰው “ይህ አስደንጋጭ ነው” ሲሉ አቶ ብርሃኑ ያስረዳሉ። “ሞትን የመሰለ ከባድ ነገር በቀጠሮ ወስነህ ስታደርገው ውጥረታችን እና ጭንቀታችን በሰው፣ በምድር እና በሰማይ ተስፋ መቁረጣችን ምን ያህል እንደሆነ በትክክል ይገለጻል። ልጆችን ተሰናብቶ ወደ ሞት መሄድ ወደየት እየሄድን እንደሆነ ያሳያል” ሲሉ ያክላሉ። “እንደተከታታይ ፊልም በላያችን ላይ የሚመላለሰው ጦርነት፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳቱን እንጂ ሥነልቦናዊ አደጋው ታስቦ እየተሠራበት አይደለም” ይላሉ። ይህም ልጆች ተስፋ እንዲቆርጡ፣ ነገን እንዳያስቡ፣ እንዳያልሙ፣ የሰውነት ክብርን እና ሰብዓዊነትን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል በሚል ይገልጻሉ። “የሰብዓዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ በኢኮኖሚው ላይ ተደምሮ የምንይዘው የምንጨብጠው አጥተናል” በማለት የእለት ከዕለት ሕይወት ጫናም የእራሱ አሉታዊ ውጤት አለው ይላሉ። “የመኖር ትርጉም ሲያጣባቸው የማያውቁትን ዓለም መሞትን ወደ መምረጥ ይሄዳሉ” የሚሉት አቶ ብርሃኑ “ከዚህ አንጻር እንደባለሙያ የሚያሳስበን ትኩረት ማጣት ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ይህ ‘ጊዜ ቦንብ’ ነው የሚሉት አቶ ብርሃኑ ያውም ‘ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ’ ይላሉ። ቤተሰብ በሙሉ ቴክኖሎጂ ላይ ተጥዶ ሰው አፍ ለአፍ የማይነጋገርበት ሁኔታ እያደገ ነው። ሰው ችግሩን የሚነግረው ለሚሰማው ለሚያዳምጠው ነው። ወላጆች የራሳቸውን ችግር ለማለፍ ወይም ዓላማቸውን ለማሳካት እንጂ ልጆችን ለመስማት ጊዜ የላቸውም። “ወላጆች ልጆቻቸውን፣ መምህራን የተማሪዎቻቸው ችግር ከማዳመጥ የራሳቸውን ችግር ነው የሚያሰላስሉት። ‘እኔ ለመግባችሁ ስሯሯጥ’ በሚል የልጆቹን ችግር እንደምቾት እና ድሎት ነው የሚያዩት” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። ልጆቹ ችግራቸውን ያጠራቅሙና ከወላጆች። ከመመህራን እና ከማኅበረሰቡ ደብቀው በራሳቸው መንገድ ለመፍታት ይሞክራሉ። ያውም “ጥሩ ባልሆነ፣ በማይመከር እና ችግሩን በሚያባበስ መልኩ ለመፍታት ይሯሯጣሉ።” “ይህንን አድርገው ሲያቅታቸው ደግሞ ራሳቸውን ይጠላሉ፣ እንቅለፍ ያጣሉ። እያደረ ፍርሃት ውስጥ ይከታቸዋል። ሁሉም እያወቀበቸው መሆኑን ከፍተኛ እርምጃ ይወስዳሉ” ይላሉ። የቅድስት ወላጆች ልጃቸው ያላትን ለውጥ መከታተል ነበረባቸው። ለእሷም ከባድ ቢሆንም ችግሩን ለቤተሰቦቿ ማሳወቅ የተሻለ ቀላል ያደርግላት ነበር። “እነዲህ ዓይነት ነገር በብዛት ያጋጥማል። ከትንንሽ ልጆች ጀምሮ በማይታወቅ ድባቴ ውስጥ ያሉ አሉ” ይላሉ ባለሙያው። ስለ ቅድስት ያጫወትናቸው አቶ ብርሃኑ እሳቸውም በርካታ ተመሳሳይ ታሪክ እንደሚያውቁ ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱን አውግተውናል። “አንድ በጣም ጎበዝ ወጣት ነበር። በጥሩ ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ነው። ዩኒቨርሲቲ ሲገባ ችግሩን የሚሰማው ስለሌለ ይጨነቅ ጀመረ። ቤተሰቡ ለእሱ ያላቸው ግምት ትልቅ በመሆኑ፣ ትምህርቱን መከታታል አልቻለም። በኋላም ትምህርቱን አቋረጠ። ወላጆቹ ይህን ሁሉ አያውቁም።” ነጻ አገልግሎትም የሚሰጡት አቶ ብርሃኑ ተማሪው ቢሯቸው ሲደርስ ፊታቸውን አላዞሩበትም። “እና ተገቢውን ድጋፍ ሰጥተነው ወደ ትምህርቱ ተመልሶ ዓላማው እንዲያሳካ እገዛ አደረግንለት” ሲሉ ያስታውሳሉ። “ብዙ ወላጅ ልጆቼ ጥሩ ናቸው። ጎበዝ እና ሥነ ምግባር ያላቸው ናቸው ይላሉ እንጂ ብዙ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ድባቴ ውስጥ ነው ያሉት።” “በአገራችን ብዙ ነገር ተስፋ የሚያስቀርጥ ይሆንባቸዋል። ወላጆች ትልልቅ ርዕሶችን ቤት እና መኪና ውስጥ ያወራሉ። ቲቪው እና ስልካቸው የሚዘገንን መረጃ ይሰጣል። ልጆቹ ትምህርት ቤት ሌላ፣ ቤት ሌላ ናቸው። ጓደኞቻው ጋርም ሌላ ናቸው። በዚህ ምክንያትም የተለያየ ስብዕና ያዳብራሉ” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። ለአቶ ብርሃኑ እነዚህን ከፍተኛ ችግሮች በአነስተኛ ድርጅቶች ብቻ መፍታት ከባድ ነው። “ከቁስ እና ኢኮኖሚው በላይም በዘመቻ ከምንም በላይ መሠራት አለበት ብለን የምናምነው የሰው አዕምሮ ላይ ነው” ይላሉ። ይህ ሕብረተሰቡ እና መንግሥት ኃላፊነት ነው። ወጣቶች ደግሞ ሌላ ኃላፊነት አለባቸው። “ወጣቶች እውቀት ላይ ትኩረት ያድረጉ። አካላዊ እንቅስቃሴ አለባቸው። ከዲጂታል ይልቅ መጽሐፎችን በእጅ ይዞ እያገላበጡ ማንበብ። በተቻለ መጠንም ከቴክኖሎጂ ጋር የሚቆዩበትን ጊዜ መቀነስ አለባቸው” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። በተጨማሪም በቀን ስንት ሰዓት ማየት እንዳለባቸው መለየት እና ከቻሉ በሳምንት አንድ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ከቴክኖሎጂ ውጪ መሆን ያስፈልጋል። ከተፈጥሮ ጋር መገናኘት፣ ስፖርት መስራት፣ በበጎ አድራጎት መሳተፍ እና ህይወታቸውን በተቻለ መጠን መንፈሳዊ ማድረግ እንደሚያስፈለግ ባለሙያው አጥብቀው ይመክራሉ። “ዘመኑ ፈጣን ነው። ይህን ሊታደግ የሚችል ፈጣሪ እንዳላቸው በማየት ለሕይወታቸው ቅርጽ መስጠት። በሕይወት ክህሎት ሥልጠናዎች እንዲሳተፉ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለይ ደግሞ ወጣቶች የትምህርት፣ የሥራ እና ሌሎች መከወን ያለባቸው ነገሮች መብዛት ሳይሆን ለበርካቶች የጭንቀት ምንጭ የሚሆነው፣ እያንዳንዱን ሥራ በጊዜ አለመሥራት መሆኑን እንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህ ወላጆች እና ልጆች ያላቸውን ጊዜ እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው መልመድ ይገባል የሚሉት አቶ ብርሃኑ “የሰዓት አስተዳርን ከቤት ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።” ወደተነሳንበት ታሪክ እንመለስ። አሁን ቅድስት በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ህክምናዋን በደንብ ተከታትላለች። “ሐኪም ቤት ደርሼ የተመለስኩ ቀን ነው የሆነ ነገር የቀለለኝ” ስትል ታስታውሳለች። “ቤት የደረስኩት ፈገግ ብዬ ነበር። ከረዥም ጊዜ በኋለ ጥሩ እንቅልፍም ተኛሁኝ” ብላለች። ሕክምናውም ቢሆን ግን መዘዝ ነበረው። በተለይ ቤተሰብ ሳያውቅ መድኃኒት ደብቆ መዋጥ ፈተና ነው። አንዴ ወስና የገባችበት በመሆኑ ግን ተወጣችው። ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግባት በመዘጋጀት ላይ ትገኛለች። ቤተሰቦቿ እንደሚጠብቋት በትምህርቷ መግፋት ትፈልጋለች። ያውም አባቷ በሚፈልጉት የትምህርት ዘርፍ ነው መቀጠል የምትፈልገው። አባት እና ልጅ በአንድ የትምህርት መስክ ሊጓዙ ነው። አሁንም ግን ከስጋት ነጻ አይደለችም። ጉዳዩን ለቤተሰቦቿ አለመንገሯ ያሳስባታል። ቢያውቁስ የሚል ስጋት አለባት። ግን ከቀድሞው የተሻለ ጥንካሬ ስላላት ምንም ቢመጣ ከቤተሰቦቿ ጋር እንደምታልፈው ታምናለች። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c5152vjxv3no |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች | የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ "ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች። | ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ "ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-56330257 |
3politics
| እነ አቶ ጀዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍቃድ ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ | አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፍ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍላጎት ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የዛሬውን ቀጠሮ ይዞ የነበረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በሚሰሙበት ሁኔታ ላይ ክርክር ለማድመጥ እና ከዚህ ቀደም ችሎት ሳይገኙ የቀሩት ተከሳሾች ከችሎት የቀሩበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ነበር። በዛሬው ችሎት በእነ አቶ ጀዋር የክስ መዝገብ ስር ከተዘረዘሩ ተከሳሾች መካከል ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት አራት ግለሰቦችን ጨምሮ አቶ አማን ቃሉ የተባሉ ተከሳሽ ችሎት ሳይገኙ ቀርተዋል። አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ ችሎት ያልተገኙበትን ምክንያት በጠበቃቸው በኩል ለችሎቱ አድርሰዋል። ዐቃቤ ሕግ ግን ተከሳሾች ችሎት የማይቀርቡበትን ምክንያት በጠበቃቸው በኩል መናገር የሚፈቅድ የሕግ አካሄድ የለም በማለት ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾች ጠበቃ እድል እንዳይሰጥ ጠይቋል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች ጠበቃ ሐሳባቸውን እንዲያቀርቡ እድል ሰጥቷል። በዚሁ መሠረት "የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚው አካል የፍርድ ቤት ውሳኔን እያከበረ አይደለም፤ ከእስር የወጡ ጓደኞቻችን የት እንዳሉ አናውቅም" ሲሉ እነ አቶ ጀዋር በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። ተከሳሾቹ በፍርድ ቤት ነጻ ተብለው ከእስር ቢወጡ ተመሳሳይ እጣ ሊገጥመን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አራቱ ተከሳሾች በጠበቃቸው በኩል አስታውቀዋል። እነ አቶ ጀዋር በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ፤ አራት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ተከሳሾቹ ችሎት ሳይቀርቡ የቀሩበት ምክንያት አጥጋቢ አይደለም ብሏል። በዚህም መሠረት ማረሚያ ቤቱ አራቱን ተከሳሾች "ሌሎች ተከሳሾችን ችሎት እንደሚያቀርበው እነዚህንም ያቀርብ" ሲል ትዕዛዝ በመስጠት ለሐምሌ 21/2013 ዓ. ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። | እነ አቶ ጀዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍቃድ ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፍ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍላጎት ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የዛሬውን ቀጠሮ ይዞ የነበረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በሚሰሙበት ሁኔታ ላይ ክርክር ለማድመጥ እና ከዚህ ቀደም ችሎት ሳይገኙ የቀሩት ተከሳሾች ከችሎት የቀሩበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ነበር። በዛሬው ችሎት በእነ አቶ ጀዋር የክስ መዝገብ ስር ከተዘረዘሩ ተከሳሾች መካከል ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት አራት ግለሰቦችን ጨምሮ አቶ አማን ቃሉ የተባሉ ተከሳሽ ችሎት ሳይገኙ ቀርተዋል። አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ ችሎት ያልተገኙበትን ምክንያት በጠበቃቸው በኩል ለችሎቱ አድርሰዋል። ዐቃቤ ሕግ ግን ተከሳሾች ችሎት የማይቀርቡበትን ምክንያት በጠበቃቸው በኩል መናገር የሚፈቅድ የሕግ አካሄድ የለም በማለት ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾች ጠበቃ እድል እንዳይሰጥ ጠይቋል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች ጠበቃ ሐሳባቸውን እንዲያቀርቡ እድል ሰጥቷል። በዚሁ መሠረት "የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚው አካል የፍርድ ቤት ውሳኔን እያከበረ አይደለም፤ ከእስር የወጡ ጓደኞቻችን የት እንዳሉ አናውቅም" ሲሉ እነ አቶ ጀዋር በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። ተከሳሾቹ በፍርድ ቤት ነጻ ተብለው ከእስር ቢወጡ ተመሳሳይ እጣ ሊገጥመን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አራቱ ተከሳሾች በጠበቃቸው በኩል አስታውቀዋል። እነ አቶ ጀዋር በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ፤ አራት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ተከሳሾቹ ችሎት ሳይቀርቡ የቀሩበት ምክንያት አጥጋቢ አይደለም ብሏል። በዚህም መሠረት ማረሚያ ቤቱ አራቱን ተከሳሾች "ሌሎች ተከሳሾችን ችሎት እንደሚያቀርበው እነዚህንም ያቀርብ" ሲል ትዕዛዝ በመስጠት ለሐምሌ 21/2013 ዓ. ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57737839 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ዶ/ር ፋውቺ ለክትባት መጣደፉ ቢቀርብን ይሻላል አሉ | የአሜሪካ ዕውቅ የማኅበረሰብ ጤናና የተላላፊ በሽታዎች ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ‹‹እኔ ተናግሪያለሁ! ይሄ ለክትባት የምንጣደፈው ነገር አላማረኝም›› እያሉ ነው፡፡ ይህን የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የመጪው ምርጫ በለስ እንዲቀናቸው በሙከራ ላይ ያለን ክትባት ያለጊዜው ወደ ሕዝብ በማውጣት ‹ክትባት ደርሷልና ተከተቡ› እንዳይሉ ስጋት መፈጠሩን ተከትሎ ነው፡፡ ዶ/ር ፋውቺ በአሜሪካ ህዝብ ከትራምፕ የበለጠ ተሰሚነትና የመታመን ፀጋን ያገኙ ጎምቱ የጤና ባለሞያ ናቸው፡፡ ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት አንድን ክትባት የሕክምና ደንብና መርሆችን ሳይከተሉ ወደ ሕዝብ ማውጣት የሌሎች ክትባቶችን ተስፋ ያጨልማል፡፡ ትራምፕ አንድን ክትባት ሙሉ ሒደቱን ሳይጨርስና በብዙ ሰዎች ላይ ሙከራ ሳይደረግበት ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ የሚገኙት ካለፈው ሳምንት ወዲህ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን ለማድረግ የተበረታቱት በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት በኅዳር ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለመጨመር በመሻት ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ትራምፕ ከጆ ባይደን ያነሰ ቅቡልና እንዳላቸው የሕዝብ ፖለቲካዊ ሙቀት መመተሪያ ዳሰሳ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ዲሞክራቶች ‹‹እኚህ ትራምፕ የሚባሉ ሰውዬ ለዝናቸው ሲሉ የአሜሪካውያንን ሕይወት ለፖለቲካ ቁማር እያዋሉት ይገኛሉ›› ብለው ከሰዋቸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት ከሆነ የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ለመድኃኒት አምራቾች ሥራቸውን እያደናቀፈባቸው ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚሉት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹ክትባት አምራቾች ትክክለኛውን የመድኃኒት አመራረት ሒደት ተከትለው እንዲሄዱ› በተደጋጋሚ በማሳሰቡ ነው፡፡ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዶናልድ ትራምፕ በኦክስፎድና በአስትራዜኔካ አማካኝነት እየተሞከረ ያለው ክትባት ለአስቸኳይ የሕክምና አገልግሎት በአቋራጭ ለሕዝብ እንዲቀርብ የሚቻልበትን መንገድ እየፈለጉ እንደሆነ ዘግቦ ነበር፡፡ እነ ኦክስፎርድ እየሞከሩት ባለው ክትባት ለመሳተፍ 10 ሺ አሜሪካዊያን ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን 30ሺህ ፈቃደኞች ካልተሟሉ ይሁንታን አልሰጥም እያለ ነው፡፡ የኦክስፎርድ ክትባት አሁን ዓለም ላይ እየተሞከሩ ካሉ በዐሥራዎቹ ከሚገኙ ምርምሮች እጅግ ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡ ባለፉት ሳምንታት ታዋቂ መድኃኒት ፋብሪካዎች መድኃኒቶቻቸውን በመሞከር ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የኤሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የወባ መድኃኒት የሆነው ሀይድሮክሲክሎሮኪዩን ለኮሮና ታማሚዎች ቢሰጥ እንደማይቃወም ተናግሮ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቱ ከጥቅሙ ጉዳት ማመዘኑ በምርመራ በመረጋገጡ እውቅና ነፍጎታል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ይህን መድኃኒት ለሳምንታት መውሰዳቸውንና ፍቱን እንደሆነ እንደደረሱበት በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ ዶ/ር ፋውቺ እንደሚሉት ክትባቶች ትክክለኛውን አካሄድ ካልተከተሉ አደጋ ማስከተላቸው ብቻም ሳይሆን ሰዎች በቀጣይ በሚወጡ መድኃኒቶች እምነት ያጣሉ፣ እንዲመከርባቸው የሚፈቅዱ በጎ ፈቃደኞችንም ማሸሽ ይሆናል፡፡ ዶ/ር ፋውቺ ፖለቲካ ሕክምና ውስጥ ገብቶ መፈትፈት የለበትም፡፡ ሕክምና የራሱን መንገድ እንዲከተል ሊተው ይገባል የሚል አቋም አላቸው፡፡ | ኮሮናቫይረስ፡ ዶ/ር ፋውቺ ለክትባት መጣደፉ ቢቀርብን ይሻላል አሉ የአሜሪካ ዕውቅ የማኅበረሰብ ጤናና የተላላፊ በሽታዎች ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ‹‹እኔ ተናግሪያለሁ! ይሄ ለክትባት የምንጣደፈው ነገር አላማረኝም›› እያሉ ነው፡፡ ይህን የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የመጪው ምርጫ በለስ እንዲቀናቸው በሙከራ ላይ ያለን ክትባት ያለጊዜው ወደ ሕዝብ በማውጣት ‹ክትባት ደርሷልና ተከተቡ› እንዳይሉ ስጋት መፈጠሩን ተከትሎ ነው፡፡ ዶ/ር ፋውቺ በአሜሪካ ህዝብ ከትራምፕ የበለጠ ተሰሚነትና የመታመን ፀጋን ያገኙ ጎምቱ የጤና ባለሞያ ናቸው፡፡ ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት አንድን ክትባት የሕክምና ደንብና መርሆችን ሳይከተሉ ወደ ሕዝብ ማውጣት የሌሎች ክትባቶችን ተስፋ ያጨልማል፡፡ ትራምፕ አንድን ክትባት ሙሉ ሒደቱን ሳይጨርስና በብዙ ሰዎች ላይ ሙከራ ሳይደረግበት ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ የሚገኙት ካለፈው ሳምንት ወዲህ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን ለማድረግ የተበረታቱት በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት በኅዳር ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለመጨመር በመሻት ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ትራምፕ ከጆ ባይደን ያነሰ ቅቡልና እንዳላቸው የሕዝብ ፖለቲካዊ ሙቀት መመተሪያ ዳሰሳ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ዲሞክራቶች ‹‹እኚህ ትራምፕ የሚባሉ ሰውዬ ለዝናቸው ሲሉ የአሜሪካውያንን ሕይወት ለፖለቲካ ቁማር እያዋሉት ይገኛሉ›› ብለው ከሰዋቸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት ከሆነ የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ለመድኃኒት አምራቾች ሥራቸውን እያደናቀፈባቸው ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚሉት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹ክትባት አምራቾች ትክክለኛውን የመድኃኒት አመራረት ሒደት ተከትለው እንዲሄዱ› በተደጋጋሚ በማሳሰቡ ነው፡፡ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዶናልድ ትራምፕ በኦክስፎድና በአስትራዜኔካ አማካኝነት እየተሞከረ ያለው ክትባት ለአስቸኳይ የሕክምና አገልግሎት በአቋራጭ ለሕዝብ እንዲቀርብ የሚቻልበትን መንገድ እየፈለጉ እንደሆነ ዘግቦ ነበር፡፡ እነ ኦክስፎርድ እየሞከሩት ባለው ክትባት ለመሳተፍ 10 ሺ አሜሪካዊያን ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን 30ሺህ ፈቃደኞች ካልተሟሉ ይሁንታን አልሰጥም እያለ ነው፡፡ የኦክስፎርድ ክትባት አሁን ዓለም ላይ እየተሞከሩ ካሉ በዐሥራዎቹ ከሚገኙ ምርምሮች እጅግ ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡ ባለፉት ሳምንታት ታዋቂ መድኃኒት ፋብሪካዎች መድኃኒቶቻቸውን በመሞከር ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የኤሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የወባ መድኃኒት የሆነው ሀይድሮክሲክሎሮኪዩን ለኮሮና ታማሚዎች ቢሰጥ እንደማይቃወም ተናግሮ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቱ ከጥቅሙ ጉዳት ማመዘኑ በምርመራ በመረጋገጡ እውቅና ነፍጎታል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ይህን መድኃኒት ለሳምንታት መውሰዳቸውንና ፍቱን እንደሆነ እንደደረሱበት በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ ዶ/ር ፋውቺ እንደሚሉት ክትባቶች ትክክለኛውን አካሄድ ካልተከተሉ አደጋ ማስከተላቸው ብቻም ሳይሆን ሰዎች በቀጣይ በሚወጡ መድኃኒቶች እምነት ያጣሉ፣ እንዲመከርባቸው የሚፈቅዱ በጎ ፈቃደኞችንም ማሸሽ ይሆናል፡፡ ዶ/ር ፋውቺ ፖለቲካ ሕክምና ውስጥ ገብቶ መፈትፈት የለበትም፡፡ ሕክምና የራሱን መንገድ እንዲከተል ሊተው ይገባል የሚል አቋም አላቸው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-53900469 |
3politics
| የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው ድርድር የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ | የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው የሰላም ድርድር የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት እንዲቻል የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥትን እና የትግራይ ኃይሎችን ድርድር እንዲጀምሩ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ነበር ጥሪ ያቀረበው። መንግሥት በኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኩል የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን አረጋግጧል። የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቁ ናቸው በማለት፤ ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆን እና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጽ መቆየቱን አመልክቷል። ስለዚህም መንግሥት ግጭቱን ለመፍታት ሲወስዳቸው የቆዩትን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። በተመሳሳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ንግግር ጥሪውን መቀበሉን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የድርድር ጥሪውን የተቀበለው “ግጭቱን በሰላም ለማብቃት እና ካለቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር ካለው አቋም ጋር የሚጣጣም” በመሆኑ ነው ብለዋል። በኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐማት ተፈርሞ ቅዳሜ መስከረም 21/2015 ዓ.ም. በተጻፈው የንግግር የግብዣ ጥሪ ላይ የመጀመሪያ ደረጃው ንግግር በመጪው ቅዳሜ ወይም እሁድ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ቢቢሲ የተመለከተው ከአፍሪካ ኅብረት ተጽፏል የተባለው ደብዳቤ ድርድሩ የሚጀመርበት ቀንን በተመለከተ ስህተት እንዳለ ያሳያል። ደብዳቤው እሁድ መስከረም 28 የሚል ቢሆንም እሁድ ግን መስከረም 29 ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል በበኩሉ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋገጥኩ እንዳለው፣ የአፍሪካ ኅብረት ለህወሓት ሊቀ መንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የግብዣ ደብዳቤ መጻፉን ዘግቧል። የዜና ወኪሉ ስለ ግባዣው የህወሓት ቃል አቀባይ ከሆኑት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ማረጋገጫ ለማግኘት ጥያቄ አቅርቦ፣ በቅርቡ ይካሄዳል ስለሚባለው ንግግር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል ብሏል። በኅብረቱ ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ እንደሚለው በሁለቱ ወገኖች መካከል ከቀናት በኋላ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ንግግር ለቀጣይ ድርድር አስፈላጊ በሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አመልክቷል። የጦርነቱ መባባስን ተከትሎ የአፍሪካ ኅብረት የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካዩ አድርጎ ሰላም ለማውረድ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ከቀናት በኋላ ለማድረግ የታሰበው ይህ የሰላም ንግግር በኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የሚመራ ሲሆን፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ጨምሮ ሌሎች አሸማጋዮች እንደሚሳተፉበት ተነግሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር ከሰኞ መስከረም 23/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አፍሪካ በመምጣት ሰላም እንዲወርድ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጹ ይታወሳል። ልዩ መልዕክተኛው ከሚጎበኟቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ስትሆን፣ ከሰኞ መስከረም 23 አስከ ጥቅምት 08/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከየአገራቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል። ባለፈው መጋቢት ወር የሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ጦርነት ፈርሶ በበርካታ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ውጊያዎች ከተቀሰቀሱ በኋላ፣ የአሁኑ የማይክ ሐመር ጉዞ ሁለተኛው ነው። ከአንድ ወር በኋላ ሁለት ዓመት የሚሞላው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኝነት የሰየመቻቸው ሦስተኛው ዲፕሎማት የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ ባለፉት አራት ወራት በአዲስ አበባ እና በመቀለ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ከትግራይ አመራሮች ጋር ተገናኝተዋል። ግብ ብሎ የነበረው ጦርነት ማገርሸቱን ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ ጠይቀው፣ ውጥረቱን በማርገብ በተለይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሁሉ እንዲደርስ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ይህ ጦርነት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱበት የሚታመን ሲሆን፣ በመቶ ሺዎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሁሉም የጦርነቱ ተሳታፊዎች ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንደፈጸሙ በተደጋጋሚ ሲከሰሱ የነበረ ሲሆን፣ በተጨማሪም ቁሳዊ ውድመትን ባስከተለው በዚህ ጦርነት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ነዋሪዎች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። አስተማማኝ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ አሁንም ጦርነቶች እንደሚካሄዱ ከተለያዩ ምንጮች የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ሁለቱም ወገኖች ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ከገለጹ ወራት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ አስካሁን በይፋ ንግግር ጀምረው ተጨባጭ እርምጃዎች አልታዩም። ይልቁንም ጋብ እያለ የሚቀሰቀሰው ጦርነት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን አለመረጋጋት በማባባስ ለነዋሪዎች መፈናቀል እና ለእንቅስቃሴዎች መስተጓጎል ምክንያት ሆኗል። | የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው ድርድር የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው የሰላም ድርድር የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት እንዲቻል የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥትን እና የትግራይ ኃይሎችን ድርድር እንዲጀምሩ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ነበር ጥሪ ያቀረበው። መንግሥት በኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኩል የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን አረጋግጧል። የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቁ ናቸው በማለት፤ ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆን እና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጽ መቆየቱን አመልክቷል። ስለዚህም መንግሥት ግጭቱን ለመፍታት ሲወስዳቸው የቆዩትን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። በተመሳሳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ንግግር ጥሪውን መቀበሉን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የድርድር ጥሪውን የተቀበለው “ግጭቱን በሰላም ለማብቃት እና ካለቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር ካለው አቋም ጋር የሚጣጣም” በመሆኑ ነው ብለዋል። በኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐማት ተፈርሞ ቅዳሜ መስከረም 21/2015 ዓ.ም. በተጻፈው የንግግር የግብዣ ጥሪ ላይ የመጀመሪያ ደረጃው ንግግር በመጪው ቅዳሜ ወይም እሁድ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ቢቢሲ የተመለከተው ከአፍሪካ ኅብረት ተጽፏል የተባለው ደብዳቤ ድርድሩ የሚጀመርበት ቀንን በተመለከተ ስህተት እንዳለ ያሳያል። ደብዳቤው እሁድ መስከረም 28 የሚል ቢሆንም እሁድ ግን መስከረም 29 ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል በበኩሉ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋገጥኩ እንዳለው፣ የአፍሪካ ኅብረት ለህወሓት ሊቀ መንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የግብዣ ደብዳቤ መጻፉን ዘግቧል። የዜና ወኪሉ ስለ ግባዣው የህወሓት ቃል አቀባይ ከሆኑት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ማረጋገጫ ለማግኘት ጥያቄ አቅርቦ፣ በቅርቡ ይካሄዳል ስለሚባለው ንግግር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል ብሏል። በኅብረቱ ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ እንደሚለው በሁለቱ ወገኖች መካከል ከቀናት በኋላ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ንግግር ለቀጣይ ድርድር አስፈላጊ በሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አመልክቷል። የጦርነቱ መባባስን ተከትሎ የአፍሪካ ኅብረት የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካዩ አድርጎ ሰላም ለማውረድ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ከቀናት በኋላ ለማድረግ የታሰበው ይህ የሰላም ንግግር በኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የሚመራ ሲሆን፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ጨምሮ ሌሎች አሸማጋዮች እንደሚሳተፉበት ተነግሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር ከሰኞ መስከረም 23/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አፍሪካ በመምጣት ሰላም እንዲወርድ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጹ ይታወሳል። ልዩ መልዕክተኛው ከሚጎበኟቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ስትሆን፣ ከሰኞ መስከረም 23 አስከ ጥቅምት 08/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከየአገራቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል። ባለፈው መጋቢት ወር የሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ጦርነት ፈርሶ በበርካታ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ውጊያዎች ከተቀሰቀሱ በኋላ፣ የአሁኑ የማይክ ሐመር ጉዞ ሁለተኛው ነው። ከአንድ ወር በኋላ ሁለት ዓመት የሚሞላው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኝነት የሰየመቻቸው ሦስተኛው ዲፕሎማት የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ ባለፉት አራት ወራት በአዲስ አበባ እና በመቀለ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ከትግራይ አመራሮች ጋር ተገናኝተዋል። ግብ ብሎ የነበረው ጦርነት ማገርሸቱን ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ ጠይቀው፣ ውጥረቱን በማርገብ በተለይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሁሉ እንዲደርስ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ይህ ጦርነት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱበት የሚታመን ሲሆን፣ በመቶ ሺዎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሁሉም የጦርነቱ ተሳታፊዎች ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንደፈጸሙ በተደጋጋሚ ሲከሰሱ የነበረ ሲሆን፣ በተጨማሪም ቁሳዊ ውድመትን ባስከተለው በዚህ ጦርነት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ነዋሪዎች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። አስተማማኝ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ አሁንም ጦርነቶች እንደሚካሄዱ ከተለያዩ ምንጮች የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ሁለቱም ወገኖች ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ከገለጹ ወራት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ አስካሁን በይፋ ንግግር ጀምረው ተጨባጭ እርምጃዎች አልታዩም። ይልቁንም ጋብ እያለ የሚቀሰቀሰው ጦርነት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን አለመረጋጋት በማባባስ ለነዋሪዎች መፈናቀል እና ለእንቅስቃሴዎች መስተጓጎል ምክንያት ሆኗል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgrd55vr82go |
5sports
| ኢትዮጵያ ጫፍ በደረሰችበት የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሰባት አገራት ትላንት ተለዩ | ትላንት በተካሄደ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወደ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ተጨማሪ ሰባት አገራት ተለዩ። ጋምቢያ፣ ኮሞሮስ፣ ጋቦን፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ዚምባብዌ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ናቸው ወደ አህጉራዊው ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡት አገራት ናቸው። ጋምቢያ አንጎላን በሜዳዋ 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አልፋለች። በምድብ አራት የምትገኘው ጋምቢያ ከሁለቱ አላፊ ቡድኖች አንዷ የሚያደርጋትን ወሳኝ ጎል አሳን ሴሳይ ከዕረፍት መልስ አስገኝቷል። በዚህ ምድብ የምትገኘው ጋቦን ዲሞክራቲክ ኮንጎን 3 ለ 0 በማሸነፍ ሌላኛዋ አላፊ አገር ሆናለች። በዚህም ጋቦን የ2019ኙ ውድድር ካመለጣት በኋላ ወደ ውድድር መድረኩ ለመመለስ በቅታለች። ፒየር-ኤሚሪክ ኦባሜያንግ፣ ዴኒስ ቡዋንጋ እና አሮን ቡውፔንዛ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። ባለፉት 4 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተሳትፋ የነበረውች ኮንጎ፤ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። በካሜሩን አዘጋጅነት ለመኪሄደው ውድድር ለማለፍ በምድብ 6 የምትገኘው ግብጽ የሚያስፈልጋትን አንድ ነጥብ ለማግኘት ከኬንያ ጋር ተጫውታ 1 ለ 1 አቻ ተለያይታለች። ፈርኦኖቹ ከኮሞሮስ ጋር እኩል ዘጠኝ ነጥብ ይዘዋል። ኬንያ አራት ነጥብ ሲኖራት ቶጎ በሁለት ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች። በናይሮቢ በተካሄደው ጨዋታ ማግዲ አፍሻ በሁለተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ግብጽ ቀዳሚ ሆናለች። ከእረፍት መልስ ኬንያ በአብደላህ ሃስ አማካኝነት አቻ ለመሆን ችላለች። ቀድም ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ መሳተፏን ያረጋገጠችው ኮሞሮስ ከሜዳዋ ውጪ ከቶጎ ጋር 0 ለ 0 ተለያይታለች። ከዚህ በፊት በውድድሩ መሳተፍ ያልቻሉት ቡድኖች ከ2019 ጀምሮ 16 የነበረው የተወዳዳሪ አገራት ቁጥር ወደ 24 በማደጉ ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል። ከምድብ ሦስት ለማለፍ ከደቡብ አፍሪካ ጋር 1 ለ 1 በሆነ ውጤት አቻ በመውጣት ጋና ወደ ውድድሩ የሚያስገባትን ትኬት ቆርጣለች። መሐመድ ቁዱስ ከ2010 የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በኡራጓይ ተሸንፈው በወጡበት ስታዲየም ቀዳሚ የሚያደርጋቸውን ጎል ቢያስቆጥርም በደቂቃዎች ልዩነት ፐርሲ ታው ደቡብ አፍሪካን አቻ አድርጓል። ካለፉት 15 ውድድሮች በአንዱ ብቻ ያልተካፈሉት ጥቁሮቹ ከዋክብት አስር ነጥብ በመያዝ ከደቡብ አፍሪካ እኩል ሆነዋል። በስድስተኛው እና በመጨረሻው የምድቡ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ዘጠኝ ነጥብ ካላት ሱዳን ጋር ትጫወታለች። ጋና ከሱዳንም ሆነ ከባፋና ባፋናዎች ጋር በነበራት ጨዋታ ያላት ውጤት የተሻለ በመሆኑ የአራት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮኗ ከውድድሩ ውጭ የምትሆንበት ሁኔታ የለም። ዚምባብዌ ከሜዳዋ ውጪ ቦትስዋናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። አልጄሪያ በሌላ የምድቡ ጨዋታ ከዛምቢያ ጋር 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቃለች። በዚህም ዚምባብዌ እና አልጄሪያ ተያይዘው ሲያልፉ የ2012ቱ ውድድር አሸናፊ ዛምቢያ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ኤሚሊዮ ንሱ በመጨረሻው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ኢኳቶሪያል ጊኒ ታንዛኒያን 1ለ 0 በማሸነው ማለፏን አረጋግጣለች። ሊቢያን 5 ለ 2 በሆነ ውጤት ያሸነፈችው ቱኒዚያ ከምድብ አንድ ቀድማ ነበረ ለውድድሩ ማለፏን ያረጋገጠችው። በከፍተኛ ጎል ልዩነት ቢሸነፉም ሊቢያውያን ከሰባት ዓመታት እገዳ በኋላ ብሔራዊ ቡድናቸውን በሜዳው ሲጫወቱ ለማየት በመቻላቸው ተደስተዋል። በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ውድድር ላይ ከሚሳተፉ ቡድኖች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተለይተዋል። ኮሞሮስ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ዚምባብዌ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ እና አስተናጋጇ ካሜሩን በውድድሩ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። ኢትረዮጵያስ ምን ተስፋ አላት? በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር፣ ማደጋስካር እና ኒጀር ጋር የተመደበችው ኢትዮጵያ፤ በመጀመሪያው ጨዋታ በማደጋስካር አንድ ለባዶ ተሸንፋ የነበረ ሲሆን፤ በቀጣይ በባሕር ዳር በተደረገ ጨዋታ ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በመቀጠል ዋልያዎቹ ወደ ኒጀር ተጉዘው፤ አንድ ለባዶ ቢሸንፉም በመልሱ ጨዋታ ሦስት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። ዋልያዎቹ ከማደጋስካር ጋር በነበራቸው የምድብ ጨዋታ ደግሞ አራት ለባዶ በማሸነፍ ነው ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ መምራት የቻሉት። በምድቡ ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ ኮትዲቯር ከኒጀር የሚያደርጉት ሲሆን ጨዋታው በኮትዲቯር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ኢትዮጵያ በምድቡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ትላለች። ጨዋታው በኒጀር አሸናፊነት አልያም አቻ የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ዋልያዎቹ መሪነታቸውን አስጠብቀው ወደ መጨረሻው የምድብ ጨዋታ ይጓዛሉ ማለት ነው። ዋልያዎቹ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በኮትዲቯር የሚያደርጉ ሲሆን ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉትም ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን የምታሸንፍ ከሆነ በካሜሩን አዘጋጅነት በሚካሄደው ጨዋታ ተሳታፊነቷን የምታረጋግጥ ሲሆን፤ ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ በኒጀር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ሰፊ የማለፍ ዕድል ይኖራታል። ዋሊያዎቹ ለመጨረሻው የምድቡ ቸዋታ ዛሬ ኮትዲቯር አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም የብሔራዊ ቡድን አባላት "ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው ያስገኙት ድል ትልቅ አርአያነት አለው" በማለት እስካሁን ያስመዘገቡትን ውጤት አድንቀው ለቀጣዩ ጨዋታ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። 33ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወሳል። | ኢትዮጵያ ጫፍ በደረሰችበት የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሰባት አገራት ትላንት ተለዩ ትላንት በተካሄደ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወደ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ተጨማሪ ሰባት አገራት ተለዩ። ጋምቢያ፣ ኮሞሮስ፣ ጋቦን፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ዚምባብዌ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ናቸው ወደ አህጉራዊው ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡት አገራት ናቸው። ጋምቢያ አንጎላን በሜዳዋ 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አልፋለች። በምድብ አራት የምትገኘው ጋምቢያ ከሁለቱ አላፊ ቡድኖች አንዷ የሚያደርጋትን ወሳኝ ጎል አሳን ሴሳይ ከዕረፍት መልስ አስገኝቷል። በዚህ ምድብ የምትገኘው ጋቦን ዲሞክራቲክ ኮንጎን 3 ለ 0 በማሸነፍ ሌላኛዋ አላፊ አገር ሆናለች። በዚህም ጋቦን የ2019ኙ ውድድር ካመለጣት በኋላ ወደ ውድድር መድረኩ ለመመለስ በቅታለች። ፒየር-ኤሚሪክ ኦባሜያንግ፣ ዴኒስ ቡዋንጋ እና አሮን ቡውፔንዛ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። ባለፉት 4 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተሳትፋ የነበረውች ኮንጎ፤ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። በካሜሩን አዘጋጅነት ለመኪሄደው ውድድር ለማለፍ በምድብ 6 የምትገኘው ግብጽ የሚያስፈልጋትን አንድ ነጥብ ለማግኘት ከኬንያ ጋር ተጫውታ 1 ለ 1 አቻ ተለያይታለች። ፈርኦኖቹ ከኮሞሮስ ጋር እኩል ዘጠኝ ነጥብ ይዘዋል። ኬንያ አራት ነጥብ ሲኖራት ቶጎ በሁለት ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች። በናይሮቢ በተካሄደው ጨዋታ ማግዲ አፍሻ በሁለተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ግብጽ ቀዳሚ ሆናለች። ከእረፍት መልስ ኬንያ በአብደላህ ሃስ አማካኝነት አቻ ለመሆን ችላለች። ቀድም ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ መሳተፏን ያረጋገጠችው ኮሞሮስ ከሜዳዋ ውጪ ከቶጎ ጋር 0 ለ 0 ተለያይታለች። ከዚህ በፊት በውድድሩ መሳተፍ ያልቻሉት ቡድኖች ከ2019 ጀምሮ 16 የነበረው የተወዳዳሪ አገራት ቁጥር ወደ 24 በማደጉ ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል። ከምድብ ሦስት ለማለፍ ከደቡብ አፍሪካ ጋር 1 ለ 1 በሆነ ውጤት አቻ በመውጣት ጋና ወደ ውድድሩ የሚያስገባትን ትኬት ቆርጣለች። መሐመድ ቁዱስ ከ2010 የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በኡራጓይ ተሸንፈው በወጡበት ስታዲየም ቀዳሚ የሚያደርጋቸውን ጎል ቢያስቆጥርም በደቂቃዎች ልዩነት ፐርሲ ታው ደቡብ አፍሪካን አቻ አድርጓል። ካለፉት 15 ውድድሮች በአንዱ ብቻ ያልተካፈሉት ጥቁሮቹ ከዋክብት አስር ነጥብ በመያዝ ከደቡብ አፍሪካ እኩል ሆነዋል። በስድስተኛው እና በመጨረሻው የምድቡ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ዘጠኝ ነጥብ ካላት ሱዳን ጋር ትጫወታለች። ጋና ከሱዳንም ሆነ ከባፋና ባፋናዎች ጋር በነበራት ጨዋታ ያላት ውጤት የተሻለ በመሆኑ የአራት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮኗ ከውድድሩ ውጭ የምትሆንበት ሁኔታ የለም። ዚምባብዌ ከሜዳዋ ውጪ ቦትስዋናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። አልጄሪያ በሌላ የምድቡ ጨዋታ ከዛምቢያ ጋር 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቃለች። በዚህም ዚምባብዌ እና አልጄሪያ ተያይዘው ሲያልፉ የ2012ቱ ውድድር አሸናፊ ዛምቢያ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ኤሚሊዮ ንሱ በመጨረሻው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ኢኳቶሪያል ጊኒ ታንዛኒያን 1ለ 0 በማሸነው ማለፏን አረጋግጣለች። ሊቢያን 5 ለ 2 በሆነ ውጤት ያሸነፈችው ቱኒዚያ ከምድብ አንድ ቀድማ ነበረ ለውድድሩ ማለፏን ያረጋገጠችው። በከፍተኛ ጎል ልዩነት ቢሸነፉም ሊቢያውያን ከሰባት ዓመታት እገዳ በኋላ ብሔራዊ ቡድናቸውን በሜዳው ሲጫወቱ ለማየት በመቻላቸው ተደስተዋል። በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ውድድር ላይ ከሚሳተፉ ቡድኖች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተለይተዋል። ኮሞሮስ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ዚምባብዌ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ እና አስተናጋጇ ካሜሩን በውድድሩ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። ኢትረዮጵያስ ምን ተስፋ አላት? በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር፣ ማደጋስካር እና ኒጀር ጋር የተመደበችው ኢትዮጵያ፤ በመጀመሪያው ጨዋታ በማደጋስካር አንድ ለባዶ ተሸንፋ የነበረ ሲሆን፤ በቀጣይ በባሕር ዳር በተደረገ ጨዋታ ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በመቀጠል ዋልያዎቹ ወደ ኒጀር ተጉዘው፤ አንድ ለባዶ ቢሸንፉም በመልሱ ጨዋታ ሦስት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። ዋልያዎቹ ከማደጋስካር ጋር በነበራቸው የምድብ ጨዋታ ደግሞ አራት ለባዶ በማሸነፍ ነው ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ መምራት የቻሉት። በምድቡ ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ ኮትዲቯር ከኒጀር የሚያደርጉት ሲሆን ጨዋታው በኮትዲቯር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ኢትዮጵያ በምድቡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ትላለች። ጨዋታው በኒጀር አሸናፊነት አልያም አቻ የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ዋልያዎቹ መሪነታቸውን አስጠብቀው ወደ መጨረሻው የምድብ ጨዋታ ይጓዛሉ ማለት ነው። ዋልያዎቹ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በኮትዲቯር የሚያደርጉ ሲሆን ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉትም ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን የምታሸንፍ ከሆነ በካሜሩን አዘጋጅነት በሚካሄደው ጨዋታ ተሳታፊነቷን የምታረጋግጥ ሲሆን፤ ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ በኒጀር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ሰፊ የማለፍ ዕድል ይኖራታል። ዋሊያዎቹ ለመጨረሻው የምድቡ ቸዋታ ዛሬ ኮትዲቯር አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም የብሔራዊ ቡድን አባላት "ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው ያስገኙት ድል ትልቅ አርአያነት አለው" በማለት እስካሁን ያስመዘገቡትን ውጤት አድንቀው ለቀጣዩ ጨዋታ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። 33ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56539796 |
0business
| ኤሎን መስክ ለትዊተር ሰማያዊ ምልክት በወር ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ | ኤሎን መስክ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት (ገጽ) መሆኑን የሚያመለክተውን ሰማያዊ ምልክት በስማቸው ለሚፈልጉ የትዊተር ተጠቃሚዎች ወርሃዊ ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ። በ44 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ የማህበራዊ ድረ-ገጹን ትዊተርን የገዛው ኤሎን መስክ ይህንን የወሰነው “የማያስፈልጉ መረጃዎችንና ማጭበርበሮችን ለመቆጣጠር ነው” ብሏል። በትዊተር አካውንት ከተጠቃሚዎች ስም ቀጥሎ ያለው ሰማያዊ ምልክት በዋነኝነት ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ገጻቸውን ለማረጋገጥ የሚጠቀሙበት ሲሆን ክፍያም የለውም። ይህ እርምጃ አስተማማኝ ምንጮችን ለመለየት ፈታኝ እንደሚያደርገው ተቺዎች ተናግረዋል። የዓለማችን ባለጸጋ የሆነው ኤሎን መስክ አክሎ እንደተናገረው የሚከፍሉ ተጠቃሚዎች ምላሽ ለማግኘት፣ ለፍለጋዎች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውና ከሌሎች በተለየ መልኩ ግማሽ ማስታወቂያ ብቻ በገፃቸው ላይ እንደሚደርስ ተናግሯል። “ስልጣን ለህዝቡ! ለሰማያዊ ስምንት ዶላር በወር!” በማለት ቢሊዮነሩ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሮ “የጌቶችና የጭሰኞች” ስርዓት በማለት የቀድሞውን የሰማያዊ ምልክት (ብሉ ቲክ) የማረጋገጫ ዘዴን ተችቷል። ከዚህ ቀደም ተጠቃሚዎች ብሉ ቲክ እንዲኖራቸው ለማድረግ አጠር ያለ የኦንላይን ማመልከቻ ቅጽን መሙላት አለባቸው። ብዙዎቹም ማንነታቸውን በማስመሰል ኢላማ ለሆኑ ታዋቂ ሰዎች ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች የታሰበ ነበር። ትዊተር ይህንን ያስተዋወቀው በአውሮፓውያኑ 2009 ነበር። ለዚህም መነሻ የሆነው ኩባንያው ታዋቂ ሰዎችን በማስመሰል የሚያጭበረብሩ አካላትን ለመከላከል በቂ ጥራት አላደረገም በሚል ክስ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ኤሎን መስክ ለዓመታት ትርፍ ያላስገኘውን የትዊተርን የቢዝነስ አሰራር ለማደስ እየሰራ ባለበት ወቅት ከባድ ፈተና ገጥሞታል። ትዊተር በማስታወቂያ ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ እንደሚፈልግም ተናግሯል። ከወዲሁ አንዳንድ ኩባንያዎች በእርሳቸው አመራር በትዊተር ገጽ ላይ የማስተዋወቁ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው እየገለጹ ነው። የመስክ የኤሌክትሪክ መኪና ኩባንያ ቴስላ ተቀናቃኝ የሆነው ጄኔራል ሞተርስ ባለፈው ሳምንት በትዊተር ላይ የሚያደርገውን ማስታወቂያዎችን ማቆሙን ተናግሯል ። | ኤሎን መስክ ለትዊተር ሰማያዊ ምልክት በወር ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ ኤሎን መስክ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት (ገጽ) መሆኑን የሚያመለክተውን ሰማያዊ ምልክት በስማቸው ለሚፈልጉ የትዊተር ተጠቃሚዎች ወርሃዊ ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ። በ44 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ የማህበራዊ ድረ-ገጹን ትዊተርን የገዛው ኤሎን መስክ ይህንን የወሰነው “የማያስፈልጉ መረጃዎችንና ማጭበርበሮችን ለመቆጣጠር ነው” ብሏል። በትዊተር አካውንት ከተጠቃሚዎች ስም ቀጥሎ ያለው ሰማያዊ ምልክት በዋነኝነት ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ገጻቸውን ለማረጋገጥ የሚጠቀሙበት ሲሆን ክፍያም የለውም። ይህ እርምጃ አስተማማኝ ምንጮችን ለመለየት ፈታኝ እንደሚያደርገው ተቺዎች ተናግረዋል። የዓለማችን ባለጸጋ የሆነው ኤሎን መስክ አክሎ እንደተናገረው የሚከፍሉ ተጠቃሚዎች ምላሽ ለማግኘት፣ ለፍለጋዎች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውና ከሌሎች በተለየ መልኩ ግማሽ ማስታወቂያ ብቻ በገፃቸው ላይ እንደሚደርስ ተናግሯል። “ስልጣን ለህዝቡ! ለሰማያዊ ስምንት ዶላር በወር!” በማለት ቢሊዮነሩ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሮ “የጌቶችና የጭሰኞች” ስርዓት በማለት የቀድሞውን የሰማያዊ ምልክት (ብሉ ቲክ) የማረጋገጫ ዘዴን ተችቷል። ከዚህ ቀደም ተጠቃሚዎች ብሉ ቲክ እንዲኖራቸው ለማድረግ አጠር ያለ የኦንላይን ማመልከቻ ቅጽን መሙላት አለባቸው። ብዙዎቹም ማንነታቸውን በማስመሰል ኢላማ ለሆኑ ታዋቂ ሰዎች ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች የታሰበ ነበር። ትዊተር ይህንን ያስተዋወቀው በአውሮፓውያኑ 2009 ነበር። ለዚህም መነሻ የሆነው ኩባንያው ታዋቂ ሰዎችን በማስመሰል የሚያጭበረብሩ አካላትን ለመከላከል በቂ ጥራት አላደረገም በሚል ክስ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ኤሎን መስክ ለዓመታት ትርፍ ያላስገኘውን የትዊተርን የቢዝነስ አሰራር ለማደስ እየሰራ ባለበት ወቅት ከባድ ፈተና ገጥሞታል። ትዊተር በማስታወቂያ ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ እንደሚፈልግም ተናግሯል። ከወዲሁ አንዳንድ ኩባንያዎች በእርሳቸው አመራር በትዊተር ገጽ ላይ የማስተዋወቁ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው እየገለጹ ነው። የመስክ የኤሌክትሪክ መኪና ኩባንያ ቴስላ ተቀናቃኝ የሆነው ጄኔራል ሞተርስ ባለፈው ሳምንት በትዊተር ላይ የሚያደርገውን ማስታወቂያዎችን ማቆሙን ተናግሯል ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c72z7eg9600o |
5sports
| የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠሪያውን እና የብሮድካስት መብቱን ሊሸጥ ነው | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ ማውጣቱን ገለፀ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማህበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ተናግረዋል። አንደኛው፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም አቀፍ እንዲሁም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ማውጣቱን ገልፀዋል። ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ የሚጠራበትን ስም ለመሸጥ ጨረታ ማውጣታቸውን አቶ ክፍሌ ሰይፈ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 16 ቡድኖች በጋራ ያቋቋሙትና በንግድ ድርጅትነት የተመዘገበ ማህበር መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ጨምረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት በዝግ ስታድየም የሚታይ ከሆነ፣ እንዲሁም ምርመራ እንዲደረግ ግዴታ የሚቀመጥ ከሆነ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቅ እነዚህን ነገሮች ለመሸፈን በማሰብ የተለየ አማራጭ ማሰባቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የአክሲዮን ማህበሩ አባል ቡድኖች ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁም በአፍሪካም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ያሉ የስፖርት ቡድኖች እንደሚያደርጉት የስፖርት ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ከጨረታው የሚገኘው አብዛኛው ገቢ የሚሰጠው ለእግርኳስ ቡድኖቹ መሆኑን የተናገሩት አቶ ክፍሌ፣ ቀሪው የድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል ብለዋል። ማሕበሩ የተቋቋመው የእግር ኳስ ቡድኖቹ ከመንግሥት ድጎማ ነፃ እንዲወጡ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚሳተፉ 16 ክለቦች መካከል ሁለቱ ቡድኖች ብቻ የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ደጋፊ አካላት (ስፖንሰርሺፕ) እንዳላቸው ገልፀዋል። ቀሪዎቹ 14 የእግር ኳስ ቡድኖች የከተማ ክለቦች ወይም ስፖንሰር የሌላቸው መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህን ቡድኖች በገቢ ራስን ማስቻል የዚህ ማህበር ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ችግሮች እንዳለባቸው የሚጠቅሱት ኃላፊው፣ በአመራር ችግር ደሞዝ የማይከፈላቸው በመኖራቸው ከጨረታው የሚገኘው ገንዘብ አብዛኛው ለክለቦች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህንን የገቢ ክፍፍልን በሚመለከት የማስፈፀሚያ ሰነድ ተዘጋጅቶ 16ቱም ክለቦች መስከረም ወር ላይ ውይይት ካደረጉበት በኋላ የሚፀድቅ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ማህበሩ በርካታ ተጫራቾች እናገኛለን ብሎ ያሰበው ከዓለም አቀፍ ተጫራጮች መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጨረታው ላይ የአገር ውስጥ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉ የገለፁት አቶ ክፍሌ በሚወዳደሩበት ወቅት ምክረ ሃሳብ አዘጋጅተው ገቢ የሚያገኙበትን መልክ እና የድርሻ ክፍፍሉ ምን እንደሚመስል ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፟። በኢትዮጵያ እግርኳስ ረዥም ታሪክ ቢኖረውም፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከማይሸጥባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠሪያውን እና የብሮድካስት መብቱን ሊሸጥ ነው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ ማውጣቱን ገለፀ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማህበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ተናግረዋል። አንደኛው፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም አቀፍ እንዲሁም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ማውጣቱን ገልፀዋል። ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ የሚጠራበትን ስም ለመሸጥ ጨረታ ማውጣታቸውን አቶ ክፍሌ ሰይፈ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 16 ቡድኖች በጋራ ያቋቋሙትና በንግድ ድርጅትነት የተመዘገበ ማህበር መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ጨምረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት በዝግ ስታድየም የሚታይ ከሆነ፣ እንዲሁም ምርመራ እንዲደረግ ግዴታ የሚቀመጥ ከሆነ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቅ እነዚህን ነገሮች ለመሸፈን በማሰብ የተለየ አማራጭ ማሰባቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የአክሲዮን ማህበሩ አባል ቡድኖች ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁም በአፍሪካም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ያሉ የስፖርት ቡድኖች እንደሚያደርጉት የስፖርት ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ከጨረታው የሚገኘው አብዛኛው ገቢ የሚሰጠው ለእግርኳስ ቡድኖቹ መሆኑን የተናገሩት አቶ ክፍሌ፣ ቀሪው የድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል ብለዋል። ማሕበሩ የተቋቋመው የእግር ኳስ ቡድኖቹ ከመንግሥት ድጎማ ነፃ እንዲወጡ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚሳተፉ 16 ክለቦች መካከል ሁለቱ ቡድኖች ብቻ የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ደጋፊ አካላት (ስፖንሰርሺፕ) እንዳላቸው ገልፀዋል። ቀሪዎቹ 14 የእግር ኳስ ቡድኖች የከተማ ክለቦች ወይም ስፖንሰር የሌላቸው መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህን ቡድኖች በገቢ ራስን ማስቻል የዚህ ማህበር ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ችግሮች እንዳለባቸው የሚጠቅሱት ኃላፊው፣ በአመራር ችግር ደሞዝ የማይከፈላቸው በመኖራቸው ከጨረታው የሚገኘው ገንዘብ አብዛኛው ለክለቦች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህንን የገቢ ክፍፍልን በሚመለከት የማስፈፀሚያ ሰነድ ተዘጋጅቶ 16ቱም ክለቦች መስከረም ወር ላይ ውይይት ካደረጉበት በኋላ የሚፀድቅ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ማህበሩ በርካታ ተጫራቾች እናገኛለን ብሎ ያሰበው ከዓለም አቀፍ ተጫራጮች መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጨረታው ላይ የአገር ውስጥ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉ የገለፁት አቶ ክፍሌ በሚወዳደሩበት ወቅት ምክረ ሃሳብ አዘጋጅተው ገቢ የሚያገኙበትን መልክ እና የድርሻ ክፍፍሉ ምን እንደሚመስል ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፟። በኢትዮጵያ እግርኳስ ረዥም ታሪክ ቢኖረውም፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከማይሸጥባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። | https://www.bbc.com/amharic/53864758 |
3politics
| የትራምፕ መኖርያ ቤት በፖሊስ መፈተሹን ተከትሎ የፀጥታ አካላት እንዳይገደሉ ተፈርቷል | ባለፈው ሳምንት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት (ማር ኤ ላጎ) ላይ ድንገተኛ አሰሳና ፍተሻ ተደርጎበት ነበር። ይህን ተከትሎ በአሜሪካ የፀጥታ አካላት ላይ ስጋት ነግሷል። በድርጊቱ የተቆጡ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይል አባላትን እያስፈራሩ ነው። የአሜሪካ የፀጥታ እና ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለባልደረቦቻቸው ባስተላለፉት የተጠንቀቁ መልዕክት ‘አደጋ እንደተደቀነባችሁ አውቃችሁ በጥንቃቄ ተንቀሳቀሱ’ ሲል ያሳስባል። ከዚህ የትራምፕ መኖሪያ ቤት ፍተሻ በኋላ በተለይም በፖሊሶች፣ በዳኞች፣ በዐቃቤ ሕግ ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው የግድያ ዛቻ በእጥፍ ጨምሯል። ባለሥልጣናቱ በዚህ የተጠንቀቁ ማሳሰቢያቸው ሁሉም የፀጥታ አባላት ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል። ኤፍቢአይ የአንድን የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቤት ዘልቆ ገብቶ ብርበራ ሲያደርግ ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው። በፍሎሪዳ ፓልም ቢች የባሕር ዳርቻ የሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ ማር ኤ ላጎ መኖርያ ቤት ድንገተኛ ብርበራ ከተደረገበት በኋላ በርካታ ሰነዶች ማግኘቱን የአሜሪካ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ ተገኙ ከተባሉ ሰነዶች መካከል በዶናልድ ትራምፕ ቤት በፍጹም መገኘት ያልነበረባቸው ጥብቅ የአገር ምሥጢሮች ይገኙበታል ተብሏል። የአገር ምሥጢሮች ‘ጥብቅ ምሥጢር’፣ ምሥጢር እና ለሕዝብ ያልተፈቀደ በሚል ይከፈላሉ። ጥብቅ የአገር ምሥጢር ተደርገው ከተቀመጡ ሰነዶች መካከል ደግሞ እጅግ ጥብቅ የአገር ምሥጢር ተብለው የተሰነዱ ይገኙበታል። እነዚህ ሰነዶች በአሜሪካ አስተዳደር ውስጥ ሦስት እና አራት የተመረጡ የደኅንነት ሰዎች ብቻ ሊያውቋቸው የሚገቡ ፍጹም ምሥጢር ሆነው መቆየት የነበረባቸው ናቸው ተብሏል። እነዚህ ሰነዶች ለምን በዶናልድ ትራምፕ ቤት ተገኙ የሚለውን ፖሊስ እየመረመረ ነው። ትራምፕ በበኩላቸው እነዚህ ዶሴዎች ቀድሞውንም ከምሥጢራዊ ሰነድነት ሰንዱቅ እንዲወጡ መደረጋቸውን ይናገራሉ። ይህን ውዝግብ ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ትራምፕ ራሳቸውን በሚያስተዳድሩት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች ጭምር በመጠቀም ለፖሊሶችና የፀጥታ አካላት የግድያ ዛቻ እያደረሱ ነው። እነዚህ ዛቻዎች ዛቻ ብቻ አይደሉም። ለምሳሌ ባለፈው አርብ በኦሃዮ ግዛት የኤፍቢአይ ቢሮን ጥሶ ጥቃት ሊፈጽም የነበረ አንድ ወጣት በፖሊስ ተገድሏል። ሟች ይህን የግድያ ሙከራ ከማድረጉ በፊት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚባለው የትራምፕ ማኅበራዊ የትስስር መድረክ ላይ የፀጥታ አካላትን ለመግደል እንደተዘጋጀ ጽፎ ነበር። አንዳንድ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ይህ በትራምፕ ላይ እየተደረገ ያለው ማሳደድ እሳቸውን በቀጣይነት ዳግም ወደ ሥልጣን እንዳይመጡ ለማሸማቀቅ በዲሞክራቶች የተጎነጎነ ሴራ ነው ብለው ሲተቹ ቆይተዋል። ይህ ትችት እየሰፋ በመሄዱ ፖሊስ በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ ያገኘበትን ማስረጃ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ተገዷል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ አንድ ምርመራ ሳይገባደድ ለፍርድ ቤት ብርበራ እንዲያካሄድ እንዲፈቀድለት ያቀረባቸውን መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ አያደርግም ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ብርበራውን ተከትሎ ሦስት ፓስፖርቶቼ ተወስደውብኛል ብለዋል። ብርበራውን ተከትሎ በተገኙ ሰነዶች ትራምፕ አዲስ ክስ ይከፈትባቸው እንደሆነ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ትናንት ሰኞ ምሽት ዐቃቤ ሕግ የዶናልድ ትራምፕ ወዳጅና ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒን ለመክሰስ ሰነዶች እየሟሉ እንደሆነ ተዘግቧል። | የትራምፕ መኖርያ ቤት በፖሊስ መፈተሹን ተከትሎ የፀጥታ አካላት እንዳይገደሉ ተፈርቷል ባለፈው ሳምንት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት (ማር ኤ ላጎ) ላይ ድንገተኛ አሰሳና ፍተሻ ተደርጎበት ነበር። ይህን ተከትሎ በአሜሪካ የፀጥታ አካላት ላይ ስጋት ነግሷል። በድርጊቱ የተቆጡ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይል አባላትን እያስፈራሩ ነው። የአሜሪካ የፀጥታ እና ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለባልደረቦቻቸው ባስተላለፉት የተጠንቀቁ መልዕክት ‘አደጋ እንደተደቀነባችሁ አውቃችሁ በጥንቃቄ ተንቀሳቀሱ’ ሲል ያሳስባል። ከዚህ የትራምፕ መኖሪያ ቤት ፍተሻ በኋላ በተለይም በፖሊሶች፣ በዳኞች፣ በዐቃቤ ሕግ ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው የግድያ ዛቻ በእጥፍ ጨምሯል። ባለሥልጣናቱ በዚህ የተጠንቀቁ ማሳሰቢያቸው ሁሉም የፀጥታ አባላት ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል። ኤፍቢአይ የአንድን የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቤት ዘልቆ ገብቶ ብርበራ ሲያደርግ ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው። በፍሎሪዳ ፓልም ቢች የባሕር ዳርቻ የሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ ማር ኤ ላጎ መኖርያ ቤት ድንገተኛ ብርበራ ከተደረገበት በኋላ በርካታ ሰነዶች ማግኘቱን የአሜሪካ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ ተገኙ ከተባሉ ሰነዶች መካከል በዶናልድ ትራምፕ ቤት በፍጹም መገኘት ያልነበረባቸው ጥብቅ የአገር ምሥጢሮች ይገኙበታል ተብሏል። የአገር ምሥጢሮች ‘ጥብቅ ምሥጢር’፣ ምሥጢር እና ለሕዝብ ያልተፈቀደ በሚል ይከፈላሉ። ጥብቅ የአገር ምሥጢር ተደርገው ከተቀመጡ ሰነዶች መካከል ደግሞ እጅግ ጥብቅ የአገር ምሥጢር ተብለው የተሰነዱ ይገኙበታል። እነዚህ ሰነዶች በአሜሪካ አስተዳደር ውስጥ ሦስት እና አራት የተመረጡ የደኅንነት ሰዎች ብቻ ሊያውቋቸው የሚገቡ ፍጹም ምሥጢር ሆነው መቆየት የነበረባቸው ናቸው ተብሏል። እነዚህ ሰነዶች ለምን በዶናልድ ትራምፕ ቤት ተገኙ የሚለውን ፖሊስ እየመረመረ ነው። ትራምፕ በበኩላቸው እነዚህ ዶሴዎች ቀድሞውንም ከምሥጢራዊ ሰነድነት ሰንዱቅ እንዲወጡ መደረጋቸውን ይናገራሉ። ይህን ውዝግብ ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ትራምፕ ራሳቸውን በሚያስተዳድሩት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች ጭምር በመጠቀም ለፖሊሶችና የፀጥታ አካላት የግድያ ዛቻ እያደረሱ ነው። እነዚህ ዛቻዎች ዛቻ ብቻ አይደሉም። ለምሳሌ ባለፈው አርብ በኦሃዮ ግዛት የኤፍቢአይ ቢሮን ጥሶ ጥቃት ሊፈጽም የነበረ አንድ ወጣት በፖሊስ ተገድሏል። ሟች ይህን የግድያ ሙከራ ከማድረጉ በፊት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚባለው የትራምፕ ማኅበራዊ የትስስር መድረክ ላይ የፀጥታ አካላትን ለመግደል እንደተዘጋጀ ጽፎ ነበር። አንዳንድ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ይህ በትራምፕ ላይ እየተደረገ ያለው ማሳደድ እሳቸውን በቀጣይነት ዳግም ወደ ሥልጣን እንዳይመጡ ለማሸማቀቅ በዲሞክራቶች የተጎነጎነ ሴራ ነው ብለው ሲተቹ ቆይተዋል። ይህ ትችት እየሰፋ በመሄዱ ፖሊስ በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ ያገኘበትን ማስረጃ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ተገዷል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ አንድ ምርመራ ሳይገባደድ ለፍርድ ቤት ብርበራ እንዲያካሄድ እንዲፈቀድለት ያቀረባቸውን መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ አያደርግም ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ብርበራውን ተከትሎ ሦስት ፓስፖርቶቼ ተወስደውብኛል ብለዋል። ብርበራውን ተከትሎ በተገኙ ሰነዶች ትራምፕ አዲስ ክስ ይከፈትባቸው እንደሆነ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ትናንት ሰኞ ምሽት ዐቃቤ ሕግ የዶናልድ ትራምፕ ወዳጅና ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒን ለመክሰስ ሰነዶች እየሟሉ እንደሆነ ተዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c03z223d85no |
3politics
| ኡሁሩ ኬንያታ በአገራቸውና በአካባቢው አገራት እንዴት ይታወሳሉ? | ከኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ በሚነሱ የሰላም ድርድሮች ላይ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በበለጠ ሲጠቀሱ ይሰማል። በተለይም የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ወገንተኝነትን አሳይተዋል በሚል በትግራይ ኃይሎች የሚወቀሱ ሲሆን፣ በትግራይ ያለውን ሁኔታ እንደተከታተሉት የተነገራላቸው ኡሁሩም አደራዳሪ ይሁኑ ሲሉም ተሰምተዋል። ከአምስት ወራት የተኩስ አቁም አዋጅ በኋላ ያገረሸው ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ የተለያዩ ተቋማትና አገራት ጥረት እያደረጉ ሲሆን፣ ኡሁሩ ከሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ምን አይነት ሚና ሊኖራቸው ይችል ይሆን የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተው ነበር። በአሁኑ ወቅት ይህ ጥያቄ ምላሽ ያገኘ ሲሆን አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ኡሁሩ የሚያከናውትን ተግባር እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል። ሩቶ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት የሚያስመሰግን ተግባር አከናውነዋል ብለዋል። “በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና የተጀመሩ የሰላም ጥረቶች ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ” ያሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት ሩቶ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጀመሩትን ሰላም የማምጣት ጥረት ለመቀጠል ተስማምተዋል ብለዋል። በኢትዮጵያ እና በቀጣናው ያከናወኑት ተግባር እንዳለ ሆኖ በአገራቸው ኬንያስ እንዴት ይታወሳሉ? ወቅቱ ከአራት ዓመት በፊት ነበር። አንድ ተማሪ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሥልጣን ሲሰናበቱ እንዴት መታወስ ይፈልጋሉ? ብሎ ጠየቃቸው። ለአሁሩ ያልጠበቁት ነገር ቢሆንም ሁለት ጉዳዮች ላይ አትኩሮት ሰጥተው ተናግረዋል። “አንደኛ አንድነቱን የጠበቀ፣ የተቀናጀ ማኅበረሰብን ማምጣት ችያለሁ። ሁለተኛ በሙስና ላይ የከፈትነውን ጦርነት ማሸነፍ ችለናል” ሲሉም ከፍተኛ ጭብጨባ ነው የጠበቃቸው። ከሁለት የሥልጣን ዘመናቸው በኋላ መንበራቸውን ለቀድሞ አጋራቸውና ለአሁኑ ተቃናቃኛቸው ዊሊያም ሩቶ ሥልጣን ባስረከቡበት ወቅት አሁሩ የጠቀሷቸውን ስኬቶች አሳክተው ይሆን? ሌሎች የሚጠቀሱባቸው ተግባራትስ ምን ይሆኑ? ኡሁሩ ለአገራዊ አንድነት ትልቅ ትርጉም ያለው እርምጃ ወስደዋል ከሚባልላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ በአውሮፓውያኑ 2018 ከተቃዋሚ መሪ እና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ጋር ፖለቲካ እርቅ ማሳያ የተባለው መጨባበጥ ነበር። በአውሮፓውያኑ 2017 የተደረገው ምርጫ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጎ በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ በዚህም ድጋሚ ምርጫ ኦዲንጋ ሳይሳተፉ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ራሳቸውን የሕዝብ መሪ በማለት የይስሙላ ቃለ ሐላ ሥነ ሥርዓት አካሂደው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ለወራት የዘለቀ አለመረጋጋት የተከተለ ሲሆን፣ የሁለቱ ፖለቲከኞች “የእጅ መጨባበጥ” ይህንን እንዲቋጭ አድርጎታል። ነገር ግን የኡሁሩ እና የኦዲንጋ ስምምነት በወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩት ዊሊያም ሩቶ በጥሩ መልኩ አልታየም። ዊሊያም ሩቶ የምግብ ዋስትናን የማሳደግ፣ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎትን ለማስፈን፣ መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማሳደግ የነበራቸውን ትልልቅ አጀንዳዎች እንዳይሳኩ ምክንያት ሆኗል ይላሉ የሁለቱ ፖለቲከኞች ጥምረት። ይህንንም ተከትሎ የኡሁሩ ኬንያታ እና የዊሊያም ሩቶ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን፣ ኡሁሩ ለዊሊያም ሩቶ ያላቸውን ድጋፍ በማቆም በምትኩ ተቀናቃኛቸው የነበሩትን ራይላ ኦዲንጋን በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል። በኡሁሩ ኬንያታ እና በምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ መካከል ያለው ውጥረት ከምርጫው በኋላም ቀጥሏል። ዊሊያም ሩቶ በመመረጣቸው ደስተኛ አለመሆናቸውን የተናገሩት ኡሁሩ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ያስተላለፉትም ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሰየማቸው አንድ ቀን በፊት ነው። ኡሁሩ ኬንያታ አስበውት የነበረው አንድነት ይህንን ላይሆን ቢችልም፣ በአውሮፓውያኑ 2007 የተከሰተውን የምርጫ ውዝግብ ተከትሎ በነበረ የብሔር ግጭት 1200 ሰዎችን በሞቱባትና እንዲሁም በርካታ ሺዎች በተፈናቀሉባት አገር ወሳኝ ነበር ተብሏል። በተለይም በቅርቡ የነበረው ምርጫ በሰላም መጠናቀቅ ተንታኞች እንደሚያምኑት ኡሁሩ የራሳቸው ዕጩ ራይላ ኦዲንጋ ቢሸነፉም አንድነትን ለማምጣት እና የጋራ ማኅበረሰብ ለመገንባት ያደረጉትን ጥረት አሳክቷል። የሁለቱ ፓለቲከኞች መጨባበጥ ሁሉም የሚሳተፉበት እና የመገለልም ስሜትን ያስወገደ እንደሆነ በማሲንዴ ሙሊሮ ዩኒቨርስቲ የሥነ ጽሁፍ እና ኮሚዩኒኬሸን ፕሮፌሰር የሆኑት ኤጋሪ ካባጂ ይናገራሉ። ሆኖም በኡሁሩ እና በራይላ ኦዲንጋ መካከል የተደረገው እርቅ በተቃዋሚ ዘንድ ክፍተትን ፈጥሯል። የመንግሥትን ኃላፊነት የሚቆጣጠር፣ መንግሥት ያልተገባ ተግባር ሲፈፅም የሚፈትሽ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር ምክንያት ሆኗል ይላሉ የፖለቲካ ተንታኟ ኔሪማ ዋኮ ኦጂዋ። ይህም ኡሁሩ ኬንያታ ሙስናን እና የሕዝብ ሃብት ምዝበራን ማስቆም ያለመቻላቸው ሚና ሳይጫወት እንዳልቀረም ተንታኝዋ ያስረዳሉ። ለራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ወቅት ሙሰኞችን ለመቆጣጠር ችላ ብለው እንደነበር አምነዋል። እንዲሁም በአውሮፓውያኑ 2012 አገሪቱ በየቀኑ 2 ቢሊዮን የኬንያ ሸልንግ (17 ሚሊዮን ዶላር) በሙስና በየቀኑ ታጣለች ብለዋል። ይህንንም አስመልክቶ “ፕሬዝዳንቱ ካወቁ በዚህ ጉዳይ ላይ ለምን አንድ ነገር አላደረጉም? በርካታ ጉዳዮች ፍርድ ቤት ቢሆኑም ፍርድ ማግኘት አልተቻለም” ሲሉ በኮዲ አፍሪካ የግብር ኤክስፐርት የሆኑት ኒኪል ሂራ ይጠይቃሉ። የኡሁሩ አስተዳደር በአገሪቱ ውስጥ ግድቦች እና ስታዲየም በመገንባት፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች ዝርጋታ፣ የናይሮቢ ፈጣን የባቡር መንገድን ጨምሮ የባቡር ሃዲዶች ግንባታ በመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሷል። እነዚህ ኢንቨስትመንቶች የተከናወኑት በከፍተኛ ብድር ሲሆን ፈሶባቸዋል የተባለው ወጪም ጥያቄ አስነስቷል። ለምሳሌ በቻይና የተገነባው ከሞምባሳ እስከ ናይሮቢ የተዘረጋው የባቡር መስመር 3.2 ቢሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን፣ ይህም በጎረቤት አገራት ታንዛንያ እና ኢትዮጵያ ከተከናወኑ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ጋር ሲነፃፀሩ ዋጋው እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። በቀጣዮቹ ዓመታት መመለስ ያለባት ብድርም ጣራ እንዲነካ አድርጎታል። በአውሮፓውያኑ 2021 መገባደጃ ላይ የአገሪቱ እዳ 72.6 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ ይህም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ውስጥ 68 በመቶ ነው። ኡሁሩ በአውሮፓውያኑ 2013 ወደ ሥልጣን ሲመጡ 38 በመቶ ነበር። የምሥራቅ አፍሪካ ግዙፉን ኢኮኖሚ ለማፋጠን አገሪቱ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን መገንባት እንደሚያስፈልጋት ታዛቢዎች ቢስማሙም፣ የገንዘብ አያያዝ በአግባቡ ጥቅም ላይ አልዋለም የሚለው ስጋት ፈጥሯል። ከፖሊሲዎች ባሻገር የኡሁሩ ቀለል ያለ ስብዕና በርካቶች የሚናፍቁት ነው። ፕሬዚዳንቱ በአደባባይ ላይ በሚታዩበት ሁሉ ከሰዎች ጋር እንደ ጓደኛ ነው የሚያወሩት። ኡሁሩ ጥበቃዎቻቸው ራቅ ብለው እየተከታተሏቸው በናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ በእግራቸው ሲዘዋወሩ ማየት፣ ኛማ ቾማ ብለው ኬንያውን የሚጠሩትን የሥጋ ጥብስ በገበያ ላይ በአካባቢው ሰዎች ተከብቦ መብላት እና የጎልፍ ጨዋታን ከታዳሚዎች ጋር እያወሩ ይከታተሉ ነበር። ለህፃናት እና ለታዋቂ ሰዎችም ቤተ መንግሥታቸው በመጋበዝና እንዲጎበኙ በማድረግ ሥልጣን ብቻ ያላቸው ብቻ የሚገቡበት የሚለውንና እንደ ብርቅና ድንቅ የነበረውን ሁኔታ ለመሻር ሞክረዋል። በተጨማሪም ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ከተጻፈው ውጪ በመውጣት ለሕዝብ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለውን ፍንጭም ይሰጡ ነበር። ምንም እንኳን በአገር አቀፍ ደረጃ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎትን ለመዘርጋት የነበራቸው ሰፊ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባይሆንም፣ የሆስፒታል አልጋዎች አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሏል፤ እንዲሁም አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተዋል። ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኬንያ የምትታይበት ሁኔታ ባለፉት አስር አመታት ተሻሽሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተዘዋዋሪ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ኬንያ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረገችውን ወረራ አውግዛለች። በተባበሩት መንግሥታት የኬንያ አምባሳደር ማርቲን ኪማኒ በማኅበራዊ ሚዲያ በሰፊው ባሰራጩት መግለጫቸው፣ አፍሪካ በቅኝ ግዛት ቀንበር ያሳለፈችውን ታሪክ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ካደረገችው ወረራ ጋር አነጻጽረውታል። በሩሲያና እና በዩክሬን ግጭት ውስጥ ቀጥታ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት ዝምታን መርጠዋል። ኡሁሩ ኬንያታ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር በመሆን በኢትዮጵያ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭቶችን ለመፍታት አደራዳሪ ሆነውም ሰርተዋል። በአጠቃላይ ኬንያ በኡሁሩ ኬንያታ የሥልጣን ዘመን ያልተጠበቁ ተግዳሮቶች ገጥሟት ነበር። ከእነዚህም መካከል በናይሮቢ እና በሌሎች ቦታዎች ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲሁም በከፊል በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የተከሰተው የኑሮ ውድነት ይጠቀሳሉ። ኡሁሩ ሥልጣናቸውን በሚያስረክቡበት ወቅት ለቀጣዩ መንግሥት የቤት ሥራዎች የሆኑት በምርጫ ዘመቻ ወቅት ተወዳዳሪዎቹ ቃል የገቡት የዜጎችን አንገብጋቢ ችግሮች መፍታት ነው። ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ የሥራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት መጨመርን የሚጠቀስ ሲሆን በነሐሴ ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 8.5 በመቶ ከፍ ብሏል። | ኡሁሩ ኬንያታ በአገራቸውና በአካባቢው አገራት እንዴት ይታወሳሉ? ከኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ በሚነሱ የሰላም ድርድሮች ላይ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በበለጠ ሲጠቀሱ ይሰማል። በተለይም የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ወገንተኝነትን አሳይተዋል በሚል በትግራይ ኃይሎች የሚወቀሱ ሲሆን፣ በትግራይ ያለውን ሁኔታ እንደተከታተሉት የተነገራላቸው ኡሁሩም አደራዳሪ ይሁኑ ሲሉም ተሰምተዋል። ከአምስት ወራት የተኩስ አቁም አዋጅ በኋላ ያገረሸው ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ የተለያዩ ተቋማትና አገራት ጥረት እያደረጉ ሲሆን፣ ኡሁሩ ከሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ምን አይነት ሚና ሊኖራቸው ይችል ይሆን የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተው ነበር። በአሁኑ ወቅት ይህ ጥያቄ ምላሽ ያገኘ ሲሆን አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ኡሁሩ የሚያከናውትን ተግባር እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል። ሩቶ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት የሚያስመሰግን ተግባር አከናውነዋል ብለዋል። “በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና የተጀመሩ የሰላም ጥረቶች ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ” ያሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት ሩቶ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጀመሩትን ሰላም የማምጣት ጥረት ለመቀጠል ተስማምተዋል ብለዋል። በኢትዮጵያ እና በቀጣናው ያከናወኑት ተግባር እንዳለ ሆኖ በአገራቸው ኬንያስ እንዴት ይታወሳሉ? ወቅቱ ከአራት ዓመት በፊት ነበር። አንድ ተማሪ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሥልጣን ሲሰናበቱ እንዴት መታወስ ይፈልጋሉ? ብሎ ጠየቃቸው። ለአሁሩ ያልጠበቁት ነገር ቢሆንም ሁለት ጉዳዮች ላይ አትኩሮት ሰጥተው ተናግረዋል። “አንደኛ አንድነቱን የጠበቀ፣ የተቀናጀ ማኅበረሰብን ማምጣት ችያለሁ። ሁለተኛ በሙስና ላይ የከፈትነውን ጦርነት ማሸነፍ ችለናል” ሲሉም ከፍተኛ ጭብጨባ ነው የጠበቃቸው። ከሁለት የሥልጣን ዘመናቸው በኋላ መንበራቸውን ለቀድሞ አጋራቸውና ለአሁኑ ተቃናቃኛቸው ዊሊያም ሩቶ ሥልጣን ባስረከቡበት ወቅት አሁሩ የጠቀሷቸውን ስኬቶች አሳክተው ይሆን? ሌሎች የሚጠቀሱባቸው ተግባራትስ ምን ይሆኑ? ኡሁሩ ለአገራዊ አንድነት ትልቅ ትርጉም ያለው እርምጃ ወስደዋል ከሚባልላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ በአውሮፓውያኑ 2018 ከተቃዋሚ መሪ እና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ጋር ፖለቲካ እርቅ ማሳያ የተባለው መጨባበጥ ነበር። በአውሮፓውያኑ 2017 የተደረገው ምርጫ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጎ በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ በዚህም ድጋሚ ምርጫ ኦዲንጋ ሳይሳተፉ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ራሳቸውን የሕዝብ መሪ በማለት የይስሙላ ቃለ ሐላ ሥነ ሥርዓት አካሂደው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ለወራት የዘለቀ አለመረጋጋት የተከተለ ሲሆን፣ የሁለቱ ፖለቲከኞች “የእጅ መጨባበጥ” ይህንን እንዲቋጭ አድርጎታል። ነገር ግን የኡሁሩ እና የኦዲንጋ ስምምነት በወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩት ዊሊያም ሩቶ በጥሩ መልኩ አልታየም። ዊሊያም ሩቶ የምግብ ዋስትናን የማሳደግ፣ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎትን ለማስፈን፣ መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማሳደግ የነበራቸውን ትልልቅ አጀንዳዎች እንዳይሳኩ ምክንያት ሆኗል ይላሉ የሁለቱ ፖለቲከኞች ጥምረት። ይህንንም ተከትሎ የኡሁሩ ኬንያታ እና የዊሊያም ሩቶ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን፣ ኡሁሩ ለዊሊያም ሩቶ ያላቸውን ድጋፍ በማቆም በምትኩ ተቀናቃኛቸው የነበሩትን ራይላ ኦዲንጋን በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል። በኡሁሩ ኬንያታ እና በምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ መካከል ያለው ውጥረት ከምርጫው በኋላም ቀጥሏል። ዊሊያም ሩቶ በመመረጣቸው ደስተኛ አለመሆናቸውን የተናገሩት ኡሁሩ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ያስተላለፉትም ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሰየማቸው አንድ ቀን በፊት ነው። ኡሁሩ ኬንያታ አስበውት የነበረው አንድነት ይህንን ላይሆን ቢችልም፣ በአውሮፓውያኑ 2007 የተከሰተውን የምርጫ ውዝግብ ተከትሎ በነበረ የብሔር ግጭት 1200 ሰዎችን በሞቱባትና እንዲሁም በርካታ ሺዎች በተፈናቀሉባት አገር ወሳኝ ነበር ተብሏል። በተለይም በቅርቡ የነበረው ምርጫ በሰላም መጠናቀቅ ተንታኞች እንደሚያምኑት ኡሁሩ የራሳቸው ዕጩ ራይላ ኦዲንጋ ቢሸነፉም አንድነትን ለማምጣት እና የጋራ ማኅበረሰብ ለመገንባት ያደረጉትን ጥረት አሳክቷል። የሁለቱ ፓለቲከኞች መጨባበጥ ሁሉም የሚሳተፉበት እና የመገለልም ስሜትን ያስወገደ እንደሆነ በማሲንዴ ሙሊሮ ዩኒቨርስቲ የሥነ ጽሁፍ እና ኮሚዩኒኬሸን ፕሮፌሰር የሆኑት ኤጋሪ ካባጂ ይናገራሉ። ሆኖም በኡሁሩ እና በራይላ ኦዲንጋ መካከል የተደረገው እርቅ በተቃዋሚ ዘንድ ክፍተትን ፈጥሯል። የመንግሥትን ኃላፊነት የሚቆጣጠር፣ መንግሥት ያልተገባ ተግባር ሲፈፅም የሚፈትሽ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር ምክንያት ሆኗል ይላሉ የፖለቲካ ተንታኟ ኔሪማ ዋኮ ኦጂዋ። ይህም ኡሁሩ ኬንያታ ሙስናን እና የሕዝብ ሃብት ምዝበራን ማስቆም ያለመቻላቸው ሚና ሳይጫወት እንዳልቀረም ተንታኝዋ ያስረዳሉ። ለራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ወቅት ሙሰኞችን ለመቆጣጠር ችላ ብለው እንደነበር አምነዋል። እንዲሁም በአውሮፓውያኑ 2012 አገሪቱ በየቀኑ 2 ቢሊዮን የኬንያ ሸልንግ (17 ሚሊዮን ዶላር) በሙስና በየቀኑ ታጣለች ብለዋል። ይህንንም አስመልክቶ “ፕሬዝዳንቱ ካወቁ በዚህ ጉዳይ ላይ ለምን አንድ ነገር አላደረጉም? በርካታ ጉዳዮች ፍርድ ቤት ቢሆኑም ፍርድ ማግኘት አልተቻለም” ሲሉ በኮዲ አፍሪካ የግብር ኤክስፐርት የሆኑት ኒኪል ሂራ ይጠይቃሉ። የኡሁሩ አስተዳደር በአገሪቱ ውስጥ ግድቦች እና ስታዲየም በመገንባት፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች ዝርጋታ፣ የናይሮቢ ፈጣን የባቡር መንገድን ጨምሮ የባቡር ሃዲዶች ግንባታ በመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሷል። እነዚህ ኢንቨስትመንቶች የተከናወኑት በከፍተኛ ብድር ሲሆን ፈሶባቸዋል የተባለው ወጪም ጥያቄ አስነስቷል። ለምሳሌ በቻይና የተገነባው ከሞምባሳ እስከ ናይሮቢ የተዘረጋው የባቡር መስመር 3.2 ቢሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን፣ ይህም በጎረቤት አገራት ታንዛንያ እና ኢትዮጵያ ከተከናወኑ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ጋር ሲነፃፀሩ ዋጋው እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። በቀጣዮቹ ዓመታት መመለስ ያለባት ብድርም ጣራ እንዲነካ አድርጎታል። በአውሮፓውያኑ 2021 መገባደጃ ላይ የአገሪቱ እዳ 72.6 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ ይህም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ውስጥ 68 በመቶ ነው። ኡሁሩ በአውሮፓውያኑ 2013 ወደ ሥልጣን ሲመጡ 38 በመቶ ነበር። የምሥራቅ አፍሪካ ግዙፉን ኢኮኖሚ ለማፋጠን አገሪቱ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን መገንባት እንደሚያስፈልጋት ታዛቢዎች ቢስማሙም፣ የገንዘብ አያያዝ በአግባቡ ጥቅም ላይ አልዋለም የሚለው ስጋት ፈጥሯል። ከፖሊሲዎች ባሻገር የኡሁሩ ቀለል ያለ ስብዕና በርካቶች የሚናፍቁት ነው። ፕሬዚዳንቱ በአደባባይ ላይ በሚታዩበት ሁሉ ከሰዎች ጋር እንደ ጓደኛ ነው የሚያወሩት። ኡሁሩ ጥበቃዎቻቸው ራቅ ብለው እየተከታተሏቸው በናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ በእግራቸው ሲዘዋወሩ ማየት፣ ኛማ ቾማ ብለው ኬንያውን የሚጠሩትን የሥጋ ጥብስ በገበያ ላይ በአካባቢው ሰዎች ተከብቦ መብላት እና የጎልፍ ጨዋታን ከታዳሚዎች ጋር እያወሩ ይከታተሉ ነበር። ለህፃናት እና ለታዋቂ ሰዎችም ቤተ መንግሥታቸው በመጋበዝና እንዲጎበኙ በማድረግ ሥልጣን ብቻ ያላቸው ብቻ የሚገቡበት የሚለውንና እንደ ብርቅና ድንቅ የነበረውን ሁኔታ ለመሻር ሞክረዋል። በተጨማሪም ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ከተጻፈው ውጪ በመውጣት ለሕዝብ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለውን ፍንጭም ይሰጡ ነበር። ምንም እንኳን በአገር አቀፍ ደረጃ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎትን ለመዘርጋት የነበራቸው ሰፊ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባይሆንም፣ የሆስፒታል አልጋዎች አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሏል፤ እንዲሁም አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተዋል። ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኬንያ የምትታይበት ሁኔታ ባለፉት አስር አመታት ተሻሽሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተዘዋዋሪ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ኬንያ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረገችውን ወረራ አውግዛለች። በተባበሩት መንግሥታት የኬንያ አምባሳደር ማርቲን ኪማኒ በማኅበራዊ ሚዲያ በሰፊው ባሰራጩት መግለጫቸው፣ አፍሪካ በቅኝ ግዛት ቀንበር ያሳለፈችውን ታሪክ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ካደረገችው ወረራ ጋር አነጻጽረውታል። በሩሲያና እና በዩክሬን ግጭት ውስጥ ቀጥታ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት ዝምታን መርጠዋል። ኡሁሩ ኬንያታ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር በመሆን በኢትዮጵያ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭቶችን ለመፍታት አደራዳሪ ሆነውም ሰርተዋል። በአጠቃላይ ኬንያ በኡሁሩ ኬንያታ የሥልጣን ዘመን ያልተጠበቁ ተግዳሮቶች ገጥሟት ነበር። ከእነዚህም መካከል በናይሮቢ እና በሌሎች ቦታዎች ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲሁም በከፊል በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የተከሰተው የኑሮ ውድነት ይጠቀሳሉ። ኡሁሩ ሥልጣናቸውን በሚያስረክቡበት ወቅት ለቀጣዩ መንግሥት የቤት ሥራዎች የሆኑት በምርጫ ዘመቻ ወቅት ተወዳዳሪዎቹ ቃል የገቡት የዜጎችን አንገብጋቢ ችግሮች መፍታት ነው። ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ የሥራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት መጨመርን የሚጠቀስ ሲሆን በነሐሴ ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 8.5 በመቶ ከፍ ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/crg2q0dv1gvo |
0business
| አልጄሪያ ለሥራ አጦች ወርሃዊ ክፍያ ልትሰጥ ነው | ከፍተኛ የሥራ እጦት ባለባት አልጄሪያ መንግስት ለወጣቶች የሥራ አጥነት ድጎማ እንደሚጀምር ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ። ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ተቡን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከ19 እስከ 40 ዓመት ለሆናቸው ሥራ ፈላጊዎች ከመጋቢት ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያ ያገኛሉ። ለክፍያው ብቁ የሆኑ ዜጎች ሥራ እስኪያገኙ ድረስ በወር ወደ 100 ዶላር የሚጠጋ ክፍያ እና አንዳንድ የሕክምና ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ። ተቡን አክለውም ይህን መሰሉን ጥቅማ ጥቅም በማስተዋወቅ ከአውሮፓ ውጪ አልጄሪያ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗን አስታውቀዋል። በአልጄሪያ ከ600 ሺህ በላይ ስራ አጦች እንዳሉም አክለዋል። | አልጄሪያ ለሥራ አጦች ወርሃዊ ክፍያ ልትሰጥ ነው ከፍተኛ የሥራ እጦት ባለባት አልጄሪያ መንግስት ለወጣቶች የሥራ አጥነት ድጎማ እንደሚጀምር ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ። ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ተቡን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከ19 እስከ 40 ዓመት ለሆናቸው ሥራ ፈላጊዎች ከመጋቢት ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያ ያገኛሉ። ለክፍያው ብቁ የሆኑ ዜጎች ሥራ እስኪያገኙ ድረስ በወር ወደ 100 ዶላር የሚጠጋ ክፍያ እና አንዳንድ የሕክምና ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ። ተቡን አክለውም ይህን መሰሉን ጥቅማ ጥቅም በማስተዋወቅ ከአውሮፓ ውጪ አልጄሪያ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗን አስታውቀዋል። በአልጄሪያ ከ600 ሺህ በላይ ስራ አጦች እንዳሉም አክለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60387663 |
2health
| የካንሰር ህዋስን የሚገድለው ቫይረስ ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ እንደሚሰጥ ተገለጸ | ቫይረስ በመጠቀም የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተገለጸ። የዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ በዚህ ሕክምና አንድ ካንሰር ታማሚ ሲፈወስ ሌላ ታማሚ ደግሞ ከፍተኛ ማገገም አሳይቷል። ለሕክምና የዋለው ቫይረስ በዋናነት የጉሮሮ መከርከር የሚያስከትለው ኸርፕስ ሲምፕሊክስ ሲሆን፣ ቫይረሱ እንዲዳከም ተደርጎ ነው ጥቅም ላይ የዋለው። በሕክምናው ዙሪያ ተጨማሪ ጥናቶች ቢያስፈልጉም፣ ለካንሰር ሕሙማን ተጨማሪ ዕድሜ የመስጠት ተስፋ እንዳለው ሳይንቲስቶች ገልጸዋል። የ39 ዓመቱ ክሪስቶፍ ዎጂኮስኪ በሕክምናው የሙከራ ደረጃ ከተሳተፉ አንዱ ነው። ምዕራብ ለንደን የሚኖረው ክሪስቶፍ በሮያል ማርስደን ኤንኤችኤስ ፋውንዴሽን ትረስት በሚገኘው የካንሰር ምርምር ማዕከል ለምርምር በጎ ፈቃደኛ ሆኗል። እአአ በ2017 ነበር የምራቅ አመንጪ ሕዋስ ካንሰር እንዳለበት የተነገረው። ቀዶ ሕክምና ቢደረግለትም አልተሻለውም። “የመኖር ተስፋ የለህም ተብዬ ነበር። የሕይወት ማገባደጃ እንክብካቤ እየተደረገልኝ ነበር። እጅግ ልብ ይሰብራል። አሁን ግን ተስፋ የሚሰጥ ምርምር ውስጥ መግባቴ ተስፋ አጭሮብኛል” ብሏል። የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ቫይረስ ሙከራ ከተደረገለት በኋላ ክሪስቶፍ ካንሰሩ ጠፍቶለታል። ለተከታታይ አምስት ሳምንታት በየሁለት ሳምንቱ መርፌ ይሰጠው ነበር። ሰውነቱ ውስጥ ያለው በካንሰር የተጎዳ ሕዋስ ላይ አነጣጥሮ ነው ቫይረሱ የሚሠራው። ይህም በሽታ የመከላከል አቅሙ እንዲዳብር አግዟል። በሙከራ ደረጃ አርፒ2 የተባለውን ቫይረስ በመርፌ ይወስዱ የነበሩት 40 ሰዎች ናቸው። ከመካከላቸው ከመርፌው በተጨማሪ ኒቮሎማብ የተባለ የካንሰር መድኃኒት በተጨማሪ ሲሰጣቸው የነበሩም ይገኙበታል። ክሪስቶፍን ጨምሮ አርፒ2 ከተሰጣቸው ዘጠኝ ሕሙማን ሦስቱ ሰውነታቸው ውስጥ ያለው ካንሰር ተመናምኗል። አርፒ2 መርፌን ከኒቮሎማብ መድኃኒት ጋር አጣምረው ከወሰዱ 30 ሰዎች ሰባቱም አገግመዋል። እንደ ድካም ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ውስን ነበሩ። ዋና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ኬቨን ሀሪንግተን ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ የምርምሩ ውጤት “እጅግ አስደናቂ” ነው። በተለያየ የካንሰር ደረጃ ላይ ላሉ ሕሙማን ተስፋ ሰጭ እንደሆነ አክለዋል። ሕክምናው እምብዛም ለማይታየው የዐይን ካንሰር እና የኢሶፎገስ ካንሰር እንደሚውልም ተመራማሪው ተናግረዋል። “በሕክምና ምርምር የመጀመሪያ ደረጃ እንዲህ ያለ ተስፋ ሰጭ ውጤት ማግኘት አልተለመደም። በርካታ የካንሰር ሕሙማንን ማከም ስንጀምር ምን ውጤት ልናገኝ እንደምንችል እስከማይ ጓጉቻለሁ” ብለዋል። ዶ/ር ማሪን ቤከር የተባሉት የካንሰር ተመራማሪ፣ የካንሰር ሕክምና አንድ ደረጃ ከፍ እንዲል ያገዘ ጥናት መሆኑን ተናግረዋል። “ሳይንቲስቶች ቫይረስን ተጠቅመው ካንሰርን መዋጋት እንደሚችሉ የደረሱበት ከ100 ዓመታት በፊት ነበር። ነገር ግን ደኅንነቱ በተጠበቀና በውጤታማ መንገድ ሕክምናውን ማስኬድ ቀላል አልሆነም። ይህ አዲሱ ሕክምና በጥቂት ሰዎች ሲመረመር ተስፋ ፈንጥቋል። ወደ ሰፊ ምርምር ማደግ አለበት” ሲሉ አስረድተዋል። ሳይንቲስቶች ቫይረስ ተጠቅመው ካንሰርን ለመዋጋት ሲሞክሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ቀደም የቆዳ ካንሰርን ለማከም ቫይረስ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሕክምና ፈቃድ ተሰጥቶታል። | የካንሰር ህዋስን የሚገድለው ቫይረስ ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ እንደሚሰጥ ተገለጸ ቫይረስ በመጠቀም የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተገለጸ። የዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ በዚህ ሕክምና አንድ ካንሰር ታማሚ ሲፈወስ ሌላ ታማሚ ደግሞ ከፍተኛ ማገገም አሳይቷል። ለሕክምና የዋለው ቫይረስ በዋናነት የጉሮሮ መከርከር የሚያስከትለው ኸርፕስ ሲምፕሊክስ ሲሆን፣ ቫይረሱ እንዲዳከም ተደርጎ ነው ጥቅም ላይ የዋለው። በሕክምናው ዙሪያ ተጨማሪ ጥናቶች ቢያስፈልጉም፣ ለካንሰር ሕሙማን ተጨማሪ ዕድሜ የመስጠት ተስፋ እንዳለው ሳይንቲስቶች ገልጸዋል። የ39 ዓመቱ ክሪስቶፍ ዎጂኮስኪ በሕክምናው የሙከራ ደረጃ ከተሳተፉ አንዱ ነው። ምዕራብ ለንደን የሚኖረው ክሪስቶፍ በሮያል ማርስደን ኤንኤችኤስ ፋውንዴሽን ትረስት በሚገኘው የካንሰር ምርምር ማዕከል ለምርምር በጎ ፈቃደኛ ሆኗል። እአአ በ2017 ነበር የምራቅ አመንጪ ሕዋስ ካንሰር እንዳለበት የተነገረው። ቀዶ ሕክምና ቢደረግለትም አልተሻለውም። “የመኖር ተስፋ የለህም ተብዬ ነበር። የሕይወት ማገባደጃ እንክብካቤ እየተደረገልኝ ነበር። እጅግ ልብ ይሰብራል። አሁን ግን ተስፋ የሚሰጥ ምርምር ውስጥ መግባቴ ተስፋ አጭሮብኛል” ብሏል። የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ቫይረስ ሙከራ ከተደረገለት በኋላ ክሪስቶፍ ካንሰሩ ጠፍቶለታል። ለተከታታይ አምስት ሳምንታት በየሁለት ሳምንቱ መርፌ ይሰጠው ነበር። ሰውነቱ ውስጥ ያለው በካንሰር የተጎዳ ሕዋስ ላይ አነጣጥሮ ነው ቫይረሱ የሚሠራው። ይህም በሽታ የመከላከል አቅሙ እንዲዳብር አግዟል። በሙከራ ደረጃ አርፒ2 የተባለውን ቫይረስ በመርፌ ይወስዱ የነበሩት 40 ሰዎች ናቸው። ከመካከላቸው ከመርፌው በተጨማሪ ኒቮሎማብ የተባለ የካንሰር መድኃኒት በተጨማሪ ሲሰጣቸው የነበሩም ይገኙበታል። ክሪስቶፍን ጨምሮ አርፒ2 ከተሰጣቸው ዘጠኝ ሕሙማን ሦስቱ ሰውነታቸው ውስጥ ያለው ካንሰር ተመናምኗል። አርፒ2 መርፌን ከኒቮሎማብ መድኃኒት ጋር አጣምረው ከወሰዱ 30 ሰዎች ሰባቱም አገግመዋል። እንደ ድካም ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ውስን ነበሩ። ዋና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ኬቨን ሀሪንግተን ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ የምርምሩ ውጤት “እጅግ አስደናቂ” ነው። በተለያየ የካንሰር ደረጃ ላይ ላሉ ሕሙማን ተስፋ ሰጭ እንደሆነ አክለዋል። ሕክምናው እምብዛም ለማይታየው የዐይን ካንሰር እና የኢሶፎገስ ካንሰር እንደሚውልም ተመራማሪው ተናግረዋል። “በሕክምና ምርምር የመጀመሪያ ደረጃ እንዲህ ያለ ተስፋ ሰጭ ውጤት ማግኘት አልተለመደም። በርካታ የካንሰር ሕሙማንን ማከም ስንጀምር ምን ውጤት ልናገኝ እንደምንችል እስከማይ ጓጉቻለሁ” ብለዋል። ዶ/ር ማሪን ቤከር የተባሉት የካንሰር ተመራማሪ፣ የካንሰር ሕክምና አንድ ደረጃ ከፍ እንዲል ያገዘ ጥናት መሆኑን ተናግረዋል። “ሳይንቲስቶች ቫይረስን ተጠቅመው ካንሰርን መዋጋት እንደሚችሉ የደረሱበት ከ100 ዓመታት በፊት ነበር። ነገር ግን ደኅንነቱ በተጠበቀና በውጤታማ መንገድ ሕክምናውን ማስኬድ ቀላል አልሆነም። ይህ አዲሱ ሕክምና በጥቂት ሰዎች ሲመረመር ተስፋ ፈንጥቋል። ወደ ሰፊ ምርምር ማደግ አለበት” ሲሉ አስረድተዋል። ሳይንቲስቶች ቫይረስ ተጠቅመው ካንሰርን ለመዋጋት ሲሞክሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ቀደም የቆዳ ካንሰርን ለማከም ቫይረስ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሕክምና ፈቃድ ተሰጥቶታል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c19jrd08nl2o |
5sports
| የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020፡ የትኞቹ አገራት የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 የሜዳሊያ ሰንጠረዥ | የ2020ው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር ከዚህ በፊት ከተካሄዱት በበለጠ በ33 የስፖርት አይነቶች ውድድሮች የሚካሄድበት ነው። ባለፈው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ይህ የኦሊምፒክ ውድድር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደዚህኛው ዓመት የተሸጋገረ ሲሆን ውድድሩ ጃፓን ውስጥ በሚገኙ 42 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ ይካሄዳል። ይህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽም በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚደረጉ ውድድሮች አገራት የሚያገኙትን የሜዳሊያ ዝርዝሮች የያዘ ሰንጠረዥ ነው። በዚህ ሰንጠረዥ ላይ ተወዳዳሪዎች የሚያገኙት ሜዳሊያ ከሚወክሉት አገር እና ከሚይዙት ደረጃ ጋር በየደቂቃው እየተከታተልን የምናቀርብበት ነው። በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ በውድድሩ የሚሳተፉ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ቡድኖች የሚያስመዘግቧቸው የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች በዝርዝር ይቀመጣሉ። | የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020፡ የትኞቹ አገራት የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 የሜዳሊያ ሰንጠረዥ የ2020ው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር ከዚህ በፊት ከተካሄዱት በበለጠ በ33 የስፖርት አይነቶች ውድድሮች የሚካሄድበት ነው። ባለፈው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ይህ የኦሊምፒክ ውድድር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደዚህኛው ዓመት የተሸጋገረ ሲሆን ውድድሩ ጃፓን ውስጥ በሚገኙ 42 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ ይካሄዳል። ይህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽም በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚደረጉ ውድድሮች አገራት የሚያገኙትን የሜዳሊያ ዝርዝሮች የያዘ ሰንጠረዥ ነው። በዚህ ሰንጠረዥ ላይ ተወዳዳሪዎች የሚያገኙት ሜዳሊያ ከሚወክሉት አገር እና ከሚይዙት ደረጃ ጋር በየደቂቃው እየተከታተልን የምናቀርብበት ነው። በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ በውድድሩ የሚሳተፉ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ቡድኖች የሚያስመዘግቧቸው የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች በዝርዝር ይቀመጣሉ። | https://www.bbc.com/amharic/57662275 |
3politics
| ባይደንን ከሞት ያተረፏቸው አፍጋናዊ አስተርጓሚ አሜሪካ ገቡ | ጆ ባይደን ሴናተር እያሉ አፍጋኒስታን ውስጥ ከአደጋ ያተረፏቸው አስተርጓሚና ቤተሰቦቻቸው ጓዛቸውን ጠቅልለው ከሃገራቸው መውጣታቸው ተሰምቷል። ጊዜው 2008 ነበር። በፈረንጆቹ። የአሁኑ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና ሌሎች ሴናተሮችን የያዘ ሄሊኮፕተር በከባድ አየር ምክንያት ከአንዲት የአፍጋኒስታን መንደር ለማረፍ ይገደዳል። ሥፍራው ለወትሮው የበረዶ ጥጥ የሚዘንብበትና ታጣቂዎች ጥቃት አከታትለው የሚያደርሱበት ነው። አማን ካሊል በአሜሪካ መንግሥት ተቀጥረው ከሚሠሩ አፍጋናዊያን መካከል ነበሩ። አሜሪካዊያኑን ሴናተሮች በመኪናቸው አሳፍረው ወደ ድብቅ ሥፍራም ወስደዋል። አስተርጓሚው ከባለፈው ነሐሴ ጀምሮ ወደ አሜሪካ የሚያስገባ ቪዛ ማግኘት አቅቷቸው ላይ ታች ሲኳትኑ ቆይተዋል። ነገር ግን አሁን በታሊባን ቁጥጥር ሥር ያለችውን ሃገራቸውን እንደ ሌሎች በርካታ ሺህ አፍጋናዊያን ወደኋላ ጥለው ወጥተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ፤ አስተርጓሚው ካሊልና ቤተሰቦቻቸው ከአፍጋኒስታን በሰላም ወጥተዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አስተርጓሚው ከአፍጋኒስታን የወጡት በአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ ነው። ይህ ጉዳይ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉልን ምስጋና እናቀርባለን" ብለዋል ቃል አቀባዩ። ካሊል የአሁኑን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጨምሮ ሴናተር ቻክ ሄግልና ሴናተር ጆን ኬሪን በአካል ካገኙ ከ13 ዓመታት በኋላ ወደ አሜሪካ የሚያስገባቸውን ቪዛ ለማግኘት እየጣሩ ነው። አሜሪካ አፍጋኒስታንን ለታሊባን ጥላ ከወጣች በኋላ ካሊል ፕሬዝደንት ባይደን እንዲያድኗቸው ጥሪ ማቅረባቸው አይዘነጋም። እሳቸውንና ሚስታቸውን እንዲሁም አምስት ልጆቻቸውን ከአፍጋኒስታን እንዲያስወጣቸው በሲኤንን ጥሪ ያቀረቡት ካሊል "አምናቸዋለሁ። ሁሉን የማድረግ አቅም እንዳላቸው አምናለሁ" ብለው ነበር። ባለፈው መስከረም ስለ አቶ ካሊል ጉዳይ የተጠየቁት የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አስተርጓሚው ላደረጉት ነገር አመስግነው መንግሥታቸው ሰውዬው ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ቁርጠኛ መሆኑን መናገራቸው አይዘነጋም። ካሊል አሁን ከአፍጋኒስታን ወጥተው ፓኪስታን እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ሂዩማን ፈርስት ኮአሊዥን የተሰኘውና አሁን ፓኪስታን የሚገኙ 200 አፍጋናዊያንን ከካቡል ያስወጣው የተራድዖ ድርጅት የባይደን አስተርጓሚ በሕይወት በመውጣታቸው ደስተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። አሜሪካ በአፍጋኒስታን በኢራቅ በነበሩት ጦርነቶች አሜሪካዊያን ወታደሮችን በማስተርጎምና በሌሎች መስኮች ላገዙ ዜጎች ልዩ ቪዛ አዘጋጅታለች። ካሊል ወደ ዋሺንግተን የሚያስገባቸውን ቪዛ አግኝተው ወደ አሜሪካ ያቀኑ እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም። ከፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ 70 ሺህ አፍጋኒስታናዊያን በአሜሪካ እርዳታ ሃገራቸውን ለቀው ወጥተዋል። | ባይደንን ከሞት ያተረፏቸው አፍጋናዊ አስተርጓሚ አሜሪካ ገቡ ጆ ባይደን ሴናተር እያሉ አፍጋኒስታን ውስጥ ከአደጋ ያተረፏቸው አስተርጓሚና ቤተሰቦቻቸው ጓዛቸውን ጠቅልለው ከሃገራቸው መውጣታቸው ተሰምቷል። ጊዜው 2008 ነበር። በፈረንጆቹ። የአሁኑ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና ሌሎች ሴናተሮችን የያዘ ሄሊኮፕተር በከባድ አየር ምክንያት ከአንዲት የአፍጋኒስታን መንደር ለማረፍ ይገደዳል። ሥፍራው ለወትሮው የበረዶ ጥጥ የሚዘንብበትና ታጣቂዎች ጥቃት አከታትለው የሚያደርሱበት ነው። አማን ካሊል በአሜሪካ መንግሥት ተቀጥረው ከሚሠሩ አፍጋናዊያን መካከል ነበሩ። አሜሪካዊያኑን ሴናተሮች በመኪናቸው አሳፍረው ወደ ድብቅ ሥፍራም ወስደዋል። አስተርጓሚው ከባለፈው ነሐሴ ጀምሮ ወደ አሜሪካ የሚያስገባ ቪዛ ማግኘት አቅቷቸው ላይ ታች ሲኳትኑ ቆይተዋል። ነገር ግን አሁን በታሊባን ቁጥጥር ሥር ያለችውን ሃገራቸውን እንደ ሌሎች በርካታ ሺህ አፍጋናዊያን ወደኋላ ጥለው ወጥተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ፤ አስተርጓሚው ካሊልና ቤተሰቦቻቸው ከአፍጋኒስታን በሰላም ወጥተዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አስተርጓሚው ከአፍጋኒስታን የወጡት በአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ ነው። ይህ ጉዳይ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉልን ምስጋና እናቀርባለን" ብለዋል ቃል አቀባዩ። ካሊል የአሁኑን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጨምሮ ሴናተር ቻክ ሄግልና ሴናተር ጆን ኬሪን በአካል ካገኙ ከ13 ዓመታት በኋላ ወደ አሜሪካ የሚያስገባቸውን ቪዛ ለማግኘት እየጣሩ ነው። አሜሪካ አፍጋኒስታንን ለታሊባን ጥላ ከወጣች በኋላ ካሊል ፕሬዝደንት ባይደን እንዲያድኗቸው ጥሪ ማቅረባቸው አይዘነጋም። እሳቸውንና ሚስታቸውን እንዲሁም አምስት ልጆቻቸውን ከአፍጋኒስታን እንዲያስወጣቸው በሲኤንን ጥሪ ያቀረቡት ካሊል "አምናቸዋለሁ። ሁሉን የማድረግ አቅም እንዳላቸው አምናለሁ" ብለው ነበር። ባለፈው መስከረም ስለ አቶ ካሊል ጉዳይ የተጠየቁት የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አስተርጓሚው ላደረጉት ነገር አመስግነው መንግሥታቸው ሰውዬው ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ቁርጠኛ መሆኑን መናገራቸው አይዘነጋም። ካሊል አሁን ከአፍጋኒስታን ወጥተው ፓኪስታን እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ሂዩማን ፈርስት ኮአሊዥን የተሰኘውና አሁን ፓኪስታን የሚገኙ 200 አፍጋናዊያንን ከካቡል ያስወጣው የተራድዖ ድርጅት የባይደን አስተርጓሚ በሕይወት በመውጣታቸው ደስተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። አሜሪካ በአፍጋኒስታን በኢራቅ በነበሩት ጦርነቶች አሜሪካዊያን ወታደሮችን በማስተርጎምና በሌሎች መስኮች ላገዙ ዜጎች ልዩ ቪዛ አዘጋጅታለች። ካሊል ወደ ዋሺንግተን የሚያስገባቸውን ቪዛ አግኝተው ወደ አሜሪካ ያቀኑ እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም። ከፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ 70 ሺህ አፍጋኒስታናዊያን በአሜሪካ እርዳታ ሃገራቸውን ለቀው ወጥተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58880580 |
5sports
| አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ | የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትናንትናው እና በዛሬው እለት ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ኢሳያስ ጅራ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ። ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸንን በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት እንደተመረጡ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ሶስት እጩዎች ቀርበው የነበረ ሲሆን በእጩ ተወዳዳሪነት የቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅ እንዲሁም አቶ ቶኪቻ ዓለማየሁ 17 ድምፅ አግኝተዋል። ሦስቱ ለፕሬዚዳንትነት የቀረቡት ዕጩዎች ሁለት ክልልን እና አንድ የከተማ አስተደደርን ወክለው ነው የተወዳደሩት። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዳኛቸው ነገሮን (ዶ/ር) የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። በዛሬው ምርጫ በተጨማሪም ስድስት ወንዶችና ሶስት ሴቶች፣ ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚዎች የተመረጡ ሲሆን እነዚህም አዲሱ ቃሚሱ፣ ዳኛቸው ነገሮ፣ ሸረፋ ደለቾ፣ ሙራዶ አብዶ፣ አሰር አብርሃም፣ ሃቢባ ሲራጅ፣ ፋይዛ ረሻድ፣ብዙአየሁ ጀንበሩ ናቸው። ፌዴሬሽኑን በቀጣይነት የሚመሩት ፕሬዝዳንት ስፖርቱን ማሳደግ፣ ማዘመን እንዲሁም ብሔራዊ ቡድኑ ደረጃውን የጠበቀ መጫወቻ ሜዳ እንዲኖረው ማድረግ ከሚጠበቁበት ዐበይት ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ። ይህ ጠቅላላ ጉባኤ መጀመሪያ ጎንደር ከተማ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጓል። አቶ ኢሳያስ ጅራ ላለፉት አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት የመሩ ሲሆን፣ ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ በድጋሜ ተመርጠዋል። ከፌደሬሽኑ ውጪ የሴካፋ፣ የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ውድድር ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። አቶ ኢሳያስ የኦሮሚያ ክልልን ወክለው ነው የተወዳደሩት። ከአራት ዓመት በፊት በ2010 ዓ.ም፣ የጂማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ሥራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገሉ ባለበት ወቅት ነው ተወዳድረው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት። ከ20 ዓመታት በላይ በስፖርት አመራርነት የቆዩት አቶ ኢሳያስ፣ በጂማ እና በሰበታ እግር ኳስ ቡድኖች በአመራርነት ሠርተዋል። ባለፉት ዓመታት “ደረት የሚያስነፋም ባይሆን አንገት የማያስደፋ ሥራ” መስራታቸውን ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት ተናግረው ነበር። “ተጨባጭና በአይን የሚታይ ሥራ ሰርተናል” የሚሉት አቶ ኢሳያስ ዳግም ቢመረጡ የጀመሯቸውን መልካም ነገሮች ማስቀጠል፣ ሊሰሯቸው አቅደው በተለያየ ምክንያት ያልተሳኩትን ደግሞ ማከናወን እቅዳቸው ነው። ከእቅዳቸው መካከል ዐቢይ የሆነው “የክለቦች አደረጃጀት ላይ መሥራት” መሆኑን ተናግረዋል። | አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትናንትናው እና በዛሬው እለት ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ኢሳያስ ጅራ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ። ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸንን በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት እንደተመረጡ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ሶስት እጩዎች ቀርበው የነበረ ሲሆን በእጩ ተወዳዳሪነት የቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅ እንዲሁም አቶ ቶኪቻ ዓለማየሁ 17 ድምፅ አግኝተዋል። ሦስቱ ለፕሬዚዳንትነት የቀረቡት ዕጩዎች ሁለት ክልልን እና አንድ የከተማ አስተደደርን ወክለው ነው የተወዳደሩት። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዳኛቸው ነገሮን (ዶ/ር) የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። በዛሬው ምርጫ በተጨማሪም ስድስት ወንዶችና ሶስት ሴቶች፣ ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚዎች የተመረጡ ሲሆን እነዚህም አዲሱ ቃሚሱ፣ ዳኛቸው ነገሮ፣ ሸረፋ ደለቾ፣ ሙራዶ አብዶ፣ አሰር አብርሃም፣ ሃቢባ ሲራጅ፣ ፋይዛ ረሻድ፣ብዙአየሁ ጀንበሩ ናቸው። ፌዴሬሽኑን በቀጣይነት የሚመሩት ፕሬዝዳንት ስፖርቱን ማሳደግ፣ ማዘመን እንዲሁም ብሔራዊ ቡድኑ ደረጃውን የጠበቀ መጫወቻ ሜዳ እንዲኖረው ማድረግ ከሚጠበቁበት ዐበይት ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ። ይህ ጠቅላላ ጉባኤ መጀመሪያ ጎንደር ከተማ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጓል። አቶ ኢሳያስ ጅራ ላለፉት አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት የመሩ ሲሆን፣ ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ በድጋሜ ተመርጠዋል። ከፌደሬሽኑ ውጪ የሴካፋ፣ የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ውድድር ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። አቶ ኢሳያስ የኦሮሚያ ክልልን ወክለው ነው የተወዳደሩት። ከአራት ዓመት በፊት በ2010 ዓ.ም፣ የጂማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ሥራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገሉ ባለበት ወቅት ነው ተወዳድረው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት። ከ20 ዓመታት በላይ በስፖርት አመራርነት የቆዩት አቶ ኢሳያስ፣ በጂማ እና በሰበታ እግር ኳስ ቡድኖች በአመራርነት ሠርተዋል። ባለፉት ዓመታት “ደረት የሚያስነፋም ባይሆን አንገት የማያስደፋ ሥራ” መስራታቸውን ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት ተናግረው ነበር። “ተጨባጭና በአይን የሚታይ ሥራ ሰርተናል” የሚሉት አቶ ኢሳያስ ዳግም ቢመረጡ የጀመሯቸውን መልካም ነገሮች ማስቀጠል፣ ሊሰሯቸው አቅደው በተለያየ ምክንያት ያልተሳኩትን ደግሞ ማከናወን እቅዳቸው ነው። ከእቅዳቸው መካከል ዐቢይ የሆነው “የክለቦች አደረጃጀት ላይ መሥራት” መሆኑን ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1q65nw626o |